ሰብዕዊነት ሲበጠስ ትዕግስትም ይበጠስ ...
እንኳን ደህና መጡልኝ። „በሰዎችና፡ በመላእክት፡ ልሳን፡ ብናገር፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ እንደሚጮኽ፡ ናስ፡ ወይንም፡ እንደሚንሽዋሽ ው ፡ ጽናጽል፡ ሆኜአለሁ። ትንቢትም፡ ቢኖረኝ ፥ ምሥጢርን፡ ሁሉና፡ እውቀትን፡ ሁሉ፡ ባውቅ፡ ተራሮችንም፡ እስካፈልስ፡ ድረስ፡ እምነት፡ ሁሉ፡ ቢኖረኝ፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ ከንቱ፡ ነኝ። ድሆችንም፡ ልመግብ፡ ያለኝን፡ ሁሉ፡ ባካፍል፥ ሥጋዬንም፡ ለእሳት፡ መቃጠል፡ አሳልፌ፡ ብሰጥ፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ ምንም፡ አይጠቅመኝም። „ ( ዬሐዋርያው ዬቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ቆረንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፫) ፕ/ለማ መገረሳ ይማሩበት ዘንድ እንደ አዶልፍ ሂተለር በግሎባሉ ከመወገዛቸው በፊት። ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 08.03.2019 ከእመ ዝምታ። ቃል የእምነት ዕዳ ነበር! · ቁጥር አንድ ለእኛ በጥቁር። ዛሬ ሦስት የህሊና ዳኝነት የኦሮምያ ፕሬዚዳንት እና የ ኢትዮጵያ ጠ/ሚር ለማ መገርሳ ይሰጡበት ዘንድ ሦስት ጉዳዮችን ነው እማነሳው። ሦስቱም ተወራራሽ ናቸው። የኢትዮጵያን መንፈስ ሃይልነት እና 21ኛው ምዕተ ዓመትን ጭንቅ ስለሚለው ሰብዕዊነት እና ተፈጥሯዊነት። የመጀመሪያው ዛሬ „የኔ የነፃ...