የዓለም የስጋት ቀጠና የሲኦል ዚታው አቤቶ ኦፌኮን ይሆን?!
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።
የዓለም የስጋት ቀጠና የሲኦል ዚታው
አቤቶ ኦፌኮን
ይሆን?!
„በታካች ሰው እርሻ አዕምሮ በጎደለው ሰው ወይን
ቦታ አለፍሁ። እንሆ ሁሉም እሾህ ሞልቶበታል።
ፊቱም ሳማ ሸፍኖታል፤ የድንጋዩም ቅጥር ፈርሷል።“
(መጽሐፈ ምሳሌ {ተገሳጽ} ምዕራፍ 24 ከቁጥር 30 እስከ 31)
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
31.12.2019
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።s
·
በር።
ዛሬ ዝምታው ያስፈራል። ሻሾም ብቅ አላለም። የአውሮፓ አድዮ ነበር። ግን ጠላታችሁ
እልም ይበል አልመጣም። እኔ አኮፋዳዬን አሰናድቼ ነበር። አሻቦ ለቸገረው ልቸበችብ። ግን ትውር የለም። የአውሮፓው አዲስ አመት
ውበቱ የሰማይ ነጭ አበባ መልካ ምድርሩን ሲያንቆጠቁጠው ነበር። ቀኑም ከፍቶታል። ጭልምልም ከብዶታል። ጸጥታው ግን አለ። እሱም
ግጥሜ ነው። ከሰሞናቱ ሁሉ እንደዚህ የሚመቸኝ የለም። ሁካታ እርጋ ስለሚባል። ችሎቱ ግን የእዮር ነው። አላዛሯ ኢትዮጵያስ
እንዴት ናት?
·
መቅድም።
እንዴት ናችሁ የእኔዎቹ?
የነጮችን አዲስ ዓመት ለምታከበሩ እንኳን አደረሳችሁ። ክህሎት የሃሳብ ልዕልና -በስክነት፤ ክህሎት የመቅደም ጥሞና - በህሊናዊነት፤ ክህሎት የጥበብ ኪናዊነት -
በእኛዊነት፤ ክህሎት የመተንበይ ተስጥኦ - በማግስታዊነት፤ ክህሎት የስኬት መዳረሻ - በድርጊታዊነት፤ ክህሎት የማስተዋል ህብራዊነት
- በመሆንነት፤ ክህሎት የእርምጃ አወሳሰድ ቅደም ተከተል - በጥራት፤ እርቆናል ወይንስ ቀርቦናል? ሳስተናል ወይንስ ደርበናል?
ቀፎናል ወይስ ቀፍቅፎናል? ህሊናችን እኛን ይፈትሽ ዘንድ እንፈቅድለት። ከቻልን ሙግቱን። የማንሸሸውን ነገር እጬጌውን ህሊና
ነውና።
·
እፍታ።
የፈተና ዓውድ አቅም ያለው
ተፈተኝንም ይጠይቃል። እኛ እንደ ዜጋ የዓለም ቀጣይ የስጋት ቀጠና ስለመሆናችን አስተውለነው ይሆን? መንፈሱ የለውጡ ተጠለፈ ስንል „አክ ወሬ“ በማለት ታላቁ የሁለገብ ሙያ ሊሂቅ
የአገር ሃብትም ፕ/አለማርያም አዳፈኑት። እናም አቅማችን፤ ሞጋቹ ኃይላችን፤ ብቁው ተደማጭነታችን፤ ተፈሪው የመንፈስ ጥሪታችን
ቁጥብነት አንሶት ወደ አገር ቤት በልቅነት ተተመመ እናም
„በሬ ሆይ እሳሩን አይተህ ገደሉን ሳይታይ“ በደማቅ አቀባበል ተቀበለው። እምቁ አቅማችን ድምዳሜው እራቃኑን ሆነ።
ከተፎካካሪነት ወደ ደጅ ጠኝነት ወረድን። ትጥቃችን ደስ ብሎን በዕልልታ ልዕልና ፈታን። ደስ አይልም¡¡¡
እንሆ በምርኮኝነት ወርደን
ተዋርደንም በባዶ እጅ ህልም ላይ እንገኛለን። ልባሞች ደግሞ በተደራጀ የቀውስ ዓውድ ውስጥ እኛ በገፍ በሰጠነው በኢትዮጵያዊነት
አቅም ላይ ተቆናጠው የአትላንታውን እና የለንደኑን ጉባኤ ቻፕተር ውሳኔ ካለምንም ሳንክ በሰላ አስፓልት ወይንም ጥርጊያ መንገድ
እዬከወኑ ነው። ከቶ አሁንም „ለውጥ እንዳይቀለብስ“
ከሚለው ሞቶ ላይ ተንሳፈን ወይንም ቴንብር ሆነን እንሆን ይሆን?! መቼስ ተደግሞብን የለ? የለት ሰውነት አጠቃን መሸነፍን
አስተቃቅፎ። ውስጥ ሲበግን ይመግል።
·
ገበታ።
ጭንቅላት ሳይሆን ህሊና
ላላቸው፤ ህሊና ኖሯቸውም ቅን ሆነው ለሚያደምጡኝ ብቻ ነው እኔ እምጸፈው። የት ላይ ነን? ምን እዬሆን ነው? ማግሥትስ እንዴት
ሊሆነው ይሆን? ውስጣችን ውስጣችነን የማድመጥ አቅሙ ምን ያህል ነው? በዲናር - በኪሎ - በክናድ - በጋሻ - በሜትር በምን
ይሰፈር? ግን የዝቅጠታችን ልክ መለኪያዎቹ ይችሉትን ይሆን? ወይንስ ዘመንኛው ሜጋ - ጌጋ - ዋት ይሻለው ይሆን?
ጃዋሪዝምን + ጃራዊዝምን
ይሁን እያልን የምናልፈው ሊሆን ይሆን - ይሆንን? የባሰ አታምጣ እንልውን ይሆን - ይህን ውሃ ያዘለ ውርዝ የተራራ ሸክም
ጉዳይ? ከሰሞኑ በተደመጠው ዜና አቶ ጃዋር መሃመድ የኦፌኮ አባልነትን ማመልከቻ አስገብቶ ድርጀቱ እንደ ተቀበለው ተጥቅሷል።
በዬትኛው ዜግነት? ሥርዓት ለኦሮሙማ ሊሂቃን አልፈጠረላቸውም መቼስ ሃራማቸው ነው። ህግ መተላለፍ ክብራቸው እና ድንቃቸው ነውና።
የድርጅቱ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር
መራራ ጉዲና ከዚህ የሲኦል ዚታ መንፈስ ጋር አብረው ሲሰሩ እንደቆዩም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲዛዋወር አንድ መረጃ
አንብቤያለሁኝ። አሁን ለባጀብን የቀውስ ናዳ በዓለም የፊት ረድፈኝነት ለተቀመጥንበት የቁልቁለት ውርዴ ኒሻን ተጨማሪ ተጠያቂ
ባለቤት ተገኜለት ማለት ይሆን?
በቀንበጥ ብሎጌ ወንበሩ ባዶ ነው ብዬ የጻፍኩት ሀምሌ 19 /2010 እ.ኢ.አ. ዋዜማው ሌሊት ላይ ጠቅላይ
ሚንስተር አብይ አህመድ ጉዞ ወደ ስሜን አሜሪካ ባደረጉበት ዕለት ነበር። ብዙ ጊዜም ከዛን ጊዜ ወዲህ ያሉ አመክንዮችን ስሞግት
ስውሩ መንግሥት እያልኩኝ እጽፍ ነበር በቀንበጥ ብሎጌ።
ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ እና
ቡድናቸው ከጉዞ ሲመለሱ የዘሃበሻ „ሹክሹክታ“ የተወገዘበት ጊዜም ነበር። እኔም ያን ጊዜ ከትክክለኛ ቦታ ዕውነተኛው መረጃ
ስለነበረኝ „ሹክሹክታ“ እውነት ነው የተናገረ፤ አልተሳሰተም ብዬ ብሎጌ ላይ ጽፌያለሁኝ። በነገራችን ላይ „የሹክሽኩታ“ መረጃ
አመዛኙን ለተከታተለው የቀጣዩን የትግል አቅጣጫ፤ የኃይል አሰላለፍ፤ የቤተ - መንግሥቱን ጣዕምና ዜማ በጥሞና ያመሳጥራል።
ሌላው ቢቀር ቢያንስ በሆነ ጭረትም፣
ብልጭታም፣ ሽራፊም ሊሆን ይችላል ህሊናዊ ሙግትም ፍትጊያም ከራስ ጋር
ይጭራል። በዛን ጊዜ በሌላ በኩል „አክ ወሬ“
በሚልም ከፕ/ አልማርያም፤ እንዲሁም ከዲያቆን ዳንኤል ክብረት በስሜን አሜሪካ ጉዞ ላይም አብሮ ስለነበረም „ማን ይናገር
የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ“ ዓይነት „የሹክሹክታን“ ምንጭ አቃለው፣ አጣጥለው ሁለቱም ጽፈውታል። ዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ አቶ
አለምነህ ዋሴም በዛ ነጎድጓዳማ ድምጹ „አክ ወሬን“
በንባብ ማቅረቡ ብቻ ሳይሆን እንደሚያምንበትም አስረግጦ ተናግሮ ነበር። የእሱ ድምጽ ደግሞ አንዳች ቀልብ ገዢ ነው። ማግኔት
ነገር አለው። እኔ እራሴ እወደዋለሁኝ።
የሆነ ሆኖ ያው ሥርጉትሻ
ፈንገጥ ያለች ስለሆነች መዘናጋት እንደሌለብን አበክሬ ብሎጌ ላይ ጽፌያለሁኝ። የቅድሚያ ደወሉን አታደፍርሱ፤ አታጉሹትም ብዬ። በተከታታይም ሞግቼዋለሁኝ „አክ ወሬን“። ይህም ብቻ ሳይሆን ለአቶ ኦባንግ ሜቶም
የተስፋ ጠለፋ እንዳለ፤ ትጥቁን መፍታት እንደሌለበት፤ የነበረው የተጋድሎ መስመር መቋረጥ እንደማይኖርበት፤ ሙቀቱም ፍሪጅ
እንዳይጎበኜው መደረግ እንዳለበት ደውዬ ነግሬዋለሁኝ። የተስፋ ውጥኑ መደገፍ አስፈላጊ ቢሆን እንኳን፣ ሰፊ ክትትል እና
አትኩሮት እንደሚያስፈልገው፣ ዝም ብሎ መለቀቅ እንደሌለበትም አክዬ አስታውሸው ነበር።
እኔ በተፈጥሮዬ ስልክ
መደወልም ማንሳትም አልወድም። ነገር ያን ጊዜ የነበረውን አለርም ኢትዮጵያን ሊያድን የሚችል፤ አቅማችን ሳይማረክ በሙሉ አቅም
ልንደራደር የምንችልበት አዲስ መንገድ ቀያሽ ስለነበር ሃሳቤ ትኩረት እንዲሰጥበት በጥብቅ አሳሰብኩት። የያዘ፤ ያለው ነው
ተደራዳሪ መሆን የሚችለው። ነገር ግን በሳምንቱ ኢትዮጵያ መግባቱን አዳማጥኩኝ። „መደመር“ የሚባለ ነገር እኔ አልሞከርኩትም።
እስከ ወዲኛውም አልሞክረውም። እንዲህ መሞገት አይቻልም። ጥልቅ ካሉ በኋላ የሚያስር ህሊናዊ የመታመን ዲስፕሊን አለ።
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ
ለዚህ ሁሉ የአቅም ብክነት እና ምርኮኝነት፤ ቀስ በቀስ እንደ ኤድስ እንደያዘው በሽተኛ የነፃነት ታጋዩ የአቅም ጎራ ባዶ
እጅነት ሁለመናችን እዬሳሳ የሄደበት ጉዳይም የዛ „የአክ ወሬ“ የፕ/ አለማርያም
ጉልበታም አዘናጊ ሰላቢ ጹሑፍ ነበር። ሙሉ ለሙሉ ትጥቅ አስፈቺ ነበር።
የሚያሳዝነው አሁንም አደንዛዥ
ጹሑፍ ነው የሚጽፉት። ምን እንደ ነካቸው አላውቅም። „ፍቅር ዕውር ነው“ የሚለው ብሂል በሳቸው የሠራ ይመስለኛል። ዘነዘናችን
ቀርትን አሁንም ውዳሴ - ቅዳሴ - ወረብ ላይ መገኜት የጤንነት አይመስለኝም። ከአንድ ሰው የሰብዕና ግንባታ የ100 ሚሊዮን
ነፍስ ይበልጣል። የጨረቃ ግርዶሽ ይባል የጸሐይ ግርዶሽ አይታወቅም ተልዕኮው። የጠፋውንም ነፍስ ለማዳን ይዞ መገኜትን ማስቀደም
ይገባል። ጓዝን ጠቅልሎ እጅ ከመስጠት። ሁለመናንም ከመስገበር። ከቶ የጥገኝነት ልመና ይናፍቃልን?! እንጃ - ለስጋጃ ይሸለማልን?!
