ኢትዮጵያዊው ዕውቅት የህልውና አደጋ ላይ ነው።
· ዕውቀትም ስደት ላይ ነው፤ እዬነደደ።
· ልሙጧ ኢትዮጵያም ታጭታለች ….
· ኢትዮጵያዊው ዕውቅት የህልውና አደጋ
ላይ ነው።
· ኢትዮጵያን የበጃት ጥበብ ቃጦሎ ታዞበት
እየጋዬ ነው …
ዕለተ ማክሰኞ ማዕዶተ ይግቡ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
„ዝም ብዬም የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።“
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17)
· ኢትዮጵያዊው ዕወቀትም፤ ኢትዮጵያዊው ጥበብም ነዲድ ላይ ነው።
· ኢትዮጵያ
በጠላቷ እጅ ወድቃለች እና።
o ዕውቀት የጀንበር ሥራ ነውን?
ዕውቀት ህሊናዊ አቅም ነው በእኔ ዕድምታ። ፍልስፍናም፤ ጥበብም፤ ሳይንስም ነው። ያ ህሊናዊ
አቅም በተለያዬ ሁነት ሊገኝ ይችላል።
o ዕውቀት ዘርፈ ብዙም ስጦታ ነው። በአራት ከፍለን ልናዬው
እንችላልን።
(1)
በትምህርት
በሥልጠና የሚገኝ፤ ክህሎት እንደማለት …
(2)
በልምድ በሥልጠናም
ከሥልጠና ውጪም የሚገኝ የተመክሮ ክፍል ነው።
(3)
ከፈጣሪ የሚገኝ
የብልህነት ዘርፍ ነው።
(4)
የተለዬ ጸጋ ጥበብ የምንለው ነው፤
ያደላቸው በገኃዱ ዓለም ተምረው ተመረቅው፤ በተማሩበት የዕውቀት ዘርፍ ዕድል አግኝተው ሲሰሩበት የህልና ንድፉ ከተግባር ጋር ሲዋደድ፤
በተጨማሪም ፈጣሪ አምላክ ሳይማሩ ጥበብ እንደ ተሰጣቸውም በድርብነት ብልህነትም የጥበብ ጸጋው ሲኖራቸው እንኝህ ሙሉዑ የሆነ ሰብዕና
ያላቸው ይሆናሉ።
የፈጣሪ ስጦታ ምንም የቀለም ትምህርት ሳይገበዩ በተፈጥሯቸው ብልህ፤ አዋቂ ሆነው የሚፈጠሩ አሉ።
ኢትዮጵያን ያበጃት ያ ሰማያዊ ዲግሪ ነበር።
ጸጋ ተለዬ የጥበብ ስጦታ ማለት ነው። እንደ ሥዕል፤ እንደ መጻፍ፤ እንደ መተወን ወዘተ ያሉ
ማለት ነው።
ዕውቀት ዕድሜ ጠገብ ሲሆን ታሪክም፤ ትውፊትም፤ ትሩፋትም፤ ትውልድም ይሆናል። እያንዳንዱ ዛሬን
የሰጠን የመኖር አኗኗሪ ገቢር ሁሉም የትናንት የዕውቀት፤ የጥበብ ውጤት ነው። አንድ ትውልድ በአንድ ቀን አይፈጠረም። አንድ አገርም
በአንድ ጀንበር አይገነባም። ሁሉም የሂደት ውጤት ነው። ሂደቱ ደግሞ ህሊናዊ አቅም የፈሰሰበት ነው። ፍሰቱ የህብራዊነት ውቅር ነው።
የብዙ ንጥረ ነገር አብሮነት ነው።
v የተቃጠለው ዛሬ።
· ዛሬ የተቃጠለ
ነው። ዛሬ ብቻ ሳይሆን ትናንትንም ዛሬ እራሱ እያቃጠለው። አንድ ኩታ ለማስራት ጥጥ ፍሬ ዘር፤ አራሽ ያስፈልገዋል። ከዛ ግብይት
አለ። ከዛ ሴት ልጅ ትፈትለዋለች አሳስታ - ባዝታ - ነድፋ በደጋንን እና በመቀንጠቢያ። ከዛ ሸማው በባለሙያ ይሰራል። ከዛ ኩታ
ይሆናል። ኩታው እራሱ ተግጥሞ የሚሰፋበት ክርም እና መርፌ ያስፍልገዋል። በዚህ ልክ የሰው ልጅ በመኖሩ ውስጥ ያሉ ሁነቶችን እሰሷቸው።
