ልጥፎች

ከጃንዩወሪ 21, 2020 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ለቆጠራ ዬተቀመርን።

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። ለቆጠራ ዬተቀመርን። „እኔ ልናገር ብወድ ሰው ይናገረዋልን?“ መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ 37 ቁጥር 20 ሥርጉተ©ሥላሴ Seregute©Selassie 21.01.2020 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ለቆጠራ ዬተቀመርን። ፍቅር ነስቶን ኢጎ ወሮን በዕብን - ነት ተሰውረን፣ በምንትሶ ተዋቅረን ተንተክትከን ወዬ ብ ን። ተጣፍተን አጣፍተን ማሰብን አደረግነው ብን። መኖር ጠፎቶን እልል ብለን ተስፋን ቀበርን። ትዕግስት ነስቶን ተነ ን ። መቻል‘አጥተን ባከን። ምንስ ብንሆን ምንም። በጭካኔ ሰግረን በመታበይ እትብት ቆርጠን ቂም ንብረት ሆኖ ቆጣጥረን ጧ ብለን ተዘረጋግተን ሟሟን። ከእንፋቅቅ ጋር ተርትመን በማነስ ተደምረን፤ በሽሚያ ደንብረን በጥድፊያ ተሸርብን፣ በራስ ምልኪያ ተሸንሽነን ተሸብልለን - ተጠምጥመን - ተበጥብጠን ተቀሽረን። በክፍልፍል ሰ ክ ረን በዲስኩር ብቻ አ በ ድን፤ ዝለን በድነን በራስ ፍቅር አ ረ ግን፤ እፍ ብለን በነ …ን። ተፈጥሮን ዘቅዝቀን ባለማወቅ ቀ በ ርን። በምሻምሾ ተረት ተዛለን ላ ሸ ቅን። ኢትዮጵያ ለማለት እንሆ ተሳነን ዛልን። ግን ምንድን ነን ? እኮ ማነን ? የማን ነን ? ማንስ ነን ? ምንስ ነን ? ለማንስ ነን ? ተ ወዴት ነን? ተ ማንስ ነን? ለቆጠራ የተቀመርን። ለማ ባ ያ የተሰበርን ተአልቦሽ ነን። ·          ተጣፈ። # ሥርጉተ   ሥላሴ። 11.33 November 24, 2019 ቢንቲ ሲወዘርላንድ። የኔዎቹ ኑሩልኝ መሸቢያ ጊዜ።