ልጥፎች

ከጁን 10, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ከስቃይ ወደ ሰላም የሚወስድ እውቀት | ዶ/ር አብርሃም አምሃ እና ገነት አህፈሮም | Manyazewal Eshetu...

ምስል

የኢትዮጵያ ፖለቲካ መለያ ባህሬ #ስስታምነት ብቻ አይደለም #ቆንቋነትም።።

ምስል
  የኢትዮጵያ ፖለቲካ መለያ ባህሬ #ስስታምነት ብቻ አይደለም #ቆንቋነትም። ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሶሻሊዝምን ርዕዮት መከተል ከጀመረበት ጀምሮ ስስታም የሆነ ይመስለኛል። ባለፈም ቆንቋነነት። ከስስታምነት ያለፈ #ስግብግብነት ። ተዳብለህ በተወሰነ ደረጃ ህሊናህ የሚልህን አድምጥ እንኳን አይፈቀደም። #ልጠቅልልህ ፤ #ልሰልቅጥህ የተሰጠህ ህሊና በእኔ ቁመና ከሆነ ይሁን በስተቀር ቆልፈህ ተቀመጥ። የአንተ ህሊና በእኔ ህሊና ይመራ ነው መከራው። ይህ የሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች በሽታ ሲሆን ወታደሮች ደግሞ ደጋፊወች ናቸው። አይታወቃቸውም እንጂ ሳይለንት ዲስክርምኔሽንም ነው። በራሱ ህሊና ሊመራ የወሰነ፤ አለኝ የሚለው የራሱ የሆነ ነገር ያለው ባይፈጠር ይሻላል። ተረባርበው ድራሹን ያጠፋታል። ይህ ስልጣን ላይ ሆነ ስልጣን ላይ አልሆነ የሁሉ ድዌ ነው። #ወረርሽኝ ። አሻም ያሉ እንደ እኔ አፈንጋጮች ህሊናቸውን ያላከራዩ ወይንም ያልገበሩ በውራጅ ማንነት ፋንታዚ ያለቀዘፋ ወይንም የማይቀዝፋ በስውር እስከ ቤተሰባቸው ይመነጠራሉ። ከእስር ሳንፈታ እናልፋለንም። እስሩ ቤት ለቤት ስለሆነ ብቻችን እንዳአዝን ይሆናል እምናልፈው። በዚህ መሰል ህይወት ለመጣው ለሄደው ያላደገደጉ የእኔ መሰል መከረኞች አሉ። ትልቁ ፀጋቸው ግን በነፃነታችው ልክ መኖርን ፈቅደው ማሸነፋቸው ነው ሳይገብሩ። ስለዚህም ኢትዮጵያ ጥሪ ይዘው ከሚወለዱ ልጆቿ በረከት #እዬተነፈጋት አሁን ካለችበት ደርሳለች። በጥንት ዘመን በ13ኛው መቶ ክ/ ዘመን ጎንደር ያደገው በሊሂቃኑ፤ በሊቃናቱ የመጠቀም ደንበር የለሽ መብት ስለነበረ ነው። እኔ ሳድግም የጎንደር ትውፊቱ ብልህ ሰው ከተገኜ ወደ እትብቱ ወደ ተፈጠረበት እንዳይሄድ #በጋብቻ ይያዛል። የጎንደር ስልጣኔ ሁለገብነቱ