ልጥፎች

ከሜይ 1, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የቀንበጥ የአንድ ዓመት ጉዞ እንደዋዛ?

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  የቀንበጥ የአንድ ዓመት ጉዞ እንደዋዛ? „የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ   ወራት ፈጠሪህን አስብ።“ መጽሐፈ መክብብ ፲፪ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie   01.05.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ እንዴት ናችሁ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ቀንበጥ ብሎግ ሥራ የጀመረችበት አንደኛ አመቷ ነው። ቀንበጥ ብሎግ በ2015 መጋቢት ላይ አደራጅቸው በዝምታ 3 ዓመት በሱባኤ ከቆዬች በኋዋላ ተስፋን ተከትሎ በትጋት የበኩልን ለማድረግ ቀለል ባለ መንፈስ ተግባሩን አህዱ ያለችው ልክ የዛሬ ዓመት ግንቦት 1.2018 ነበር። ከቀደሙ ጹሑፎቼ ወደዚህ አርኬቡ ያሻገርኳቸው ጥቂት ጹሁፎች፤ ለህትምት ከበቁት ግጥሞቼ እና የወግ ገበታዎች ያከልኳቸው፤ እንዲሁም የጸሐፊ እና የተርጓሚ የአቶ መስፍን ማሞ ጹሑፍ አክሎ፤ በዋናነት አገራዊ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮችን አዳዲስ ጹሑፎችን ጨምሮ በዓመቱ ውስጥ ፖስት የተደረጉት ከግንቦት 1. 2018 እስከ ታህሳስ 2018 ድረስ 537 የህሊና ውጤቶች፤ ከጥር አንድ እስከ ሚዚያ 30 ቀን 2019 ድረስ ደግሞ 144 ጹሑፎች ፖስት ተደርገዋል። በድምሩ ከግንቦት አንድ 2018 እስከ ግንቦት አንድ 2019 ድረስ 681 ጹሑፎች ለንባብ በቅተዋል። በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ በአመዛኙ ድጋፋዊ አመክንዮዎችን፤ ከድጋፍም ወጣ ያሉ ወቀሳዎችን ያዘሉ ጹሑፎች ሲሰተናገዱ እኔ ባስበኩት ልክ ግን የአብይ ሌጋሲ ዝንባሌው አዎንታዊ መሆን በለመቻሉ አዝኛለሁኝ። እኔ አብሶ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ እኩል፤ ፍትሃዊ እና ተጠያቂነት ያለበት አያያዝ እጠብቅ ነበር። አብሶ ከመሰከረም 2018 ወር ጀምሮ ያሉ ነገሮች ግን ተስፋን የሚፈታተኑ ነበሩ ማ