የፕሮፌስር መስፍን ወ/ማርያም የሀዘን መግለጫ ወደ ብሄራዊ ሃዘን ቀንነት ተቀዬረ።

እንኳን ደህና መጡልኝ።

የፕሮፌስር መስፍን ወ/ማርያም የሀዘን
መግለጫ ወደ ብሄራዊ ሃዘን ቀንነት ተቀዬረ።
እንደ ሥርጉተ ኮቦታው ላይ አንድ ሐውልት ሊሠራበት የሚገባ ይመስለኛል።

„አቤቱ እኔን ለማዳን ተመልክት አቬቱ እኔን ለመርዳት ፍጠን“
መዝሙር ፳፱ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergurt©Selassie
11.03.2019
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።



·       ሀዘን 

የሰማይ ቁጣ ማዋራረጃ ለሆኑት ንጹሐን የዐለም ዜጎች ፈጣሪ አምላክ ነፍሳቸውን አርያም ገነት ያስገባልን። አሜን! ከሞቱ አሟሟቱ የከፋ ስለሆነ እንደ ሰው ለሚያስብ ዜጋ ከእህል እውሃ፤ ከእንቅልፍም ጋር የሚያገኛኝ አይደለም።

ነፍስ ሰማይ ላይ አመድ መሆን? እጅግም ሰቅጣጭ፤ እጅግም አስደንጋጭ፤ እጅግም የሚያርድ መከራ ነው ሰው ለሆነ ሰው። በሰውነት ሞራል ውስጥ ላለ ፍጡር።

ቀንበጥ ልቧ ስስ፤ መንፈሷ አዛኝ፤ ህሊናዋ ንጹህ የሆነች ብራና ናት። ስለዚህም የተሰማትን ድንግላዊ የውስጥ ሃዘን እዬገለጠች የዚህ ማዕት፤ የዚህ መከራ ምክንያት ወደ ሆነው የልብ ሽፍትነት አስመልክቶ ትንሽ ማለትን እንሆ ወደደች። ሌሊት እንቅልፍ መተኛት አልቻልኩም። ቀንም ትናንት ማስረሻ የሆነው ብዕሬ ብቻ ነበር።

ዳርዳር ብልም ዛሬ ግን የሚሰማኝን እውነተኛ ስሜት ለመግለጽ ወሰንኩኝ። የዚህ  መዓት መሰረት ቲም ለማ የተሰጠውን መታመን ጥሶ ማዕት አውርድ ብሎ መሬት በመደብደቡ ምክንያት የአቤል ዕንባ ያመጣው ጩኽት ስለመሆኑ መግለጽ ግድ ይለኛል

ጭካኔ ነገሰ በሜንጫ ሱናሜ! ያ ለዛ ከቶ ምኑ በላው? አዘን አምርረን አለቀሰን!

እኔ የእዮርን የቁጣ ወይንም የፍሰሃ ምልክቶች በዝምታ ውስጥ ከዝኜ አላስቀምጣቸውም፤ ሁልጊዜም አትኩሮት ሰጥቼ እጽፋለሁኝ። ይህ አመስተኛ እዮራዊ የማስጠንቀቂያ ምልክት ከፈጣሪያቸው ጋር ያሉ ወገኖች ወደ ራሳቸው እንዲመለሱ በተወሰነ ደረጃም ይረዳል ብዬ አስባለሁኝ። እምነቱ ካለ።



የፈጣሪ ሥም በመጣራቱ ሳይሆን ለፈጣሪ ታማኝነት በፈጣሪ አምሳል ለተፈጠሩት ፍጡራን እንደ ሰው የማዬት አቅሙ እዬወረደ ስለሆነ መከራችን ቀጣይ ነው። ሰውኛነት ተጥሶ አዲስ ናዚያዊ ፖሊስ ክትለት እዬታዬ ነውና።

ሌላ ከዚህ ጋር አብረን የምናዬው ነገር ዶር ወርቅነህ ገበዬሁ ከውጭ ጉዳይ ሚ/ርነት ተነስተው የተባበሩት መንግሥታት ረ/ጸሐፊ ሆነው ኬኒያ ተሹመዋል። ቀጣዩ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር እንደ እኔ ፕ/ ለማ መገርሳ ይሆናሉ ብዬ አስባለሁኝ። ሁሉንም መጠቀለል መቆጣጠር ነው ፍላጎቱ ... 
ወደ ቀደመው ሃሳቤ ስመለስ በዶር ወርቅነህ ገበዬሁ ወደ ኬኒያ ያማተር ጉዳይ ይህን ከሰባዕዊ መብት አንጻር ያለውን ዕድምታ ሌላ ጊዜ ብመለሰብትም፤ እሳቸውም በግማሹ ያው የኦዴፓ ሰው ናቸው። አውሮፕላኑ መነሻው ለጨረታ ከተዘጋጀው ኢትዮ አፍሪካ መዲና አዲስ አባባ ላይ ነው፤ መዳረሻም ኬኒያ ነበር። አብዛኛው ተሳፋሪ ተጎጂም ኬኒውያን ነበሩ ሊንኩን ከሳተናው ያገኙትን መሸረሻ ላይ ለጥፌዋለሁኝ፤ ፎቶውንም የወሰዱት ከ እሱ ነው። በሌላ በኩል አብራሪውም ግማሹ ኬኒያዊ እንደሆነ ነው የተደመጠው ይህ በምን መንፈሳዊ አቅም ይመርመር?አቅም አለን ይህን የሚስጢር ዕድምታ የምናፈታታበት። 