እራሱ የጠሚሩ በእኛ ፍላጎት
እንዲጓዙ ለማድረግ እኮ እጅ ሰጥቶ ሳይሆን አቅምን ገንብቶ፤ አቅም ሆኖ፤ አቅምን በስልት እና በጥበብ እያሳደጉ፤ አቅምን
እያበራከቱ፤ አቅምን ራሱን አስችሎ ኮትኩቶ አብቅሎ፤ አስብሎ፣ አራብቶ ነው መሆን የነበረበት። ለነገሩ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቀያሽ
የለውም፤ ተንባይ የለውም። ባለቤትም የለውም። ቢፈጠርም ገና ብቅ ሳይል ተረባርቦ ማጥፋት ነው። አልመታደል።
ቅንነት መልካም ነው። ግን
በአግባቡ ሊመራ፣ ሊተዳደር ይገባል። አዎንታዊነት ሸጋ ነው፣ ግን በተገባ የአያያዝ ጥበብ ሊተዳደር ይገባል። አክብሮትም ደግ ነገር ነው፤ ነገር ግን የሰብዕዊነት እና የተፈጥሯዊነትን ጥሰትን ለማድመጥ ሰፋ ያለ ልቦና እና አድማጭ ጆሮ ያስፈልጋል።
የተስፋ ጠለፋውን ማዳን በጥዋቱ ሲቻል፤ በቀንበጡ የቀጩት እና ሰፊ አስተዋፆ እኒህ የአገር ሊሂቅ ፕ/ አለማርያም ለሙሉ ሽንፈታችን እሰዋፆ አበርክተዋል ብዬ አስባለሁኝ። ነገ የጸጸቱን ቋያም፤ ዶፍም ሆነ ቸነፈሩን ከቻሉት።
የዚህ ሁሉ ግርዶሽ ዕድምታ
መዳረሻ አሪወሳዊ መንፈስን የሥልጣን ቁንጮ ማድረግ እንሆ ሆነ። አሁን ኦፌኮ ተልዕኮውን ጨርሷል። እኛ ደግሞ በምን አቅማችን
ይህን እንሞግታለን? በባዶ እጅ ጃራውያንን እሰከ ሰራዊቱ ሞግቶ
መርታት ይቻል ይሆን? 1+1= 2 ከሆነ ዕሳቤው ገና አልተወለድንም። በዬሚዲያው አልደፈረም፣ ቀበቶን ፈቶ ይቻላልን? ፉገራ።
እንኳንስ እልቂት
የተሰናዳለትን ትውልድን፤ ፍርሰት የተሰናዳላትን አገር ልናድን ቀርቶ እራሳችን በነፍስ ወከፍ ማትረፍ አንችልም። የኩርድሾችን
ታሪክ ማንበብ የሚጠቅም ይመስለኛል። ማንነት አላቸው የእኔ የሚሉት በደንበር የተከለለ ለልጅ ልጅ የሚያወርሱት ብትን አፈር
ግን የላቸውም። መኖራቸው እራሱ አደብ የነሳው ነው። ፈልገውት ሳይሆን ተገደው። መኖራቸውን ተነጥቀው። የራዲዮ ጋዜጠኛ ጓደኞች
አሉኝ አፈር ስንቀምስ እናርፋለን ይሉኛል። የጃራዊው መንፈስ ተልዕኮ ይኸው ነው። ይህን የሚያሳካው ደግሞ „ለውጥ
እንዳይደናቀፍ“ በሚል ሽፋን በሚዋጣው ማስተዋል በነሳው፤ አደብ ባጣው፤ ጥበብ በተነፈገው በገፍ በሚቸረው የሊሂቃን ኢትዮጵያዊ
አቅም ነው። ያለ የሚመስለው ሰው ሁሉ ያለ አይመስለው። ቀለም የሌለው ቀፎ እስክሪቢቶ ይጽፋልን?
·
ለመሆኑሳ ዛሬ ሮል ሞዴል
የምንለው አለን?
ዛሬ አለን የምንለው የራሳችን
የሆነ አቅም አለን? ዴሞግራፊ የህሊና ነቀላ እና ተከላ ነው። አለን የምንለው የተስፋ ቋት ሁሉ መለመላውን ነው የቀረው። ሁሉም
ተጽዕኖ ፈጣሪ በሉት ታዋቂ ነፍስ፤ ተቋምም ሁሉ ምልምል ነው። እንዲያውም „ጃዋር ሆይ!“ በሚል ልመና ላይ ነው። አፍራለሁ
እንዲህ ዓይነት ነገር ሳነብ። የራስን ሙሉ አቅም በግዴለሽነት የትሜና ወርውሮ ባዶ እጅ ሆኖ አንቃሮ ሰማይን የሚጠበቅ የመና፤ የላመ ምኞት
ነው ያለን። ይህን ያደረገው የስውሩ መንግሥት ስልታዊ የድንገቴ ተውኔታዊ ጉዞ ነበር። የዛ የስውሩ መንግሥት አልጋ ወራሽ እንሆ
ኦፌኮ ሆኖ ጉብ ብሏል። ሁሉም ነፍስ በጃራዊ ሥር ነው። መራራ ነው ግን ከፈቀዱ ማጣጣም ነው።
ጠሚር አብይ አህመድ
የተሰጣቸው ግዳጅ አለ። ከዛ ግዳጃቸው ውትልፍ ሳይሉ ሁሉመናውን በሥርዓት ያስኬዳሉ። እሳቸው በሚሰጡት ቅልስል ሽፋን የአትላንታ
እና የለንደኑ የጃዋርዊው ጉባኤ ዕድምታ ደግሞ በቀዬሰው መስመር ልክ ሥራውን አሳምሮ ይሠራል።
ለውጭ መንግሥታት ሽፋን
ጠ/ሚር አለ፤ በዲፕሎማሲያዊ ማህበረሰብ ኮሽ ባለች ቁጥር እግር ከወርች የሚያስር ስልት ቀይሰው እራሳቸው ጠሚር አብይ አህመድ
ይንቀሳቀሳሉ። ሲያስፈልግም ፈጽሞ ያልተሰበ፤ ያልታቀደ ጉዞ ከእጅ መጥኛ ጋር ይከውናሉ። ይህን የእስራኤል ጉዞ እና
ኤርትራውያንን ወደ አገራቸው በመመለስ ባለ ሚና እሆናለሁ ያሉበትን ቃለምህዳን ማጣጣም ነው። የሰሞኑ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ
አፈወርቂ ጨነቀኝ፤ በዛብኝ ሽልማቱ፤ ድንገቴው በዛብኝ የሥጦታ ያሉት መንበሽበሽም ይህን ያክላል፤ የኖቤሉ ፖለቲካዊ ዕድምታን አክሎ።
ኢትዮጵያን ቢጠዬቁም በሲሶ መንግሥትነት ይፈቅዳሉ። ምን ሲገድ። ይህን በስማ በለው ሳይሆን እኔ በግል የምከታተላቸው መሰረታዊ
መሰል በርካታ አመክንዮዎች አሉ።
አገር ውስጥም ለጃዋራዊው
ፍላጎት ማስፈጸሚያ የኢትዮጵያ ሙሉ አቅም አለ፤ እንደልብ ተንበርክኮ የሚዛቅ። ግርዶሾ ይኽው ነው። ለዚህም ነው ቁርጠኛ በሆኑ
አገራዊ ጉዳዮች ላይ
መደበቅን እንደ ጥበብ የያዙት ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ
አህመድ። ጭንቅ ሲመጣም ደጅ ለደጅ የሚንጎባለሉት ለዚህ ነው። ሲያሰኛቸውም ምህረት ጥዬቃ አንቦና ሐረር ይጓዛሉ። ወይንም
ነቀምት ሜዳ ላይ የኳስ ጨዋታ ተውኔት ይጋብዙናል። አክተር መሪ አይተን አናውቅም ነበር። አጋጠመን። አንዲት ወዳጄ በቀደመው ጊዜ
አምንስቲ የሰራች በኖቤል ሽልማቱ ዙሪያ ስንጨዋወት ለሳቸውስ ኦስካር ነበር የሚመጥናቸው ስል የተቀመጥነበት ቤት እስኪነቃነቅ
ነበር የሳቀችው። የውነቴን ነው። ጥሩ የፕለይ ጸሐፊ አልተገኜም እንጂ በዬወሩ አንዳንድ መጸሐፍ ማሳተም ይችል ነበር።
·
ጃዋራዊው መንፈስ መነሻው ምን ነበር?
