ልጥፎች

ከሴፕቴምበር 20, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#የፈቃድ ጉዳትን ፍቀደው እና ተዋወቁ።

  #የፈቃድ ጉዳትን ፍቀደው እና ተዋወቁ። #ቸር ሁን እና ተጎዳ።   #ሩህሩህ ሁን እና ተጎዳ። #አዛኝ ሁን እና ተጎዳ።   #አጽናኝ ሁን እና ተጎዳ።   #አይዟችሁ ባይ ሁን እና ተጎዳ።   #ቅን ሁን እና ተጎዳ።   #ዕውነተኛ ሁን እና ተጎዳ።   #የመርኽ ሰው ሁን እና ተጎዳ። #ታጋሽ ሁን እና ተጎዳ።   #እዩኝ እዩኝ አትበልና ተጎዳ። #ህግ አክባሪ ሁን እና ተጎዳ።   #ርጉ ሁን እና ተጎዳ። #ቅጽበታዊነትን ተጸየፍ እና ተጎዳ።   #ሰውኛ ሁን እና ተጎዳ። #ተፈጥሮኛ ሁን እና ተጎዳ።  ደስታ #መጋቢ ሁን እና ተጎዳ። ቂመኛ #አትሁን እና ተጎዳ።  በቀለኝነትን #ተጠየፍ እና ተጎዳ።  ብቁ #አድማጭ ሁን እና ተጎዳ።  ትሩፋትህ መንገድህ የቀና - የውስጥ ሰላምህ የከበረ - ንዑድ ህሊናህ ለችሎት የማያቀርብህ ትሆናለኽ። ሥርጉትሻ 2025/09/17

"#ፕሮፌሰር ዶር ብርሃኑ ነጋ "ጉራጌ ስለሆኑ ወጀብ በዛባቸው ያልከው" በፍጹም #አይመስለኝም - ለአቶ ኤርምያስ ለገሰ።

  " #ፕሮፌሰር ዶር ብርሃኑ ነጋ "ጉራጌ ስለሆኑ ወጀብ በዛባቸው ያልከው" በፍጹም #አይመስለኝም - ለአቶ ኤርምያስ ለገሰ።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን!     ጤና ይስጥልኝ አቶ ኤርምያስ ለገሰ እንደምን ሰነበትክ? ሁለቱንም በፕሮፌሰር ዶር ብርሃኑ ነጋ በግልህም ለሁለትም ሆናችሁ ያደረጋችሁትን ውይይት አዳመጥኩት። ስለምን በፕሮፌሰር ብርኃኑ ነጋ ላይ ወጀብ በዛ በሚለው አመክንዮ የሰጠኽው አስተያዬት " ፕሮፌሰር ዶር ብርሃኑ ነጋ ጉራጌ ስለሆኑ ነው " ብለህ ያቀረብከው አመክንዮ በፍጹም አይመስለኝም የሚል ሃሳብ አቀርባለሁኝ።    አንተም እንደምታውቀው "ከኢትዮጵያ ሱሴ ነው" ንቅናቄ በፊት በዓለም ዓቀፍ አሉ የሚባሉ አብዛኞቹ ሙሁራን፤ ውጭም አገር፤ አገር ውስጥም ያለው ኢትዮጵያዊ ተስፋውን ያሳካልኛል ብሎ የሚጠብቀው በፕሮፌሰር ዶር ብርሃኑ ነጋ ስኬት ልክ ነበር። ሚሊዮኖች ከውስጣቸው ያከብሯቸው፤ ከህሊናቸው ይፈቅዷቸው እንደ ነበረ አንተው እራስህ ያዬኽው የሃቅ እንክብል ነበር። አብሶ በአውሮፓ ህብረት የነበራቸው ዕውቅና እና ተቀባይነት ልዩ ነበር።    ሙግታችን ኢትዮጵያን ለመረከብ ጎደለ የምንለውን ንቅናቄያቸው እንዲያስተካክል ነበር። እርግጥ አገር ቤት ከገቡ በኋላ ብዙ ደጋፊያቸውን ለከቅላይ ሚር አብይ አህመድ እንዳስረከቡ ይረዳኛል። የሳቸው ማህበራዊ መሠረት ምንጩ ዜግነት ነበር። አብዛኛው ተስፋ የጣለባቸውም አማራ ነበር።    ደጋፊያቸው፤ አክባሪያቸው አማራ ነበር። ነገር ግን ከአማራ #መደራጀት ጋር በሚነሱ ሃሳቦች ዙሪያ ተስፋ እና ተስፈኛው እንደተፋጠጡ አስተውያለሁኝ። አማራው የራሱን ድርጅት ሲፈጥር በእሳቸው ድርጅት፤ የሳቸው ራዕይ ችግር እንደሚገጥመው ያው...

#ምንጊዜም #ኢትዮጵያ!

