ልጥፎች

ከሴፕቴምበር 27, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ቴዎድሮስ፤ ብቻውን የቆመ የለውጥ ሐዋርያ መስፍን ማሞ ተሰማ

ምስል
ቴዎድሮስ፤ ብቻውን የቆመ የለውጥ ሐዋርያ መስፍን ማሞ ተሰማ አፄ ቴዎድሮስ (1847 ዓ / ም - 1860 ዓ / ም ) በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ቴዎድሮስ አንጀት የሚበላ በክብር የወደቀ ታላቅ ሰው እንደ ነበር ፈፅሞ የሚያጠያይቅ አይደለም። ታዲያ ሰብዕናውን አሳዛኝና ተከባሪ የሚያደርገው ህይወቱን ያጠፋበት አስደናቂ ሁኔታ ሳይሆን፤ ከሁሉ በላይ ታላቁ ብቸንነቱና የኖረበት ዘመን ባጠቃላይ ዓላማውን ሊረዳለት ሳይችል መቅረቱ ነው። ቴዎድሮስ ማንኛውንም የመገንጠል እንቅስቃሴ ሁሉ በቆራጥነት ይታገል የነበረውና አጋር ፍለጋ እንደዚያ ሲባዝን የኖረው ከዚህ / ታላቋን ኢትዮጵያን የመገንባት ዓላማ / የተነሳ ነው። ዳግማዊ ቴዎድሮስ ከወሰዳቸው ዋና ዋና እርምጃዎች ውስጥ አንዱ የባሪያ ንግድ ማስቆሙ ነው። ከዚህም ጋር የሀገሪቱ ነዋሪ ሁሉ ሥራ እንዲኖረው የሚል ደንብ በማውጣት፤ ተስፋፍቶ የነበረው የዝርፊያ ወንጀል እንዲገታ አድርጓል። ይህን የሚመለከተው አዋጅ እንዲህ ይነበባል፤ “ ገበሬ ይረስ፤ ነጋዴ ይነግድ፤ እያንዳንዱ ሰው በየሥራው ይሰማራ። ” በኢትዮጵያ ንግድና የህዝብ ግንኙነት እንዳይስፋፋ እንቅፋት ሁኖ የኖረውን የሽፍታ መቅሰፍት ከሞላ ጎደል ለማስታገስ በመቻሉ ቴዎድሮስን ሊያስመሰግነው የሚገባ ነው። የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት / ደግማዊ ቴዎድሮስ / የሀገር ውስጥ አቋሙን ካጠናከረ በሁዋላ በውጪ ፖሊሲ ረገድ ታላላቅ ዕቅዶችን ነደፈ። … ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሰጠው ኢትዮጵያን የባህር በር በለቤት የማድረጉን ተግ