በተጨማሪ አቶ ንጉሡ ጥላሁን እና አቶ ጃዋር መሃመድ ደግሞ በፌድራል ደረጃ አብረው የታደሙበት ልዩ የዕወቁልን የአጽድቁልን የማህተም ቀንም ነበር። ሁለቱም የኦነግ መንፈስ የረበባቸው ለዛም የሚተጉ፤ የሁሉም ሴራ ቁልፍ እድምታ፤ ይፋዊም ቅይጥም ዝንቅም ድብልቅ መሪዎች የድላችን ቀን ባሉበት ነው ይህ አሳዛኝ ክስተት የተከሰተው። ይህም ሌላው የዕድምታ አውራ ነው።

ሌላም አንድ ነገር እንከል ከኬንያ ጋር የተያያዘ የኬኔያ መንግሥት እና ህዝብ ሚደያውን ጨምሮ ለጠ/ሚር አብይ አህመድ ከእጩነታቸው ጀምሮ የሰጠው ክብር መለኪያ የለውም። ናልን ብሎ በደብዳቤ አልጠዬቀም። በልዑክ ነው ግብዣው የተላከው፤ ከዛ ሲሄዱም 21 ጊዜ መድፍ እስከመተኮስ ተደርሷል። ኬንያ የፓን አፍሪካ ህልም ይሳካልኛል ይደረጅልኛል የሚል ህልም ነበራት።

ሰሞኑም የኬኒያው መሪ መጥተው ነበር። በአግራቸው ይህ ተከሰተ? በዚህ ማህል የዚህን የአውሮፕላን አደጋ ስትመረምሩት ኬንያ ለኦዴፓ ክብር የሰጠችው ደረጃ እና ኦዴፓ አፍሪካን ምልክት አልባ ለማድረግ የሄደበት የክህደት መንገድ ማስታዋል ይቻላል። ኦዴፓ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ፓን አፍሪካንም እዬታገለ ነው ያለው። ሁኔታውን በጥሞና መርምሩት ውዴቼ … ክህደቱ በብዙ ዘርፉ ነው የተከወነው።

ክህደቱ መጋለጡ ደግሞ ለመልካም ነው። ክህደቱ መጋለጡ ብቻ ሳይሆን ክህደቱ መኖሩም የኢትዮጵያ መዳኛ ነው። ለወደፊቱ የፋሽስት ናዚ አርማ ንግግር በዓለም አንደተከለከለው ሁሉ ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑት የኦነግ እና የህወሃት ዓርማም የሚከለከልበት ዘመን ይመጣ ይሆናል። ከጠነከርን።

ምክንያቱም ኢትዮጵያ የእኛ ብቻ አይደለችምና። እነሱ ደግሞ የ አንድ ዘውግ ለማድረግ እዬተጉ ነው። ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መፈጠሪያም ናት። ለጥቁር ህዝቦችም የነፃነት ዓርማ ናት። ይህም ብቻ አይደለም ዛሬ በምህዋር የምታዮዋቸው የኮከብ ጥናት ምልክቶች ስያሜ ከነስዕላቸው የሰዬመችው ኢትዮጵያ ናት። ኢትዮጵያ የምድር ብቻ ሳይሆን የምህዋርም ልዕልት ሳየንቲስት ፈላስፋም ናት። ይህን ተጻሮ የሚወጣ ነፍስ ሁሉ ቅጣቱ እዮራዊ ነው።

·       ቁስለት።

እንዴት ናችሁ ውዶቼ ደህና ናችሁ ወይ? ሰላምታውን አዘገዬሁት። አመል አለብኝ እንዲህ ራዲዮ ፕሮግራምም ሞደሬት ሳደርግ እንዲህ እዘገያለሁ። ደብዳቤ ላይም እንዲሁ ነኝ። ይቅርታ። ዛሬ ቪንቱ በረዶ ያዘለ ዝናብ በወጀብ እያስተናገደች ነበር ማለዳ ላይ። የአላዛሯን ኢትዮጵያ ብሄራዊ የሀዘን ቀንም አብራ እዬታደመች ነው - በመንፈስ።

ይህ መከራ አብዛኛውንዓለም አገሮች ዜጎች የያዘ ሰቅጣጭ ሀዘን ነው ኢትዮጵያ እያስተናገደች የምትገኘው። ከአለም አገሮች የቀሩት ጥቂት ናቸው። በአህጉር ደረጃ ሁሉም አሉበት። 157 ነፍስ ቤተሰቡ፤ ቤተዘመዱ ማህበራዊ ትስስሩ ሲሰላ ደግሞ እጅግ በርካታ መረቦች ይኖሩበታል። 100ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ጥቁር ቀኑ ነው። እንግዶቹ አዬር ላይ አመድ ሲሆኑ ሰዋዊ ኢትዮጵያዊነት ጸጋው  ጥቁር ይለበሳል በኢኮኖሚ፤ በሥም ረገድም ሰፊ ድቀት ነው።

