ለቆጠራ ዬተቀመርን።


እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።
ለቆጠራ ዬተቀመርን።
„እኔ ልናገር ብወድ ሰው ይናገረዋልን?“
መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ 37 ቁጥር 20
ሥርጉተ©ሥላሴ
Seregute©Selassie
21.01.2020
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ





ለቆጠራ ዬተቀመርን።
ፍቅር ነስቶን
ኢጎ ወሮን
በዕብን - ነት ተሰውረን፣
በምንትሶ ተዋቅረን
ተንተክትከን ወዬን።
ተጣፍተን አጣፍተን
ማሰብን አደረግነው ብን።
መኖር ጠፎቶን
እልል ብለን ተስፋን ቀበርን።
ትዕግስት ነስቶን
ተነ
መቻል‘አጥተን
ባከን።
ምንስ ብንሆን
ምንም።
በጭካኔ ሰግረን
በመታበይ እትብት ቆርጠን
ቂም ንብረት ሆኖ ቆጣጥረን
ብለን ተዘረጋግተን
ሟሟን።
ከእንፋቅቅ ጋር ተርትመን
በማነስ ተደምረን፤
በሽሚያ ደንብረን
በጥድፊያ ተሸርብን፣
በራስ ምልኪያ ተሸንሽነን
ተሸብልለን - ተጠምጥመን - ተበጥብጠን
ተቀሽረን።
በክፍልፍል ረን
በዲስኩር ብቻ ድን፤
ዝለን በድነን
በራስ ፍቅር ግን፤
እፍ ብለን በነ …ን።
ተፈጥሮን ዘቅዝቀን
ባለማወቅ ርን።
በምሻምሾ ተረት ተዛለን
ቅን።
ኢትዮጵያ ለማለት እንሆ ተሳነን
ዛልን።
ግን ምንድን ነን?
እኮ ማነን?
የማን ነን?
ማንስ ነን?
ምንስ ነን?
ለማንስ ነን?
ወዴት ነን?
ማንስ ነን?
ለቆጠራ የተቀመርን።
ለማ የተሰበርን
ተአልቦሽ ነን።
·         ተጣፈ። #ሥርጉተ ሥላሴ። 11.33 November 24, 2019 ቢንቲ ሲወዘርላንድ።
የኔዎቹ ኑሩልኝ መሸቢያ ጊዜ።



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።