#እንቁጣጣሽ።
አዲስ ዓመት እየመጣ ዋዜማ ላይ ነን። አገር ቤት በተለይ ጎንደር ዋዜማው ላይ ልዩ ሥርዓት አለ። ያ ይናፍቀኛል። ማምሻ ላይ በግ፣ ዶሮ እየጮኽ፣ ቡና ተፈልቶ፣ አበባ ቆሎ እና ኑግ ተዘጋጅቶ ዳቦ ቀርቦ ልዩ የሆነች ፍቅር የሆነች የቤተሰብ አባል፣ ወይንም ወዳጅ ቡና ታፈላለች። ያ ድባብ እጅግ ይናፍቀኛል።
አዱኛወቼ ምዕራፍ ፲፮ በዚኽው ይከወናል። ከሁሉም ምዕራፎች አጭሩ ምዕራፍ ፲፮ ነው። ምክንያቴ አዲስ ዘመን በሩን ነገ ይከፍታል። በተጨማሪም አጤ አባይም ትልቅ ግሎባል ክስተት ነው። ስለሆነም ምዕራፍ ፲፮ ማጠናቀቅ ይገባዋል።
በመጪው ጥቂት ቀናት ምዕራፍ ፲፯ እጀምራለሁኝ። ተከባብረን የምንደማመጥበት የጨመተ ጊዜ እንዲሆንልን አምላኬን አላህን በርከክ ብየ እለምናለሁኝ። ኑሩልኝ። አሜን።
"አቤቱ #ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። ጎዳናችን ንጹህ ልብ እንዲመራው ብንፈቅድ ተራራ የሚያክለውን ጥቅል የፈተና #ቱቦ መቋቋም ያስችለናል አምላካችን። እስኪ ደፍረን እንሞክረው።
ለቅኑ ጨዋ የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ለብሩሁ አዲስ ትውልድ ሲባል ቅን፣ ንጹህ፣ ሩህሩህ፣ አጽናኝ መሆን እንዴት ያቅተናል። ደርባባውን፣ #እርጉውን ህዝባችን በመሆን እንካሰው። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ቸር አስበን፣ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን ቀና እንሁን። አሜን።
እህት ሥርጉትሻ አገልጋይ 10/09/2025
እመቤቴ ሆይ! አትርሽን። አሜን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