ኢትዮጵያ ለተጎጂዎች ካሳ ሁሉ መከፍል ይኖርበታል። ያ ደግሞ በዶላር ነው። ከዛ በላይ የአደጋው ጉዳይ የቦይንግ ከበረራ ለተወሰነ ጊዜ መታገድ ሳይሆን አደጋውን ዓለም በመደዴ የሚያው አይደለም። የአሸባሪነትም መከራ አለበት።

የሚገርመው ፖለቲካዊ ትርፍ እና ኪሳራው ሲታይ ደግሞ ሁለት አውራ የደህንነት ብሄራዊ ባለሙያዎች በጣምራ ምትመራ አገር ነው ይህ የደረሰው። ኢትዮጵያ በሁለት ጠ/ሚር እንደምትመራ ነው እኔ የሚረዳኝ ይህን ደግሞ መሰከረም ላይ በነበሩት ጹሑፎች አበክሬ ገልጫለሁኝ።
የትኛው ፕላኔት ይሆን ያላችሁት?

ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳም ሆኑ ጠ/ሚር አብይ አህመድ በሲቢሉም በወታደራዊውም ሙያቸው ደህነንት ነው። ወርቃም ዘመን ብዬው የነበረው - እኔ። ይህ የአቅም የክህሎት ደረጃ በምን መልኩ ይታያልም ሌላው የተስፋ መንፈስ የሚጎሳቆልበት ወይንም የሚዳምንበት ወይንም የሚዳመጥበት ሁኔታም አለበት። ጥጥና ጥፍጥሬው የሚለይበት።  
በአዬር መንገዱ የወደፊት የመታመን ጉዳይም በተወሰነ ደረጃ ተጽዕኖ ይኖረዋል አብሶ አመራሩን በተለመደው መንገድ በገዢው ብሄር የመበወዝ ሂደት ከመጣም አዲስ አበባ የተጎሳቆለችበት መንገድ አይቀሬ ነው። ፍላጎትም ሌላ፤ አቅም ሌላ፤ አደብም ሌላ ስለሆኑ። ኦነጋውያን እነሱ ያዩት ሁሉ የሚያመራቸው ናቸውና። አንድ መረጃ ሰሞኑን ወጥቷል አዲስ የአየር መንገድ ምልምሎች በሙሉ ከዬትኛው ብሄር እንደሆኑ …

ስለሆነም የዚህን መከራ ምንጭ መመርምር የሚገባን ከገሃዳዊ ዓለም ወጣ ብለን በመንፈሳዊ ጥሞና መሆን ይኖርበታል። ምርቃት እና አያያዝ፤ በረከት እና አጠቃቅም ብለን። መውደቅ እና መድቀቅ፤ መብነንና መትነን ብለንም።

·       ልቤ።

እኔ የሰብዕዊ መብት ተሟጋቹ ጀግና ሃይለመድህን አበራ ያን ሰላማዊ ተጋድሎ አድርጎ ስለሰው ልጅ ተቆርቁሮ፤ ስለ አገሩ ክብር ተቆርቁሮ፤ የተጓዦችን ነፍስ ካዳነበት፤ አንገታችን ከቶም ሳያስደፋ፤ ደም ሳያቃባን ከቀረበት የብልህነት ብስለት፤ የፍጹም የማስተዋል ጊዜ ጀምሮ ሰማይን አንጋጥጬ ነው የማዬው። የምኖርበት አካባቢም ብዙም ለዙሪክ አውሮፕላን ማረፍያ ርቀት ስለሌለው ሰማይ ላይ ድምጹን ስሰማ እንኳን የሆነ የተለዬ ስሜት አለኝ።

ይህ ማለት በአውሮፕላን በረራ ውስጥ እንደ ሰራ ሰው ማንነቴ ተቀይሯል ማለት እችላለሁኝ። እንደ አንድ ባልደረባ በመንፈስ ደረጃ ሆኛለሁኝ። ይህም በመሆኑ የጀርመን ዊንግ አደጋ በዚህው በመጋቢት ወር በ2014 ሲደርስበት ታቅዶ የተከወነ ስለነበር ስለምን የሰው ልጅ ስለሰው ማሰብ፤ መጨነቅ ተሰናው ብዬ ዜናውን 15 ቀን በሀዘን ስከታተል ከቆዬሁኝ በኋዋላ የቀረን፤ የተውነው፤ የዘነጋነው፤ ትኩረት ያልሰጠነው፤ እንክብካቤ የነሳነው ትልቅ ተፈጥሮ አለ ብዬ ምርምር ውስጥ ገባሁኝ።