ይህ የጃዋራዊ ጃራዊ መንፈስ
የተነሳው ከግራኝ አህመድ የህልፈት ቀጠና ነው። የግራኝ አህመድ ህልፈት ጎንደር ነው። መቼም ጎንደር የሚስጢራት ማህደር ነው። ጎንደር
ግራኝ በር የሚባል አለ። ይህ ቁጭት ነው ጃዋሪይዝምን የፈጠረው። የመፈናቀሉ ታሪክም ከዚህ ጋር በውል ኪዳን የፈጸመ ነው።
በማዕከላዊ ጎንደር ወደ 90ሺህ ህዝብ መፈናቀል ከ40ሺህ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት መስተጓጎል የዛ ቂም የእፍታ ማወራረጃ ነው።
የሊሂቃኑም መተራ በዚህ ጥልቅ ቅኔ እንዲቃኝ ለዕድምታ ሊቃውንት የቤት ሥራ መስጠት እሻለሁኝ - በአክብሮት።
ሌላ ትኩረት የተነፈገውን
እንድ አመክንዮ ላንሳ። ጠሚር አብይ አህመድ በተደጋጋሚ ጎንደር ተገኝተዋል። አንድ ጊዜ እንዲያውም የኤርትራው ፕሬዚዳንት እና
የሱማሌው አብረው ታድመዋል። የአፍሪካ የመጀመሪያው ደረጃውን የጠበቀ የንግሥና ፓላስን ግን አላስጎበኙም።
የአፍሪካው ህብረት ጉባኤ ከዛ ሁሉ የመሆን ጥበብ ያስፈልገው ነበር። ይህንም በቀደመው ተስፋዬ ላይ ለሳቸው በክብር አሳስቢያቸው
ነበር።
በዓለም የቅርስና ውርስ
የተመዘገበ ሉላዊ ድንቅ፤ በተራ ቀን ተራ ጉብኝ የሚሹትን ግድብ እና ቅብጥርሶ ነበር ሁለቱን መሪዎችን ያስጎበኙት። ለምን? ሌላው
ታስታውሱ እንደሆን አቶ ጃዋር መሃመድ ለትግሬው አክሱም፤ ለአገው ላሊበላ እያለ ሲጠቅስ ፋሲልን ዘሎታል። ከፍተኛ የሆነ
የጎንደር እና የአማራ ጥላቻ ስለአለበት። መክደኛ ልኩን ደግሞ አግኝቷል። ለእሱ መንፈስ የተነጠፉ ጃዋራዊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን።
የአማራን ክልልን አስበርክከው እያስገበሩት ነው። ምስጥ።
ኢትዮጵያዊነት ባለቤት አልባ ነው። ለኢትዮጵያ እንጨነቃለን የሚሉት ኢትዮጵያዊነት ከወገብ በላይ እና በታች ስሌለው በሁሉም አቅጣጫ ሁለመናውን በአትኩሮት መከታተል ይገባቸዋል። ጠብታውን ሁሉ የእኔ ማለት ይጠይቃል - ኢትዮጵያዊነት።
ኢትዮጵያዊነት ባለቤት አልባ ነው። ለኢትዮጵያ እንጨነቃለን የሚሉት ኢትዮጵያዊነት ከወገብ በላይ እና በታች ስሌለው በሁሉም አቅጣጫ ሁለመናውን በአትኩሮት መከታተል ይገባቸዋል። ጠብታውን ሁሉ የእኔ ማለት ይጠይቃል - ኢትዮጵያዊነት።
·
ጃዋሪይዝም አሉታዊ ሉላዊ ክስተት
ነው።
በጣም ይገርመኛል ከሌሎች
ኢትዮጵያዊ ፍጹም ጤነኛ ሰብዕዊ እና ተፈጥሯዊ መንፈስ ጋር ፉክክር ላይ ይህን ለተለዬ የጥፋት ተልዕኮ ናጭነት የተፈጠረን መንፈስ
እኩል ሲያስቀምጡት፤ ሲያፊካክሩትም። አይደለም ከጤነኛ መንፈስ ጋር ከራሱ የታወኩ ማህበርተኞቹ ጋር ጃዋሪይዝምን በአቻነት
ማወዳደር፣ ማለካካትም አይቻልም።
እኔ ለደቂቃ ብዕሬም ብራናዬም
ስለ አቶ ጸጋዬ አራራሳ፤ ስለ ፕሮፌሰር ህዝቃኤል ጽፌም ድምጻቸውንም አድምጨሜ አላውቅም። የጠፉ ነፍሶች ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን
ሉላዊ ክስተት በአሉታዊነት የመሆን አቅም ስሌላቸው። ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ዛሬ በብራነዬ ሥማቸው የተጻፋው። ወደ ቀደመው ጉዳዬ
ምልሰት ሳደርግ ጃዋሪይዝም አዶልፍ ሂትለር የተቃባው የመቀጣጫ ቅብዕ አለው ብዬ አስባለሁኝ። ስለዚህም በእልህ፤ በቁጣ፤
በፍጥጫ፤ በበቀል፤ በጥላቻ ሳይሆን በጥሞና እከታተለዋለሁኝ። አቶ ጃዋር መሃመድ የአደጋ ምልክት ነውና።
አሁን ኦፌኮ።
ጃዋሪይዝም ዛሬ ዓለም ቸል
ብላ ብትመለከተው ነገ ዋጋ ትከፍልበታለች። ፕላኔታችን በቁጥጥሯ ሥር ልታደርገው የሚገባ ነፍስ ነው። ድርጅቱን ኦፌኮንም
እንዲሁ። ያጋነንኩት እንዳይመስላችሁ። በዬዘመኑ እንዲህ ዓይነት ጠንቅ የሆኑ ነፍሶች ከዬትኛውም ማህበረሰብ ይፈጠራሉ። ልተቋጥሯቸው
የማትችሉት። በልቅ ሰብዕና፣ በሥርዓተ አልበኝነት ክህሎት ይፈጠራሉ።
ስለሆነም ኢትዮጵያ ሆነች
አፍሪካም የመከራቸው ዋዜማ ነው የጃዋሪይዝም ፖለቲካ ህጋዊ ሆኖ በተቋም መልክ መከሰት። ለዚህም
ነው እኔ ጉዳዩ የተረኝነት፤ የፈረቃ አይደለም ከዛ
የከፋ እና የሰፋ ነው ስል የባጀሁት። ስለዚህም ነው የሶልዳሪት ትግል ያስፈልጋል የምለውም። በዚህም አንድ ቀንጣ አጋዥ ነፍስ ባለገኝም
በሎቢም ስሠራበት ባጅቻለሁኝ። ለአንዲት ቀንም ትጥቄን አልፈታሁኝም። ኦህዴዶች ተስፋ የአገር ይሆናሉ ብዬ ሳስብ በነበረበት
ጊዜም ያስተካክሉ በማለት እዬሞገትኩም ነበር እደግፋቸው የነበረው።
ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን
እና ብጄ አሳምነው ጽጌ ያለብን መከራ „ኢትዮጵያ ከ500 ዓመት በፊት ከገጠማት በላይ“ ነው ትንቢት ይኸው ነው ቅኔ ተርጓሚ
ከተገኜ። እጅግ ብልህነት ያለው፤ የቀደመ፤ የበሰለ፤ የራቀ ፖለቲካዊ ብጡል ምልከታ ነበር። አንድም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊሂቅ
ሆነ ድርጅት እንዲህ ዓይነት ዕውነት ተኮር ትንበያ ላይ አልደረሰም። አይደለም ትናንት ዛሬ እንኳን።
ነፍሳቸውን ይማረው እና
የነብዩ የብጄ አሳምነው ጽጌ ህልፈታቸው የኦሮሙማ ሥርዕዎ መንግሥት የጋራ ስውር ውሳኔም ከኽው ጃዋሪይዝም + ጃራዊዝም ተልዕኮ
ስኬት ጋር መታዬት ያለበት ጉዳይ ነው። የአባ ቅንዬም የጄኒራል ሳህረ መኮነንም ሰማዕትነትም ጉዳይ እንዲሁ። አይደለም
ኢትዮጵያዊው ክርስትና ኢትዮጵያዊ እስልምናም ወዬልህ ነው። ይህን እኔ የዛሬ ዓመት ብሎጌ ላይ ጽፌ ነበር። ኢትዮጵያዊ እስልምና
ቀለሙ ልዩ ነው። ሳቢ እና አጓጊ። ጠረኑ እኛዊነት ነው። ካህዲ ባጥለቀለቀው ምርኮኛ ዘመን እኛ ግን ይህን ነበርን። ካህዲነት
ይቀፋል አይደል? የመርገምት ዋሻ ነውና። ይህ አጭር ፊልም ያላንኳኳበት ደጅ አልነበረም። ሥርጉተ ሥላሴ ኢትዮጵያን ለአረማዊነት
ለመሸለም አልነበረም የታገለችው።
Ungerecht (injustice) neue
ለዚህም ነው በዛ መከራ ወቅት
በግራ ቀኝ ወጀብ እዬተገርፍኩኝ እኔ ድምፃችን ይሰማ ነኝ ብዬ ወጥቼ ሞገትኩ። ብዙ ነገር ሠርቼበታለሁኝ። የተጋድሎውን ክወና
እራሱ በድምጽ ለታሪክ በሚስማማ መልኩ ሠርቸዋለሁኝ።
"የድምፃችን
ይሰማ የስኬት
ተመክሮ ዕድምታ
እና የሥርጉተ
ዕይታ።" (07.05.2019)
ምክንያቱም አገር ጠቀም
ተመክሮው ንጥር ስለነበር። ዕውነትን፤ መርኽን ስትወግን ደንበር የለም። ኢትዮጵያም የውስጥህ ጽላትህ ስትሆን ወሰን የለም።
የሚያውክህ፣ አቋም አልቦሽ የሚያደርግህ አንዳችም ክፉ መንፈስ የለም።
እርግጥ አሁን አሁን ያን
መሰል መስዋዕትነትን የሚያጎሳቁሉ ግለሰቦች አያለሁኝ። ቢሆንም ግን ኢትዮጵያዊው እስልምና እንደ ሃይማኖት ህብራዊነቱ እና ፈርኃ
አላህነቱ ለጥያቄ የሚቀርብ ነው ብዬ አሁንም አላምንም።
ጃዋሪይዝም + ጃራዊይዝም
ኢትዮጵያዊ ቃና ያለው ቅርስን፤ ውርስን፤ ባህልን፤ ትውፊትን፤ ሰብዕናን፤ ዕውቅናን፤ አንድም ነገር አያተርፍም። አምካኝ ነው።
ሰው ለዚህ አውሬ መንፈስ የዶሮ ያህል ክብር የለውም። የሚቀርም፤ የሚተርፍም አንዳችም ነገር የለም። ይህን መከራ አርቆ ማዬት
ሟርት አይደለም። እዬሆነ ያለ ነገ ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው። ሰው ሁሉ በጭፍጫፊ ሲጫፈጨፍ ሳይ ይገርመኛል።
·
የማንነት ቀውስ አሪወሳዊነትን ወላድ ነው።
ሌላው በዚህ ውስጥ የምናዬው
ቁም ነገር አቶ ጃዋር መሃመድ ያለበት የማንነት ቀውስ ነው። የማንነት ቀውስ ያለበት ነፍስ በዚህ መልኩ አሪዋስዊነትን ምራኝ
ብሎ ከተነሳ መነሻውም መድርሻውም ጥፋት ነው። ዘመንን ማጥቆር፤ ምዕትን ማጠልሸት ተልዕኮው ነው። ውዶቼ አይቻልም ብላችሁ
አትሰቡት ቢሆን ብላችሁ እሰቡት? እምታጡት አንዳችም ነገር ይለም። ይልቁንም ትውልድን ታታርፋላችሁ። ስለ ትውልድ ቀጣይነት እና
ሞራላዊ ዕሴት እንጨነቅ። የአቶ ጃዋር መሃመድ ጲላጦሳዊ ጥሪ አለው። ጥሪው ደግሞ ክስመት ነው። ቧልቦላችን ለሚሉት ነፍሶች
እራሱ ምህረት የለሽ ጣምራ ሰይፍ ነው።
ትግሉን የሚመራ ልባም መንፈስ
