„አብይ ጭንብልህን ግለጥ“ የዛሬ የአማራ ክልል የሰልፍ ውሎ።
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።
„አብይ ጭንብልህን ግለጥ“
„ልጄ ሆይ ተግሳጽን ከሰማህ በኋላ
ከእውቀት ቃል መሳሳትን ተው።“
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 19 ቁጥር 27)
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02.02.2020
· እፍታ።
ዕለቱ ጭፍግግ ብሎታል። እኔም ዛሬ ሌሊት የረባ እንቅልፍ አልወሰደኝም። በሰንበቱ ሰላማዊ ሰልፍ
ምን ይፈጠር ይሆን ብዬ ስጋት ነበረኝ። ከንጋቱ 5.00 ሰዓት በሲዊዝ አቆጣጠር የተቆራረጠውን እንቅልፍ መብተክትክ ክላ ብዬ ተነሳሁኝ።
በኢትዮጵያ ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ነበር። ስነሳ በዬከተሞች ሰልፉ መጀመሩን የሚያበስሩ ትዕይንቶች አዬሁኝ።
· የተግሳጽ ትዕይንት ለኦነጋዊው የአብይ ሌጋሲ።
ድርግም ለማድረግ የአማራ ብሄርተኝነትን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እና ዶር ዳኛቸው አሰፋ ብዙ
ታክተዋል። ይህን መሰል ጥቃት ቢመጣም አማራነት ለሽ ብሎ ተኝቶ
ከፈጣሪ የታዘዘ ማዕት እያለ „የባሳ አታምጣ“ እንዲል ነበር የእንቅልፍ መዳህኒት ክኒን ሲያድሉ የባጁት። ግን የተሳካ አይመስልም።
አብይዝም እና የጭፍጨፋ ተልዕኮው ወሸኔ በሉት አጨበጭቡለትም ፍደስት ተሸልሟል።
በዚህ ማህል ሴራው ሳይፈተሽ በቅንነትም ሆነ በሆድ አደርነትተሰልፎ አማራን ሲያሳርድ፤ ሲያስነቅል፤
ሲያስድድ ውሎ ለሚያድረው ዝልቡ እና ቁንጥንጡ የኦነግ መንፈስ የአቅም ስንቅ ሲያቀብል የባጀው አማራዊ ታጋይ ሁሉ ቅሱም እንኩትኩት
ብሏል። ውስጥን የፈተሹ በፍጹም ሁኔታ የተደራጁ መንፈሶች ናቸው እኔ ያስተዋልኩት አማራነት በአንድነት መከራውን ለመተጋል ቆርጦ
ተነስ።
የዛሬ ሰልፍም እንደ ባለፈው ሁሉ በጣም ሞጋች ሰልፍ ነበር። ከሁሉ ድንቁ ነገር ለልዩ ተልዕኮ የራሳቸውን የውስጥ ኢንፓዬር ለመፍጠር እዬባዘኑ ያሉት፤
ከራስ ጸጉራቸው እስከ ፊንጢጣቸው በሥልጣን የነተከሩት የኦነጓ
እና የሞጋሳ ቁንጮ ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜል ከኦነግ እና ከከጸረ አማራ የፊት ረድፈኞች ጋር ፎቷቸው ከፍ ብሎ አዬሁት። የውስጥን ለሚያውቅ
አምላክ የአምልኮ ስግደትም ሰገድኩለት።
ቂማቸው በማን እና በምን ላይ እንደ ሆን ተሰውሮ ኢትዮጵያን ለማፈረስ ታጥቀው የተነሱት የዘመኗ ጉዲት
እንዲህ ህዝብ ሚስጥራቸውን አውቆ አደባባይ ላይ በይፋ ውግዘት ማሰማቱ የማህበራዊ ንቃተ ህሊናን ልዕልና በፍጽምና እንዳስተውልበትም
እረዳኝ። እኒህ ሴት ሲፈጠሩ ለጥፋት ከስለው ነው።
በውነቱ እኔ በጣም ተስፋ ያደረግኩባቸው ሴት ነበሩ። በአንድም በሌላም ስለሳቸው የአቤት ወዴት
ታዛዥነታቸው ቢገለጽም እኔ ግን ተግባራቸውን ለክቼ ቢሆን ይሻላል በሚል በተደሞ ስከታተላቸው ባጅቼ ነበር። እርግጥ ነው ገና አፈ
ጉባኤ ሳሉ የአማራ ተጋድሎ ውጤት የነበረው HR 128 በአሜሪካ
ኮንግረስ የጸደቀውን ውሳኔ እንዲነሳ በውቅቱ ከአገረ አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ለተጓዘው ልዑክ ጠይቀው ነበር። እንዳሰቡትም የውሃ ሽታ
ሆኖ ቀርቷል።
የሆነ ሆኖ በትእግሥት ብጠብቃቸውም ከዕለት ወደ ዕለት ለኢትዮጵያ መፍረስ ትልቁን ድርሻ ይዘው
