ፕሬዚዳንት ዶር አብይ አህመድ እና ሹመታቸው ለእኔ #አናርኪዝም ነው። ውጤቱም #እሮ። ዶር ጌዲዮን ጢሞቲወስ ከጠቅላይ ሚኒስተር አብይ በላይ ሁለት ድምጽ ይኖራቸዋል። #ሎተሪ።
ፕሬዚዳንት ዶር አብይ አህመድ እና ሹመታቸው ለእኔ #አናርኪዝም ነው። ውጤቱም #እሮ ። ዶር ጌዲዮን ጢሞቲወስ ከጠቅላይ ሚኒስተር አብይ በላይ ሁለት ድምጽ ይኖራቸዋል። #ሎተሪ ። 1) አይዋ የኢትዮጵያ #ፓርላማስ መራራ ስንብትህን እንደምን አዬኽው? ለነገሩ ላም ጣም የለህም። በማታውቀው አጀንዳ ስታጨበጭብ ነው እምናውቅህ። ማህያው ካልቀረ ግድየለም። 2) ህወሃት የሚመካብህ አቤቶ #የኢህዴግ #ህገ - መንግሥትስ እንደምን እዬሆንክ ይሆን በዚህ #አናርኪዝም ጉዞ። እያለህ #የተለሞጥክ ። https://w "በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጡ ሹመቶች" ww.youtube.com/watch?v=nRNIv64Xg6g "የቤትህ ቅናት በላኝ።" የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ህልም ማለቂያ የለውም። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ከሚባሉ ይልቅ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ቢባሉ ይወዳሉ ብዬ በተደጋጋሚ ጽፌያለሁኝ። ምኞታቸውን የሚፈጽሙት ግን በህግ #ጥሰት ሊሆን አይገባም። ፓርቲያቸው ሳይወለድ ዕውቅና አገኜ። እኔም የጨነገፈ ብዬ ምርጫ ቦርድን በወቅቱ ሞገትኩኝ። ሰሚ ባይኖርም። አሁን ምርጫ ቦርድ የዘራውን እንክርዳድ እያፈሰ ነው። የአንድ ፖለቲካ ድርጅት ኦክስጅኑ የአደረጃጀት መርሁ ነው። የሚያድነውም የሚገድለውም። ስንት ነገር ከተፋለሰ በኋላ ጉባኤ ተካሄደ። ከዛም ዶር አብይ አህመድ አሊ በራሳቸው የአስመራጭ ኮሜቴ ሰብሳቢነት #ፕሬዚዳንት ሆኑ። ዓለም እንዲህ አይነት ገመና አስተናግዳ አታውቅም። ዶር አብይን ይህ አላረካቸውም። ሁሉንም ስልጣን ጠቅልለው #ፕሬዚዳንት ለመሆን በማይችሉበት ሁኔታ በህግ ጥሰት በጠራራ ፀሐይ አጤ እንደልቡ ይኽው ያሻቸውን በአሻቸው ጊዜ በአናርኪዝም እንዲህ ያወራርዱታል - ምኞታቸውን። ...