የርዕሰ መዲናን ደህንነት ከአቅሙ በላይ ከሆነ የፌድራሉ መንግሥት ጠቅልሎ ገዳም ይግባ።
እንኳን ደህና መጡ። የርዕሰ መዲናን ደህንነት ከአቅሙ በላይ ከሆነ የፌድራሉ መንግሥት ጠቅልሎ ገዳም ይግባ። „ በዚያ ዘመን ንጉሡ ሄርድስ መከራ ያጸናባቸው ዘንድ ከቤተ ክርስትያኑ በአንዳንዶቹ ላይ እጁን ጫነባቸው። “ የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፲፪ ቊጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 01.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። እጅግ የሚገርሙ እርስ በእርሳቸውም በጥፊ የሚጯጯሉ ጉዳዮች ይሰተዋላሉ በጠ/ሚር አብይ አህመድ ቢሮ። ግንባራችንም መንግሥታችንም የምንመራበትም አይዲኦሎጂ አለ፤ አቅም አለን ያሉት ጠ/ሚር አብይ አህመድ በሰሞናቱ ጋዜጣዊ መግለጫቸው የጋዜጠኛ እስክንድርን ጋዜጣዊ መግለጫ ግን አስግድበውታል። አሳግደውታል፤ ጉልበታቸውንም አሳይተዋል። በጣምም ፈርተውታል። መንፈሳቸውንም እረፍት ነስቶታል። መሰከረም ላይ ማህል አዲስ አባባ በበቀል 5 ሰማዕትታ ደማቸው ሲዛራ በግፍ ይህን ያህል አልተጨነቁበትም ነበር። የቆሞስ ስመኘው በቀለ ህልፈትም ከመጤፍ አልቆጠሩትም። በወጣቶች እስር እና ድብደባም ህልፈትም ወጥተውም ያሉት አልነበረም። የሚገርመው ባለማስቲካው የጃዋር መንፈስ ሴክሬታሪ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የሰጡት መልስ ደግሞ ግርም የሚያደረግ ነው። ለካናስ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሞጋች ሃሳብ ሲመጣ፤ አቅም ያለው ወገን ሲመጣ ይህን ያህል ይርዳሉ ማለት ነው። ምነው ፈሩት ይህን መንፈስ? ስንት አሉ የሚባሉ የፖለቲካ ሊሂቃን ጋር ቁጭ ብለው እዬተወያዩ አይደለም ወይ? ነው እነሱን አንደባልያቸዋለሁ በስብከት ብለው አስበው ይሆን? መቼም የህዝብ ማዕባል ከመጣ እጅግ የከፋ ነው የሚሆነው። ሰላማዊ ተጋድሎ...