"#ማንም ዜጋ መለመን የለበትም።" (ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ።) እንደ ምኞተወት ያድርግልን። አሜን።
" #ማንም ዜጋ መለመን የለበትም።" (ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ።) እንደ ምኞተወት ያድርግልን። አሜን። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #ምዕራፍ ፲፱። #እፍታ ። ትሁታዊ ሰላምታ አቀርባለሁኝ ለቤተ - ቅንነት እንዴት አደራችሁ? እንደምን አረፈዳችሁ? ለመጀመሪያ ጊዜ ይመስለኛል በአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት ዙሪያ የምጽፈው። የሚሞገቱበት ጠፍቶ ሳይሆን፤ በሴት የፖለቲካ ሊቃናት ላይ በአንፃራዊነት ለዘብተኛ ነኝ። የኢትዮጵያ ሴት የፖለቲካ ሊቃናት አዋን መድረክ አግኝተው፤ ወጥተው እኔ ታክዬ #ቲካቲካ የተገባ ነው ብዬ አላምንም። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሴቶችን ተጫኝ፤ የገበርዲን እና የከረባትም ስለሆነ ንጥረ ነገር የጎደለበት፤ የእናታዊ ጸጋ የተነነበት ስለሆነ ስኬቱም ሲትበሰበስ ነው የኖረው። በሰሞኑ የምግብ ማዕከል ምርቃት እና ንግግር መነሻነት ዛሬ የተሰማኝን ለመግለጽ አህዱ ብያለሁኝ። #መቅድም ። ከንቲባ አዳነች አበቤ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ "ድረሽልኝ" ባሏቸው የኃላፊነት ደረጃወች ሁሉ በመገኜት የልብ አድራሻቸው ብቻም ሳይሆኑ፤ የቅርብ፤ የሚያምኑት፤ የማይጠረጥሩት ሰብ ከኖራቸው፤ ከንቲባ አዳነች አበቤ ነው ሊሆኑ የሚችሉት። በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃወች ፈቃዳቸውን በመፈጸም ቁጥር ፩ የጠሚሩ አጋር ይመስሉኛል - የዛሬዋ የመዲናችን የአዲስ አበባ ከንቲባ። ናቸው አላልኩም። ሊሆኑ ይችላሉ፤ ይመስሉኛል ነው ያልኩት። እምከታተለው በርቀት ስለሆነ። #እንደ በር። ዕድሜ ልኩን ታግሎ ኦነግ አንዲት አቅም ያላት አንስት ፖለቲካ ማብቀል አልቻለም። ኦፌኮ ጋር ፕሮፌሰር ዶር. መራራ ጉዲናን በአካል ሳገኝ በወጣቶች ፖለቲከኞች...