እዬሰሩ ስለመሆናቸው ለእኔ ገሃድ እዬሆነ ቢመጣም፤ ህዝብ እስከዚህ ድረስ ይረዳዋል ብዬ ግን አላሰብኩም ነበር። መነቀል ካለባቸው
ሰዎች ውስጥ አንዷ ሲሆኑ፤ በኽረ መርዝም ናቸው። ደቡብን ያህል ታላቅ መንፈስ በፋስ ነው የፈለጡት አኃቲነቱን። ዩዲት ጉዲት።
· ልዕልተ ጎንደር።
ልዕልት ጎንደር አትኩረት የሰጠችበት ሌላው ጉዳይ የሚዲያን ተሳትፎ ነው። እነዚህን የዘር ጭፍጨፋ
መሳሪያዎች ናቸው ብላለች። ዋልታ፣ ፋና፣ DW EBC OMN። ሌሎችን ደግሞ አመስግናለች። ATV, AMN, BBC News, France
24, the voice of amhra Ethio 360, The Washington post, አስራት, አህዱ፣ ሌላ ሁለት ሚዲያዎች ጹሑፋቸው
ያልታዩኝም Thank you ብላለች።
ሰልፉ ካመሰገናቸው ውስጥ ርዕዮት ሚዲያ እና አሁን ከሆነ በነገረ አማራ አዲስ ድምጽ፤ በተጨማሪም
ዘሃበሻና ሳተናው ድህረ ገፆች ለአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ከመጀመሪያው ጀምሮ ሲዘግቡ በጽናት የቀጠሉ ስለሆኑ እነሱም
ውስጥነት ሊሰጣቸው እና ምስጋናው ሊዲረግላቸው ይገባል እላለሁኝ። በዛ በክፉ ቀን ሁሉ አብረው ነበሩ ደጉ ዘሃበሻ እና ደጉ ሳተናው ድህረ ገፆች። ሙሉ ድምጽም ነበሩ።
ኢትዮ 360 ከተመሰጋኞቹ ውስጥ አንዱ ነው። ይጨርስለት ብያለሁኝ ፈታኝ መንፈሶች እያዬሁኝ ስለሆነ።
ለኢትዮ 360 እንደ መደበኛ ታዳሚ በዚህ አጋጣሚ እማሳስበው የትኛውም ቤት የሚቆመው በአማራ አቅም መሆኑን ልብ ሊሉት ይገባል። የትኛውም ተቋም የሚጸናው
በአማራ መንፈስ ነው። ይህን አቅም በጥንቃቄ መያዝ የሚገባቸው ይመስለኛል። በብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ እና በአማራዊ ጉዳይ ጥርት ያለ
አቋም ሊኖረው ይገባል ሚዲያው። በጣም ስርክራኪዎችን እያዬሁኝ ስለሆነ።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማን የሚጻረሩ ወጣቶችም ይደመጡ የሚል አቋም
ውስጤ ቁስል እያለ አዳምጫለሁኝ። የሚበጅ አይመስለኝም። ታማሚ ሃሳብ ነው።
በውነቱ ለዚህ ዘመን ከግንቦት 7 ሆነ ከሚዲያው ከኢሳት በተጨማሪም ከዶር አብይ ሌጋሲ ቅቡልነት
ዝቅዝቅ ጉዞ መማር ይኖርባቸዋል ኢትዮ 360። የተዛነፉ ነገሮችን ጠርቦ ወጥ ማድረግ ይገባል። ጠቅልሎ መደመር ወይ ደግሞ ጠቅልሎ አለመደመር። ግማሽ መደመር አይበጅም። የግንጥል ጌጥ ትግል ለዚህ መራራ ዘመን
የሚሆን አይደለም። ቆርጦ የለዬለት ትግል ይሻል። የምናስታምመው አብይዝም ሊኖር አይገባም። የተበከለ ነው። ኢትዮጰያዊ ዜጋ እስፖርት
ጨዋታ ገብቶ ማዬት የተከለከለበት አፓርታይድ ዘመን ነው። ቆፍጠን ያለ ተጋድሎ አድርግንም ትውልዱንም አገርም ከተረፈ መልካም ነው።
ለኢትዮ 360 ባዶ እጅ ወጥቶ ከዚህ መድረስ ፈተናው ቀላል አይደለም። የሙያ የህልውና ተጋድሎ
አድርጓል። ልፋትንም ማፍሰስ አይገባም። በግንቦት 7 ምክንያት ያለፈም ቀን ቢሆን በቤተኝነት እና በባይታዋርነት የአንዱ መገፋት
የእኔም ብሎ ማስብ ለመርኽ ሰው ሊነገር የሚገባ አይመስለኝም።
አሁን እኔ እማላዳምጣችሁ ቃለ ምልልሶች ውይይቶች እዬኖሩኝ ነው።
በፊት ሲያመልጠኝ በማልችልበት ሁኔታ ሁኜ እንኳን ውሰጤን ሰጥቼ እምከታታለው ሁሉንም ነበር። ኦነግ እና ተደማሪ ሚዲያዎች የሚያቆስሉን
ይበቃል። የተጨነቀ መንፈስ አለ። ነጥቡ ማህበራዊ ሚዲያ ላይም እዬተነሳ ነው። አስተያዬቶችንም እያነበብኩ ነው። ጥንቃቄ!