ፓይለቱ ፈቅዶ እና ወዶ ነበር ከተራራ ጋር እንዲጋጭ ያደረገው። አንድም የተረፈ ሰው ካለመኖሩ ጋር ቅሪተ አካሉን አሰባስቦ የወጉን ለማድረስ የተለቀመው አስከሬን የተሸከመው ሰው ኤሊኮፍተር ላይ አስከሬኑን እንደተሸከመ በገመድ ተንጠልጥሎ በወጀብ እዬተቃጣ ነበር ሲጓጓዝ የነበረው፤ ፈረንሳይ፤ ጀርመን ስፔን በጋራ ተቀናጅተው በመሥራት እና ሀዘኑን በወልዮሽ በመጋራት ነበር ያን መከራ የተወጡት። 

ዲታዎች ስለሆኑ ነበር እንጂ በርደኑ የሚቻል አልነበረም። በዚህም ፈጣሪ አላዛሯን ኢትዮጵያ ታድጓታል በማይቻልበት ቦታ ቢሆን፤ ሜዳ ላይ ባይሆን፤ በ60 ኪ/ሚትር ርቀት ብቻ አደጋው የደረሰ ባይሆን ብሎ ማሰብ ይገባል ... ያ የጀርመን ዊግ አውሮፕላን ሰቆቃ ሁለመናዬን ነበር የቀየረው።

ሰው መሆን እስከሚፈትን ድረስ ነበር ሁኔታው እና ታሪኩ። በማይችለበት ተራራ ማህል ነበር መከራው እንደ ላርባ የቀለጠው። ቀደም ብሎ የረ/አውሮፕላን አብራሪ ሃይለመድህን አበራ መልካም ዜና አንዲትም ነፍስ ሳይጠፋ የወሰደው የአስተውሎት እርምጃ፤ እንደገናም በዛው ሰሞናት የማላዢያ አውሮፕላን ያን የመሰለ ውቅያኖስ ውስጥ የመከስከስ ጥልቅ ሃዘን እና ግሎበሉን ዓለም በተቀናጀ ሁኔታ የፈተነ መከራ መከሰት፤ የጀርመን ዊንግ ታቅዶ የከወነ ሃዘን፤ የራሺያም ሲታከልበት እኔ የአዬር መንገድ የስሜት ቤተኛ ሆንኩኝ እና በጥልቀት ማሰብ ጀምርኩኝ - ስለበረራ።

የምርምር ተግባሬ ዓለም ያላትን ስልጡን ሥልጣኔ በጥልቀት እንዳይ፤ እንዳስተውል እረዳኝ። ዓለም ምን ያህል በጀት ለሥልጣኔ እንደምታፈስም አሰብኩት። ዲጅታሉ ዓለምን እምርታም አስተዋልኩት።

በዛው ልክ ሥልጣኔው አንገት አልባ ስለመሆኑም ተረዳኝ። የዓለም ሥልጣኔ አንገት የፍቅርን ተፈጥሯዊ መርሆዎች ሙያ አለማድረግ፤ ፍልስፍና አለማድረግ፤ ሳይንስ አለማድረግ እና በዚህ ሙያ መደበኛ /ቤት ውስጥ ትምህርቱ አልመሰጠት፤ ለዚህ ኢንስቲቲዩት ተቋማት አለመኖር፤ ለዚህ ኮሌጆች ዩንቨርስቲዎች አለመደራጀታቸው፤ 

ለዚህ አብይ ጉዳይ በአጀንደ ደረጃ ፕላኔታችን ፓናል ዲስከሽኖች፤ ሰሚናሮች ወርክ ሾፓች አለማደራጀቷ፤ ስለ ፍቅር ተፈጥሮ የሚሰብክ፤ በሚዲያ የሚያስተምር ራዲዮ፤ ቴሌቪዥን አለመኖር፤ መጋዚኖች፤ ጋዜጦች፤ መጽሄቶች፤ በራሪ ጹሁፎች አለመታሰብ፤ ፈላስፋዎች፤ ኤክስፐርቶች ሳይንቲስቶች አለመኖራቸው፤ ዓለም የፍቅር፤ የመቻቻል፤ የትዕግስት፤ የመቀበል፤ የመታመን፤ የመስጠት፤ የምስጋና ቀናትን ለማክብር የፍቅር የመርህ ቀናት መወሰን ባለመቻሏ ምክንያት ዓለምን የፍርሃት ጉም እንዲውጣት ሆኗል ብዬ አሰብኩኝ።

ስለዚህም ከቤተሰብ ጀምሮ በሚደራጁ መዋቅሮች የፍቅር ተፈጥሮ መርሆዎች የትምህርት ካሪክለም ተዘጋጅቶላቸው የሰው ህሊና ሰዋዊ፤ ተፈጥሯዊ አድርጎ ማነጽ ይገባል የሚል ውሳኔ ላይ ደርስኩኝ። ሰውን ብቻ ሳይሆን ለፍጡራን ነፍስ ላላቸውም ሌላቸውም የሐሤት ምንጭ ናቸው እና እንክብካቤ የፍቅር ሊደረግ ይገባል ነው ሃሳቡ።

