ቢያንስ አውሮፕላኑ ሰርጎ ከገባበት ጥልቀት ባነሰም እራስን መፈተሽ ወደ ፈጣሪዬ መመለስ ይጠይቃል
እንኳን
ደህና
መጡልኝ።
ቢያንስ አውሮፕላኑ ሰርጎ ከገባበት ጥልቀት ባነሰም
እራስን መፈተሽ ወደ ፈጣሪዬ መመለስ ይጠይቃል፤
- የወቅቱ የመከራ አስተምህሮ - ይህ ይመስለኛል።
„እግዚአብሄር የበቀል አምላክ ነው።
የበቀል አምላክ ተገለጠ።“
መዝመር ፺፫ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
08.03.2019
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።
ነፍስ ይማርልን አማኑኤል አባታችን!አሜን!
· ፍላሎት …
የሲንጋኮፕር እርምጃ
ደግሞ ይገርማል። ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን በዬር ወሰኗ ለተወሰነ ጊዜ ትውር እንዳይል እገዳ ጣለች። በዚህ በመጋቢቱ መባቻ
2011 ዕለት በተከሰተው አደጋ መሰረት ኢትዮጵያ፤ ደቡብ አፍሪካ፤ ሜክስኮ እና ቻይና በዚህ አውሮፕላን በረራ የማድረጉን ነገር ጊዜያዊ
ማዕቀብ ጥለዋል። የቦይንግ 737 ማክስ የሱባኤ ጊዜ።
እኛም እንደለመደብን እንደ አምናው ዘንድሮም ሱባኤ ላይ ነን። ሁዳዴው የግሎባሉም
ሆኗለኝ። እንዲህ ለመከራ ጊዜ አንድ የሃዘን ወቅት እንደሚኖርንም ግሎባሉ እንደሚሆነው በተለመደው የመኖር ዘይቤስ ምን አለ ፍቅሩን ቢሰጠን?
· ነገረ በረራ።
እንዴት ናችሁ ውዶቼ? ነፍሴ ከበረራ ጋር ከተጣመረ አምስት አመት ሆነኝ። የዛ ጀግና
የዛ የሰባዕዊ መብት ተሟጋች፤ የዛ ጠንቃቃ፤ የዛ አስተዋይ የረዳት አውሮፕላን አባራሪ ሃይለመድህን አበራ ጄኔባ አውሮፕላን ማርፊያ
በሰከነ ጥበብ ከረገጠባት ቀን ጀምሮ በበራ መንፈስ ተጠመድኩኝ።
የሚገርመው ያ ምራቁን የዋጠ፤ አሳዳጊውን ይባርከውና ምስጉን ወጣት እጁን ለመስጠት
ከአውሮፕላኑ ሲወርድ እንኳን ግርግር ጠብ እንዳይፈጠር፤ አገሩን በክፉ ላለማስነሳት ብሎ በመስኮት ነበር የወረደው። በእሱ ዙሪያ
የሠራሁትን ሥሙን ብተሰጡት ለተከበረው የዘሃበሻ ድህረ ገጽ ሂደቱን ታሪኩን በሙሉ ታገኙታላችሁ። በዬወሩ
ነበር እምጽፈው።
ይህ የእሱ ብቃት ተፈጥሮውም ታክሎበት የ ኢትዮጵያን አዬር መንገድ የሥልጠናውን የጥራት
ደረጃም፤ የጥንቃቄ ልኩንም የሚያሳይ ይመስለኛል። የኢትዮጵያ መንግሥት ትናንትም ዛሬም ጉዳይ አልሰጠውም እንጂ የውስጡን ጥበብ ያሳዬ
ታማራዊ ተግባር ነበር የተፈጠመው ጄኔባ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ። ቀለሙ የማይነጥብ ፍጹም የሆነ የብቃት ክህሎት ህብራዊነት የታዬበት
ወቅት ነበር።
መጋቢት 29 በ ዐለም አቀፉ የሴቶች ቀን ጠ/ሚር አበይ አህመድ ጀግና የላትም ኢትዮጵያ
የሚል ዕድምታ ያለው ንግግር አድርገዋል። ጀግና ሃይለመደህን አበራ አጀንዳቸው አይደለምና። አኔ በጥዋቱ ነበር ያመለከትኩት እሱን
በሚመለከት። ግን ታለፈ… ለነገሩ ለበጎ ነው። ለእሱም ባለበት ቢቆይ ነው የሚሻለው … እኔ ከቤተሰቦቹ የተለዬ አቋም ነው ያለኝ።
መኖሩ ነው የሚጠቅመው እዚኸው ከቅድስት፤ ከጭምት ክውን ሽክፍ ካደረገቸው የክት አገር ሲዊዝሻ። ስለዚህ የዋና አብራሪ አቶ ያሬድን
የብቃት ድንግልና አልጠራጠረውም ባይ ነኝ።
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ …. አሁን መሬቱ ላይ በሆነው አለምን ባስደነገጠው አስቃቂ
ነገር ምን ያህል ያ ብልህ ወጣት ለኢትዮጵያ መንግሥት በረደኑን እንዳስቀረ ህሊና ካለው የኢትዮጵያ አዬር መንገዱ መስተዳደር ልብ
ሊለው ይችላል። በዚህም በዚያም ቢባል አገር ለሚለው ወገን የራስ ጉዳይ ነውና የኢትዮጵያ አዬር መንገድ ጉዳይ የራስጠረን ነው።
ያ ጀግና ሊሸለም፤ ሊወደስ፤ አይከን ሊሆን፤ ትውልድ ሊማርበት ሥሙ
ላቅ ብሎ ሊጠቀስ ሲገባ እንዲህ ጀግነንቱ የውሽማ ሞት ሆኖ ይገኛል። ቁስለት!
