ፕላኔታችን አጽናኝ አባቷን አጣች።
ፕላኔታችን አጽናኝ አባቷን አጣች። • ትንሳዔን ዓውጆ በትንሳዔ ወደ አባት ጥሪ፤ መታደል። “አፈር ነህና፣ ወደ አፈርም ትመለሳለህ።” (ዘፍጥረት ፫ ቁጥር ፲፱- ፳) የተመረጡት ንጹህ አባት ሰው ሆኖ መፈጠር የከበረ የመዳህኒዓለም ስጦታ መሆኑን በድርጊት ያመሳጠሩ ሩሁሩህ አባት፤ ትንሳዔን ዓውጀው ወደ ናፈቃቸው አባት በብርሃን ዕለት መጠራት ሚስጢር ነው። የካቶሊክ ሃይማኖት የዓለም ሃይማኖት እስኪመስል ድረስ ደግነታቸው ሐዋርያ ነበር። ለመላ የዓለም ህዝብ መጽናናትን እመኛለሁኝ። ለአባ ዘላለማዊ እረፍት እመኛለሁኝ። ቅብዓ እንዲህ ነው። ሲፈጠሩም፤ ሲኖሩም፤ በሥጋ ሲለዩም ተመስጥሮ። መታደል። አስታውሳለሁኝ አንድ ጠሎተ ሃሙስ እስር ቤት ተገኝተው ቀለም፤ ዞግ፤ ሃይማኖት ሳይገድባቸው እስረኞችን ሁሉ ተጎንብሰው እግር አጠቡ። እኔም በመደነቅ አንድ ጹሁፍ ጽፌ ነበር። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 22.04.2025 "ወደ እግዚአብሄር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።"