እሳተ ጎመራ በማዬት የሚደስት ይኖራል፤ አለት በማዬት የሚደስት ይኖራል፤ መሬት በመቆፈር የሚረካ ይኖራል ስለዚህ ፕሮጀክቱ ተፈጥሮን በፍቅር የሚያስካን ሃስብ ነበረው።
ይህን ሃሳቤን ለተባባሩት መንግሥታት ለወቅቱ ጸሐፊ፤ ለአውሮፓው ህብረት እና አቅም አላቸው ለምላቸው ፋውንዴሽኖች ላኩኝ። መልስም ጽፈውልኛል። 

ከዚህም ቀጥዬ በ2016 አንድ የቃላት ፖስተር ዩቱብ ጀምርኩኝ ዕለቱ የትንሳኤ ዕለት ነበር። በዬ 4 ዓመቱ የእኛ እና የካቶሊክ አማንያን ጋር ትንሳዬን በጋራ እናከብራለን። ቀኑ ከዚህ ጋር ግጥም ነበር። የአስፈሪው ዓለምን ትንሳኤ በፍቅር መክሊት በማሰብ በጸሎት።

ቻናሉ ግላዊ ወይንም ወላዊ አለረም የሚፈጥር እንዲሆን በጥቂቱ ፓስተር ሰርቼ ለማቆም ነበር የጀመርኩት አንድ 10 ፖሰተሮችን። ወደ ውስጡ ስገባ ጥልቅ ነው የፍቅር ተፈጥሮ የሚያቅፋቸው መሰረተ ሃሰቦች ውቅያኖስ ነው። አንድ ሰው ልማረው ቢል ዕድሜ ልኩን አይጨርሰውም። ለመነሻ የሚሆኑትን በክፍል በምዕራፍ ከፋፍዬ እኔ ባልፍም ሃሳቡን የሚጋራ ቅን የዓለም ዜጋ ለዘላቂ ተግባራዊነት ይተጋል በሚል ነው የጀመርኩት።

የተረጋጋ የጥሞና ጊዜ ስለሚፈልግ በአላዛሯ ኢትዮጵያ ፖለቲካ መታወክ ምክንያት ለሁለት ወራት ያህል አልተጋሁበትም፤ እንጂ በዬሳምነቱ አንድ ቪዲዮ ፖስት አድርግ ነበር። ከሃይለኛ ስንኝ ጋር።

የተጀመረ ክፍል አለ „የፍቅር ተፈጥሮ  ልዑካን“ የሚል እቀጥለዋለሁኝ … ቃላት ብቻ ቢሠራበትም፤ የቃላት ሃይለ መልዕክት ድርብ እንዳይሆን እና አንዱ አሉታዊ ሌላው አዎንታዊ ሆኖ ተልዕኮው ሆኖ ግዳጁን የቻናሉን እንዳያዛባ ጥንቃቄ ስለሚያስፈልገው፤ በጥሞና ሊሠራ ስለሚገባ ነው የተስተካከለ ጊዜ እዬጠበቅኩኝ ያለሁት …. እንጂ እቀጥለዋለሁኝ …
 
https://www.youtube.com/channel/UCb4Maqp24liAGdbPE553WGA/videos

የዚህ መንገድ መሰረቱ ግን ከአውሮፕላን አደጋ ጋር ያሉ እጅግ አሰቃቂ ድንገተኛ ጉዳዮች ጋር የተያያዘ ነበር። አሁን እነ ዶር ለማ መገርሳ ወደ ሃላፊነት ሲመጡ ተስፋዬ የነበረው በፍቅር የታነጸ ማህበረስብ መፍጠር ነበር። „መባቻ“ በሚለው ጹሑፌ በስፋት አባራርቼው ነበር። ተስፋዬ ጥልቅ ነበር።

እኔ እንዲህ ዓይነት የዲሞግራፊ የዲስክርሚነሽን ሃሳብ በቀጥታ የናዚ ትልምን ኦሮማማን ልዕል አድርጎ በማውጣት እረገድ ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ይኖራቸዋል የሚል ቅንጣት ጥርጣሬ አልነበረኝም። አሁን እሳቸውም እራሳቸው ት/ቤት መግባት ይኖርባቸዋል። ሰው በሚል ተቋም ውስጥ።

ሥርጉተም ኦሮሞ ባትሆንም ሰው ናት የሚል መንፈስ እንዲያድርባቸው። ተከታዮቻቸውም እንዲሁ። መዳን አለባቸው ብዬ አስባለሁኝ ቢያንስ ለቤተሰቦቻቸው። ታሪካቸው ጠቀራ ተጎናጽፏል የዶር ለማ መገርሳ። በግሎባል ዓለምም ሊወገዝ የሚገባው አዲስ ውጥን ነው ያቀዱት። ጀርመኖች እኮ ይህን ለማክሰል ስንት ነው የተጉት። የጀርምን ምስል ሁሉ በዚህ ኢተፈጥሯዊ ምስል የተቀረጸ ስለነበር ያን ለማስፋቅ ነው ከ አቅም በላይ የሆነ ስደተኛም በመቀበል ላይ የሚገኙት። ብልህ ፖለቲከኞች አሏቸው። 