ሥሙን ማንሳት እንኳን አይቻልም። በአሸባሪነት በህወሃት የተፈረጁት፤ ዛሬ ቀን መልካም
ነውና የቴሌቪዥን አውድ ፎቷቸው ሲሆን እሱ ግን ከጀግኖች ጎራ አልተመደበብም። ልጄ ነው እሱ ለእኔ አብዝቼ እምሳሳለት።
በዝምታው ውስጥ ያለ የነፃነት ጥማት ልኩን ስመዘነው ብጡልም ነው። ጨዋነቱ፤ በልክ
ለመኖር መፍቀዱ፤ ፈተናን ለመሸከም ጽናቱ ይገርመኛል። አሁን ስለ እናት አገሩ ያስባል፤ ይብሰለሰላል … የዚህ ብጡል ፎቶው አዬር
መንገዱ መግቢያው ላይ ሁሉ በክብር ሊቀመጥ ይገባል። ፍጹም ጠንቃቃ ነው። ፍጽምናው ደግሞ ከሙሉ ጨዋነት ጋር ነው ለእናት አገር
ብሄራዊ ክብር።
የሆነ ሆኖ የረባ እንቅልፍ ለመተኛት አልተቻለኝም። እንዴያውም ዛሬ ሳወጣ ሳወርድ ያደርኩት
በዛው ሰሞን በ20.20.19 አንድ የተቀበረ ብረት በብረት የተሠራ ሳጥን ከመሬት በታች ተቆፍሮ እንደወጣ ሜዳው ሳር በቀል እንደነበር፤
ያወጡት ደግሞ አቶ ሃይለማርያም ደስለኝ እንደሆኑ እና መጨረሻው ለማዬት ብጓጓም በርቀት እርቃኑን የሆነ ልጅ እግር ያልተገረዘ እብድ ስለመጣ ፈርቼ ሸሸሁኝ ብዬ
ነበር። ስቋጨውም ጹሑፉን ፍቱት
ብዬ ነበር …
ምን እንዳዬሁኝ በዚህ ቀን … በ20.02.2019 የተጻፈ ነው
ያዬሁት ግን 19 ለ20 መንፈቀ ሌሊት ላይ ነበር። በምልስት እስኪ ይቃኝ
„መንፈቀ ሌሊት - አንድ።
እንዴት አላችሁልኝ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ አንድ ህልም አዬሁኝ። አንድ የተዘጋ በር ተከፈተ። ከዛ የተዘጋ በር ሲከፍት ሜዳ አለው። ሜዳው ላይ ትንሽ ሳር በቅሎበታል። አንድ ሰው ከአቶ ሃይለማርያም ደስለኝ ጋር አለ። ያ ሰው ግን ግርዶሽ ጥሎበታል።
እናም አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሳሩን ገፋ ገፋ አድርገው ከሉት። አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ ሳሩን ገለጥለጥ ሲያደርጉት በሰው ቁመት ልክ የሆነ ጉድጓድ ተከፈተ። ከዛም አንድ ብረት በብረት የሆነ የተቆለፈ ትልቅ የብረት ሳጥን ወጣ። እንደወጣ ቀረብ ብዬ ላይ ስፈልግ በሌላ አቅጣጫ ከአንገቱ ላይ ራፊ ያደረገ አንድ እርቃነ ነፍስ የሆነ ከ9 እስከ 11 ዓመት ዕድሜ የሚሆን ታዳጊ ወጣት መለመላውን መጣ። ታዳጊ ወጣቱ ያልተገረዘ ነው። ታዳጊ ወጣቱ ዕብድ ነው። እሱ ሲመጣ እኔ ፈርቼ ቦታውን ለቅቄ ወጣሁኝ። ስወጣ ያ ሳጥን ሳይከፈት ነበር ... ህልሙ የውነት ነው። ፍቱት… ኢትዮጵያ መንፈቀ ሌሊት ላይ ነው ያለችው።
ውሃ በቀጠነ ቁጥር መበርገግ አያስፈልግም።
ዛሬ ሌሊት እሱን ሳብሰለስል ያደርኩት ከብላክ ቦክሱ መገኘት ጋር
ተያያዘብኝ። እኔ ያዬሁት
ያ ብረት በብረት የሆነው ሳጥን እሱ ይሆን አልኩኝ። ምክንያቱም ብላክ ቦከስ እጅግ በጥንቃቄ የሚሠራ ብቻ ሳይሆን ከሁሉም
በላይ አቅም ያለው፤ የሰጡትን በአደራ ለረጅም ጊዜ ማተቡን ጠብቆ የሚያኖር፤ ራሱን በራሱ ቆልፎ ነው የመፈጠረው። ሚስጢር።
ብላክ ቦክስ አደራ የማይበላ ሲሆን ከሁሉም በውሃም በቃጠሎም በቀላሉ የማይደፈር እጁን
ለምንም እና ለምንም የማይሰጥ ብርቱ ነው። እኔ ከመቃብር የወጣውን ሳጥን ለማዬት እንደጓጓሁ ነበር እብዱ መጣ ብዬ ስሰሽ ሲከፍት
ሳላዬው እንደወጣ ብቻ አይቼው የቀረሁኝ።
የህዝቡ የአሁኑ ጉጉትም እንዲሁ እኔ ካዬሁት ህልም ጋር ተቀናጀብኝ። የኢትዮጵያ ህዝብ
የብላክ ቦክሱ መረጃ ተሎ ማወቅ ይፈልጋል። እግዚአብሄር ረድቶ በቀላሉ ሜዳ ላይ ስለሆነ አደጋው የተፈጸመው ተገኝቷል።
በ2014 መጋቢት 8
ቀን በሁለት ቀን ልዩነት ማለት ነው ከአሁኑ አደጋ ጋር ወደ 239 ሰዎችን ውቃዬኖስ ውስጥ ያስቀረው የማልዢያ አውሮፕላን ብላክ ቦክስ ግን