ቤት መገንባት ከባድ ነው ሲፍርስ ግን አይታወቅም። ድሮ ድሮ ነው ይህን ለግንቦት 7 ስጽፈው
ነበር። ይድን መስሎኝ። ይኸው በዬሄደበት የወንበር ስብሰባ ብቻ ያካሂዳል። ስለዚህም ኢትዮ 360ም በጀመሩት ጥንካሬ ልክ እውነትን
እና መርኽን ወግነው ቢቀጥሉ መልካም ነው። ሚዛን ለመጠበቅ የሚያደረጉት ልዝ ነገሮች ጥሩ አይመስሉኝም።
የለዬለት እና የጠራ መስመር ሚዲያው ሊኖረው ይገባል። የሚወግነው የፖለቲካ ድርጅትም ካለ እንደዚኸው።
እኛም ይበቃናል። የግንቦት 7 በአማራ ላይ ያለው ሸፍጥ እና ሴራ፤ አሁን እንኳን ከራሳችን ሊወርድ አልቻለም። ልቦና ባለው አቅሙ
ሁሉ አሁንም ምን እያደረገ እንደሆን አሳምረን እናውቃለን። አገር ከገባ ስንት ነገር እንዳጠፋ። ልብ አለን። የቀደመውን ከተጠቂዎች
ውስጥ አንዷ እኔ ስለሆንኩኝ አስተርጓሚ አልሻም። የእሱን መንፈስ ያዘሉ ነፍሶችን ማዳመጥ አቅም የለኝም እኔ በግሌ።
እንደ ልዩ አማራጭ የተስፋ ማህደር የሚታዬው የኢትዮ 360 ሚዲያ ከጥዋቱ እክል እንዳይገጥመው
እሰጋለሁኝ። ይህም ሆኖ ደፋር አመክንዮዎቹን የሚጋፈጡ ርቱዑዎች ስላሉ ደግሞ መጽናናት አለ። ስለሆነም ይቅናው። አሁን ላለው የተጋድሎው
ብቃት ጎንደሮች ማመስገናቸው የተገባ ነው ባይ ነኝ። በምስጋናው ልክ እንዲዘልቅ ነው ጥንቃቄ ይኑር የምለው። ይህ ማለት ሁለት የተለያዩ
ሃሳቦች መሟገታቸው የተገባ ነው።
ነገር ግን የቆሰልንበተን የድርጅት መንፈስ ተሸከሙ ግን ለራሱ ለሚዲያው አይጠቅመውም። የኖርንበትን በደል ማስታመም ግን ለማንም አይበጅም። ባይተዋር የነበርን ዜጎች ነበርን ወንድም
እህትም ብረት መዝጊያ ያልነበረን።
በደል ይረሳል ወይስ ይለመዳል? ሌላው ትልቁ አምክንዮ „ወንዝ የወረደችበት እና እናቱ የሞተችበት“
እኩል አይታይም። የአማራ ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ እዬተመነጠረ ያለ
ማህረሰብ ሆኖ ሳላ ሌሎቹም አሉ እያሉ ማስታመም ለእኔ ቅምጥ ፍላጎት ነው። ነፍሱ፤ መንፈሱ፤ ሥነ ልቦናው፤ ትውፊቱ ላይ ነው ጦርነት
የታወጀበት አማራ። አማራን መመንጠር ኢትዮጵያን መጠቅላል ይህ ነው መሰራዊ ጉዳይ የኦነግ ዓላማ። ሙግቱ ከዚህ አንጎል ነው መነሳት ያለበት።
አማራ ጦርነት ታውጆበታል።
ይህን ውስጥ ማድረግ ኢትዮጵያዊነትን የውስጥ ጽላት ማድረግ ይጠይቃል። ኢትዮጵያዊነት ከወገብ በላይ እና በታች የለውም። ስለነገው
ቀጣይ ጉዞ ሳይሆን በዬዕለቱ አስከሬን ስለምትቀበለው ድምጽ አልባዋ
የአማራ እናት ጎን መቆምን ይጠይቃል።
· የግሰብ ሰብዕና ግንባታ ወደ መቃብር ጉዞ።
ያስደሰተኝ የዛሬ ሰልፍ አውራ የነበረው ጎንደር ነው። የግለሰብ ሰብዕና ግንባታን ሙሉ ለሙሉ
