ፕሬዚዳንት ዶር አብይ አህመድ እና ሹመታቸው ለእኔ #አናርኪዝም ነው። ውጤቱም #እሮ። ዶር ጌዲዮን ጢሞቲወስ ከጠቅላይ ሚኒስተር አብይ በላይ ሁለት ድምጽ ይኖራቸዋል። #ሎተሪ።

 

ፕሬዚዳንት ዶር አብይ አህመድ እና ሹመታቸው ለእኔ #አናርኪዝም ነው። ውጤቱም #እሮ
ዶር ጌዲዮን ጢሞቲወስ ከጠቅላይ ሚኒስተር አብይ በላይ ሁለት ድምጽ ይኖራቸዋል። #ሎተሪ
 
1) አይዋ የኢትዮጵያ #ፓርላማስ መራራ ስንብትህን እንደምን አዬኽው? ለነገሩ ላም ጣም የለህም። በማታውቀው አጀንዳ ስታጨበጭብ ነው እምናውቅህ። ማህያው ካልቀረ ግድየለም።
2) ህወሃት የሚመካብህ አቤቶ #የኢህዴግ #ህገ - መንግሥትስ እንደምን እዬሆንክ ይሆን በዚህ #አናርኪዝም ጉዞ። እያለህ #የተለሞጥክ
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ህልም ማለቂያ የለውም። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ከሚባሉ ይልቅ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ቢባሉ ይወዳሉ ብዬ በተደጋጋሚ ጽፌያለሁኝ። ምኞታቸውን የሚፈጽሙት ግን በህግ #ጥሰት ሊሆን አይገባም። ፓርቲያቸው ሳይወለድ ዕውቅና አገኜ። እኔም የጨነገፈ ብዬ ምርጫ ቦርድን በወቅቱ ሞገትኩኝ። ሰሚ ባይኖርም። አሁን ምርጫ ቦርድ የዘራውን እንክርዳድ እያፈሰ ነው። የአንድ ፖለቲካ ድርጅት ኦክስጅኑ የአደረጃጀት መርሁ ነው። የሚያድነውም የሚገድለውም።
 
ስንት ነገር ከተፋለሰ በኋላ ጉባኤ ተካሄደ። ከዛም ዶር አብይ አህመድ አሊ በራሳቸው የአስመራጭ ኮሜቴ ሰብሳቢነት #ፕሬዚዳንት ሆኑ። ዓለም እንዲህ አይነት ገመና አስተናግዳ አታውቅም። ዶር አብይን ይህ አላረካቸውም። ሁሉንም ስልጣን ጠቅልለው #ፕሬዚዳንት ለመሆን በማይችሉበት ሁኔታ በህግ ጥሰት በጠራራ ፀሐይ አጤ እንደልቡ ይኽው ያሻቸውን በአሻቸው ጊዜ በአናርኪዝም እንዲህ ያወራርዱታል - ምኞታቸውን። 
 
ኢትዮጵያን ከነሥርዓቷ ነው በመዳፋቸው አስቀምጠው ጭፍልቅልቅ የሚያደርጓት። ምን ታመጫለሽ ዓይነት። አክብሮት ለእናት አገራቸው ቅንጣት የላቸውም። የሚገርመኝ እሷን ሳያከብሩ፤ ልጆቿን ሳያከብሩ ስለ ሉዓላዊነት፤ ስለ ብሄራዊ ጥቅም ሲናገሩ ግርም ይለኛል። 
 
ኢትዮጵያ በውስጣቸው የለችም። ያማ ባይሆን ኖሮ እንዲ አናርኪዝም #የሥርዕወ - መንግሥታቸው መለያ አሻራ ባልሆነ ነበር።
ለማህበረ - ኦነግ፤ ህገ መንግትሥት፤ ፓርላማ፤፦ካቢኔ፤ የፍትህ አካል፤ ፓርቲያዊ ዲስፕሊም ምናቸውም አይደለም። እነሱ የፈጠሩት ሥርዓተ አልበኝነት ነው አሁን አገር ምድሩ #በአናርኪዝም ሂደት እዬታመሰ የሚገኜው። 
 