ጠፍቶ 19 ወራት ሙሉ ውስጣችን ተቦርቡሮ፤ ተሸርሽሮ፤ ተመርምሮ ገቫሪ ሆኗል። ይህ የማያርመጠምጠው ነፍስ አሁንም „ለውጥ
እንዳይቀለበስ“ ይለናል። ሌላው ቀርቶ ብአዴን የነበረው ጥንካሬ አለን? ቀዝቃዛው ደህዴን የነበረው ለብታ አለን? ተሰልስሎ፤
ተሰብሮ፤ ደመ ነፍሳቸውን ነው እዬተወዛወዙ የሚገኙት። ለዛውም ሁለት ሦስት ቀንጣ ነፍሶች። ደህዴን ላይ አንዲት ነፍስ ከራስ
ጸጉራቸው እስከ ፊንጢጣቸው በሥልጣን፤ በሹመት የተነከሩ፤ ሁለት ብአዴኖች በዝምበሉን ደመቀወገዱ ያሉ።
·
የሥርጉትሻ ብዕር እና አቶ ጃዋር መሃመድ።
እኔ ያው ሙግት ነው መስመሬ።
ያልሞገትኩት ነፍስም ተቋማም የለም። ያልተሟገትኩለት አገራዊ ኃብት ነፍስም የለም። በሌላ በኩል ከእኔ ሙግት የተረፈም የለም።
ተርፎ ቢሆን እንኳን አሁን ባለው አፍቅሮተ አብይዝም የወደቀ ማናቸውም ነፍስ ተሰልቋል። ዘግይቶም ቢሆን አልቀረለትም።
የምሳሳላቸው፤ የምጠነቀቅላቸው ነፍሶች ቢሆንም ሥም ሳላነሳ በብዕሬ ሰንካላ መንገዳቸው እስቲበቃው ተወቅቷል። እንቅልፍ ላይ
ስለሆኑ። የቡና ፓለቲካ ስለሚያስፈልጋቸው። ከአብይዝም ፍቅር በስተጀርባ ያለው ግዙፍ የሚከረፋ፤ የሚጎፈንንነውን መከራ ዓይናቸውን
ገልጠው ማዬት ስለተሳናቸው። ኢትዮጵያ ቀራንዮ ላይ ናት።
በዚህ ሁሉ የብዕር ብራና
የሙግት ዘመኔ ቅንጣት ደቂቃ ጫን ያለ ጹሑፍ በአቶ ጃዋር መሃመድ ግን አቅርቤ አላውቅም። ለምን? እንዲህ በሙግት እሰጣ ገባ የሚሰከን ራዕይ ስሌለው። እሱ እሩቅ ነው። በጣም እሩቅ። እኛ አጭር ነን - ዱካ። እሱ ዝልቅ ፍላጎት አለው እኛ
የወሮች ነን - ዕለታዊ። ወረተኞችም ነን። ለዘላቂ ፍላጎትም፤ ጽኑም ሃላፊነት ለመወሰድን የፈቀድንም አይደለንም። ለደቂቃ ከእሱ
አንደበት ዕውቅና የሚገኝ ኢትዮጵያዊ ጠረን የለም። ለክፉ ስኬቱ መንገድ ለመጥረግ ካልሆነ።
የተጋሩ ሊሂቃን እራሱ የአባት
አደሩ ብልህነት የነጠፈባቸው ይመስለኛል። የእሱን አዋኪ ቅይጥ መንፈስ ማስጠጋት ምን ያህል ኪሳራ መሆኑ ገና አልተገለጠላቸውም።
እንዲያውም አሽኮኮ ያደረጉትንም አስተውላለሁኝ። ለመደርመሻ። ወደ ዩዲት ፍልስፍናዊ ግንዛቤ ዓይነ ልቦናቸውን ያብራላቸው።
አሜን። ያን ሲፈትሹ እሱና ሲኦል መንፈሱን መጥነው መንቀሳቀስ ይችላሉ። ሚዛን። አሁን አረና የመድረኩ ሆኖ ሊቀጥል ይሆን? ከቅኑ
አቶ አምዶም መንፈስ መቼም ይህን አልጠብቅም።
አቶ ጃዋር መሃመድ በጥልቀት
መሰናዶ ይጓዛል እኛ በግልቢያ፣ በምናብ፣ በፋንታዚ ሃኒሙን እንዳክራለን ወይንም እንቦጨረቃለን። አንድ ቀንጣ ነፍሱን
ይበልጠናል። በወረፋ በሉት፤ በደቦ ሲሰድቡት፤ ሲያቃልሉት አያለሁ። አንዳንድ ጊዜ አታውቁትም ብዬ ከሥር እጽፋለሁኝ። በብራና
ላይም እንዲሁ ጽፌያለሁኝ። በጥንቃቄ ሊያዝ የሚገባው ወጣት ነበር። ለፍርሻ ቅርብ ነው ስሜቱ። ለድማ ትጥቁ ሙሉ ነው።
ለስኬቱ ራሱን፤ ጤንነቱን ሳይጎዳ በጥንቃቄ ይራመዳል። ይበልጠናል። ልዩነቱ ይሄ ነው። ጎርፍ እና የዝናብ ውሃ አንድ ነው
እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋለሁኝ።
ዝናብ ከሰማይ ሲወርድ ንጹህ
ነው። መሬት ላይ ከአፍር ጋር ሲቀላለቀል ግን ይቆሽሻል፤ ወይንም ከበከተ ኩሬ ውሃ ጋር ሲቀላለቀልም እንዲሁ ተፈጥሮውን
ይቀይራል። ከወራጅ ወንዝ ጋርም ሲሆን መልኩ እና አወራረዱ ይለያል፤ ተራራ ላይ ሲወርድ ደግሞ ይለያል። በአንድ የዝናብ ጠብታ
ውስጥ ብዙ ትዕይንቶች አሉ። የትዕይንት ዥንጉርጉር ቡፌ። በእኛ አገራዊ ፍላጎት እና እራሱን ነፍሱን አገር አድርጎ በሚንቀሳቀሰው
መንፈስ ማህል ያለው ልዩነት እኔ እንዲህ ነው እማዬው። ቅኔ እንማር።
ለዚህ ነው የኢትዮጵያ ህዝብ
ግዕዝ በመደበኛ መማር አለበት ብዬ እምመክረው። በተለይ አማራው። በቄስ ተማሪነቴ በልጅነቴ ጀማምሬው ማቋረጤ ብዙ ነገር
አሳጥቶኛል። ከዚህ በላይ መሆን ይቻል ነበር በሥነ - ጹሑፉ አለም። የቤተሰብም ሊቃውንትነት ውርስም ነበር። እንደገና በግዕዝ
ውስጥ ሚስጢር አለ። ገኃዱን እና መንፈሳዊ ዓለምን አገናኝቶ የኪናዊ ቅብዕ ባለቤት የሚያደርግ።
·
ወደ ቀደመው ምልሰት ላድርግ።
የሚገርመው አቶ ጃዋር
መሃመድን የሚያጣጥለው፤ የሚንቀው፤ የሚወርፈው መብዛቱ ነው። እኔ ደግሞ ከዛ መደብ አይደለሁም። እንቀጣበት ዘንድ የተፈጠረ ልዩ የእርግማን የመዶሻ ጥሪ ያለበት ስለመሆኑ በጥልቀት እንቅስቃሴዎቹን ተነሳ
ከተባለበት ዘመን ጀምሮ ተከታትዬዋለሁኝ። ጎግማንጉግ የፉካሬ እዬሱስ ነገር ይመጣብኛል እሱን ሳስተውል። አለደንቀውም
አላንኳሰውም። አላኮርፈውም አላቀለውም። ውስጤም አያገለውም አይለግምበትም። አለማችን በዬዘመኑ እንዲህ ያሉ ከደቂቅ አንስት
የተፈጠሩ ወጣ ገብ፤ የክፉነት ሰብዕናዎችን አስተናግዳለች። ለዚህ አስፈሪው መጽሐፈ ሄኖክ ተንብዮታል። አቶ ጃዋር መሃመድን
እማዬው ከእነዛ አስፈሪ ፍጡራን ተርታ ነው። ስለዚህም አጠናዋለሁኝ። ጠንቁ የዓለም ነውና። አሁን ኦፌኮም አብሮነቱን ዓውጇል።
የመርገምቱ ልክ ቅርጽ ይዟል። በፊት ልቅ ነበር።
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ በተመጣጠነ
ሙቀት ፍጥረተ ነገሩን እከታተለዋለሁኝ። አዕምሮ አውልቆ የመትከል አቅም አለው። አሁን አቶ በቀለ ገርባ ያሉ ይመስላቸኋዋል።
ነገር ግን በተገጠመላቸው ቱቦ ነው የሚተነፍሱት። አቶ ሽምልስ አብዲሳም አለሁ ይላሉ። እሳቸውም በተተከለው አዲስ አንጎል ነው
የሚንቀሳቀሱት። ሌሎችም እንዲሁ። ከእሱ ጋር አንዲት ደቂቃ የቆዬን ስብዕና አይሆኑ አድርጎ ያዛውርዋል። ይበውዘዋል። እንደካርታ
ያሸጋሽገዋል። መስከረም 2011 ጉባኤ በኦህዴድ ጉባኤ ላይ የአቶ ጃዋር መሃመድ ላሙ ወለደች ቀን ብዬ ጽፌ ነበር። ያ የስለት
ዕለቱ ነበር። ቀዶ ጥገና የሚያሟላበት። ሌላው የጉባኤ ተሳታፊ በጭብጨባ ላይ ነበር። እሱ ደግሞ ኦፕራሲዮን ላይ ነበር። ያገኛቸውን ነፍሶች ሁሉ አዲስ የማያውቁት ሰብዕና ሸልሞ ነው የላካቸው። ብአዴንን ወክለው የተገኙት ገዳ ንጉሡ ጥላሁን እንደነበሩ
እንዳትዘነጉ።
·
ተግባሬ።
1) እኔ ሳደርግ የኖርኩት በመሸነፍ ወስጥ መሸነፍን እንዴት ጥሶ ማሸነፍ እንደ ቻለ ነው ሰብዕናውን በእርጋታ ሳጠናው የኖርኩት። ኢሳት ላይ የገጠመውን መገለል የተወጣበት
መንገድ እሱን ይተረጉመዋል። ሌላው ግን አይችልም። ወድቆ ይቀራታል እንጂ። ማንኛውም ጥቃቱን ተቋቁሞ አያገግም። ይልቅ አሁን
ከጨረሰላቸው ኢትዮ 360 እያዬሁ ነው። የጠቀማቸው ወላዊ ተጋድሎ ማድረጋቸው ይመስለኛል። እሱ ግን ብቻውን ዕጣ ነፍሱን ተጋፍጦ
ተፎካካሪ ብቻ ሳይሆን መሪ ሆኖ ነው ቁጭ ያለው። ከልባችሁ ሆናችሁ አቅሙን መርምሩት። ከጥላቻ ከተነሳችሁ ያቅታችኋል። ሚዛን
አልባም ትሆናላችሁ። ቅን ሆናችሁ ለኩት። አሁን የኢትዮጵያ መሪ ሃሳብ አፍላቂ ነው፤ እስትራቴጅም ነዳፊ። ይህ አይካድም።
2) በዛ ወቅት የነበረውን ተጽዕኖ ፈጣሪነት ድቀት፣ ወጀብ፤ ቸነፈር ሲገጥመው እሱን ለማካካስ የወሰደው እርምጃ እና ምላሹን
ባስተውሎት ላዬው ጃዋር ማለት ምን ማለት እንደሆን ያስተረጉማል። አቶ ጃዋር መሃመድ የተፈጠረበት፤ የተፈጠረለት ግጥግጥ አለ።
ቀደም ባለው ጊዜ የተፈታተኑትን
ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በዬተራ አሰልፎ ያንበረከከበት እልህ እና ስኬቱ እሱን ይገልጸዋል። በኦሮሞ ንቅናቄ እቤቱ ድረስ እዬሄዱ „ምን
እንርዳችሁ?“ ያሉትን ለናሙና መውሰድ ይቻላል። አሁን ያለው ደረጃቸውማ አይነሳ። የሰማይ እና የመሬት ያህል በድጠት ዳጥ አድርጎ
አድቅቆታል እስቲበቃው አሽቶታልም።
ይህን ሰው በማጥናት መንፈሱን
መግራት፤ ወደ አዎንታዊነት ሙሉ ለሙሉ ለማምጣት ደሙን የመቀዬር ያህል ከባድ ተልዕኳዊ ሥራ ነው። እሱን ቅን፤ አዎንታዊ፤ ሰዋዊ፤
የረጋ፤ በሃሳቡ ጸንቶ የሚቆይ፤ ተፈጥሯዊ ለማድረግ መሻት አዲስ የአያያዝ ተቋም ከፍቶ በመደበኛ
ሥራ መስራት ካልሆነ ከእሱ ጋር ቁጭ ብሎ ፖለቲካ በማውራት፤ በመሟገት፤ ዲያሎግ በማድረግ የሚጠፋ ቅንጣት ጊዜ ሊኖር እንደማይገባ
አምንበታለሁኝ። ለዚህ ነው ሞግቼው እማላውቅ።