መቃብር ልኮታል። ጎሽ! ከእንግዲህ በዚህ ዙሪያ አቅም ማፍሰስ አይገባም።
ተቋምን ብቻ በሚሰራውም ሆነ በሚያገድፈውም ሊወቀስም ሊደገፍም ይገባል። እንደ አማራ ቅን ህዝብ፤ ቸር ህዝብ ገር ህዝብ የለም።
የአማራ ህዝብ መለኪያው ብቃት ብቻ ነው። ስለሆነም ብቃትን
ሲያበቃ፤ ለቀንም ሲያደርስ እናመሰግናለን ቀርቶ ቅጠቱ ሞት ነው የሆነው። እኔ ብዙ ደክሜያለሁኝ። ግን አማራ አመድ አፋሽ ነው።
ብቻውን ነው ያለው። ፈጣሪው አላህ ግን አለለት።
ስለዚህ ለወደፊት ይህን መንገድ የአማራ ልጅ ማቆም ይኖርበታል። አቅሙን ለራሱ ብቻ መንፈስ ማዋል።
አማራን አክብሮ መነሳት ለማይችል ለማንኛውም ግለሰብ፤ ድርጅት ሆነ ተቋም አቅም ማባከን አያስፈልግም። የራሱ ባንዳ ልጆችም ቢሆኑ። ጥንቅር ይበሉ። ታሪካችን፤ ትውፊታችን፤ ሥነ
- ልቦናችን፤ ማንነታችን እያሳረዱት በይፋ በአደባባይ እያስወገዙት ነው የሚገኙት።
· የተዳፈነውን የሴራ ሹርባ ጊዜ የገለጠው ዕውነት።
የአማራ ሊሂቃን ጭፍጨፋ አማራ ዳግም እንዳይነሳ ፤ ዳግም እነሳለሁ ቢል ምዕራብውያን እና አውሮፓውያን
እንዳይቀበሉት ብቻ ሳይሆን፤ ዳግም እንዳይነሳ በሚወሰዱት ቀጣይ
የዶር አብይ የመንጥር ዘመቻ ከሰባአዊ መብት አንጻር እንዳይታይ
በጣም ጎምዛዛ የሆነ ጥቅል የሴራ መርዝ ነበር።
የጎንደር ሰልፍ አስኳል ነበር ይህ ጉዳይ። ስለሆነም የሰኔ 15ቱ 2011 ዓም የግድያ
ሴራ ክሽፈት መጋለጡ እርር ድብን ያሉ ግለሰቦች ሁሉ እንዴት አጀንዳ ሆነ በማለት ሲያብዱ ተመለከትኩኝ።
እነሱ ይቃጠሉ እንጂ የህዝቡ ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ልቅና በልዕልና፤ ጥሞና በጥበብ እጬጌ ሆኖ
በሁሉም ቦታ ሰልፎቹ ሰማዕት መሪዎችን አንግሶ አይቻለሁኝ። ሁለቱንም ሰማዕት ዶር አንባቸው መኮንን እና ነብዬ ብርጋዴር ጄኒራል
አሳምነው ጽጌን። በዚህ ዙሪያ ጎጥ ላይ ተቀርቅረው የአማራነትን ልዕለ አቅም ሊበትኑ የተጉ ነቀዞችም ወና ሆነዋል። ይህ የመንፈስ
ብቃት የዘመን ሐዋርያ ነበር ማለት ይቻለኛል። ተመስገን!
የዱዳው የአብይ ሌጋሲ ዋና መንጠቋዊ
ሂደቱ ተጽእኖ ፈጣሪዎችን እያደኑ ማዛል ነው። በግልም በቡድንም። ከዛ አማራነትን መቅበር መመንጠር። አሁን ተመስገን ነው።
የአናባቢ አልቦሹ ዱዳው የአብይ ሌጋሲ እርቃኑን መቆሙ ታውጇል። ህዝባችን ብጡል ነው። ህዝባችን ሊቀ - ሊቃውንት ነው።
ይህን ያህል
ሥር የሰደደ የጥበብ ተሰጥኦ አለው የአማራ ህዝባችን። የአማራ ህዝብ ዛሬን የሚፈትሽበት ልበማህተም -፤ ዛሬን የሚመዝንበት ኪሎ -፤ ዛሬን
የሚለካበት ሚዛን- ፤ የዛሬን አቅጣጫ የሚያስተውልበት አኒሞ ሜትር -፤ የዛሬን ሙቀት የሚለካበት ቴርሞ ሜትር በመዳፉ አለ። ተመስገን!
· ቁርጠኝነት ከመንዝ!
በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ የታዝብኩት ዛሬ ቁመን እዬለመን ከላደመጣችሁ ጦር የያዝን ለት ብትለምኑን
አንመለሰም የመንዝ አማራ ድምጽ ነበር። ዕውነት ነው። አማራን መሪ አልባ በማድረግ በልብጥ ጭንብል እንዲመራ እና የኦነግ ሎሌ እንዲሆን
የተሰራው ዘመን ይቅር የማይለው የሴራ ቱባ በጥልቀት የአማራ ህዝብ ተረድቶታል። ለዚህ ነው ባዶ ወንበር ያሸከመው አገር ውስጥም
ውጭም።
ይህ መንፈስ ጥልቅ ነው። ይህ መንፈስ መምህርም ነው። ይህ መንፈስ ውስጥ ነው። ይህ መንፈስ
ሥርዬትን ጠያቂ ነው። ይህ መንፈስ እርቅ ለማኝ ነው። ይህ መንፈስ ሽማግሌ ነው። ይህ መንፈስ ማስጠንቀቂያም ነው። ስለዚህ በትዕቢት
ተወጥሮ፤ ንቀትን ጎርሶ አማራን እንደ ጤፍ እያጨደ ያለው የኦህዴዱ ኦነግ እና ግርባው ብአዴን ቢያስቡበት መልካም ነው።
· የጠቅላይ ሚኒሰትር ቤቢሲተርነት ዘመን።
·
በዚህ ዘመን ያላስተዋልነው ነገር የለም። በተለይ የአማራሩ ጭድነት እና ገለባነት። የህዝብ ንቃተ
ህሊና መሪነት እና በሳል ሥነ ልቦናዊ አቅም ይበል ያሰኛል። እኔ ያዬሁት ወርቅ ነገር የዶር አብይ አህመድ ለአቶ ጃዋር ቤቢሲተርን
መሆናቸውን ህዝብ መርምሮ ፈትሾ ደርሶበታል። ይህ ዕንቁ አምክንዮ ነው።
መቼም ልብ እና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ የገለጠው እዮራዊ
ሚስጢር ነው። ቤቢሰቲርነቱን ለጥ ብለው ተቀብለው የሚያገለግሉትን የሴት ሚኒስተሮች፤ የካሜራ እና የሙድ ውሎ ላይም ሰልፉ ተግሳጽ ልኳል።
ቅኔው ጎንደር ቅኔንም ዘርፏል በአቶ ጃዋር ቤቢሲተር በኮ/ አብይ አህመድ በጥይት ተደብድበው
ሰማዕትነትን ለተቀበሉት ለነብያዊ ጀግናው ለብ/ አሳምነው ጽጌ እንዲህ ይላል
„ቅኔው ወይ ፍንክች፤ የበርሃው መብረቅ የአማራ ህዝብ አንበሳ
አሳምነው ጽጌ ምነው ብትነሳ! አማራው።
ይላል።
እኔ ደግሞ እላለሁኝ ለአማራው ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም መድህን ነበሩ። ከፈጣሪያቸው ጋርም ቅርብ ስለነበሩ ብዙ ነገሮችን አስቀድመው ተንብዬው ነበር። የቅዱስ
ላሊበላ በረከት ያልተለያቸው በመንፈስ የደነገሉ እንደ ነበሩ ከልብ ሆኖ የትግል ጉዟቸውን ለመመርመር ቅን ዜጋ እንዲህ ሊገለጥለት
ይችላል።
· „እባካችሁን ውሸታችሁን አደራጁት“ ይላል ጎንደር።
ጎንደር ለመሪው የኦነጉ ብአዴን በደረጃም ያወጣው አለ። ድንቁ ጉዳይ የኦነግ መሪዎቻችን ግን
„ምን እያጨሱ ነው? ተግባብታችሁ ሀገር መምራት ቀርቶ ተስማምታችሁ
እንኳን መዋሽት አትችሉም። ለእንኩቶው የኦነግ ፖለቲካ የተላከ ጉልበታም መልዕክት ነው። ቢያንስ ውሸታችሁን አስማሙት ነው። ውሻታችሁን አደራጁት። ውሸታችሁን አገር መሪ ስታደርጉት ለከት ይኑረው ነው።
ኦነጋውያን እነሱም ሆነ ልባቸውን የገጠሙለት ግልብ ሰብዕና እሚደመጥ ሰው አንድም የላቸውም።
የተፍረከረከ ነገር። ባልቦካ ምርጊት የተገናባ ቤት ነው የሆነው ሁለመናው። ወላዊም ሆነ ተናጠላዊም ብናኝ አቅም የላቸውም። ቀበሌ
መምራት አይችሉም እንኳንስ አገር። የፈረደበት የኦሮሞ ህዝብ በሥሙ ይነገዳል እንጂ። ያሳፍራል። ገመናው ነው አደባባይ የወጣው።
„ አብይ ማኪያቶ ይጣፍጣል።
ተመስገን ጥሩነህ የተለቀቁ የሉም።
ደሬሳ ተፈራ የታፈነ የለም።
ንጉሡ ጥላሁን ሁሉም ተለቀዋል።
ጁይላን አብዲ እኛ አናቅም።
ጄ መላኩ ፋንታ አውቀው ተደብቀው ይሆናል።
አበበ ገረሱ የሰማሁት የለም።
ጄይላን አብዲ የከፋ ነገር ሊኖር ይችላል የኛዎቹ ጉዶች መረጃ የለንም አይሞቀንም አይቀዘቅዘንም“ መግቢያ አለው። ሆድ ዕቃ አለው። መደምደሚያም አለው። መጽሐፍ ማለት ይቻላል።
አገርን እመራለሁ ይላል የኦነጉ መንፈስ ግን አቅም የለሽ ስለመሆኑ ደግሞ ህዝብ እንዲህ ይታዘባል። በቁመቸው ሙተዋል። ጉራ ብቻ።
ቻቻታ ብቻ። ፌስታ ብቻ። ካሜራ ብቻ። ከብት ማረድ ብቻ። መታበይ ብቻ። ማስመሰል ብቻ። ጭካኔ ብቻ። ውሸቱን እንኳን በቅጡ ማደራጀት
አለመቻላቸውን ህዝብ ይህን ያህል አንብቦ፤ ተርጉሞ አማሳጥሮታል። ተመስገን!