የሆነ ሆኖ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ታዬ አጽቀሥላሴ በሰዓታት ሂደት ሲሸኙ፤ ከዛ በፊት ደቡብ ላይ የተፈፀመ ክስተት ከድኜ ነው እማቀርበው የዚህ አናርኪዝም #መባቻ ነበር። እንዲህ በሚያረገርግ መንግሥት የህግ #ጥሰት ታክሎበት ነገ እና ዛሬ ምን ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ሲታሰብ መልሱ ኢመርጀንሲ ሩም ላይ ይሆናል። በምንም ሁኔታ የአንድ አገር መንግሥት ይሁን የአንድ ተቋም ሂደት አናርኪዝም ምራ ከተባለ ያራል። #እሮው ሁሉንም ያካትታል። 
 
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ውጭ ጉዳይ ሚር እና ኮምኒኬሽን #የዳማ መጫወቻ መዝናኛቸው ነው። "ተቀመጡበት ሥራውን እኔ እከውነዋለሁኝ" ነው። የእሳቸው የመንግሥታዊ ሥርዓት ሂደት ደግሞ በህግ በጥሰት ነው። በመጫን እና በመደፍጠጥም ነው። የገዳ ዲስፕሊን ይሁን የሳቸው ፈንታዚ ሁልጊዜ የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ውሳኔ፤ እርምጃ በህግ ጥሰት መጭ ነው።
 
ምክትል ጠቅላይ ሚር እና የውጭ ጉዳይ ሚር በአንድ ላይም አዬን አቶ ደመቀ መኮነን ሆነው። እሳቸውም የባይወሎጂ ምሩቅ ናቸው። ፈጽሞ ሊገናኝ የማይችል። የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ውጭ ጉዳይ ሚር መሆንም የሚከብድ አመክንዮ ነበረው። የዛሬውም የዶር ገዲወን ጢሞቲወስም መሰሉ ነው የተፈፀመው። በሙያቸው በህግ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። አንድ ቀን በአንባሳደርነት ያልሠራ ሰው፤ ወይንም ቆንሲላ ሆኖ ያልተሳተፈ ለቦታው ፊደል ቆጣሪ ነው የሚሆነው።
 
በሙያው፤ በተመክሮ የሚልቁ ባለሙያወችን እንደምን ሊመሩ ይችላሉ? ለዛውም ነገረ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና በዲፕሎማሲው ማህበረሰብም ውጥርጥር ባለችበት ጊዜ በቤተሰብ የቡና ወግ ቀልድም ደባም ነው። ለኢትዮጵያ የቀደመ የዲፕሎማሲ አቅም፤ ክህሎት፦ ተቀባይነት እና አክብሮት #ብቀላም ነው ለእኔ። ትንሽ አያስቡም??? የኢትዮጵያን ልዕለ ኃያላንነቷን በአፍሪካ ደረጃ #የሚሸበሽብ
 
ከዚህ በላይ ሰው በተቀያዬረ ቁጥር ተከታታይነት ያላቸው ተግባራት #ይረግባሉ። ውጥኖች ይጫጫሉ። ቆባ ነው የሚሆኑት። ለነገሩ #መንታ ዲኤታወች ከኦሮሞ ኢሊት ናቸው። 
 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ዛቢያ ባላውን እንደ አሻ የሚያሾሩት። ልክ እንደ ፓርላማው አፈ ጉባኤ። ከላይ ለስብጥር እነ እከሌ ከእስር ማህበረ - ኦነግ ቴርሞ ሜትሩን ይቆጣጠራሉ። ይህ ግን የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ ችግር አይደለም። አልጋ ላይ የዋለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህል ውርስ ሆኖ የመጣ ነው። የሳቸው ፈጣጣ መሆኑ ነው።
የዶር ጌዲወን ሌጋሲ አስፈፃሚ ደግሞ ባለቤታቸው ወሮ ሃና አርያሥላሴ ናቸው።
 
ዶር ጌዲዮን የከፋፈቱትን ሁሉ ወሮ ሃና ይከዳድኑታል። ያው ሳሎን ቤት እና መኛታ ቤት ማለት ይሆናል። #ልግጫ። ለስንብት የተዘጋጄ ከኖረም ይከወናል። እንዲህ አይነት የተዝለገለገ ጉድ ኢትዮጵያ ተሸክማለች። መጥኔ ለአንቺ እናት ዓለም።
 
