ልጥፎች

ከፌብሩዋሪ 2, 2020 ልጥፎች በማሳየት ላይ

„አብይ ጭንብልህን ግለጥ“ የዛሬ የአማራ ክልል የሰልፍ ውሎ።

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። „አብይ ጭንብልህን ግለጥ“ „ልጄ ሆይ ተግሳጽን ከሰማህ በኋላ   ከእውቀት ቃል መሳሳትን ተው።“ (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 19 ቁጥር 27 ) ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02.02.2020 ·        እ ፍታ። ዕለቱ ጭፍግግ ብሎታል። እኔም ዛሬ ሌሊት የረባ እንቅልፍ አልወሰደኝም። በሰንበቱ ሰላማዊ ሰልፍ ምን ይፈጠር ይሆን ብዬ ስጋት ነበረኝ። ከንጋቱ 5.00 ሰዓት በሲዊዝ አቆጣጠር የተቆራረጠውን እንቅልፍ መብተክትክ ክላ ብዬ ተነሳሁኝ። በኢትዮጵያ ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ነበር። ስነሳ በዬከተሞች ሰልፉ መጀመሩን የሚያበስሩ ትዕይንቶች አዬሁኝ። ·        የተ ግሳጽ ትዕይንት ለኦነጋዊው የአብይ ሌጋሲ። ድርግም ለማድረግ የአማራ ብሄርተኝነትን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እና ዶር ዳኛቸው አሰፋ ብዙ ታክተዋል። ይህን መሰል ጥቃት ቢመጣም አማራነት ለሽ ብሎ ተኝቶ ከፈጣሪ የታዘዘ ማዕት እያለ „የባሳ አታምጣ“ እንዲል ነበር የእንቅልፍ መዳህኒት ክኒን ሲያድሉ የባጁት። ግን የተሳካ አይመስልም።  በሌላ በኩል „ማቅ አውልቀን ግምጃ እንልበስ“ የሳጅን ተመስገን ጥሩነህን አመራር ተቀብለህ   የሰማዕቱን ባህርዳር የሊሂቃኑን እና የልዩ ሃይሉን አብይ ሌጋሲ ጆኖሳይድ የመከራ ጨለማ እርሱት የተባለውም ክትመትን በውርዴት ተከናንቧል።  አብይዝም እና የጭፍጨፋ ተልዕኮው ወሸኔ በሉት አጨበጭቡለትም ፍደስት ተሸልሟል። በዚህ ማህል ሴራው ሳይፈተሽ በቅንነትም ሆነ በሆ...