ልጥፎች

ከጃንዋሪ 1, 2020 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የህሊና ዕንባ።

ምስል

የዓለም የስጋት ቀጠና የሲኦል ዚታው አቤቶ ኦፌኮን ይሆን?!

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። የዓለም የስጋት ቀጠና የሲኦል ዚታው   አቤቶ ኦፌኮን ይሆን?!       „በታካች ሰው እርሻ አዕምሮ በጎደለው ሰው ወይን ቦታ አለፍሁ። እንሆ ሁሉም እሾህ ሞልቶበታል። ፊቱም ሳማ ሸፍኖታል፤ የድንጋዩም ቅጥር ፈርሷል።“ (መጽሐፈ ምሳሌ {ተገሳጽ} ምዕራፍ 24 ከቁጥር 30 እስከ 31 ) ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 31.12.2019 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።s ·          በር ። ዛሬ ዝምታው ያስፈራል። ሻሾም ብቅ አላለም። የአውሮፓ አድዮ ነበር። ግን ጠላታችሁ እልም ይበል አልመጣም። እኔ አኮፋዳዬን አሰናድቼ ነበር። አሻቦ ለቸገረው ልቸበችብ። ግን ትውር የለም። የአውሮፓው አዲስ አመት ውበቱ የሰማይ ነጭ አበባ መልካ ምድርሩን ሲያንቆጠቁጠው ነበር። ቀኑም ከፍቶታል። ጭልምልም ከብዶታል። ጸጥታው ግን አለ። እሱም ግጥሜ ነው። ከሰሞናቱ ሁሉ እንደዚህ የሚመቸኝ የለም። ሁካታ እርጋ ስለሚባል። ችሎቱ ግን የእዮር ነው። አላዛሯ ኢትዮጵያስ እንዴት ናት? ·         መቅድ ም ። እንዴት ናችሁ የእኔዎቹ? የነጮችን አዲስ ዓመት ለምታከበሩ እንኳን አደረሳችሁ። ክህሎት የሃሳብ ልዕልና -በስክነት፤ ክህሎት የመ ቅደ ም ጥሞና - በህሊናዊነት፤ ክህሎት የጥበብ ኪናዊነት - በእኛዊነት፤ ክህሎት የመተንበይ ተስጥኦ - በማግስታዊነት፤ ክህሎት የስኬት መዳረሻ - በድርጊታዊነት፤ ክህሎት የማስተዋል ህብራዊነት - በመሆንነት፤ ክህሎት የእርምጃ አወሳሰድ ቅደም ተከተል - በጥራት፤ እርቆናል ወ...