እግዚአብሄር በፈጠረው ሰው ላይ ይህን ያህል ለአሉታዊ ፍልስፍና መትጋት፤ እንደ ጢንቸል የአንተ ጠናና የፍልስፍና ተፈታኝ ማድረግ የጤናም አይደለም። እግዚአብሄር ይማራቸው ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳን። አሜን! እነ ዶር ቄስ ገመቺስ ሊሰሩበት የሚገባ ጉዳይ 
ይመስለኛል።

ጠ/ሚር አብይ አህመድም ቢሆኑ ሴቶች ባዕል ላይ „ነውር“ ነው በሉ ብለው በአጽህኖት ሲናገሩ ሰምቻለሁኝ። አሳቸውም በዛ በቤተመንግሥታቸው ስብሰባ ሲታደሙ „ለማ ገልፆታል ሁሉንም፤ አምጨምረው የለኝም“ ከማለት ከሳቸው ካራሳቸው ጀምረው፤ ወንድሜ ለማ የተናገረው „ነውር“ ነው ማለት ይገባቸው ነበር በሌላ ላይ የሚጭኑትን ማንነት ራስ ለመሸከም ራስን ማሸነፍ ስለሚጠይቅ።

ልክ አማራ ክልል የተቃዋሚ/ የተፎካካሪ/ የተቀናቃኝ አካላትን ተሸከሙ እንደተባሉትም … ማንኛውንም ጫና ለክልሉ ያለ ርህርሄ በዬጊዜው እንደሚጭኑት፤ የራሳቸው ድርጅትን ፋሽስታዊ ጉዞ በማዳበር የአማራ ብሄርተኝነትን አውግዙ እያሉ በማለዳው ነበር የአማራ ሊሂቃን በዬጊዜው በስብሰባ ከሚያሳቅቁ ሰው ጠል የሆነው ድርጅታቸውን „ነውር“ ነው ይበሉት ደፈረው። አንድ ነፍስ እኮ ነው ያላቸው። ለዬትኛው ጊዜም ... ይኸው ትናንት 157 ነፍስ አለፈ ሰማይ ላይ እሳቸው በሚሯት አገር ...

ስለዚህ ውዴቼ አሁን ለፍቅር መርህ ተልዕኮ አሉኝ ያልኳቸው የአገሬ ፈርጦች  ድርቀቱን ተጋርተው ተስፋዬም መቃብር ተልኳል። የቀሩት ደልዳላዋ ክብርት ቀዳማዊ እምቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ብቻ ናቸው “ለተባረከች አገር የተባረከ ትውልድ“ የካቲት 29 ላይም የቅድስት እናትን ፕሮጀክት ለማስቀጠል እንጦጦ ቁስቋም አንድ ፕሮጀክት ለመጀመር መሰረት እንደጣሉ አዳምጫለሁኝ። በሳቸው ትንሽ ልጽናና።

የሚገርመው የኦዴፓ ጉባኤ እንደነገረን ኦሮማማ ይህን ሃሳብ ለኢትዮጵያ ብቻ የተወጠነ ፕሮጀክት አይደለም፤ እኛ ያለስስት በሰጠነው የፍቅር መዋለ መንፈስ ድልድይነት እና ቅቡልነታቸውን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ወስደው አፍሪካንም እናጠቃልላለን ነው የሚሉት። ከገባቸው አፍሪካውያን እንሱም ተደማሪ ናቸው በዚህ የኦነጋውያን አዲስ የማንነት የመንፈስ ወረራ። እንደ ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ወራጅ አለ ካላሉ በስተቀር።

ዶር ለማ መገርሳን ልቤ ሲቀበላቸው መታመኔ መነሻቸውን እንኳን ማጥናት አልፈለግኩኝም ነበር። ደፍሬ „ለማውያን ነኝ“ ብዬ ነው የወጣሁት። የፍቅር መርህ ሃሳቡን የጥናቱን ሁሉ መሰረት እልክላቸዋለሁ ብዬ አስቤ ነበር። እንደሚያዳሉ ግን በጥዋቱ ነው ያውቅኩባቸው። እነሱ አይድኑም! ታጥበውም አይጠሩም። ጸረ አማራነት ነው ይህን ሁሉ የሚያደርጋቸው። በሽታው እሱ ነው። አማራ ደግሞ ቅንም ነው፤ የዋህም ነው ቢያንስ ፈጣሪ አይረሳውም …

·       ነፍሴ። 

የሆነ ሆኖ ነፍሴ ከላይ በጠቀስኩት መልክ ከሰማይ እና ከሰው ሰራሹ ወፍ ጋር ከተቆራኜ ጀምሮ ጉዳዬ ሆነ። ስስ ሆንኩኝ ነገረ በረራ። ዜናዎችም የእኔ ሆኑ። የትም አገር  የአውሮፕላን አደጋ ሲፈጠር በባለቤትነት ነው እምታደምበት።

