ልጥፎች

ስለተከደነ።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ስለ ተ ከደነ። „የመከረኝን እግዚአብሄር እባርከዋለሁ።“ መዝሙር ፲፬ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  13.03.2019  ከእመ ዝምታ - ከሲዊዘርላንድ እንዴት ናችሁ ውዶቼ? ደህና ናችሁ ወይ ዛሬ ከፍቶታል። የደነዘዘው ቀን ነው። እኔም አውሮፕላን አደጋ ሲከሰት ድርጭት ነው የምሆነው። ይጨንቀኛል። ለደረሰው አደጋ ብቻ ሳይሆን የአውሮፕላን አደጋ ሲደርስ እጅግ የሚያሳስበኝ ያን ተከትለው ተጨማሪ ተከታታይ አደጋዎች ደግሞ ስለሚከሰቱ ነው። ይህ ስለምን እንደሆን እኔ እንደማስበው በሌሎች አገር አብራሪዎች ላይ  አደጋው ተጨማሪ ስትረስ ስለሚፈጥር ይምስለኛል። ስሊዚህ አንድ አደጋ ሲደርስ ተከታይ ሌላ አደጋ ደግሞ ይኖራል የሚል ተጨማሪ ስጋት ያድርብኛል። ያው እኔ የግሎባል የበረራ ቤተኛ ከሆንኩኝ ዓመታት ተቆጠሩ። ብረሳው፤ ብተወው ደስ ይለኝ ነበር ግን ከነፍሴ ጋር ባላሰብኩበት ሁኔታ ተጠባቀ። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ አዬር መንገድ በድንገተኛው አደጋ ሳይደናቀፍ ተግባሩን በተለመደው መንገድ በትጋት መቀጠሉ በውነቱ የአመራሩን ብቃት ደረጃ ከፍ አድርጎታል። እነ አጅሬ ካለልካቸው ገብተው ደግሞ ለወደፊቱ ካላተራመሱት። https://www.youtube.com/watch?v=7StjNwkYTAM አስደሳች ዜና የተከሰከሰውን አውሮፕላን አስመልክቶ ከአቶ ተወልደ አውን የተሰጠ መግለጫ የሆነ ሆኖ ዛሬ ምንም ዜና የለም። የኢትዮጵያ መንግሥትም ዜናውን ተግ እንዲል ያስ ደረገ ይመስለኛል። በተጨማሪነት ሌሎችም ተጨማሪ አገሮችም የተወሰነ ጊዜ ማዕቀብ በቦይንግ 737 ማክስ 8 እንዳደረጉ ዓለም አቀፍ ዜናዎች እዬዘገቡ ነው። አውስትራልያ፤ ኖርወይ፤ ብራዚል ወ

ቢያንስ አውሮፕላኑ ሰርጎ ከገባበት ጥልቀት ባነሰም እራስን መፈተሽ ወደ ፈጣሪዬ መመለስ ይጠይቃል

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ቢያንስ አውሮፕላኑ ሰርጎ ከገባበት ጥልቀት ባነሰም እራስን መፈተሽ ወደ ፈጣሪዬ መመለስ ይጠይቃል፤  - የወቅቱ የመከራ አስተምህሮ - ይህ ይመስለኛል። „እግዚአብሄር የበቀል አምላክ ነው።  የበቀል አምላክ ተገለጠ።“ መዝመር ፺፫ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 08.03.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።                         ነፍስ ይማርልን አማኑኤል አባታችን!አሜን! ·        ፍላሎት …  የሲንጋኮፕር እርምጃ ደግሞ ይገርማል። ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን በዬር ወሰኗ ለተወሰነ ጊዜ ትውር እንዳይል እገዳ ጣለች። በዚህ በመጋቢቱ መባቻ 2011 ዕለት በተከሰተው አደጋ መሰረት ኢትዮጵያ፤ ደቡብ አፍሪካ፤ ሜክስኮ እና ቻይና በዚህ አውሮፕላን በረራ የማድረጉን ነገር ጊዜያዊ ማዕቀብ ጥለዋል። የቦይንግ 737 ማክስ የሱባኤ ጊዜ።   እኛም እንደለመደብን እንደ አምናው ዘንድሮም ሱባኤ ላይ ነን። ሁዳዴው የግሎባሉም ሆኗለኝ። እንዲህ ለመከራ ጊዜ አንድ የሃዘን ወቅት እንደሚኖርንም ግሎባሉ እንደሚሆነው በተለመደው የመኖር ዘይቤስ ምን አለ ፍቅሩን ቢሰጠን? ·        ነገረ በረራ። እንዴት ናችሁ ውዶቼ? ነፍሴ ከበረራ ጋር ከተጣመረ አምስት አመት ሆነኝ። የዛ ጀግና የዛ የሰባዕዊ መብት ተሟጋች፤ የዛ ጠንቃቃ፤ የዛ አስተዋይ የረዳት አውሮፕላን አባራሪ ሃይለመድህን አበራ ጄኔባ አውሮፕላን ማርፊያ በሰከነ ጥበብ ከረገጠባት ቀን ጀምሮ በበራ መንፈስ ተጠመድኩኝ። የሚገርመው ያ ምራቁን የዋጠ፤ አሳዳጊውን ይባርከውና ምስጉን ወጣት እጁን ለመስጠት ከአውሮፕላኑ ሲወርድ እንኳን ግርግር ጠብ እንዳይፈጠር፤ አገሩን በክፉ ላለማ