የሆነ ሆኖ ዶር ገዲዮን ጢሞቲወስ የካቢኔ ስብሰባ ሲኖር ከጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ #በላይ ሁለት ድምጽ ይዘው ይገባሉ። ላቅያለ ሥጦታ ነው ለቤተ ዶር ገዲወን ጢሞቲወስ። መክረው ይመጣሉ መክረው ይወስናሉ። ስለዚህ ዶር ጢሞቲወስ #ጣምራ አቅም አላቸው ማለት ነው። 
 
በዬትኛውም ሁኔታ ባል እና ሚስት፤ አባት እና ልጅ በአንድ ኮሚቴ ውስጥ ሊኖሩ አይገባም። አይደለም ከ100 ሚሊዮን ህዝብ የሚመራ መንግሥት፤ አለፍ ሲልም የአፍሪካ ተስፋ ለሆነች አገር። የሆነ ሆኖ በሌሎች የካቢኔ ተሰብሳቢወች ላይም ሳይለንት ዲስክርምኔሽን ያሳድራል። ይህ የተፋለሰ መንገድ በድምጽ ሥርዓት አፈፃፀም ሂደት ላይ ከፍ ያለ ተጽዕኖ ፈጣሪ ስለሆነ በአስተዳደርም፤ በአመራርም ፈጽሞ ሊሆን የማይገባ ጉዳይ ነው። 
 
አማራዬ ትምህርት ሚኒስተር፤ ጤና ሚኒስተር፤ ጉሙሩክ፤ ትራንስፖርት ሚር፤ ውጭ ጉዳይ ሚር #በማቆያ ወዘተ ጨምርኳቸው ላሏቸው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ኮታ ማሟያ እንደ ሆንክ እሰበው። እወቀውም። የማህበረ ኦነግ ኮታ በመጨመር ከምል በእምርታ መጥቋል፤ #መጠቅለል ነው የሚታዬው።
 
ለሥም በተሰዬሙትም #ሚኒስትሩ ሌላ ቢሆን ምክትሎቹ ማህበረ ኦነግ ናቸው። "በብልጽግና" ሁሉም ክልሎች እኩል ድርሻ አላቸው፤ ተደማሪወችን ሌላ የፖለቲካ ድርጅት በግልም ተወዳዳሪወችን አሳተፍኩ የሚባለው የውክልና ቦታ የሚነጠቀው የአማራው የፖለቲካ ውክልና ነው። ይህ ልብ ያልተባለ ጉዳይ ነው። 
 
የውክልናው መጠነ ሰፊ ትርፍ ፖለቲካዊ ለብልጽግና፤ የጭነቱ ተሸካሚ አንተው። በሌላ በኩል የአንተ ሊቀ ሊቃውንት እዬተለቀሙ ይታሰራሉ፤ ይገደላሉ፤ ይሰደዳሉ፤ ይታፈናሉ፤ ገና እጩወች እንዳይወጡ #ለመቀጣጫ በሚማሩበት ዩንቨርስቲ ይታገታሉ፦ ድብዛቸው ይጠፋል፥ ስለሆነም ይህ ኢ - ፍትኃዊነት ነው አመክንዮህ ሊሆን የሚገባው። ከዚህ ቀደምም በምርጫው ሰሞን ይህን ሃሳብ ጽፌበት ነበር። ያስተዋለው የለም እንጂ። የአንተ ድርሻ ነው ተሸንሽኖ ለክልል የስብጥር ውክልና የሚታደለው። 
 
አይዋ የኢትዮጵያ #ፓርላማስ ስንብትህን እንዴት አዬኽው? ለነገሩ ለጭብጨባ የሚቀጥለው ሳምንት እንጠብቃለን። አስቸኳይ ስብሰባ ተብሎ። እሱ ብቻ ሳይሆን ትዕይንትም። ጥቂት የተሰናዱ ሰወች የሚሉትን ብለው ፀደቀ እንሰማለን። ለእኔ በቁማችሁ ፈርሳችኋል።
አይዋ የህወሃት መመኪያ #ህገ - መንግሥትስ እንዴት እያደረገህ ይሆን አናርኪዝም እና ኑሮህ? 
 