· ልባም አምክንዮ።
„በሚታዬው እና በማይታዬው በመንግሥት
የታፈኑ ወገኖቻችን ይልቀቅ“ ይህ የመንግሥትን ቀውስ መሻት ሆነ በሽብሩ ውስጥ ስለመኖሩ ስውራዊው የአብይ
ሌጋሲ እና ግልጡን የአብይ ሌጋሲ ሰልፈኞቹ የሞገቱበት አምክንዮ ነው። ለዚህ ነው እኔ የ50በ60 የብልጽግና ህልም የአረጠ ነው ብዬ የሞገትኩት። ለዚህም ነው ይህ የአረጠው የብልጽግና
ፖለቲካ ማህበራዊ ንቃተ ህሊናን ዕውቅን የመስጠት አቅሙ ዜሮ ነው ብዬ የጻፍኩት።
በእነሱ የወግ ገበታ እና የቤተ መንግሥት ግብር
ብቻ አገር የሚመራ ይመስላቸዋል። ወይንም ተጽዕኖ ፈጣሪ የሚባለቱን መላሾ እዬሰጡ ማዛል መፍትሄ ይመስላቸዋል። ህይወቱን የሚኖረው
ህዝብ ህይወቱ እራሱ የሚያስተምረው ቁምነገር አለ። ይህን ይልቅ ያዳምጡት።
ይህ ታሪካዊው ሰልፍ አደራ ማውጣት ያልቻለውን፤ ቃሉን ያልጠበቀውን የኦሮሞ ህዝብንም ሰልፉ ወቅሷል።
የተገባም ነው። በአማራ ትክሻ ስልጣን ላይ ተወጥቶ አማራን መጨፍጨፍ ለሰማዩም ለምድሩም የማይመች ጉዳይ ነው። ጭጎጎት።
„የደንቢ
ደሎ ፖለቲካ አገር ያፈርሳል።“ ሌላው ስለ ደንቢ ዶሎ የተነሳው ነገር ነው። ግርም ያለኝ። እኔ እራሱን
አስችዬ በ201 ዓ.ም አቶ ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ ደንቢ ሄደው በነበሩበት ጊዜ ደንቢ የራሷን ንጉስ ነው የምትፈልገው
ብዬ ጽፌ ነበር። ደንቢ ደሎ በጥንቃቄ መያዝ አለባት ብዬ ነበር በተያያዥ ጹሑፎች ሁሉ አበክሬ ገልጬ ነበር።
ኦነጋውያን ማቆላመጡን ማብቃት ይገባል።
· ስለ አማራ ሊሂቃኑ ውስጥነት።
በግፍ እና በሴራ የታሰሩ የአማራ ሊሂቃን፤ ጋዜጠኛ አስመልክቶም ሰፊ ሽፋን ሰልፎቹ ሰጥተውታል።
ይህ ሰልፍ የመጨረሻችን ነው ብሏል። የህዝብ ልብ ከሸፈተ ጥሩ አይመስለኝም። ኦነጉ/ አዶፓ እራስን አርሞ ተከታታይ ተግባራዊ እርምጃዎችን
መውሰድ የሚገባ ይመስለኛል። አቶ ጃዋር መሃመድ የአማራን የልዕልና ጥሞና ሥነ - ልቦናዊ መንፈስ የመምራት አቅም የለውም። ፈጽሞ!