የሚገርመኝ። በጹሑፍ፤ በቃለ ምልልስም
አንቱ የተባሉ ወገኖቼ የአቶ ጃዋር መሃመድን ሰብዕና ከሌሎች ሰላማዊ ሆነው ከተፈጠሩት ጋር አስተካክለው ድርጊቱን ሲያፎካክሩ፤ ሂስ
ሲያቀርቡ ይደንቀኛል። ዩዲትን
ማሰብ የተሳናቸው ይመሰለኛል። ልዩ ተፈጥሮ ነው ያለው። ቅንጣቱ
እንቅስቃሴው በተደሞ ሊመረመር፤ ሊጠና እና ፖለቲካዊ መቋጠሪያ ሊበጅለት ይገባ ነበር። ይሁዳ እና ወይንም ጲላጦስ እና ቅዱስ ጳውሎስን
ለሩጫ ፊሻካ ነፍቶ ተኩሶ ለሻንፕዮን ሜዳ ላይ ከመልቀቅ አይተናነስም። የትወልዱ መንፈስ ብክነት ያሳዝነኛል። ጠበቃም፤ ባለቤትም
ለሌለው መከረኛ ትውልድ በፈቃዴ ባለቤቱ ነኝ። እባካችሁን ለትውልዱ ዘመን ግርዶሽ እዬሰራችሁ አታደናግሩት። እባካችሁን? ቢያንስ
መንፈሳችሁ ለሚያዘንብለው ለፍደኛው የቁቤ ትውልድ እዘኑለት።
3)
ስለዚህም እኔ ቲካ ቲካ ብዬው አለውቅም።
እረግሜውም አላውቅም። እግር እግሩን እዬተከተልኩኝ ሞግቼው አላውቅም። እንዲያውም አልፌ ተርፌ ልጄ ቢሆን? ታናሽ ወንድሜ ቢሆን፤ በአንድ ቤት ብንኖር በምን ቋንቋ እንግባባለን? እንዴትስ ከጲላጦስ መንፈሳዊ ውቅያኖስ አውጥቼ የጠረኔ ቤተኛ ላደርገው እችላለሁ
እስከ ማለት ሂጄያለሁኝ። አብረን ሠራን በሚሉት ሰዎችም አዝናለሁኝ። ሳይውቁት ነበር አብረው የሠሩት። ቢያውቁት ወይ ይገሩታል
ወይ ይተረጉሙታል። አብረን ሠራን የሚሉ የፖለቲካ ሊሂቃን ይሁኑ የኢትዮጵያንዚም ሚዲያዎች ዛሬ ሳይሆን ዕድሜውን ከሰጣቸው ከዛሬ
በላይ እራሳቸውን የሚያደምጡበት ጊዜ ይመጣል። እሱ ጢባ ጢቦሽ ሲጫወትባቸው እንደባጀም ይረዱታል።
4)
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ እኔ ከላይ
ከጠቀስኩትም አልፌ በብዙ ተጉዤ እግዚአብሄርን ባገኜው ስለምን እንደ ፈጠረው እጠይቀው ነበር ብዬ
ሁሉ ጽፌያለሁኝ በ2017። ስለዚህ እንደ አንድ አክቲቢስት፤ ወይንም እንደ አንድ ፖለቲከኛ አይደለም ሳዬው የኖርኩት። በጨለማ ውስጥ ያለ ጥቅል፣ ጥልቅ
ነፍስ፣ የተከደነ ጊዜ የሚጠበቅ፤ ለተለዬ ጲላጦሳዊ ተልዕኮ የተፈጠረ እንደሆነ
እዬተሰማኝ ነው የኖርኩት። የሚመራው አሉታዊ ረቂቅ ክፉ መንፈስ አለ። አቅም እና ጉልበቱ ያነ ነው።
5)
በእሱ ጉዳይም ከሰው ጋር እንስቼ ተወያይቼበት
አላውቅም። መጀመሪያ አካባቢ ጠሚር አብይ አህመድ አቅርበው አዎንታዊ ያደርጉት ዘንድ ወትውቼ ነበር። ከሳቸው ጋር የሰሩ ሰዎች
ከሰጡት አስተያዬት ተነስቼ። ካራቁትም ችግሩን ሊወጡት እንደማይችሉት በማሰብ። ነገር ግን አሳቸው እራሳቸው ተጠላፊ ሆነው አረፉት። አሸነፋቸው በማራድ። እሳቸው እራሳቸው ምርኮኛ ናቸው ለጃራውያን። ያው ለኦነግ ሚስጢር ያቀብሉ እንደ ነበሩ
አሁን ከመሼ ደግሞ ሰምተናል። ለነገሩ የእሱን ልቦና ለማማለል ነው ያን ሥንኝም የተጠቀሙት። እንዲራራላቸው ይመስላል።
6)
አቶ ጃዋር መሃመድ እሱ የኦነግም፤ የኦፌኮም፤
የኦህዴድም አይደለም። የአብይዝም፤ የመረራይዚም፤ የዳውድይዚም፤ የሌንጮይዝም ወይንም የለማይዝም አይደለም። ከሁሉ የሚያሰጋው
ጭምቱ ለማይዝም ይመስለኛል። የሰላማዊው እስልምናም ነው ብዬም አላስብም። በዚህ ያሰለፋቸውንም በዬተራ ያራግፋቸዋል ቀኑን
ጠብቆ። አቶ በቀለ ገርባን ከቁጥር አይጥፋቸውም። ቻርጁን፣ አዳብተሩን ሲነቅለው እንደሚንከረባበሱ ጠንቅቆ ያውቀዋል።
በኢትዮጵያንዚም ዘንድ የነበራቸውን ተቀባይነት ከፎቅ አውርዶ ከስክሶታል። በዓለም አቀፍ የነበራቸው ተቀባይነትም እንዲሁ።
ፕሮፌሰር መራራንም እንዲሁ ወረፋ ሲጠብቁ ባጅተው በተራው ውድቀትን አጎናጽፏቸዋል። እሰቡት በብሄራው ብቻ ሳይሆን በዲፕሎማሲው
ዘርፍም ጭምር እንኩትኩታቸውን ነው ያወጣው። ለማይዝም በዲፕሎማሲ ዘርፉ ብዙም ዕውቅና ባይኖረውም በኢትዮጵያኒዝም የነበረው ዕውቅና
ምድማዱን አጥፍቶታል። አብይዝም ቢሆን እዬተሸራረፈ ጉድ ሠርቶታል። ቀውስ ይፈጽማል፤ አፍ እንዲዘጋ ያስደርጋል በዚህ ስበት እና
ስበቃ ቅቡልነት ይፈጠፈጣል። ይነጥፋልም።
7)
እሱ የጃራውያን ነው። መንፈሱ ቅይጥ፤ ስርንቅ፤
ቅልቅል፤ ዝንቅንቅ ዱራኛ እና ሊተረጎም የማይችል ድፍን ወይንም ጠፍጣፋ ወይንም ልሙጥ። ቀለምየለሽ። መጠኑም ለመለካት የማይቻል
ክፉ ዕሳቤ የከተመበት፤ እልህ እና ጭካኔ የታጨቀበት የቁጣ ስሜት አንጎል ነው። ሰብዕናው ግራጫማ ሲቃዊ ነው። እሱን በተከታይ
እናዬዋለን። ብሎጌ ላይ ያለ ቀድሞ የተጻፈ ነው። እንደ አጀንዳ ሳይሆን እንደ አንድ አሉታዊ ሉላዊ ክስተት ስለሆነ እሱን ነጥዬ
ነው ሳጠናው የኖርኩት።
8) እንደሚሰማኝ ጠሚር አብይ አህመድ በሥልጣን ተርማቸው ከስሜን አሜሪካ መልስ „በቡና ፖለቲካ“ የተደራደሩበት
የስምምነት ድፍን ቦንዳ ሰንዳ እንደ አለ ይሰማኛል። ለግራ ቀኙ ፍላጎት ተፈጻሚነት እንቅፋት ይሆናሉ የሚሉትን እዬከሉ። ለራሳቸው
መስመር ሆነ ለጃራዊው መንፈስ አይመቹም የተባሉትን በትእዛዝም በራስ ፈቃድም ሲደረመስ ባጅቷል። ይህ የተከወነው ከስሜን አሜሪካ
ጉዞ ጋር ነው ብዬ አምናለሁኝ። ትሪቲው ግን ስውር ነው። የእሱ አለቅነት ብልጫ አለው።
9) ጠሚር አብይ አህመድ ጥድፊያቸው በዚህ የሥልጣን የጊዜ ዕድል ተጠቅመው፤ በአፋቸው በሚደልሉት ኢትዮጵያኒዚም አቅም
መሰላል የኖቤል ሽልማት እና የቀጣይ የስልጣን ማስጠበቂያ፤ ማጠበቂያ ዓለም አቀፍ አቅምና ዕውቅና መፍጠር ህልማቸው ነበር።
ብልጽግናውን በዚህ ውስጥ እንደ ሐዋሪያ ነው ለእሳቸው። ተቋርጠው ወይንም ተንሳፈው እንዳይቀሩ የጃዋሪይዝምን ፍላጎት በግንባር
ቀደም በማስፈጸም በአንድ ትክሻ፤ በሌላው ትክሻ ደግሞ የራሳቸውን የሥልጣን ዘመን የማስቀጠል ሲናሪዮ ነው የነበራቸው። ለዚህ
የተገበረው የሰው ልጅ ሰቆቃ አንዳንድ ትንንሽ አገሮች ያላቸው ሙሉ ህዝብ ያህል ነው። የሞተውን፤ የተሰዋውን፤ በሥነ - ልቦና
የተጎዳውን፤ የተፈናቀለውን ስታሰሉት። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ያን የሰብዕዊ መብት ንፍገት እዬጠቀጠቁ ወደፊት
በሚያደርጉት ጥድፊያ ከጃዋሪይዝም ጋር ግጭት ወይንም ስበቃ እንዳይፈጥር ሌላውን እዬተጫኑ እና እዬደፈጠጡ ወደ 16/17 ወራት
ተጉዘዋል።
10)
እኔ 16/ 17 የማደርገው የ100 ቀናት ጉዟቸው
ጤናማ እና የመንፈስ ጠለፋ ያልተካሄደበት፤ በሙሉ ክህሎታቸው እና አቅማቸው የተጓዙበት ነው ብዬ ስለማምን ነው። ያው ነገረ
አማራን ከጥዋቱ ነው መጫን የጀመሩት እሱን ታገስ ብዬ ማለት ነው። በዚህ ውስጥ የጥቅምቱን የ2012 ግርግር አፈጣጠር „የባለ
ሁለት መታወቂያ ቃና“ እና ክብሪት አስተውላችሁ፤ የፈጠረው ቀውሱ እና ሉላዊ ውጤቱ፤ የዓለም አቀፍ ንቅናቄ ዕድምታው ከምርጫው
የመሳተፍ መብቱ - ከአሜሪካዊ ዜግነቱን የማስመለስ አመክንዮ ጋር ስታገናኙት ራሱን የቻለ ሌላ ጅረት ይፈጥራል። ሁለቱንም ጠሚር
አብይ አህመድ ማለት እና አቶ ጃዋር መሃመድ ማለትን ያሳያችኋል። በተደሞ ታደሙበት። ትርፍ እና ኪሳራውንም ለኩት። ያን
ለማጣጣት የኦፌኮን ካታሊስትነት ወይንም ጆከርነትንም አከልላችሁ አዳምጡት። ቀላል ቀመር አይደለም። የኢትዮጵያዊነት የፈተና ልኬታ
ያሳያችኋል።
11)
አሳዛኙ ትራጂዲ የህዝብ አደራ እና የአገር
ህልውና አጀንዳ የሁለቱ የኦሮሙማ አጤዎች የመፈታተኛ ማሳ ሆኖ፤ እንደ ጥንቸል የመሞከሪያ ጣቢያ፤ ህዝብ የከፈለው የዘመናት
መስዋዕትነት መና ሆነ። በማህል የአቶ ለማ መገርሳ እና የአቶ አባ ዱላ ገመዳም እጅ ለአዎንታዊም ሆነ ለአሉታዊም ሁኔታ እንደ
ገባሪ ወንዝ ያገለገለ ይመስለኛል። ዋናው የመሪዎች መሪ ሆኖ የባጀው ግን ስውሩ እጅ ጃዋሪይዝም ነው። ጉዝጓዙ ከኦዴፓ ያለነሰ
ኦፌኮ መሆኑን ዕድምታውን ያጦዘዋል። ኦነግም የነፍስ አባት ነው ቀውስ እና የኦሮሞ ፖለቲካ አንገት እና ማተብ ናቸውና።
በዚህ ውሎ ጉዞው በጠፋበት ሂደት
ሥውሩ እጅ ልውስ የፖለቲካ አቋም ያለው ኦፌኮ ከፍ ያለውን ድርሻ ወስዶ የጲላጦስ መንፈስ ማረፊያ - ማህደር፤ የፍርሻ ስምምነት የህሊና
ማሳ ነበር ማለት ነው አሁን ከምንሰማው መረጃ አንጻር። ለመሆኑ መድረክ ግን አድራሻው የት ይሆን?!