ዓለም በሙሉ ቢታደምበትም ሊገኝ አልቻለም። ብዙ መዋለ ንዋይ ነው የፈሰሰበት። በዓለም ደረጃ እንደሱም ዓይነት ከጥፋት በሆዋላ ውድ ዋጋ ያስከፈለ
አደጋ አላዳመጥኩኝም። መረጃውም ሆነ የአደጋው ሰለባ የሆኑትም ድብዛቸው ጠፍቶ ነው የቀረው። ወደ አንድ ዓመት ገዳማ በልዩ ጠንካራ
የባለሙያ ቡድን በተቀናጀ፤ በተደራጀ ሁኔታ ሲታሰስ ነበር። ግሎባል ነበር ጉዳዩ …
ስለሆነም የኢትዮጵያው አደጋው ሜዳ ላይ መሆኑ በራሱ ግራጫማ ዕድልም ቢሆን አደጋው
ብላክ ቦክሱ እንዲህ በቀላሉ መገኘቱ ግን መልካም ነው። ከመጀመሪያ እስከ ፍጻሜ ያለው ነገር ሁሉ ተመዝግቦታል፤
የዚህ የጥቁር ሰሞናት ቤዛነት ወገኖቻችን አጣን፤ የዓለም ቅስም በውነቱ ተሰበረ።
የጀርምን ዊንግ ከአልፐስ ተራራ ጋር ስለነበር የከፋ እና አሰቃቂ ነበር። ፎቶውን እዩት
… ከተማም ሆነ ገጠር ላይ በሰዎች መኖሪያ ቤት አለመከስከሱም የፈጣሪ ቁጣ ማሰተዛዘኛ እንደሰጠን ወደ ንሰሃ እንገባ ዘንድ
ጊዜ ሰጥቶናል ብዬ አስባለሁኝ። አደጋው
ከ6 ደቂቃ በረራ ቀድሞ በ2 ደቂቃ በራራ እንኳን ቢሆን መከራው ከዚህም በላይ ነበር። ይህም ተመስገንን እንዳንረሳው ነው።
ይህ መቼም ግራጫም ቢሆን ዕድለኝነት ነው፤ መረጃው ግን በጥብቅ ቁጥጥር ሥር ነው የሚውለው።
ለዚህም ነው አሜሪካኖች እራሳቸው ለመያዝ ያሰቡበት ምክንያት። ከ አሜሪካ ራሱ ሁለት ቡደን ነው የሚመጣው። ለ ኢትዮጵያ የሚረዳው
ሌላው ጉዳይ በመሬቱ በመሆኑ የመረጃ ተጠጊ አያደርገውም። ይህም ሌላው ዕድል ነው።
ብቻ መረጃውን በትክክሉ ይገለጻል ለህዝብ ለሚለው ግን ቦይንግ እና አሜሪካ ብቻ ሳይሆን
የኢትዮጵያ መንግሥት የአቋም መንግሥት ለመሆን መንገዱን ስላልጀመረው … ብዙም ግልጽነቱ ላይ እኔ እምነት የለኝም።
ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ጀምሮ ያሉት መረጃዎች እንዳመጡ ስለሚገኙ። በሌላ በኩል ከውጥን ቀጥሎ የተቋጨ ነገር አላዬሁም ሁሉም ቦታ
ይተከላል ይብቀል ይስበል ክፍት ነው …
· ዕድምታ።
በአዬር አለመመጣጠን በከፍታ እና በዝቅታ በረራ አለመጣጣም፤ በአወሮፕላኑ የቴክኖሎጂ
የጥራት ችግር የሞተሩ አቀማመጥ ሚዛን አለመጠበቅ አስመልክቶ፤ ለአብራሪዎች ቦይንግ አዲሱን የቴከኖሊጂ ውጤት ኮርስ አልሰጠበትም
በብዙዎች ዘንድ የተነሳው ጉዳይ ነው፤ ያልተነሳው በዛች ቅጽበት የአብራሪዎች የጤና ሁኔታ ሲሆን የደህንነት
ምክንያታዊ ሁኔታም ሁሉም በዛ ብላክ ቦክስ ላይ በሚስጢር ተመዝግቧል ብዬ አስባለሁኝ።
ምን አልባት የውስጥ ስሜት
የመርጋት እና የህመም ስሜት ግን ካልተገለጸ በመረጃ ማገጣጠም ካልሆነ የሚከበድ ይመስለኛል። በቅጽበት የሚሰሙ ስሜቶች አሉና በሰዎች
ተፈጥሮ ይህም ከግምት ውስጥ በ እኔ ህሊና ይታደማል … እንደሰውኛ።
ባለማተበኛው ብላክ ቦክስ ያለውን ተፈጥሮ ያህል እኛ የሌለን ስለሆነ
ነው ዕውነትን ወግነን ከመቆም ወቅት እና ዝናን አሽኮኮ አድርገን የወለሌለ ገበታ ስንል እምንገኘው። የ አቋም ጉዳይ ከሰው ሰራሹ
ብረት በታች እዬሆን ነው። ቢያንስ ለሰብ። ያደለው ለ እንሰሳትም ለወንዞችም ይቆረቆራል …
የሆነ ሆኖ በጥድፊያ መልሱን ለማግኘት እምትሹት ደግ ወገኖች በተፈጥሮው ይህ መሰሉ
የአውሮፕላን አደጋ እና ብላክ ቦክስ አፈጣጠር ሁሉንም ችግሩን ከራሱ ወገን ለማግለል ያለ ቀዝቃው ጦርነት
ስላለ አደብ፤ ስክነት ብቻ ሳይሆን የተሰጡትን መቀበልም ይጠይቃል፤ በተሎም የመጀመሪያ ደረጃ የቅድሚያ መረጃውን እንኳን ማግኘት
አይቻልም፤ እንኳንስ ጥልቀት ያለውን ሁለተኛ ደረጃውን በሳሉን ለማግኘት። ጨዋታው ኢኮፖለቲክስ ስለሆነ - የውጭ ምንዛሬ እና ስክነትም።