እጅግ ቁጥር ስፍር የሌለው የበርካታ ዕውቀት ተዋፆ ነው። ያ ነው እዬነደደ ያለው።
· ሻሸመኔ፤
ዝዋይ፤ ትግራይ፤ አጣዬ፤ ሽዋ ሮቢት ሲነዱ ለሄሮድስ ጠሚር አብይ አህምድ እና ለካቢኔያቸው የሠርግ ውሎ ነው። አይደለም አንድ ከተማ፤
አይደለም አንድ ፋፍሪካ፤ አይደለም አንድ ት/ቤት አንድ ኩታ እንኳን የብዙ ህብራዊ ዕውቀት ውጤት ነው። ዛሬ አይደለም ኩታ መሥራት
የተጀመረው የዘመናት ውጤት ነው።
· እውሩ አብይዝም
ሰውን፤ ቅርስን፤ ተፈጥሮ፤ ቃለ - ወንጌልን፤ ቃለ - ቁራንን ብቻ ሳይሆን ዕውቀትንም እያነደደው ነው። እንድዶም እዬሞቀው ነው።
· የሚገርመኝ
በሚነዱ ቅርስ ወርስ ከተሞቻችን ውስጥ የፈሰሰው የዘመናት መዋዕለ መንፈስ፤ መዋዕለ ንዋይ፤ መዋዕለ አቅም ከቁጥር አይገባም። እሳቸው
የሚያሳስባቸው እስከ ቲማቸው የኮሮጆ ካርድ ቁጥር ብቻ ነው። ወይንም የተገነባን እዬናዱ የፒኮክ ህገ - መንግሥት መገንባት ነው።
ድውይ አርቲፊሻል። የሚያስፈነጥዛቸው የአሻንጉሊት ውሎ ነው።
· እያንዳንዱ
ኢትዮጵያዊ ዕውቀት መንደዱ ብቻ ሳይሆን ት/ምህርት ቤት እንዲህ ዝግትግት ሲል ልሙጧ ኢትዮጵያ አትታዬውም። ትምህርት ቤቶች መቃጠል
ብቻ አይደለም። መማር አልመቻሉ ብቻ አይደለም። ትምህርት ቤት ማስፈራሪያ ካቴናም ሆኗል። እነኛ የደንቢደሎ፤ እነኛ የቤንሻንጉል
ጉምዝ ተማሪዎች የታገቱት በአማራ ክልል ኃራም ት/ቤት ይባል ዘንድ
ነው። የተማሩትንም እያደኑ ረሽነዋቸዋል። ነገም ይቀጥላል።
· የማቃጠሉ
ኢላማ የስሜን ጠረን አለበት የተባለውን ሁሉ ነው። ቅርሶች፤ ውርሶች አስተርጓሚ አይሹም እነሱ እራሳቸው ይናገራሉ። እነሱም ነደዋል
ዛሬ። በዚህ ውስት ቱሪዝም ነዷል። ሰሜን ተራራ ላይ የወረደው ነዲድ፤ በሌሎች ገዳማትም፤ የተፈጥሮ ሃብቶችም ላይ ማዕቱ ተዳርሷል።
የቀሩት ፋሲል ግንብ እና ላሊበላ ናቸው። እነሱም ቀናቸውን እዬጠበቁ ነው።
· በነዲድ
ውስጥ ሆኖ ኢትዮጵያዊው ሰው ስለ ከረባት እና ገበርዲን ሲያስብ፤ ሲያሰላ ግርም ይለኛል። ከዛም አልፎ ተርፎ ስለ ምርጫ እርግጫ?
· ዕወቀት፤
ጥበብ፤ ትሩፋት በአንድ ጀንበር አመድ እዬሆነ መኖር እራሱ ተቃጥሎ መምሸት መንጋቱ በፈጠሪ ጥበብ ሆኖ ዘመናይነቱ ስታዩት ሰው ውደ
እንሰሳ ተለወጠን ያሰኛል?
· ኢትዮጵያዊው
ዕወቅት ኢትዮጵያን አበጅቶ ከዓለም ቀደምት አገሮች ተርታ ያሰለፈው ባለቤት ተቆርቋሪ ቀርቶ ዕውቀት ህልውና አደጋ ላይ ነው ብሎ
የሚጮኽለት የለም። አዝናለሁኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ሲዊዘርላንድ ቪንተርቱር።
27.04.2021
ተጋድሎዬ ለኢትዮጵያዊው ዕውቀት እና ጥበብ ህልውናም ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