በዚህ ውስጥ ብዙ ነገር ማነሳት ብችልም የኢትዮጵያ አዬር መንገድ አደጋ እኔ ያዬሁበት ጥግ ሌላው ከሚያስበው ውጪ ነው። ወደ ዋናው ጉዳዬ ከመግባቴ በፊት /መስፍን ሰሞኑን ቃለ ምልልስ ያደረጉትን ሳዳምጥ እኔ የሃዘን መግለጫ ነበር ያልኩት። ሳምንት ሳይሞላ ብሄራዊ የሀዘን ቀን ታወጀ።  እኔ ደግሞ እንዲህ ብዬ ጽፌ ነበር።

ለአቶ አዲሱ አረጋ ማስተባበያ ጉልበታም ምላሽ።

„ዛሬ / መስፍን አንድ የሀዘን መግለጫ አውጥተዋል። ለእኔ የሐዘን መግለጫ ነው እምለው። እሳቸው እንኳን ሁሉን በመተቸት የሚታወቁት እንሱንከሰማይ የተላኩሲሉ እነ ገዱን ገፋ አድርገው ነበር። የሆነ ሆኖ በዛሬው የሀዘን መግላጫቸው መቋጠሪያ እንዲህ ብለዋል … ዛሬ

የእነ ለማና አብይ አብዮት እተቀለበሰ ነው ለማለት ይቻላል [ይመስለኛል]:: ደግሞ ሌላ ስው ቀልብሶባቸው አይደለም:: እራሳቸው [ለማአብይእየቀለብሱት ነው:: ”

ዛሬ ብሄራዊ የሀዘን ቀን ነው። እንግዲህ ፕሮፌሰሩ ቀድመው የሐዘን መግለጫ ስጥተውበታል። በሌላ በኩል ጣሪያ የነካው መታበይ ማዕት ያመጣል በልክ ያዙት መታመን ሲረገጥ መታመንን የፈጠረ አምላክ ቀናተኛ ነው እና ማዕት ያወርዳል ብዬም ጽፌያለሁኝ። በዚኸው ጹሑፌም - እኔው። ምክንያቱም በፕሬዚዳንት ለማ የዘር ማጥራት እርምጃ ፕሮጀክት ላይ ላስተባብል ብለው ጃዋርውያኑ አቶ አዲሱ አረጋ ደፍረው ማስተባባያ ስለወጡ ነበር ይህን የጻፍኩት። 

ለአቶ አዲሱ አረጋ ማስተባበያ ጉልበታም ምላሽ።

መሬት ለመሬት መሄድ የትም አያደርስም እዮር አለና። እዬር ፍርድና ዳኝነቱን ይሰጣል - ለቅኖች። ዕውነት እንዲህ ተከድታ በጠራራ ጸሀይ የተሰቀለችበት ዘመን አሁን ነው የታዬው። ዕውነትን ቅርጥም አድርጋችሁ ነው የባለችሁት። ማተብ የሚባል አልፈጠረላችሁም። ደግሞ ዝም ማንን ገደለ?! ዝም ብትሉ ከነገማናችሁ ምን አለበት?! አሁን ይሄ ምኑ ይሰተባበላል?

የሆነ ሆኖ ጥጋብን በልክ መያዝ ይገባል። እናንተ ዘመነኞች ናችሁ። ግን ዘመንተኞችን የሚቀጣ ንጹህ አምላክ ደግሞ እንዳለ አትርሱ፤ በበረድ፤ በተባይ፤ በመሬት መራድ፤ በቃጠሎ፤ በአውሎ በብዙ ነገር የሚቀጣ። ክህደት አያበረክትም። ካዳችሁት 100ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብን። አማራንም ጎንደር ላይ ቀጥታችሁታል። ሆን ተብሎ ታቅዶ የተከወነ ነው። ንጹህ የኦሮሞ ማህበረሰብን ቅራኔ ውስጥ ሰተት አድርጋችሁ ከተታችሁት።“ 

ይህም አሁን ፊርማው አልደረቀም አዲስ አባባ ላይ የተነሳ አውሮፕላን ነው እዛው ከሚመኩበት ባዕታችን ከሚሉት  ደብረዘይት አካባቢ የኢትዮጵያ የቀረ አንድ የመለያ ተቋም ነው አደጋውን ያስተናገደው። ትግሉ ከኢትዮጵያዊነት ጋር ነውና። ይህ በቅጡ ሊፈተሽ ይገባዋል።

https://www.satenaw.com/amharic/archives/64898
ከስብሰባው በኋላ በርካታ ሰላማዊ ወጣቶች ታፍሰዋል፣ ተደብድበዋል

ይህ ፍጽምና ትህትና እዳወጣ ተሸጠ ተለወጠን?!


