የርዕሰ መዲናን ደህንነት ከአቅሙ በላይ ከሆነ የፌድራሉ መንግሥት ጠቅልሎ ገዳም ይግባ።

እንኳን ደህና መጡ።

የርዕሰ መዲናን ደህንነት
ከአቅሙ በላይ ከሆነ
 የፌድራሉ መንግሥት
 ጠቅልሎ ገዳም ይግባ።
በዚያ ዘመን ንጉሡ ሄርድስ መከራ ያጸናባቸው ዘንድ
ከቤተ ክርስትያኑ በአንዳንዶቹ ላይ እጁን ጫነባቸው።
የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፲፪ ቊጥር
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
 01.04.2019
 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።



እጅግ የሚገርሙ እርስ በእርሳቸውም በጥፊ የሚጯጯሉ ጉዳዮች ይሰተዋላሉ በጠ/ሚር አብይ አህመድ ቢሮ። ግንባራችንም መንግሥታችንም የምንመራበትም አይዲኦሎጂ አለ፤ አቅም አለን ያሉት ጠ/ሚር አብይ አህመድ በሰሞናቱ ጋዜጣዊ መግለጫቸው የጋዜጠኛ እስክንድርን ጋዜጣዊ መግለጫ ግን አስግድበውታል። አሳግደውታል፤ ጉልበታቸውንም አሳይተዋል። በጣምም ፈርተውታል። 

መንፈሳቸውንም እረፍት ነስቶታል። መሰከረም ላይ ማህል አዲስ አባባ በበቀል 5 ሰማዕትታ ደማቸው ሲዛራ በግፍ ይህን ያህል አልተጨነቁበትም ነበር። የቆሞስ ስመኘው በቀለ ህልፈትም ከመጤፍ አልቆጠሩትም። በወጣቶች እስር እና ድብደባም ህልፈትም ወጥተውም ያሉት አልነበረም።

የሚገርመው ባለማስቲካው የጃዋር መንፈስ ሴክሬታሪ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የሰጡት መልስ ደግሞ ግርም የሚያደረግ ነው። ለካናስ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሞጋች ሃሳብ ሲመጣ፤ አቅም ያለው ወገን ሲመጣ ይህን ያህል ይርዳሉ ማለት ነው።

ምነው ፈሩት ይህን መንፈስ? ስንት አሉ የሚባሉ የፖለቲካ ሊሂቃን ጋር ቁጭ ብለው እዬተወያዩ አይደለም ወይ? ነው እነሱን አንደባልያቸዋለሁ በስብከት ብለው አስበው ይሆን? መቼም የህዝብ ማዕባል ከመጣ እጅግ የከፋ ነው የሚሆነው። ሰላማዊ ተጋድሎ በሁሉም መስክ የሚያደርግ ዝምታ ከመጣ መግፊያ የሌለው ነው የሚሆነው።

ጭራሹን ሺ ሚሊዮን ጊዜ "አንድ ጠ/ሚር ነው ኢትዮጵያ ያላት ያ ደግሞ እኔ ነኝ" በሙሉ ድምጽ ተመርጫለሁም የሚሉት ኩዴታ ቢመጣ እና ባሰናዱት እስር ቤት ቢታጎሩ ምን ሊሆኑ ይሆን? ለነገሩ በጋዜጣዊ መግለጫ ጉለሌ ላይ ሆኖ ጦርነት ያወጀ መፈንቅለ መንግሥት የሚመስል አላሉትም፤ ይህን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ግን በምን ሁኔታ እንዲህ አድርገው ጥቁር መልክ ሊሰጡት እንደሚደፍሩ እራሱ እኛንም ደፍረን ምስክር የሰጠንላቸውን እያሳፈሩን ነው። 

ሥልጣን ለካንስ እንዲህ ነው የሚያደርገው … ሲክዱም አኮ ትንሽ አንደበታቸው አይንተባተበም … ግርም ነው ያለኝ እኔ ጋዜጣዊ መግለጫው ራሱ። ስለተሰራው ነገር እማ እኛው ባጅተንበታል እኮ … ምን እሳቸውን አደከማቸው? ! 