ማህበራዊ እና ሥነ ልቦናዊ ቅንጅትም አሉበት።
ይህ ሁሉ በሰውኛው አግድሞሽ ነው። ግን ለእኔ ሰወኛ ምክንያት አልሰጠውም የፈጣሪ መከፋት ያመጣው ፈጣን እርምጃ ነው ብዬ ነው እማስበው።
ሁሉም በራሱ የሴራ ሰረጋላ መጪ እያለ በፉክክር ላይ ስላለ ተግ ብሎ ሞት ከቅርብ ስለመሆኑ፤ ምልከት ነው ለአምስተኛ ጊዜ … የሰጠው።
አለን ብለን እምንደነክርበት መሬት ባለቤቱ የፈጣሪው ስለመሆኑ ነው አበክሮ ሂደቱ ያስተማረው
… ሲፈልግም ሰው ለበራራ የተሠራ የሰማይ ወፍ መሬትን ከማረሻ በላይ እንዴት ሰንጥቆ እንደሚገባም አሳይቶናል … ሰማይ ነደደ፤ ምድርም
ተቃጠለ፤ እነዛ ቤዛዎች ደግሞ ካለ ሃበሳቸው እንደ ወጡ ቀሩ …
·
ሳስበው እንቅልፍም የነሳኝ ነገስ የጉዟችን አቅጣጫ የቱ ይሆን ነው? ብዙ ሰዎች በዚህ
የኢትዮጵያ አዬር መንገድ ሙያዊውም፤ ግላዊም አሰተያዬት ሰጥተዋል። እኔ ደግሞ ከሁሉም የተለዬ ነው ያለኝ እይታ። የእዮር ቁጣ አድርጌ
ነው እማዬው።
የኢትዮጵያ አዬር መንገድ እኮ የአድዋን ያህል ገናና አዬር መንገድ ነው። ገናናነቱ
ጥራቱ ከድክመቱ በላይ ዕውቅናን ስላስቸረው ነው። ያው የሚወቀስበት
አስተዳደራዊ በደልም ቢኖርም። የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያዊነትን በሚመለከት ትናንትም ዛሬም ያለን የቀረ አንድ መለያችንም እርሾ እሱ ብቻ
ነው። በህሊናቸው ኢትዮጵያዊነት ያለው በድሃ ዜጎች ብቻ ነው ከአዬር መንገዱ ምልክትነት በስተቀር።
ኢትዮጵየዊነትን ቢከፋውም ቢደላውም ግማዱን ተሸክሞ ያለ ያው ይኸው መንፈስ ብቻ ነው።
ለዛውም እሱም አዲስ ትልም ተተልሞለታል ለመበወዝ …
ስለዚህ እኔ እንደ ተዋህዶ ልጅነቴ ይህ ቁጣ የፈጣሪ ነው ብዬ ነው እማስበው።
ቅኖቹ እስኪ እሰቧቸው ምስላቸውን የወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅን፤ የአቶ ጃዋር
መሃመድን ሜጫን ሰብስቦ ያደረገውን መታጀር፤ የሰብ ችግር ምናቸውም ያልሆነ ቀውስ በመጣ ቁጥር ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ ባህርዳርም
እያሉ እንደ ሰው አስተውሏቸው አቶ ንጉሱ ጥላሁንን ቅጭጭ አይላቸውም።
ስለምን ስትሉ ሁሎችም የራሳቸው ብቻ ስለሆኑ። በዚህ ማህል መሬት ለመሬት የሚሄደው ቀጣይ
ሴራ እና ሸር አለ … ኢትዮጵያዊነትን በስውርም በግልጥም እዬተገዳደረ ያለበት ወቅት ነው፤ … ይህ ለልዑል እግዚአብሄር አልተመቸውም።
ኢትዮጵያ የፈጣሪ አስራት አገሩ ናት እና
… በዚህ ውስጥ የቅዱስ
ሲኖዶስ አንጎል የፓትርያርኩ ጽ/ቤት መደፈርንም ከልብ ሆናችሁ እሰቡት። እሳቸው ጥምቀተ ባህር ላይ ቡራኬ እዬሰጡ በነበረበት ወቅት በጎን ደግሞ ይህም ተከወኑ ነበረ
…
Ethiopia -ብጹዕ
ዶ/ር
አቡነ
ኤዎስጣቴዎስ
የጥምቀት
በዓልን
በማስመልከት
በአማርኛና
በኦሮሚኛ
ቋንቋዎች
መልዕክት
አስተላልፈዋል::
· እንድናስተወል ይርዳን።
ሁሉም ሰው ከሊቅ እሰከ ደቂቅ የቆመበትን መሬት ይመረምር ዘንድ ነው ንጹሃን እንደ
ወጡ የቀሩት ቤዛም የሆኑት። እነዚህ ቅዱሳን የእኛን የሴራ ትልም ግማድ የተሸከሙ ናቸው። ከእነዚህ ወስጥ ደግሞ አንዱ በሌላ
አውሮፕላን መዘግዬት ምክንያት፤ ሌላው በራሱ መዘግዬት ምክንያት ትረፉ ለታሪክ ሲላቸውም አተረፋቸው።
ስለሆነም አመድ ነስንሶ ድንጋይ ተንተርሶ ከታበዩበት ፎቅ ወረድ ብሎ፤ ከሴራው ማህበር
ወጥቶ ሁሉም ፖለቲከኛ ሴረኛ ስለሆነ፤ ንጽህና የጎደለው ስለሆነ አዳሩ እና ውሎ በንጽህና ወደ እግዚአብሄር አቤት ማለት ይኖርበታል።
እኛ ሰው ናችሁ ብለን አክብሮት አለመስጠታችን ያዬ ቀናተኛ አምላክ ነው ኢንባሲዎችን