ዶር ገዲዮን የህግ ባለሙያ ናቸው። ባለቤታቸው ወሮ ሃና አርያሥላሴም እንዲሁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እጩ የካቢኔ አባላት አቅርቦ በፓርላማ ያፀድቃል የሚለው ህገ - መንግሥታዊ ድንጋጌ ተጥሶ ተሹማችኋል ሲባሉ ደላችሁን? የሙያ ቃል ኪዳናችሁ በዚህች ደቂቃ እኮ እራሳችሁ ጠቅጥቃችሁታል። ለማን እና ለምን ያን ያህል ዓመት ደከማችሁ? ህግ በራስ ላይም ይሠራልና። የሚሠራ ህሊና ላለው? ጭንቅላትማ ድንቢጥም አላት። እኛ መሻላችን በህሊናችን ነው።
 
ለነገሩ ዶር ገድዮን ጢሞቲወስ በሠሩበት ዘመን የአማራ ሊቃናትን፤ የተዋህዶ ልጆችን፤ የአማራ ሲቢላይዘሽን አክባሪወችን በእስር በማጣደፍ ነው የባጁት። መደበኛ ሥራቸው ይህ ነው የነበረው። በድብደባ የተሰዋ የአማራ ባንክ ሠራተኛም አለን እኮ።
 
የደቡብ አፍሪካ ስምምነት እራሱ በምን አግባብ እንደተገኙ አይገባኝም። ተስማሚወች እንዲህ ሳይስማሙ ሲቀሩ ህጋዊ መፍትሄ ለመሰጠት የአፈፃፀሙ መልፈስፈስ ምክንያቱ ይሄ ይመስለኛል። የፍትህ ተቋሙ ጭንቅላት ማህበርተኛ ስለነበሩ። 
 
ለነገሩ - ተደገመ። በውጭ ጉዳይ ሚኒስተርነት ለሚፈጽሙት ግድፈት ባለቤተወ ነገ ስህተተወትን በቁልምጫ ያስተናግዱታል ማለት ይሆናል። እንዲህ ዓይነት ዝርግ፦ ዝርግርግ እና ዝልግልግ ሁነት ውስጥ እንደ የህግ ሊቃውንትነት መሳተፍ ግርማ ሞገስ ያለው ዶክትሬት የት ይደበቅ ይሆን?????
 
በዚህ መንግሥታዊ የሥርዓት ጥሰት ውስጥ የህግ ባለሙያ ሊቃውንታት ለህግ የበላይነት በራሳቸው ሐሤት ላይ መወሰን ከተሳናቸው ኢትዮጵያ እና ህጋዊ ተስፋዋ፤ ትውልዱ እና ቀጣይ ህይወቱ በነውጥ የተሰቀዘ ይሆናል። 
 
በሌላ በኩል ወሮ ሰላማዊት ካሳም የቱሪዝም ሚኒስተር ሚኒስተር መሆናቸውን አዳምጫለሁኝ። በህግ ጥሰት ለሚገኝ ሹመትግብረ ምላሹ ህገ ወጥነትን በሐሤት ማጽደቅ ወይንስ መሞገት? ሙግት እና ጋዜጠኝነት? ፋክት እና ጋዜጠኝነት? ዕውነት እና ጋዜጠኝነት? የሥርዓተ መንግሥቱ ዕንብርት ህገ መንግሥታዊ አፈፃፀም እና ጋዜጠኝነት ምን እና ምን እንዲሆን ይፈቅዱ ይሆን ሚኒስትሯ?
የኢትዮጵያ ሊሂቃን መንግሥታቸውን ማዳን ለምን አጀንዳቸው ሊሆን እንደማይችል ይገርመኛል። 
 
መኖራቸው ከመንግሥታቸው ቀጣይነት ጋር የተዳበለ ሳይሆን የተዋህደ ነው። ብሄራዊ ግዴታም አለ። ህጋ ሲጣስ ተባባሪነት ለእኔ አብረን እንደርመስም ነው። 
 
ማህበረ ቅንነት ትውልድ በዚህ መንግሥታዊ አናርኪዝም ትውልድ፤ ብሄራዊ ጥቅም፤ ሉዓላዊነት፤ አደራ፤ ትውፊት እና ታሪክ እንደምን ከዕውነት - ከፋክት - ከመርኽ ጋር ይገናኙ???? ጉዳዬ ይኽ ነው።
መልካም ሰንበት።
 
ቸር አስበን፥ ቸር እንሁን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
19/10/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ፍቅር ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጡ ሹመቶች

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።