የሆነ ሆኖ ይህ ነው ያልገባቸው
ተደማሪ ፖለቲከኞችም፤ ተደማሪ ሚዲያዎችም፤ ተደማሪ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፤ ተደማሪ አክቲቢስቶች፤ ተደማሪ ጋዜጠኞች፤ ተደማሪ የፖለቲካ
ተንታኞች፤ እና የኢህዴግ የግንባር አባል ድርጅቶች፤ እንዲሁም አጋሮችም እህት ነው ወንድም ድርጅት የሚሏቸው። የሚመራቸው ኃይል
ማን እንደሆኑ ገና አልተከሰተላቸውም።
አብሶ ብአዴን በቁሙ ያለቀ እርካሽ ድርጅት ነው። ዋጋው የወደቀ። አገርን ቀጥ አድርጎ ሚዛን አስጠብቆ መምራት ሲችል የድቡሽት ቤት ማህበርተኛ
ሆኖ አረፈው። ተጠማኝ። በታሪክ ተጠያቂ ሊሆን የሚገባው ድርጅት ብአዴን ነው። ከዚህ ሁሉ ምስቅልቅል አገር እንዳትወጣ ሸፋን በመስጠት፤ አቅም በመሆን ሰፊውን ድርሻ ተውጥቷል
ግርባው ብአዴን። የነገው የመከራ ስንቅ አደራጅም ይኸው ድርጅት ነው። ዕውነትን ሸሽቶ የትም አይደረስም። ቁርጥ ያጠግባል። ያው
ለውርስ መሰጠቱንም ክድን አደርጌ ልለፈው። ሌላም ተደራቢ አጤ ስላለበት - ብአዴን።
·
የመጽናኛ ቋቴ የነበረው።
ትንሽ የመጽናኛ ቋቴ የነበረው
ባሰለፍናቸው የራረሮት ወራት አቶ ጃዋር መሃመድ የፖለቲካ ድርጅት አለመፍጠሩ ነበር። አሁን መጽናኛዬ ነኩቷል። ይህ ሥም የለሽ
አሉታዊ ክስተት፤ የወደፊት የሉላዊው ዓለም ብርቱ ጠንቅ መነሻ የፖለቲካ ድርጅት ሆኖ መሬት ይዟል። ፋሺዝም በኢትዮጵያ ሰተት
ብሎ ተቋማዊ ሆኗል። አሸባሪነትም ሙሉ ህጋዊ ሽፋን ተሰጥቶታል። ከተራ አክቲቢስትነት ፖለቲከኝነት ሲመጣ ምርጫ ቢካሄድ እና
የፓርላማ አባል ከሆነ የአለመከሰስ መብቱም ይጠበቅለታል ማለት ነው። እርግጥ ነው የዜግነት ጥያቄው እልባት በቅርቡ ካገኜ።
በነገራችን ላይ ኦፌኮን ምርጫ ቦርድ እንዴት ያስተናግደው ይሆን? ድርብ ዜግነት ያለው ነፍስ አባል አድርጓል ይህም ጫን ያለ ፈተና ነው እንደ ሲዊድን አገር የምርጫ አስፈጻሚነት
እራሱን የሚያዬው ኢትዮጵያዊው የምርጫ ቦርድ።
·
የስጋት ማዕዶት።
እኔ ለደቂቃ እሱ የተገኜበት
ቦታ ሁሉ ያሰቀቅኝ የነበረውን እንዳሻው ሁለት ዓመት ሙሉ በሰፊ የመንግሥት ጥበቃ ዋኜበት፤ ዳነሰበት። እያንዳንዷ ቀን ስንት
ሰዓት አለው? 24፤ እንያንዳንዱ ወር ስንት ቀን አለው? 30 ቀን። 19 ወራትን ስንት ሰዓት? ስንት ደቂቃ? ስንት ቀናት
ነበሩት? እኔ የቁጥር ተማሪ ስላይደለሁ እባካችሁ ክብረቶቼ አስሉት።
እያንዳንዱ ደቂቃ ለእሱ
የተግባር ማሳው ናት። እንኳንስ ወደ ሁለት ዓመት ለሚጠጋ። እምትፈስ ጊዜ የለችም። ለእሱ ሰከንድ ጠበል ናት። ዓላማ ያለው ወጣት ነው። አገር
እንደገባ ያደረገው ሃጂ መሆን ነበር። በዛን ወቅት ምን ሰርቶ እንደመጣም አይታወቅም። ሃይማኖቱን ወዶት አይደለም። ስለምን ይህ
ህልም ከነበረው ከለውጡ በፊት አልከወነውም? እኔ የሚረዳኝ በዚህ የማስመሰል ካባ ሥር የሚያስገብረው ሚሊዮን ቅን መንፈስ አለ።
ሌሎችን የኦሮሙማ የፖለቲካ ሊሂቃንንም በአረቡ ዓለም የላቸውን ተቀባይነት እና ታአማኝነት ያመክነዋል። ይህም የተከደነ ሲሳዩ ነው።
እንደ አትራፊ አምክንዮም ታይቶ አያውቅም።
ይህም ብቻ አይደለም በዛን
ወቅት ቃለ ምልልስ ሲሰጥ ኬኒያም ሄዶ እንደ ነበር ነግሮናል። እንዲያውም በስዋህልኛ፤ በሱማልኛ እና በኦሮምኛ በሦሰት ቋንቋዎች
ኬንያ ላይ ስትዲዮም የOMN ሊከፍት እንደ አቀደ እና ከዛ የሚገኙ ኢሊቶችን አግኝቶ በቀጣይ የፖለቲካ ሃዲድ አዘረጋግ ላይ
እንደተወያዬ ምሩን እንዳሉት ሁሉ ሲገልጽ ሰምቻለሁኝ።
በወቅቱ ይህንም ተከታትዬ
አፍሪካ ቀንድ ሊገጥመው ስለሚችል ፈተና ለቅኖቹ ለቀንበጥ ብሎግ ታዳሚዎቼ አብስዬ ጽፌ መንገዱን እንዲከታተሉት አስታውሻቸው
ነበር። ይህ ሁሉ ሲሆን የእኛ አገር እንረከባለን የሚሉ ፖለቲከኞች ለአብይዝምወለማይዝምወታከለይዝም አቅም መወጮ ላይ
ፕሮፖጋንዲስት ካድሬ ሆነው ሲታትሩ ነበሩ። እራሳቸው አክቲቢስት ሆነው አረፉ ለኦሮሙማ ፖለቲካ። በሳል ፖለቲከኛ ለማፍለቅ ማን
ያምጥ? ምንስ ማህጸን ያፍልቅ?! ቁልጮ!
አቶ ጃዋር መሃመድ ሞት
ካልቀደመው ሁሉንም ጥሶ፤ ሁሉንም ረጋግጦ፤ ሁሉንም ጨፈላልቆ ይወጣል። እኔ ሳጠናው በኖርኩት ዘመን ሁሉ ሲያሸንፍ እንጂ ሲሸነፍ አይቼ
አላውቅም። ሲያንበረክክ እንጂ ሲንበረከክ አይቼ አላውቅም። ስሜታዊነቱ ሲነሳበት ሌላ ሰብዕና ያጨዋል የጨለማው
ዓይነት ይሆናል። ሰከንኩ ሲል ደግሞ የላዩን ከታች፤ የታቹን ከላይ አመሳቅሎ ግን አልሞ ደቁሶ ያዘናጋኃል። ለክፉ ጥሪው በዥንጉርጉር
እንጉርጉሮ እያዋዛ፣ እዬጋለበ ይሄው ተዚህ ተደርሷል።
የብዙ የኦሮሞ ሊሂቃን
ሙልጭልጭነት እያስተዋልን ቢሆንም የአቶ ጃዋር መሃመድ ግን ለትርጉም የሚቸግር ነው። በህይወቱ የእኔ የሚለው የሚወደው ነገር
ቢኖር ልጁ እና እናቱ ብቻ ይሆናሉ ብዬ አስባለሁኝ። በፖለቲካ የሚያምነው ብዬ እማስበው ደግሞ ጃዋራዊው አቶ ንጉሡ ጥላሁንን
ብቻ ይመስሉኛል። የተጋመዱበት የተልዕኮ ውል ያላቸውም ይመሰለኛል። እሳቸው የመከራ ዘመን ናቸው ለኢትዮጵያ። አስኳልም ናቸው
ለጃዋሪይዝም መስፋፋት፤ መንሰራፋት፤ መለምልም እና ማስበልም። ለአማራ ህዝብ ደግሞ የእሾኽ አክሊል። ጭነት።
ከጠሚር አብይ አህመድ ጋር
እንዲሰሩ ሲደርግ የአቶ ጃዋር ሰክርታርያት በቤተ መንግሥት ብዬ ጽፌያለሁኝ። በዚህ ጊዜ ውስጥ „አገሪቱ፤ ጠሚሩ“ ሲሉ ነው
የሚደመጡት። ለምን? ስለምን? ምን አስማማቸው ብዬ ስጠረጥር እሳቸውም ጎንደር ጠል ናቸው። እዛች ባዕት ተከስተው አያወቁም።
የብአዴን ዝግጅት አጋጣሚ ሲኖር እሳቸው የሚገኙበት ከሆነ ሽዋ እና ወሎ ነው የሚያሰናዱት። እኔ ውስጥን አተኩሬ ስለማጠና
ያስተዋልኩት ይህን ነው። ከአቶ ንጉሱ ጥላሁን የተረፈው የጃዋሪይዝም የኦሮሞ ሊሂቃን ተከታይ ግን ለጊዜ ማማሻ እንጂ ተራውን
እዬጠበቀ መጋዝን የሚወረወር ነው የሚሆነው። ምን አልባት ከተረፉ ከተረፉ „የፌስታል ፖለቲካ እና የወራጅ የለም ፖለቲካ“ ባለሙሉ ባለሥልጣን
አቶ አዲሱ አረጋ ሊሆኑ ይችላሉ። ዕድል ከቀናቸው። ወፊቱ ካወጣቻቸው።
·
የፍርሻ የማዕዘን ድንጋይ ጃዋሪይዝም።
አሁን ኦፌኮ እርስተ ጉልቱ
ነው ለጃራይዚም
ተልዕኮ አንኳን ደህና መጣህ ብሏል። ያሳፍራል። ቋቅ! ይህ ድርጅት የሚፈልገው እሱን እጬጌ እስኪያደርገው ድርስ ነው። ከዛ
እንደ አሮጌ አካፋ እና ዶማ ነው የሚሆኑት ሁሎችም። ለእሱ የደቂቃ ተግባር ነው። ሲያፈርስ እንጂ ሲገነባ ታይቶ ይታወቃልን?
የተጠጋው ነገር ሁሉ ለፍርሻ አዋጅ ነጋሪ አስነጋሪ ነው። ለፍርሻ የማዕዘን ድንጋይ ነው። የተፈጠረውም፣ ጥሪውም ለፍርሻ ነውና። ፍርሻው
ደግሞ የጎሼ ፍርሻ ነው። ጠንቅ ስለሚተክል። እሱን እና ሌሎችን ቅን መንፈሶች ለፉክክር የሚያቀርቡ ነፍሰ የዋህ ሰብዕናዎች
ፈጣሪ / አላህ ይቅር ይበላቸው የሚያደርጉትን አያውቁትም እና። አሜን!