ሰብስቦ በጥድፊያ የኢትዮጵያ መንግስት ለሌሎች አገር ዜጎች ተቆርቋሪነቱን እንዲያሳይ የተገደደው። ለዛውም አክብሮ፤ ተሽቆጥቁጦ።
ይህም ሌላው አስተምህሮ ነው …
ከትናንት በስተያ ህይወታቸውን ያጡ የውጭ ሀገራት ዜጎችን አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ማብራሪያ ሰጥቷል
… 3 ሚሊዮን ህዝብ ደግሞ በሰው ሰራሽ ችግር ከትግራይ በስተቀር አፈር ለብሶ፤ ትቢያ
ተንተርሶ ይገኛል … አብሶ የጊዲዮ መከራ ተከዝኖ ነው የሚገኘው።
አሰፈርናቸው መልሰን የሚባሉትም በዲስከርሚነሽን ሰባዕዊ መብታቸው ተረግጦ ለፖለቲካ ሥልጣን ገብያ ማገዶነት ነው የዋሉት። በሌሎች ላይም ሌላ ጫና ለመጫን። ድርብ ጥፋት ነው ይሄ። ይሄን በምንም ሁኔታ መስተባባል አይቻልም።
ሰው መሆን መልኩን ያዬንበት ዘመን ነው። … ይህን ጋዜጠኛውም
ፓለቲከኛውም ጸሐፊውም ተንታኙም ባሊህ ባይለውም ከባለጊዜ ጋር ከፍና ዝቅ እያለ ሰለሆነ ልዑል እግዚአብሄር ግን እንሆ ለ5ኛ ጊዜ
ምልክት ሰጠ። እውነት እና ስለመፈጣጠራችን መንገድ መሳት ነውና ስንቃችን።
„እግዚአብሄር በአንድም በሌላም መንገድ ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም“
በዚህ ማህል አካል የሌለው አገልጋይ ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ እንደ
ቃላቸው ይሆኑ ዘንድ ከዚህ ቁጣ ድኗለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ ተገኝቷል። ብዙውን ፈታና ታግሶ።
· ባለቤት ያላቸው ዜጎች።
ጀርመን ውስጥ አንዲት ታዳጊ ወጣት ተሰውራ የመንግሥት ሰልፍ ልክ ጦርነት ጀርመን የታወጀበት
ይመስላል። የመኪናው ዓይነት፤ የእግረኛው ዓይነት ጫካ ለጫካ በእግር
በመሳሪያ በውሻ በበዛ ሠራዊት ጥረቱ ወደ ሶስት ሳምንት ሆነው እሷን ለማፈላለግ። ታዳጊዋ ርብቃ ትባላለች።
እኛ ደግሞ ተማሪ ቦርሳውን ይዞ ከቤቱ ወጥቶ በሰው ሰራሽ ችግር ከት/ቤት ሲመለስ ቤት
የለውም፤ ቤት አለመኖሩ አይደለም ጉዳዩ ለዚህ እርዳታ የሚሰጡ ሁኔታውን የሚዘግቡ ይደበደባሉ …
ምንም የማያውቁ አራስ ልጆች አገር አለን ብለው ወደ ዚህች ዓመት ሲመጡ ስደተኛ መጤ ይባላሉ፤ በግሪደር የእነሱ መንፈስ ቅዱስም አብሮ ይታረሳል፤ ሰማይ
ይቆጣል።
ለዚህ ነበርን አባት ቅድም አያቶቻችን፤ በጉንዲት፤ በዶጋሌ፤ በካራማራ፤ በማይጨው፤
በጎዴ፤ በመተማ፤ በመቅደላ ወዘተ አንገታቸውን የሰጡትን? የሞቱ አረበኞቻችን ቅርስ ውለታ ሁሉ እዬተቃጠለ ነው … እኛ አገር እንዲኖረን
ነበር እነሱ የሞቱት። እነሱ ራሳቸውን የገበሩት …
ውዶቼ የወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ ብቻ እንዳይመስላችሁ በዛው በኦዴፓ መዋቅር የድንገተኛ ጉዳዮችን
የቢሮ ሃላፊ ሲጠዬቁ አልሰማሁም ነበር ያሉት፤ … እጅግ በሚገርም ሁኔታ። ያነገራቸው ዋልታ ነበር
የ ኦሮምያ አደጋ ስጋት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሸነሩ በጉዳዩ ላይ ምንም መረጃ እንደሌለውና እንደማንኛውም መረጃ ጉዳዩን
እንደሰማ የተናገረ መሆኑን ዋልታ እንደዘገበው …
Ethiopia : የጠሚ አብይ መንግስት ቤት ያፈረሰባችውን ዜጎች አሁን ከተጠለሉበት ቤተክርስትያን ውጡ እያለ በግፍ ማባረር ጀመረ Abiy Ahmed
·
አለታማው መከራ ጠሪ።
https://www.youtube.com/watch?v=BQa4z_VbgiY
Ethiopia -ህግ መከበር አለበት ማፍረሱን እንቀጥላለን
https://www.youtube.com/watch?v=vcK9Yny65nQ
Ethiopia -የመንግስት ያለ ህገ-ወጥ አይደለንም!
