ኢትዮጵያዊው ዕውቅት የህልውና አደጋ ላይ ነው።
· ዕውቀትም ስደት ላይ ነው፤ እዬነደደ። · ልሙጧ ኢትዮጵያም ታጭታለች …. · ኢትዮጵያዊው ዕውቅት የህልውና አደጋ ላይ ነው። · ኢትዮጵያን የበጃት ጥበብ ቃጦሎ ታዞበት እየጋዬ ነው … ዕለተ ማክሰኞ ማዕዶተ ይግቡ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „ዝም ብዬም የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።“ (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17) · ኢ ትዮጵያዊው ዕወቀትም፤ ኢትዮጵያዊው ጥበብም ነዲድ ላይ ነው። · ኢትዮጵያ በጠላቷ እጅ ወድቃለች እና። o ዕ ውቀት የጀንበር ሥራ ነውን? ዕውቀት ህሊናዊ አቅም ነው በእኔ ዕድምታ። ፍልስፍናም፤ ጥበብም፤ ሳይንስም ነው። ያ ህሊናዊ አቅም በተለያዬ ሁነት ሊገኝ ይችላል። o ዕውቀት ዘርፈ ብዙም ስጦታ ነው። በአራት ከፍለን ልናዬው እንችላልን። (1) በ ትምህርት በሥልጠና የሚገኝ፤ ክህሎት እንደማለት … (2) በ ልምድ በሥልጠናም ከሥልጠና ውጪም የሚገኝ የተመክሮ ክፍል ነው። (3) ...