ልጥፎች

ከኦገስት 1, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

schweiz.

ምስል
 

ከ3000 በላይ ቀዶ ህክምናዎች? የብዙ ህፃናት አባት ዶ/ር አብይ ታደሰ ከጂማ!#Drabiytadessejimma#gi...

ምስል

የእቴጌ #ብሪቱ ሰርግ እና #ቅልቅል ወይንስ #ኑዛዜ? ምጣኔ ሃብታዊ ተህድሶው እና ሥርዓቱ። • #ብሄራዊ ስሜት አድራሻው የት ይሆን? ሚናውስ? #ኢትዮጵያዊነት መርህስ #መሪስ ነውን???

ምስል
  • የእቴጌ #ብሪቱ ሰርግ እና #ቅልቅል ወይንስ #ኑዛዜ ? ምጣኔ ሃብታዊ ተህድሶው እና ሥርዓቱ። • #ብሄራዊ ስሜት አድራሻው የት ይሆን? ሚናውስ? #ኢትዮጵያዊነት መርህስ #መሪስ ነውን??? "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   በኢትዮጵያ ገብያ መር የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ በመሆን ላይ መገኘቱን አስመልክቶ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሊቀ - ሊቃውንታት ሙያዊ ትንታኔ እዬሰጡ ነው። በተጨማሪም ገዢው የኢትዮጵያ የጠሚር አብይ አህመድ መንግሥትም የራሱን ባለሙያወች አሰልፎ ማብራሪያ እያሰጠበት ነው። በኢትዮጵያ ገለልተኛ ሚዲያ ስለለ በኢኮኖሚ ሙያ ለሌላቸው ዜጎች ግራ የሚያጋባ ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል ብዬ አስባለሁ። ሁሉም በራሱ መሻት ዙሪያ ስለሚሠራ።    የመነሻ የሆነ ሃሳብ ያላቸውም ቢሆን የኢኮኖሚ ፍልስፍናው የማይደፈር ተርም ስለሆነ ሜቶሎጂው ከባድም ስለሆነ ለአማተር ፖሊሲውን የመረዳት የአቅም ስስነት ሊኖር ይችላል። ከሁሉ የሚከፋው የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ሁሉም ዓይነት እርምጃ #በደራሽ ዜና ስለሚያውጁ የበቃ እንኳን ባይሆን የነቃ የህሊና #ጉዝጓዝ አልቦሽነቱ ሽብር ነዢ የመሆን አቅሙ የዚያኑ ያህል ከባድ ነው። ሌላው ቀርቶ ለካድሬወቻቸው እንኳን በቂ ግንዛቤ፦ መረጃ በአግባቡ ስለማይሰጡ የተበጣጠሰ ግንፍል #ስሜት #ገዢ ሆኖ ይታያል። በግራ ቀኝ ያለውን ገለፃ አቅርቦ ህዝብ ህሊናው እንዲዳኜው ከማመቻቸት የመንግሥት ልሳንን ብቻ የደገፋ እሳቤወችን ይለፍ ሲሰጡ አስተውያለሁ። ኢኮኖሚ የህልውና #ህሊና ነው።    #በዘባጣ ሥርዓት የፈለገ ዓይነት ፖሊሲ ሥራ ላይ ለመዋል ዳጥ እና ምጥ ነው። ይህም ሆኖ ህዝብ ችግሩን ተረድቶ የተረጋጋ ተሳትፎ ያደርግ ዘንድ የግንዛቤ አድማሱ የሚያሰፋ መስኮች እገዳ ሊጣልባቸው አይገባም። ...