https://www.youtube.com/watch?v=N-XubwS1duw&t=1s
OMN: ቆይታ ከለገ ጣፎ ለገ ደዲና ከሰበታ ከንቲባዎችና ከከተማ ፕላን ባለሙያዎች ጋር (Feb 24, 2019)
… ስለሆነም ዜጎቹን ዜጋዬ ላለ መንግሥት መቀጣጫ እዮር ፈለገ … እያንዳንዱ አገር
ለዜጎቹ ምን ያህል ግድ እንደሚለው ቁጭ አርጎ ለሜንጫ ሱናሜ ቤተኛ አስተማረው ፈጣሪ ራሱ መሬት ወርዶ እረዳን ግን መርቃቱን ለሜንጫ ሸለነው።
አሁን የተጎጂ ቤተሰቦችን በራሱ ወጪ የሚፈልጉትን የማዬት መብት ይሰጣል የ ኢትዮጵያ አዬር መንገድ ሲባል የ ኢትዮጵያ መንግሥት ማለት ነው። በቀዩ ላይ
ያለውን ዜጋ የናቀ፤ የረገጠ ገና አፈርሳለሁ እያለ የሚፎክር የሚዝት የአውራ ፓርቲው የኦደፓ መንግስት፤ ሌሎቹ ወገኖቹን አገር እምራለሁ
እያለ መጠለያ አገኛችሁ ብሎ የሚዝት ለሜንጫ መንፈስ ለተንበረከከ መንግሥት ባለበት አገር ነው ይህ ሁለት ህሊናን የሚፈትን ጉዳይ የተፈጸመው … ከልብ
ሆናችሁ መርምሩት … ቅኖቹ። ለዛውም የሜንጫው መንግሥት መግለጫ ሊሰጥ የሚዲያ ሊቃናት ጭካኔ እንዲማሩ የቤተ መንግሥቱ ነጋሪት በተጎሰበትም
ዕለት ስበሰባው በተጀመረበት ሰዓት. .. መርዶ …
ሌላም ሰው ልብ ያላለው ታምር አለ። ብንማርበት፤ ብናስተውለው ላይ ላዩን ገለባ ገለባውን
ቅርፊት ቅርፊቱ ከመሄድ ውስጥ መመርምር ያለበት፤
የድርጊቱ መገጣጠም ደግሞ ይህን ያህል ሰው የቤተ መንግሥት ቤተኛ ሲሆን ለ11ወራት
ከቤተመንግሥት የተገለሉ ደግሞ አሉ። እነ ኮ/ ደመቀ ዘውዱ፤ እነ ወጣት ንግሥት ይርጋ፤ ከ8 ጊዜ በላይ ካቴና የባለው አንድ የተገፋ
ተጋድሎው ምንም ዕወቅና ያልተሰጠው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ጋዜጠኛ ተመስገን ደስአለኝ፤ ፓለቲከኛው አቶ አንዱአለም አራጌ። እነ አቶ ማሙሸትም በ እጅጉ የተገፉ ናቸው።
ይህም አይበቃም ታሥሮ ሲፈታ ወገኖቹ በፍሰሃ እንዳይቀበሉት አሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነበር።
እርሙን ስብሰባ ሲጣራ ደግሞ ሌላ ሚዲያ ቀመስ ስብሰባ በቤተ መንግሥት ተካሄደ። ሴራ ብቻ ራስ እግሩ።
ከዚህ ሁሉ ከሞላው ቀን ከዚህ ሁሉ ከሞላው
ሰንበት ስለምን ይህ ቀን ተፈለገ? መሪነት ማለት ለራሱ ወገን የሚሰጠው ትእግስት ለሌላውም መስጠት ማለት ነበር፤ ትጥቅ አልፈታም ብሎ
ጉለሌለ ላይ ተቀምጦ 18 ባንኮችን እያዘረፈ፤ ህጻናትን ሲያውክ የነበረውን በአይፒ ደረጃ እያቀማጠልክ፤ በሰው ላይ ሜጫ ይዞ የዘመተውን
መኮነን መድረክ ሰጥተህ አድምጡ ብለህ ከሊቅ አስከ ደቂቅ እያስገደደክ ሌለው ደግሞ በድህነት ውስጥ ሃሳቡን ለመግለጽ እንዳይችል መንፈስ እንዲከፋፈል
ታሴራለህ? በምን ወንፊት ይህ ይዘርዘር?
እውነት እኮ ለሁሉም እኩል ነው መሆን አለባት፤ ታዲያ ፈጣሪ እንዴት በለማወይአብይ
አይዘን? እሱን መፎካካር እራሱ ግፍ ነበር።
ምን አለው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ … ከብዕር እና
ከብራና በስተቀር … ከተቆርቋሪነት እና የ የእኔ ከሚለው ከራሱ ሃቅን ከማፈላለግ በስተቀር … ይህ የነፃነት ዘመን እኮ በቤተመንግሥት እንዲህ
የተንጋለቱ ጋዜጠኞችን ጠርቶ አመስግኖ አክብሮ ሊሸለም የሚገባበት ሁኔታ ሊፈጠር ሲገባ ውጭ ውጪን ማዬት ለሰማይም
ለምድርም ፈጽሞ አይመችም። ለነገሩ
ከሀምሌ 19 ጀምሮ ወንበሩ ባዶ ሆኖ ነው እኔ ያዬሁት ….
ስለምንድነው በብሎገሮች፤ በጋዜጠኞች፤ በጸሐፊዎች፤ በአክቲቢስቶች፤ በሊሂቃን የሙያ ባለቤቶች፤ በፖለቲካ ድርጅቶች መሃከል ጠ/ሚር አብይ
አንዱን ክፍ ሌላውን ጭራሽ ከነመፈጠሩም እርስት የሚያደርገት? ለአንዱ ዕውቅናውን ሲለጥጡት አንዱን ደግሞ ቅብር ያደርጉታል። ወይንም በቅኔያቸው ይጎሳስሙታል። ይህን ስልታቸውስ በመደመሩ ፍልስፍናቸው ውስጥ ቤተኛ ሆኖ ይሆን?
በጥቅሉ ሲታይ አማራ ጠል ምልከታ አለበት ሂደቱ። ከሞትም ይለያሉ፤ ከማቋጠረም ይለያሉ፤
ከማሰብም ይለያሉ። አገር ከሚገቡት ሊሂቃንም ይለያሉ፤ ከሚሾሙትም ነጥለው ይለያሉ፤ ከሳቸው ያልጠበቅኩት ነገር ነበር። የሆነ ሆኖ በዚህ ተዛነፍ መሃል ንሰሃ ቢገቡ መልካም ነው። የሰውን ትትው ማለቴ ትችታችን ቢያንስ ሁልጊዜ የሚጠሩትን ፈጣሪ ክርስትናን ከልባቸው ተቀብለው ከሆነ … ንሳሃ ይግቡ። የሱባኤም ጊዜ ይኑራቸው። ሰልቷቸው ደክሟቸው፤ ማዕቀብ ተጥሎባቸው ከሆነ ደግሞ ይንገሩን የሥም ብቻ ታርጋ ከሆነ ጠ/ሚርነታቸው...
· ግልጽነት በድፍንነት።
ሚዲያቸው እራሱ ነፃነቱን አልሰጡትም። በማዕቀብ ውስጥ ነው ያለው። ሚዲያው ከፖለቲካ
አሸብሻቢነት በስተቀር ብዙም በሰብዕ ጉዳይ ላይ እና አሳቸው በሚያሳዩት ድክመት ላይ የሰላ ሂስ ሲያቀርብ አይታይም። ብዙ ነገር ነው ያለው። አሁንም ሚዲያው
የኢህዴግ የሙት መንፈስ ሰለባ ነው። የሚናፍቀኝ ነጻ ሚዲያ በኢትዮጵያ ነው … አንባገነነ የፖለቲካ ሊሂቃን መንፈሳቸውን አስርገው
ሲያንከባልሉት እንደ ኳስ የማይውሉት …
ስለሆነም እንደ ሻሸመኔው ገመና … አሁንም እኔ በመከድን እንደባጁት እንደ ሰኔ 16ቱ፤ እንደ ሐምሌው ዝምታ፤
እንደ መስከረሙ ኩዴታ የዚህ የብላክ ቦክስ ጉዳይም ቢሆን ሳይከፈት ነው ያየሁት ብህልሜ ውጤቱም በድርድር ነው የሚሆነው
በተከደነ ሁኔታ። በዚህ ውስጥ ብዙ ጉዳዮች አሉበት ምርት እና ሸማች፤ ፓለቲካ እና ኢኮኖሚ፤ ሥም አና ውድድር ….ዓለምን ያናጠወጠ ዜና ነው የሆነው። ቦይንግንም የሱባኤ ድንኳን ያስጣለ፤ ለቅናሽ አንግቦትም የዳረገ ... ከገብያም እንዳይወጣ በስጋት የናጠ ... አሜሪካም ሁለት ቡድን ልካለች ...
የ37 አገር ዜጎችን የቀጠፈው መከራ እና የኢትዮጵያ ገዳዊ ግራጫማ የፖለቲካ መንገድ
… የሚፋጠጡበት ሂደት ነው። ምርምሩን ጥናቱን የውጤቱን ግልጽነት
ውስብስብነት ይፈትናል፤ ታገሽነትንም እንዲሁ። ገዳዊ ሥርዓት እራሱ ሞገዱን ፈቅደው ፈጣረው በ ገዳ አሸማጋይነት ሃይል ረገበ ሰከነ ተባልን ... ሌላ የፖለቲካ ጨዋታ ... የቻላችሁ መእኔ ሥራ ላይ እያለሁኝ ኢትዮጵያ "ሞገድ" የሚባል የተተረጎመ መጸሐፍ ነበር፤ አንብቡት ከገብያ ካልወጣ... ትዕይንቱን ቁጭ ያደርግላችሁዋል። የገዳን ሥርዓት አፍሪካዊ እናደርጋለን ነበር እኮ የ ኦዴፓ የመስከረሙ ጉባኤ ... መንገዱ ጠፋብን ለምትሉ ይኸው ነው ሚስጢሩ ...
እኔ በጀረመን ዊንግ
ጉዳይ ተመስጬ ስለነበር የነበረውን እሰጣ ገባ የነበረውን የፖለቲካ ትርፍ እና ኪሳራ በወጉ ታድሜበት ነበር። ግልጽነት የጎደለው
ነገር ሁሉ አለበት።
እንኳንስ ውሉ ባለዬለት ግራጫማው ኢትዮጵያን እንደ አገር ወይንስ ተፎካካሪውን ኦሮምያን
አልቆ አዝልቆ ለመኮፈስ? ? ? አሁም ቂጡም ክፍት የሆነ የፖቲካ ከሪጢት …. ይቀጥላል … ክፍትነቱም ሆነ ልሙጥነቱ ሆነ
ድንብልብልነቱን …
ኢትዮጵያዊነት ሌላ የሴራ ግማድ ተሸከም ተብሎ በተፈረደበት ዘመን … ፈታኝም ፈተናንም
ከዓለም ሚዲያ ጋርም ፍጥጫው … ቀጣይ ነው። ነፍስ ያላቸው የዓለም የእውነት ጋዜጠኞች ፍቀረ ንዋይ፤ ክብር እና ዝና ምናቸው
ያልሆኑ ጥልቀት ያለው ተግባር ይከውኑበታል ብዬ አስባለሁኝ። ሰብዕዊነት እና ኢትዮጵያ ያለበተን ሁኔታ። ክፍቱንም እድምታ ...