ከአማራ ኪናዊ ልቅና ጫፉ መድረስ አይችልም ግራጫማው አቶ ጃዋር መሃመድ። ግራጫማ የሳሙና አረፋ
የአማራን ህዝብ እንዲመራም ሊፈቀድለትም አይገባም። የአማራ ህዝብ በዬትኛውም ምርኮኛ በሞግዚት አይመራም። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ
አህመድ እራሳቸው የአቶ ጃዋር መሃመድ ምርኮኛ ናቸው።
ሌሎችም
ተደማሪ ድርጅቶች ምርኮኛ ናቸው። ተደማሪ ሚዲያዎችም ምርኮኛ ናቸው። የአማራን መንፈስ ለመመራት ብቃት እና ክህሎት፤ ጥበብ እና
ጥሞናን ይጠይቃል። ልኩን ያላውቀ ግጥምጥሞሽ ነው አሁን እመራለሁ ብሎ እዬተንጠባጠበ የሚገኘው። ፍርክርክ።
በጣም ያበረታታኝ ነገር ለአንድ በኽረ ጉዳይ ሦስት ሚዲያዎች አሉ።
በኢትዮጵያዊነትሥም ሦሰቱም
በህወሃት ላይ ሲያላዝኑ ውለው የሚያድሩ። ይህን የህዝብ አጀንዳ እንዲሆንላቸው ይሻሉ። የኦነግ ጭካኔ እንዲጋረድ። እነሱ ተግተው
በሁለገብ የኦነግ ሴራ አማራ ላይ የዘር ጭፍጨፋውን ድልዳል እዬፈጠሩ የአማራ ሊሂቃንን በቃለ ምልልስ ጠምደው የሥነ - ልቦና ድቀት
ለመፍጠር ሲታክቱ፤ የአማራ ህዝብ የማህበራዊ ንቃተ ህሊና ከፍታ ግን አስፈንጥሯቸዋል።
ስለ ህወሃት ያዬሁት የረባ ነገር አልነበረም። አጀንዳዬ አይደለም አለ የአማራ ህዝብ። አማራ ጠላት እና ወዳጁን
የለዬ ህዝብ ነው። ወቅቱንም ማንበብ የሚችል የፖለቲካ ብስለት ያደለው
ህዝብ ነው አማራ። ከሁሉ ብቻውን መቆሙን ዕውቅና ስጥቶታል። ማንም እንደሌለውም አውጇል። ይህ ብሥራት ነው። አቅሙን ለራሱ
መንፈስ ብቻ ለማዋል እንዲወስን ይረዳዋል።
የሁሉም ሰልፎቹ ሥርዓትን የተከተሉ፤ ጨዋ እና ማስተዋል የበዛባቸው ሲሆን የጎንደሩ የታዳጊ ወጣቶች
ተሳትፎ በስካውት መልክ ጥሩ ታሪካዊ ተግባር ተከነውኗል ብዬ አስባለሁኝ። ጎንደር እና ደብረታቦር በጥዋቱ ጀመረ፤ በጥዋቱ ክሽን
ያለ ተግባር ከውኖ በሰላም መጠነቀቁንም አበሰሩ። ተመስገን።
· ልዩ።
የደብረታቦር ወጣት ሴቶች ለቅሶ
ላይ ነው የነበሩት። ይህን የዓለም ሚዲያም ሊመዘግበው የሚገባ ታሪካዊ የሰልፍ አይነት ነው። የትም አገር በዬትም ሁኔታ ታይቶ
አይታወቅም። በስውር ከተቀዳው የጌዶኦ ህዝብ የአዳራሽ ለቅሶ ጋር
ተመሳጠረብኝ። አጅግ ድንቅ፤ ፍጹም ልዩ የሆነ ውስጣዊነት ነው ያዬሁበት። ኦርጋኒክ የሆነ ሰዋዊነት!
ሌላው ጎንደር እንደ ለመደባት የአዲስ
አባባ ህዝብ ድምጽ ሆኗለች። „ለታፋኑ አዲስ አበቤዎች ነፃነት
ይሰጣቸው“ ስትል አጋርነቷን አሳይታለች። ባለፈው ጊዜ ለድምጻችን ይሰማ፤ ለኦሮሞ ፕሮቴስት፤ ለጋንንቤላ ህዝብ ድምጽ ሆና ነበር
ልዕልት ጎንደር። ምንም እንኳን የልዕልት ጎንደር ጥረቷ አመድ አፋሽም ቢሆንም። ጎንደር ላይ ያለው መንፈስ ሁለንትናዊነት ነው። የተባረከ ባዕት ነው።
አሁን አሁን የራሱ ልጆችም
ጠላት ሆነው ከዘመንኞች ጋር አብረው ሊሂቃን ልጆቹ ያለቁበትን ባዕት ለዳግም እጨዳ በርቱልን እያሉ ለኦነግ ጨካኝ መንፈስ አሳልፈው
ሲሰጡ እያስተዋልኩኝ ነው። እርግማን!