አሁንም አቤት ብሎ ወደ እግዚአብሄር የአብይ ለማ መንፈስ መጮኽ ሲገባው መታበዩ ቀጥሎ አዲስ አባባ ላይ ሌላ የመታበይ እርምጃ እዬተወሰደ ስለሆነ፤ አላዛሯ ኢትዮጵያ ሀዘን ላይ በጣምራ ተቀምጣለች።

አሸባሪን ሜንጫ ይዞ የተሰለፈን፤ የመራን አቶ ጃዋር መሃመድን ገላጭ ተንታኝ አድርገህ አቅርበህ ሌላው ሃሳቡን ስለገለጸ ደግሞ ድብደባ እስር ቀጥሏል … እሱ የ አብይን ምነፈስ ጦር መዞ በሚታገልበት ሰ ዓት አዲስ አበባ ተስፋዬ ብላ አብይን ወጥታ ነበር። ይህ ማስተዋል መድረቅ ብቻ ሳይሆን ፈጣሪም በጦር እዬተወጋ መሆኑ እዬታዬ ነው

ይህ ጹሑፍ እግዚአብሄር የተከፋባቸው ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ ትቢያ ነስንሰው መሬት ላይ እግዚኦ ሊሉበት የሚገባ ጉዳይ ነበር እንጂ ተጨማሪ መታበይ እና ንቀት ሊታይ አይገባውም ነበር። ጥቁር መልበስ ንጹሃንን ደግሞ ላለመስከፋት ቃልኪዳን መሆን ይገባዋል ትናንት በመግለጫቸው ጥቁር ለብሰው ስላየሁኝ ጠ/ሚር አብይ አህመድ።  

በሌላ በኩል /ሚር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሊመጡ በዋዜማው የእዮር ምልክቶች ነበሩ። መቀሌ አካባቢ የመሬት መራድ፤ ጉራጌ ዞን ሦስተ ድርጊቲችን በበአንድ ላይ አስተናግዳለች። ለነገሩ ለመንግሥትነት ተፎካካሪነትም መንፈሱ እኩል ለእኩል እዛው አካባቢ ስላለ ነው ፍትጊያውን ሰማይ እያጣራው የሚገኘው።

መሬት ከሁለት መከፈል፤ አደገኛ ተሰምቶ የማይታወቅ የሰማይ ድምጽ አውሮፕላኑም እንደዛው በከፈትኛ ድምጽ እንደፈነዳ ነው መረጃው የሚናገረው፤ ታይቶ የማይታወቅ ዶፍ፤ ከጥቂት ወራቶች በሆዋላም ቤት የሰነጠቀ ሌላ መራድ፤ እንደገናም አንጅባራ ላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አርማ ሰማይ ላይ እዬተንቀሳቀሰ የታዬበት፤ 

ከዚህ ባሻገር ደግሞ ምስራቅ ኢትዮጵያ ላይ ከቤተክርስትያናት ቃጠሎ በኋዋላ ሰማይ እሳት ያዘነበበት ጉዳይ ታይቷል አሁን ደግሞ ሜዳ ላይ አንደም ሰው ሳይተርፍ እንዲህ ያለ መከራ ሲመጣ ቁጭ ብሎ በጥሞና መመርምር ያስፈልጋል። ጥፈታቸውን አብይወለማ ሥርዕዎ ግዛት በስክነት ይመርምሩት። የ እኛ የድሆች መከፋት ሳይሆን የ አማኑኤል መካፍት ሊፈተሽ ይገባል ... 

ሴራ ደረጃ ተሰርቶለት፤ ሸር ፎቅ ተገንብቶለት ዘር የመመንጠር፤ የመበወዝ የህዝብ ፍቅር እና መታመን ተክዶ ኢትዮጵያን ርዕሰ መዲና አልባ ለማድረግ እዬተሰራ ስለመሆነ የገለጹትን ልክ እንደ ጋዜጠኛ አበበ ገላው መንፈስ ቅዱስ እቅም ሰጥቷቸው ነው ዶር አብርሃም ለእኛ ለዱዳዎቹ ያብራሩልን። 

ይህም በሳቸው አቅም ብቻ ነው ብዬ አይደለም እማስበው። መንፈስ ቅዱስ ነው ዶር አብርሃም አለሙን ያናገራቸው። ዶር ደረሰ ጌታቸውም መሰል አቋም ነው ያላቸው።
የፈጣሪ ታምር ነበር ያን ገመና የዘረገፈው። 

ከዚህ ቀጥሎ የሆነው ኢትዮጵውያን ሙሉ ለሙሉ ያገለለ የሚኒሶታ ቆንጺላ /ቤት ሁኔታ እና መርህ ብቻም ሳይሆን የአዲስ አበባ ተጠቃሚነት አጀንዳ ተለወጦ ደግሞ የባለቤትነት አዋጅ ከታወጀ ማግሥት ነው ይህ የእዮር እሳት የተከናወናው። የእኛ በሚሉት ባዕት። ለነገሩ እነሱ የእኛ የማይሉት ምን አላቸው እና …? 

በሌላ በኩል አዬር መንገድ ላይ በነበረው የምርቃት ሥርዓት ላይም መሰሉ የበላይነት ለማስፈን የተሄደበት እርቀት እና በደልን አላውቅህም ብሎ የራስን አዲስ አደረጃጀት ለማዋቀር ሌላም የሙሽርነት የከንቱ መወደስ ትዕይንት ነበር። እኔም በወቅቱ ጽፌበታለሁኝ። የመከላከያ ባዕልም በዚኸው መንፈስ ነበር የተከወነው።

የሰሞናቱ የአራስ ልጅ በባድማው በግሪድር መታረስ፤ ልