#እንቁጣጣሽ።
#እንቁጣጣሽ ። የማከብራችሁ ማህበረ ቅንነት፣ መጪው ዘመን የስኬት፣ የሰላም፣ የፍቅር እንዲሆንላችሁ እመኛለሁኝ። የእኔ ድንግል ጥበቃ አይለያችሁ። አሜን። በተለይ ለኢትዮጵያ #እናቶች በሙሉ መጪው ዘመን #ከዕንባ #እርፍ የምትሉበት ዘመን ይሁንላችሁ። አሜን። በዱር በገደል፣ በእስር ቤት የምትገኙ ወገኖቼ አይዟችሁ። የእኔ ድንግል ጥበቃ አይለያችሁ። አሜን። ሁላችሁንም እመቤቴ ትጠብቅልኝ። አሜን። ቅድስት አገር #ኢትዮጵያን ፣ ቅድስት አገር #ሲዊዘርላንድን ፣ ዓለማችን እግዚአብሄር አምላክ ሰላም ያድርግልኝ። አሜን። አዲስ ዓመት እየመጣ ዋዜማ ላይ ነን። አገር ቤት በተለይ ጎንደር ዋዜማው ላይ ልዩ ሥርዓት አለ። ያ ይናፍቀኛል። ማምሻ ላይ በግ፣ ዶሮ እየጮኽ፣ ቡና ተፈልቶ፣ አበባ ቆሎ እና ኑግ ተዘጋጅቶ ዳቦ ቀርቦ ልዩ የሆነች ፍቅር የሆነች የቤተሰብ አባል፣ ወይንም ወዳጅ ቡና ታፈላለች። ያ ድባብ እጅግ ይናፍቀኛል። አዱኛወቼ ምዕራፍ ፲፮ በዚኽው ይከወናል። ከሁሉም ምዕራፎች አጭሩ ምዕራፍ ፲፮ ነው። ምክንያቴ አዲስ ዘመን በሩን ነገ ይከፍታል። በተጨማሪም አጤ አባይም ትልቅ ግሎባል ክስተት ነው። ስለሆነም ምዕራፍ ፲፮ ማጠናቀቅ ይገባዋል። በመጪው ጥቂት ቀናት ምዕራፍ ፲፯ እጀምራለሁኝ። ተከባብረን የምንደማመጥበት የጨመተ ጊዜ እንዲሆንልን አምላኬን አላህን በርከክ ብየ እለምናለሁኝ። ኑሩልኝ። አሜን። "አቤቱ #ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። ጎዳናችን ንጹህ ልብ እንዲመራው ብንፈቅድ ተራራ የሚያክለውን ጥቅል የፈተና #ቱቦ መቋቋም ያስችለናል አምላካችን። እስኪ ደፍረን እንሞክረው። ለቅኑ ጨዋ የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ለብሩሁ አዲስ ትውልድ ሲባል ቅን፣ ንጹህ፣ ሩህሩህ፣ አ...