የሚገረመው ባለፈው ሳምንት የባልደረስ ባላደራ ምክር ቤት የደህንነት ችግር ሊገጥም እንደሚችል መረጃ ደርሶኛል እና ስብሰባውን ትቼዋለሁ ብሎ እቅዱ ሳይሳካ ቀረ? አሁን ሳስበው ሆን ተብሎ በተዘጋጀ ሳቦታጅ የተከወነ ነው የሚመስለው። በፌክ ኒወስ ነው እንዲደናቀፍ የተደረገው ማለት ነው። ሥነ - ልቦናን ለማወክ ነው አዲስ ስትራቴጅ የነደፈው የአብይወለማ ካቢኔ። አሁን ደግሞ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይደረግ ተደረገ። ሌላ የሥነ - ልቦና ጨዋታ …

እንደገና ደግሞ የደህንነት ችግር ስላለ በግዞት ይካሄድ የሚል ዘይቤም ያመጣሉ የወጠሯቸውን ሰላይ ካድሬዎቻቸውን አሰማርተው እነ ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ። ያሳናዱት ማፍያ ቡድን አለ ማለት ነው። ደብዳቢ፤ ገዳይ፤ አሳሪ፤ ገራፊ … ቀስ በቀስ ፋሽታዊ ጠረን እዬመጣ ስለመሆኑ ምልክት ይሰጣል። 

እንዲህ በአጭር ጊዜ መዲናዋ ላይ ይህ ይፋዊ የማሸበር ተግባር ይከወናል ብዬ አላሰብኩም ነበር። ምርጫ እና እርግጫ ፍጣጫ ነው የሚታዬው … አለ የሚባለውም ነፃነት ሊቀጥል እንደማይችል ምልክትም ነው ይሄ። ለነገሩ እኔ ከሀምሌ ጀምሮ ወንበሩ ባዶ ሆኖ ነበር ብህልሜ ያዬሁት። 

ግን ግን ይህን ያክል አንድ የአህጉሩ የህብረት ጽ/ቤት በሚገኝበት፤ የስንት አገር የውጭ አገር ኢንባሲዎች እና ቆንሲላዎች ባሉበት የአንድ አገር መዲና ላይ ለአንድ ብዕረኛ ጋዜጣዊ መግለጫ ይህን ያክል የሚንቦጨቦጭ ከሆነ ጓዙን ጠቅልሎ ገዳም ቢገባ ይሻለዋል

ኢህዴግ ግንባሩም፤ ፌድራል መንግስቱም እስከ አብይወለማ ካቢኔው ድረስ ወደ ጉድቡ ቢገባ ይመረጣል። ይህ አቅም ተይዞ ነው ነፃ ምርጫ? ይህ አቅም ተይዞ ነው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ? ይህ ኮሳሳ አቅም ተይዞ ነው የዴሞክራሲ ግንባታ ሥርዓት ንድፍ …  ድንቄም ነው …
ማፈር አለበት የአብይ ካቢኔ? አለሁም አይበል። 

ማለት ያለበት ቦታ ሙት መሬት ላይ ነውና። ይህን ያህል መርበትበት ለአንድ ከፍተኛ መኮነን ለነበረ ነፍስ ይመጥነዋል ወይ? ተደባልቆበታል … ተዝረክርኳልም። አዛዡ የመፍንቅለ መንፈስ ገዢውን መሬት ሳያስጠጣ ቀጥ አድርጎ ወደሚፈልገው አቅጣጫ እዬዘወረው ነው … 

አሁን ጭንቁ ሳይታወቅበት በሰጋር በቅሎ ለመሸመጠጥ ዕሳቤው እከል ገጠመው ...ባላሰበው፤ ባልገመተው ሁኔታ፤ መፍንቀለ መንፈሱ እኔ የጻፍኩት ሐምሌ ላይ ነበር። ያ "አክ ወሬ" አድበስብሶት አቅሙን ቀረ እንጂ ... 

የጸጥታ ስጋት ስላለው ነው ጋዜጣው መግለጫ እንዳይደረግ የተደረገውየጠ/ሚኒስተር .ቤት
March 30, 2019

በዚህ ዓይነት ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ኢንባሲዎች ምን ይሰራሉ? አፍሪካ ህብረትስ?
 ምን የደህንነት ዋሰትና አላቸው? ለአንድ ቀንጣ ጋዜጠኛ ይህን ያህል መንግሥት እሚያንዘፈዝፈው ከሆነ እና ደህንነቱን የማስጠበቅ አቅም ካጣ የለም ፈርሷል ማለት
 እኮ ነው። አዎና!

ለመሆኑ ይህን ቃለ ምልልስ ከተደረገ በኋዋላስ አለን ብለው ያ መከረኛ ገበርዲን እና ሱፍ አትቅረበኝ ተብሎ ይሆን? 

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።