  #ምንጊዜም #ኢትዮጵያ ! "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። አዎን #ለሁልጊዜም ኢትዮጵያ!   #ስለሁልጊዜም ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ እናት አገር!  ኢትዮጵያ የመንፈስ #ማረፊያ ! ኢትዮጵያ ዙሮ #መግቢያ ! ኢትዮጵያ የተስፋ #ማህደር !  ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካኒዝም ልዩ #ምህዋር !  ኢትዮጵያ የነፃነት #ዶግማ !  ኢትዮጵያ የቀደምትነት #ተምሳሌት !  ኢትዮጵያ እግዚአብሄር/አላህ አለ ብላ በጽኑ #የምታምን የሃይማኖት አገር!  ኢትዮጵያ የጥቁር ህዝብ #ትንፋሽ #ማረፊያ !  ኢትዮጵያ ለነፍስም ለሥጋም #የ13 ወራት የጸሐይነሽ በዕት!  ኢትዮጵያ ሌት እና ቀን አቨው በጸሎት - በስግደት - በምህላ - በሱባኤ - በድዋ፤ በቅዳሴ - በምህላ - በዝማሬ የሚተጉባት እናት አገር! ኢትዮጵያ - የምትናፈቅ፤ የምትወደድ - የምትስብ አገር! ይህችን አገር የፍጹም #ሰላም ፤ #የምህረት ፤ #የመግባባት ፥ #የመተዛዘን ፤ #የመከባበር ፤ #የመደማመጥ የማድረግ ብልህነት ስለምን ራቀን? እራሳችን ለመፈተሽ እንፍቀድ።  እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።  ሥርጉትሻ 2025/09/19

ትምህርት የመኖር ፍሬዘር #ኦክስጅን ነው፤ ፍጹማዊ #ሰላምን በአጽህኖት ይሻል።

ምስል
  ትምህርት የመኖር ፍሬዘር #ኦክስጅን ነው፤ ፍጹማዊ #ሰላምን በአጽህኖት ይሻል። "አቤቱ ንፁህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   ትምህርት የራዕይ፤ የትልም፤ የሰለጠነ ግብ ማስፈጸሚያ ቁልፍ ጉዳይ ነው። ሰሞኑን በትምህርት ዙሪያ ከተለያዩ ባለሙያ ወገኖቼ አቶ ሙሼ ሰሙን ጨምሮ የፃፋትን አነበብኩኝ። ደስ ብሎኝ ነው ያነበብኩት። ምክንያቴ በማህበራዊ ዘርፍም አዋቂወች ትጋታቸው ስለአረካኝ ነው። ጉዳዬ ባዩ በርከት ሲል የሚያበረታታ ሙቀት ይሰጣል። አንዳንድ ሚዲያወችም ተነጋግረውበታል። በቂ ነው ብዬ ባላስብም።   ነገረ - ትምህርት በዓመት አንድ ወይንም ሁለት ቀን በመወያዬት ብቻ ስልጣኔን፤ እድገትን፤ ስኬትን ማግኜት #ጋዳ ይመስለኛል። አብሶ ሰላም ከሌለ አይደለም ተማሪው መምህሩ፤ የትምህርት ቢሮወች፤ የበታች አስተዳደሮች እንደምን የህሊና ተግባራት ሊከውኑ ይችላሉ? ሌላው ቀርቶ የኢትዮጵያ ዜናወች " #በሰበር " በድንገቴ፤ በአስጨናቂ ዜናወች የተጨናነቁ ናቸው። እንኳንስ ለልጆች ለእኔ ሙሉ ዕድሜ ላይ ለምገኘውም ይከብዳል። ለበሽታም ይዳርጋል።    እራሱ ከስንት ጊዜ በኋላ አንድ ቀን የምትገኝ የይምስራች፤ የተስፋ ፍንጣቂ ወይንም ፍንካች ሁነት ሲገኝ እንኳን የሚለወሰው በስጋት፤ ወይንም በማቃለል፤ ወይ በማጣለል በዛው ሌት እና ቀን ጊዜውን አቅሙን ሁሉ በሚውጠው የፖለቲካ ጉዳይ ጋር ተዛምዶ ይቀርባል። ዓውደ ዓመታት ከትንፋሻችን ጋር የተዋህዱ ናቸው። እነሱን እንኳን ስክን ብለን፤ ቀልባችን እፎይ ብሎ እንዲያሳልፍ ፈቃድ የለም።   አንድ ቀን አብረን ለመሳቅ #ንፋጎች ነን - እኛው እራሳችን፤ አብረን የተሰጠንን አክብረን ከትከት ቢቀርብን #ውሽክ ለማለት እንኳን አልታደልንም ብል ይሻለኛል። ይህ ደግሞ በብዙ ሁነት የውስጥ #ጤ...