የማዝነው እሱ ውጭ አገር
በነበረበት ወቅት የእሱ አንደበት የነበሩ ቋሚ ኢትዮጵያዊ ሚዲያዎች የሸለሙት የሰብዕና የግንባታ ሂደት እና የገነቡለት የአቅም
ጥሪት ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ሆነ ለአለም ጠንቅነቱ ነገ መኖሩ ከተገኜ ሁሉም ያዬዋል። አሁን ውይይቱን ሳዳምጥ ስለ
ኦፌኮ የእሱ መቀላቀል ተቀባይነት ምንትሶ ቅብጥርሶ ነው። እም። ይሄ ነውን የሚያስሰበው ሰውን ሁሉ? ለዓለም የስጋት ቀጠና ነው
የኦፌኮን የፖለቲካ ሰብዕና ዕውቅና ምሪት የሰጠው። ኦፌኮን ሊወገዝ የሚገባው በዓለም አቀፍ ደረጃ ነው። ፋሺዝም በኢትዮጵያ
ቀጣዩ ፍዳ ነው። አፍሪካም አይቀርላትም። መርዝ ታቅፎ ኢትዮጵያንም አፍሪካንም ማሰብ ከንቱነት ነው።
አቶ ጃዋር መሃመድ አንድ ሰው
አይደለም። አንድ ሰው አልነበረምም አይደለምም። እሱ በዝምብሎሽ በመደዴ የሚተረጎም ወጣት አይደለም። አዶልፍ ሂተለርን እሰቡት።
እንዴት እንደተነሳ እና እንዴት የዓለም ጠንቅ እንደሆነ። አሁን የዓለም ፈተና ተጀምሯል ከትናንት በስትያ በ29/12/2019።
ለዚህ ተጠያቂው የኢትዮጵያ መንግሥት ነው። ግን መንግሥት ነው አሰተዳደር ነው ያለው? ይህም አይታወቅም።
መንግሥት ነኝ ካለ ግን እሱን
በቅድሚያ በወንጀሉ ሊጠይቀው ሲገባ ህግ በእሱ ላይ ስለማይሰራ ይልቁንም የፖለቲካ ተወዳዳሪ፤ ተመራጭም፤ ቁንጮ አድርጎ ለማውጣት
በተከደነ ውስኔ ታቅዶ እዬተከወነ ነው። ትናንት፤ ዛሬ፤ ወደፊት ስለሚጠፉት ነፍሶች ጠያቂ የሚሆንም፤ ተጠያቂ የሚሆንም የለም።
ልቅነት፤ ስድነት። ይህን ስታሰቡት ባዶነት ይሰማችኋዋል።
አመድ አስነስንሶ ሱባኤ የሚያስገባ ፈተና ላይ ነው ኢትዮጵያ ተሰቅዛ ያለችው።
ለእርድ የሚቀርቡ ዜጎች እልፍ
ይሆናሉ - ነገ። መዳን ወይንም መነሳት በእንቅልፋችን ልክ ይወሰናል። የሚያሳዝነው ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንዳይቸር ጠሚር አብይ
አህመድ ጠንካራ የሆነ የማዘናጋት ተግባር እዬፈጸሙ ነው። እንቅፋት ፈጣሪው ዋናው እሳቸው ናቸው። ፈተናው ፈተና ነው ከምል
የዕርግማን ዕዳ ናዳ ብለው ይሻላል።
·
የወደፊት የዓለም የስጋት ቀጠና ኦፌኮ ይሆን ይሆን?!
በድብልብል
ፍላጎት ከተፈጠረ ጀምሮ ኢትዮጵያን ሲያምሳት የኖረው ኦፌኮ አሁን ድል ላይ ነው። አፉን ሞልቶ፤ ደረቱን ነፍቶ የመጪው
የኢትዮጵያ ህልውና በመዳፉ ውስጥ እንደገባ እዬነገረን ነው። የሰሞናቱ ኢሳት ሚዲያ ላይ ጫን ጫን እዬተተነፈሰ ብትወዱም
ባትወዱም በሚል የእርግጫ መግለጫ ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ስጥተዋል። የፕሮፌሰር መራራ መራር ማንፌስቶ በሚል ጽፌዋለሁኝ።
በዛ ቃለ
ምልልስ የልባቸውን ነገረውናል። „አብረን እምንቀጥል ከሆነም“ አለበት። ከቅኔያዊ ጥቅል መርዝ በተሻለ ሁኔታ አፍታተው
ህልማቸውን ነገረውናል። ወዮላችሁም ተብለናል። የፈረደበት የአዲስ አበባ ህዝብ የእስራኤል እና የአረቦች እጣ ፈንታ
ይገጥማችኋልም ተብሏል። ድርጭት ሚዲያ ሲከፍት፤ ድርጭት ነጋሪት ሲጎስም። በህወሃት ዘመን ድርጭት መለያ ምልክት ነበር እና ለኦፌኮን።
ለነገሩ ለማሽላ አጨዳ የተሰለፈው ሁሉ ዕድሜ ለገበርዲን እና ለከረባት እኛው በሰጠነው አቅም ዛሬ ያዙኝ ልቀቁኝ ሆኗል።
ወደ ፕሮፌሰሩ
ስንመጣ በሳቸው ዘንድ መታበይ እንብዛም አይቼ ባለውቅም በዚህ መግለጫ ግን ልኩን የጠሰ በራስ መተማመን አይቻለሁኝ። ልክ የጣሰ
በራስ መተማመን አንባገነንነትን፤ ሲያንስ ደግሞ የበታችነትን ያመነጫል። ሲመጣጠን ነው ለአገርም ለትውልድም የሚበጀው። 100ሚሊዮን
ህዝብ ከቅንጣት አልቆጠሩትም። ዓለም እንዲነቃ ስላልተደረገም የሚመጣ የለም ዓይነት ነው። ኢትዮጵያኒዚም አብይዝም ካስተኛ፤
አማራን የአብይ ሌጋሲ ቅስሙን ሰባብሮ ካንበረከከ ሌላ ኃይል አለ ብለው አላሰቡም። ፈጣሪ አላህ እንዳለ እንኳን ማሰብ አልፈለጉም
የፖለቲካ ሳይንቲስቱ ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና።
እኔ
እንዲያውም የተባባሩት
መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ኃይል ኢትዮጵያ ቢገባ ምኞቴ ነው። አሁን ሁሉም በር ክፍትፍት ብሎ ያሻው እንደ አሻው ገብቶ የሚወጣበት አገር ሁናለች - ኢትዮጵያ።
አገር ጠበቂ መንግሥት አለ ለማለትም አይቻልም። የቄሮ ኢንፓዬር ቢሆን ለብጥብጥ እና ለህውከት የተሰለፈ ነው።
እርግጥ
ነው በተከታታይ ኦሮሙማ የሚያሰለጥነው ጦራቸውን በዬዙሩ እያሳዩን ነው ልክ እንደ ሶሻሊስቱ ዓለም ኦዴፓ። የጉለሌው ንጉስ አቶ
ዳውድ ኢብሳ፤ የኬምሲው መስፍን ብጄ ከማል ገልቹ፤ ጫከኛው አቶ ጃልመሮ፤ ከንቲባ ታከለ ኡማ /ኢንጂነር/ በዬፊናቸው ሠራዊት በህጋዊነት ያሰለጥናሉ ያስመርቃሉ፤
የኢትዮጵያ መንግሥት ሙሉ ሎጅክስቲክ ይሰጣል። ይገርማል። በዚህ ሁሉ ውስጥ ለተጨማሪ ስቅዛት የናዚ መንፈስ መቃብር ፈንቅሎ
ተቋም አግኝቶ መውጣቱን እያዬን ነው።
·
ምን ይደረግ?
ውጭ
የሚገኙ ሊሂቃን በአዲስ አቅም መነቃነቅ ያለባቸው ይመሰልኛል። አዲስ ማህበራዊ ንቅናቄ መፍጠር። እርግጥ ነው የዲሲው ባልደራስ
የጀመረው ነገር አለ። ያ መልካም ነው። አሁን የኦፌኮ ፋሺዝምን አዝሎ መነሳት የውጩ ሊሂቃን ከዛም በላይ መሄድ እንዳለባቸው
የሚያውጅ ይመስለኛል። የቄሮ ኢንፓዬር ብቻ ሳይሆን የፋሽታዊ ዕሳቤ አገራዊ የመሆን መከራ ተደቅኖ ነው የሚገኜው። የሚገርመው
የአቶ በቀለ ገርባን ማንፌስቶ ባልሂ ያለው አልነበረም። የአንድ ሰሞን ዘመቻ ላይ ብቻ ነበር ሆኖ የቀረው። ልብ ያላቸው ግን
ለሚመለከተው አካል ልከውታል። እሱ ብቻ ሳይሆን ይህ ፋሽሰታዊ መንፈስ ዩንቨርስቲ ላይ ህጋዊ መምህር መሆናቸውን አክሎ። ዛሬ
ዜግነት ሉላዊ ነው። ጠንቁ ዓለምንም ይነካል እና።
ሌላው
በርዮት ሚዲያ እና በቁም ሰማዕቱ ዶር አብርኃም አለሙ የተተረጎመው የዴሞክራፊ ፍልስፍና በተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉመው፤
የሰሞናቱ የፕ/ መረራራ ሦስተኛ ማንፌሰቶ አስመልክቶም በቅጡ አትኩሮት ተሰጥጥቶት ለሚመለከታቸው የመንግሥታት እና ለሰባዕዊ
ድርጅቶች መቅረብ ይኖርባቸዋል። የአፍሪካው ህብረትም ሊያውቀው የሚገባ ጉዳይ ነው። ምክንያቱም አፍሪካንም የመወረር ሰፊ ንድፍ
አለና።
ሂደቱ ሲጠና
ናዚ ተነሳ ፋሺዝምን ከመቃብር ሊያስነሳ።
ስለዚህ አክሳሪውን
ሽልት „አክ ወሬን“ በቁሙ ቀብሮ ለማያልቀው ተጋድሎ በትጋት፤ በቁርጠኝነትና በጽናት
ግን ከጥላቻ፤ ከቂም፤ ከማግለል፤ ከእርግማን፤ ከመበሻሸቅ ፖለቲካ ወጥቶ ነፍስ ያለው መስመር ቀይሶ ትውልድን ማትረፍ ይገባል።
መራራ ጉምዛዛ ሁኔታ ላይ ነን። ፍሬ ከመፈጠሩ በፊት ሲያር ነፍስ አርፋ መቀመጥ የለባትም።
ይህን
ዬትኛውም ዞግ ሙሁራን ፊት ለፊት ወጥተው በውይይት፤ በዲያሎግ መልክ እንስይዘዋለን ብለው ጊዜ ከሚያቃጥሉ ቋሚ በሆነ፤
ተከታታይነት ባለው የሎቢ ሥራ ዓለምን ከጎን ማሰለፍ ይጠይቃል። ኦፌኮን ኢትዮጵያን በቁሟ ነው የገደላት። የኢትዮጵያዊነት
ተዝከሩን የናፈቀ ወሳኔ ነው ኦፌኮን የወሰደው።
·
ራዕዬ ጃዋሪይዝም።
ራዕዬ
ጃዋሪይዝም + ጃራዊይዝም የኦሮሞ ንጉሥ መሆን ብቻ አይደለም ህልሙ። እንዲህ የሚል ቃለ ምልልስ አይቻለሁኝ። ብዙ ሰው
አዳምጦታል። ያ የተሳሰተ መንገድ ነው ትጥቅንም ያላላል። መከራውን በስፋት ያጠናም አይመስልም። የጃዋሪይዝም አነሳሱ፤ ራዕዩንና
ፍላጎቱ እንደ ገና የሰብዕዊነቱ ደረጃው ሲመዘን በጭካኔ ውስጥ የቀለመ የዓለም አሉታዊ ክስተት መሆን ነው።
ለዚህ
ደግሞ እስከ አሁን የመጠባቸውን ጉዞዎች ልብ ብሎ ለተከታተለ፤ አቅዶ ሳያስፈጽመው ይቀራዋል ብሎ ለማሰብ ይቸግራል። ቁርጥራጭ
የአገው፤ የቅማንት እያለ አማራ ክልል የጀመራቸው ጅረቶቹን እራሱ አጉልብቶ ለእሱ በሚመች መልኩ ያንጻቸዋል። ጎንደር የቅማንት