· ከመፈክሮቹ ውስጥ የተነበቡኝ እነዚህ ነበሩ
· „የታገተው አማራነት ነው።
· ለታፋኑ አዲስ አባባዎች ነፃነት ይሰጣቸው።
· በወጀብ ውስጥ ሆነን እንኳን ከአማራነት ከፍም ዝም የለም።
ጎጃም+ ወሎ+ ጎንደር+ ሸዋ= ዘላዓለም አማራ። እርማችሁን አውጡ።
· ፍትህ ለአማራ።
· በድኑ አዴፓ የአማራን ህዝብ በዝንጀሮ ፖለቲካ መመራት ይብቃው።
· የጎጥህን ጀግና ድድህ ላይ ተነቀሰው። አማራን መከፋፈል አትችልም። አትሞክረው።
አንድ አማራ /ጎንደር/
· በሚታዬው እና በማይታየው መንግሥት የታፈኑ ወገኖቻችን
ይለቀቁ።
· የአማራው ሂትለራዊ በህግ ሊጠዬቅ ይገባል።
· ሰልፍ ወጥተን ስናወግዝ የማንሰማ ከሆነ ሰይፍ ይዘን ስንነሳ ብትለምኑን
አምመለሰም {መንዝ}
· ጀግና ይሞታል ትግል ግን ይቀጥላል፤ የታገቱት ይለቀቁ! የታሰሩት ይፈቱ!
ይህ የመጨረሻ ጥያቄያችን ነው። ይለያል ዘንድሮ።
· የኦሮሞ ህዝብ ሆይ! ደምህ ደሜ ነው ላለው የአማራ ህዝብ
ምላሽህ ይህ ነው ወይ?
· መሬዎቻችን ግን ምን እያጨሱ ነው? ተግባብታችሁ ሀገር መምራት
ቀርቶ ተስማምታችሁ እንኳን መዋሽት አትችሉም።
· አማራነትን እዬገደሉ፤ እዬረሸኑ ኢትዮጵያዊያን መምራት የከሰረ ፖለቲካ ነው።
· እርሷ አማራ ናት፤ ሴት ብቻ አይደለችም።
· የደንቢ ደሎ ፖለቲካ አገር ያፈርሳል።
· ዬሴት ሚኒስተራት በበዛበት ኢትዮጵያ የሴት ልጅ መታገት ከውርዴት በላይ
ውርዴት ነው።
· Stop Babysittinge Jwar!
· አማራነት ለወንድሞችህ አለሁ ባይ አማራ ሆይ! ለራስህም፤
በሴት እህቶችህ፤ ለልጆችህ ስቃይ ብቻህን ነህ።
· አማራነት ወንጀል አይደለም
· ፍትህ ለሰኔ 15ቱ ለሞቱ መሪዎቻችን!
· ወይ ፍንክች የበርኃው መብረቅ የአማራ ህዝብ አንበሳ አሳምነው ጽጌ ምነው
ብትነሳ! አማራው።
· አብይ ሆይ ጭንብልህን ግለጥ!
· አማራ ሆይ እራስህን ውቀስ፤ የግል ሃላፊነትህን ተወጣ፤
· የተማሪዎችን ደህንነት መጠበቅ ያልቻለ መንግሥት ሀገር አይጠብቅም።
· ጠላት ደስ እንዲለው ስንት አማራ ይሙት?
· የታገቱ
እህቶቻችን በአስቸኳይ የማይለቀቁ ከሆነ እርምጃ ለመውሰድ እንገደዳልን።
/አስፊሪ ነው።/
· የአማራ
ልጆች የት ናቸው?
· የሴት ሚኒስተሮች
ዝምታ እስከ መቼ ነው?
· ገዳይ ነህ
ይሉሃል ገዳዩ ሌላ ነው። የአንተ ወንጀልህ ለእኛ መሞትህ ነው። /ለነብይ ብ/ ጄ አሳምነው ጽጌ።/
· እርገት።
ትናንት ደሴ ሰላማዊ ሰልፍ ነበር። በጥር 19 ደግሞ ከ37 ከተሞች በላይ የአማራ ህዝብ ተሳትፏል፤
በቅኔው ጎጃም ትናንሽ ከተሞች ሳይቀር እጅግ ጉልበታም ሰልፎችን ሲያክህድ ደባርቅ፤ አንባ ጊዮርጊስ፤ ጯሂት፤ ወረታ፤ ደብረብርሃን
ከሙሉ ጎጃም ጋር ተሳትፈዋል። ዛሬ ዜናውን እስከ አጠናቀርኩበት ሰአት ድረስ ዋግ ምራ ሰቆጣ፤ መተማ፤ ላሊበላ፤ የጣራ ገደሟ አዲስ
ዘመን፤ ጎንደር ከተማ፤ ሻውራ፤ ላሊበላ፤ ኮንበልቻ፤ ደብረታቦር፤ አማራ ሳይንት፤ ሰልፍ እንደተካሄደባቸው ለማወቅ ችያለሁኝ።
„የአማራ ልጆች የት ናቸው?“
የኔዎቹ ኑሩልኝ፡፤
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