ለነገሩ ጉለሌ ላይ ተቀምጦ ኢትዮጵያዊነት አጠፋለሁ ላላ መታበይ እኮ አይተናል … የሆነውን
የተደረገውን እንዳሻው ዘርፎ፤ እንዳሻው ሲያምስ እና ሲያተራመስ ከርሞ በእነጃዋር አሸማጋይነት ደግሞ ሰከነ ሲባል … ቀልድ እና
ጨዋታው ከዚህ ላይ ነው … አቶ ጃዋር ብቻ አይደለም ግራጫ ሰብዕና ያለው የኢትዮጵያ መንግሥትም ውርሴ እና ቅርሴ ብሎ መጪ እያለበት
ነው … ግራጫማ መልክ። ወይ አልነጣ ወይ ለይቶለት አልጠቆረ።
· መስመሬ።
ግማዱ ኢትዮጵያ መሬት እንደተገኘው ደግሞ ከዚህ ሁሉ ቃጠሎን ድል ነስቶ የተረፈው ቅዱስ ወንጌልም ተገኜ። ተገልጦ ነው የተገኘው። ከተገለጠበት ቦታ ላይ ያለው ቃል ቢወጣ መልካም ነው። ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቢያተኩርበት
መልካም ነው። ገደል ነውና።
እኔም ትናንት እንዲህ ብዬ ጽፌ ነበር። „የፈጣሪ ሥም በመጣራቱ ሳይሆን ለፈጣሪ ታማኝነት በፈጣሪ አምሳል ለተፈጠሩት ፍጡራን እንደ ሰው የማዬት አቅሙ እዬወረደ ስለሆነ
መከራችን ቀጣይ ነው። ሰውኛነት ተጥሶ አዲስ ናዚያዊ
ፖሊስ ክትለት እዬታዬ
ነውና።
ይህ ጹሑፍ እግዚአብሄር የተከፋባቸው ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ ትቢያ ነስንሰው መሬት ላይ እግዚኦ ሊሉበት የሚገባ ጉዳይ ነበር እንጂ ተጨማሪ መታበይ እና ንቀት ሊታይ አይገባውም ነበር። ጥቁር መልበስ ንጹሃንን ደግሞ ላለመስከፋት ቃልኪዳን መሆን ይገባዋል ትናንት በመግለጫቸው ጥቁር ለብሰው ስላየሁኝ ጠ/ሚር አብይ አህመድ።
የሰሞናቱ የአራስ ልጅ
በባድማው በግሪድር መታረስ፤ ልጆች ከት/ቤት መልስ መግቢያ ማጣታቸው፤ እራሳቸውን ያጠፉ እህቶቻችን፤
ቆሎ ሽጠው ዛኒጋባ የቀለሱ ሜዳ
ላይ መወደቅ አስተዋሽ አልባ መሆን፤ የወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ ጣሪያ የነካ ጥጋብ ናዚያዊ ዕሳቤ፤ የመሪዋ የድጋፍ ድምጽ፤ በዬቤቱ የወረደው ዕንባ ይህን አመጣ …
ገናም ይቀጥላል። እግዚአብሄር ተቆጥቷልና!
እግዚአብሄር በፍጹም ሁኔታ
አዝኗለኝ።
ይህ ሁሉ የሴራ አነባባሮ በንጹሃን ህይወት ላይ ሲደርስ ተጠያቂው ማን ነው ብሎ መጠዬቅ ይገባል። ተጠያቂው መታመን የካደው፤ ማዕት አውርድ ብሎ መሬት የደበደበው ቲም ለማ ነው። በሰው ምስል ለማዬት ይከብዳል
እንደ አድህኖ ስዕል አዬው
የነበረው ፎቷቸውን።
ቤዛነት።
የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያን በመክዳት፤ ለማጥፋት ከሚታትረው
የኦነግ መንፈስን እነሱን ለመቅጣታ ሲል ነው ፈጣሪ እዮር
እነዚህን በሰላም ከቤታቸው
የወጡ ንጹሃንን እንዲህ የሳት
አመድ እራት ቤዛ
የሆኑት። እኔን! „ለሃጣን የመጣ ለጻድቃን“ እንዲሉ።
ይህን ጠሚር አብይ አህመድ ያጡታል ብዬ አላስብም።
ብልህ ስለሆኑ የፈጣሪ ቁጣ ስለመሆኑ ይረዱታል ብዬ አስባለሁኝ።
እግዚአብሄር በእጅጉ ተከፍቶባቸዋል። የሆኑትን ገልጠው በመናገር
ንሰሃ መግባት ይኖርባቸዋል።
የፕሮፌስር መስፍን ወ/ማርያም የሀዘን መግለጫ ወደ ብሄራዊ ሃዘን ቀንነት ተቀዬረ።
አሁን ያ ሁሉ ነገር አመድ ሲሆን ቅዱስ ወንጌል ግን መዳኑን አዳመጥኩኝ። የቃልን ሃይልነትም
በተደጋጋሚ ገልጫለሁኝ። በቃል ውስጥ በስንኝ ውስጥ ሃይለ ቃል አለ። ቃል!ተደግሞ ይታይ በሚል ነው ደግሜ የለጠፍኩት።
ሌላው ኢትዮጵያዊ ዜጋው እውነት የሚለው እሱ የሚከተለው መንፈስ የሚያራምደው መንገድ
ወይንም እሱ የሚደግፈው አካል የሚከተለው መስመር ብቻ ብቻ ነው ሁልጊዜ ትክክል። ይህም ልዑል እግዚአብሄር አይወደውም። ዕውነትን ዘመድ
ማደረግ ብቻ ነው ሰብዕናን ጥሰው የሚሄዱትን ገርቶ ሰው የሚያደርጋቸው። ከመጥፋታቸው በፊትም የሚያድናቸው።
ማንም ይሁን የተሳሳተ
መንገድ ሲከተል፤ የማታምኑት ነገር ሲገጥም ከእውነት ፈጣሪ ጋር ከመታገል ፈጣሪ መርቆ ለፈጠረው እውነት ጋር መወገን፤ በዛ እውነት
ውስጥ ያሉ ነፍሶችንም ከሚለቀቅባቸው ወጀብ ቢያንስ ራስን መቀነስ ይገባል።
የእኛ ፖለቲካ አለመደበተም፤ የእኛ የፖለቲካ ድጋፍ እና ተቃውሞው ከ አውነት አንጻር
አይደለም። ቢያንስ ከእንግዲህ የ እግዚአብሄር ቁጣ ምን ያህል ቅርብ
እንደሆነ ከባዕታችን ስላሰዬን ራስን በማስተዋል መመርምር የሚገባ ይመሰለኛል። ለሁሉም ትምህርት ነው። ድጋፍ በበዛ በተበራከተ ቁጥር
ተራራ ላይ ኢጎን ከመቆለልም ዝቅ ማለት ይበጃል። ሰው መሆን አንገት ያለው መሆን ነውና። ጹሑፈ ነገም ይቀጥላል …
የጀርመኑ አደጋ ይህን ይመስል ነበር ከሁለት ሳምንት በላይ የፈጀ ነበር ሰቀቀኑ ለማቀናጀት፤ ለማደራጀት እና ሥርዓተ ቀብሩን በክብር ለማስፈጸም።
አማኑኤል ሆይ!
እንደ ቸርነትህ እንጂ እንደበዳላችን አይሁንብን። አሜን!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