ዋና ከተማ የማትሆንበት ምንም የሚገድበው አንዳችም ኃይል አይኖርም።
ያልቻለው
ትግራይ ላይ ብቻ ነው። እንደ ጃዋራዊው ገዳ ንጉሡ ዓይነት ጠረነ እሾኽ እትጌ ትግራይ አልገጠማትም። ስለዚህም አውልቆ መግጠም
አልቻለም። እትጌ ትግራይ ጋራጅ ለማስክፈት ስላልፈቀደች። አቅሙ ሲጎለበት ግን ጥሶ የመግባት ምኞት እና ህልም የለውም ለማለት
አይቻልም። የመጀመሪያው የጠሚር አብይ አህመድ ጋዜጣዊ መግለጫ ይመሰልኛል ከተሳሳትኩ እታረማለሁኝ „ኦሮሞ የሌለበት የኢትዮጵያ
ክፍል የለም ካሉ በኋላ ትግራይ የራያ ኦሮሞ አለ“ ሲሉ አድምጬ በወቅቱ በቀንበጥ ብሎጌ ሙግት ጽፌ ነበር። ድልዳሉን በህሊና የመሰናዶ ት/ቤት
ስለሰሩ አቅሙ ሲገኝ አይሆንም ብሎ ማሰብ ጅልነት ነው።
በሌላ
በኩል ደግሞ የሰላም ሚኒስተሯ ይቅርታ የዋይታ ሚኒስተሯ ወ/ሮ ሙፍርያት ካሚል ስለ አማራ የህልውና ተጋድሎ አይደለም ጭንቃቸው፤
ስለራያ ወልቃይት ጠገዴ አልነበረም ጉዳያቸው፤ ከዛ ስለሚሰቃዩት ህጻናት አልነበረም ትኩረታቸው አጀንዳቸው ቅማንት ነበር። ጭልጋ
ሰራባ ድረስ እንደሄዱ ዜና አዳምጫለሁኝ። ልክ ለኤጀቶ አቅም ተሰጥቶ ሲዳማ የራሱን ክልል እንደ ወሰነው ማለት ነው። ይህን
የሚያደረገው የጠሚር አብይ አህመድ መንግሥት ነው። ሽፋኑ ይሄ ነው። ማዘናጊያው፤ ማስተኛው። ሥልጣኑ ግን ጃዋሪይዝም ነው።
ጉዞውም ወደ ጃራውያን ነው።
·
ነገረ ለማ።
መቼም ደከምን
በኦሮሞ ፖለቲካ። እግረ መንገዴን በአደብ እንዲመረመር የምሻው ነገረ ለማይዝም ነው። ነገረ ለማ እራሱን የቻለ የጥናት የምርምር
ማዕከል ነው። „የምሥራች ነው የአቶ ለማ እንዲህ ይፋዊ ፍላጎት መታወቅ“ የሚል ዕድምታም አዳምጫለሁኝ። በልዩነት ውስጥ
የምሥራች ለእኔ አይታዬም። ልዩነትም የለም። የዓላማ የግብ ምንም
ቅንጣት ልዩነት የለም። ታክቲክ ስትራቴጅን አይተካም። የራሳቸው አፈጠጠር እና ግብዕት አላቸውና። ከዋሽንግተን ስብሰባ መልስ ሚኒያ
ላይ አቅላቸውን፤ የንግግራቸውን ምት ላዳመጥ ድንቅ ነገር አለነበረም የሰሞናቱ ኑዛዜ።
የሆነ ሆኖ
ጽሞናቸው፤ እርጋታቸው የሚመሰጥ ሰብዕና ያላቸው አቶ ለማ መገርሳ ፖለቲካዊ መንገድም ገና ድፍርስ ነው። የሚታወቅ ነገር የለም።
አቶ ለማ መገርሳ ልታይ ልታይ የሚሉ አይደሉም። አደብ አላቸው። ማይክ ናፋቂም አይመስሉኝም። እንደ ጎንደሮች ቅኔ „ሙያ በልብ“
ናቸው።
በቀጣዩ
የኃይል አሰላለፍ በጃዋሪይዝም ሥር እንደ ፕ/መራራ ጉዲና ይወድቃሉ ብዬ ለማስብ ይከብደኛል። የራሳቸው መርኽ፤ የግላቸው መንገድ እና ራዕይ ያላቸው ናቸው ብዬ
አስባለሁኝ። አቅም ተጠማኝም አይመስሉኝም። በፖለቲካ አካሄዳቸው ከሁሉም የተሻሉም ናቸው። ጥሩ ማህንዲስም ናቸው። የለማይዝም
ተከታይ የወደቀው „ኢትዮጵያ ሱሴ ናት“ ፖለቲካቸው ነው እንጂ ሌላው የኦሮሙማ ፈርስት ፍልስፍናቸው፤ ግባቸው ገና አቅጣጫው
ያልታወቅ የመከራ ቋት ነው። ማንን እንደሚቀላቀሉ አልታወቅም።
በመንግሥት
መዋቅር ያስቀመጧቸው የባለሙያ ሙሁራዊ አቅሞች ሁሉ መንፈሳቸው ሃዲድ አይኖረውም ብሎ ለማሰብ ይከብዳል። በአንድ ወቅት
በሚሊዬንም አዳራሽ „ለማ ለማ“ ያለው መንፈስም ጭራሽ ከስሟል ብሎ ማሰብ የሚቻልም አይመስለኝም። እያንዳንዱ ሰው መስጥሮ
የሚይዘው የራሱ የቅርብ መንፈስ አለውና።
እሳቸውን
ቀላል፤ ተራ ፖለቲከኛ አድርጎ ማዬቱም የሚገባ አይመስለኝም። የመከላከያ ሚኒስተር ቦታውም የሚሰጣቸው ልዩ አቅም አለ፤ እስከ አሁን
በፖለቲካ ድርጅታቸውም ምክትልነታቸው አልተነሳም፤ የኦሮሞ አንድነት ብለው በመሰረቱትም ሰብሳቢ ናቸው፤ በአሜሪካ ቆይታቸው
ሰርተው የመጡት የዲፕሎማሲ ፖለቲካም የሚታወቅ ነገር የለም። ማን ከማን ጋር እንደሚወግንም ገና አለዬለትም። ጉሽ ቅመሱ ይለን
ይሆናል የኦሮሙማ ድንገቴ ተውኔት አንድ ቀን እንደለመደበት።
ስለዚህ
ይህንን ዕውነት አቅሙ ያላቸው የኢትዮጵያንዚም አቀንቃኞች አደብ ገዝተው በዝግ ስብሰባ፤ ፓናል ዲስከሽን ሩም ከፍተው
ሊወያዩበት፤ ሊመክሩበት፤ ሊዘክሩበት እና ጠንክረው እና በርትተው በተከታታይ በሎቢ ስራ ሊተጉበት የሚገባ ይመሰልኛል። አሁን
አቅል የነሳቸው የኦነግ ሊሂቃን በሚለቁት የማዘናጊያ አጀንዳ፤ የፎቶ ሞድ ተውኔት ያን እያኘኩ አቅም አላግባብ የሚነድበት ሁኔታ
በአስቸኳይ መቆም ያለበት ይመስለኛል። ይህ የታሪክ ክርክርም ቢበቃ ምኞቴ ነው። አገር ታሪክ ሆና ልትቀር አፋፍ ላይ ሆና
ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የማዬው ነገር በተቃጠለ ቤት የሠረግ ቅልቅል የሚመስል ዓይነት ዘመናይነት ነው።
ሌላው
የጠሚር አብይ አህመድ የዕዬለት የተውኔት ስክሪፕት ተዋናይነትን ማምከን፤ ማፍለስ ከእያንዳንዱ በግል ከሁሉም በጋራ የሚጠበቅ ቀዳሚ
ድርሻም ነው። ፋሺዝም በኢትዮጵያ ዬተተከለ ያህል ይሰማኛል የአቶ ጃዋር መሃመድ የኦፌኮ አካል መሆን። ዓለም እራሷ ማዕት ነው
የታዘዘባት። አቅለን እንዬው። በጥልቀት፤ በስፋት እና በጥሞና እናስተውለው። አንድ ግለሰብ አይደለም አንድ ድርጅት እራሱ
እራሱም እኔም ጃዋር
ነኝ ብሎ በተቋም ደረጃ ሲወጣ ያስደንግጣል። የአቶ ጃዋር መንፈስ አንድም ጤናማ ቀን አላሰለፈም። ኢትዮጵያዊ ቀናት፤ ወራት፤ ወቅታት ታመው
አልጋ ቃሬዛ ላይ ነው የባጁት፤ ያሉትም - ህሊና ላለው።
·
የመከወኛ ማኛ።
ቀኑን ባላስታወስም እንዴት
ልተርጉመው አቶ ጃዋርን መሃመድን ብዬ የጻፍኩት ጹሁፍ ነበር። ትንሽ እንደ ምርምር ቢጤ። ዘሀበሻ ካወጣው በቀጣዩ
እልከለታለሁኝ። ብሎጌ ላይ ግን አለ።
በመጨረሻ በቅንጥብጣቢ ነገር
ከመነታረክ፤ አልፎ ተርፎም ከመዘላለፍ በላቀ ጥበብ፤ በጥሞናዊ ማስተዋል ቢያንስ ራስን ለማዳን እንትጋ። የሚጠፋ ጊዜ የለም።
እርሱት የጠሚር አብይ አህመድን የካሜራ ውሎ። ወይንም የኢንጂነር ታከለ ኡማን የሞድ ተውኔት፤ መቼም ኢትዮጵያዊው ካሜራ
እንደዚህ ዘመን ወፍ አላወጣውም። በአይነት የሞድ ትዕይንት ይታያል በዬቀኑ። አገር በቁሟ ተወራ። አገር በቁሟ እዬተሳደደች እዬተሰደደችም።
ይሰቀጥጣል ጭካኔያቸው እራሱ።
አሁን የሰሞኑ የፕ/ መራራ
ጉዲና የጭካኔ ዓዋጅ እሳቸውን ከ4 ዓመት በፊት ለሚያውቅ ከዬትኛው ሲኦላዊ ተቋም ተመረቁ ያሰኛል ሰሞኑን በኢሳት የሰጡት መግለጫ
ሲደመጥ። ደጋግማችሁ አድምጡት። የጦርነት ነጋሪት ነው። ሁሎቹም ግባቸው ኦሮሙማን አፍረካዊ ማድረግ ነው። በቀውስ ፖሊሲ። የሚገርመው
በዚህ ውስጥ ስለሚያልቀው ነፍስ ደንታ አይሰጣቸውም። አሽዋነት።
ቁጥር ስፍር የሌላቸው የኦሮሙማ
የፖለቲካ ድርጅት መሪ ሊሂቃን ሁሎችም ለኦሮሞ ጥቅም ሲሉ ይደመጣሉ። እስከ አሁን እንደ ታዘብኩት በጠቅላላው የኢትዮጵያ ፖለቲካ
ተመክሮ ለህዝብ ጠቀም አደር ሆኖ አያውቅም። የግለሰቦች የሰብዕና የልዕልና መወጣጫ ዋንጫ ነው። በዚህ በቀውሱ የምታዮዋቸው
ወጣቶች እኮ የዕለት ከፍን እንኳን ያላሟሉ ናቸው። እድፍ ለብሰው እድፍ ሆነው ግን ለጥቂት ባለከረባቶች ሰብዕናቸውን ይገብራሉ።
እናስተውል።
እዬዳጡ፤ እዬደፈጠጡ፤
እያሰገደዱ፤ እዬጨፈለቁ ኦሮሙማን መጫን የኦሮሞ ድርጅቶች አኃታዊ ብይን ነው። ቀደም ባለው ጊዜ ኦፌኮ እንዳለም የማልቆጥረው
ድርጅት ነበር። የሚረባ ውሳኔም የሚሻል የተግባር እንቅስቃሴም፤ የሚያደማ ሃሳብ አልነበረውም። የቅንድብ ጸጉር። ያው ማይክ ላይ
ሲገኙ ብቻ ነው መኖራቸው የሚታወቀው። እርግጥ ነው ቀደም ባለው ጊዜ በተናጠል ለፕ/ መራራ ገዲና አክብሮት ቢኖረኝም አቅሙ ግን
ይህ ያህል አለን የሚያሰኝ አልነበረም። ዛሬ ደግሞ ፉከራው፤ ቀረርቶው፤ መታበዩ፤ ዲስኩሩ ገደለን። እግዜሩ ፍርድ ይስጥ። ይህን
ቅን ህዝብ፤ ይህን ጨዋ ህዝብ በጭንቀት እንደሚያርሱት አንድዬ ማስታገሻውን ያውርድ። አሜን።
ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር
ይሰደዳል።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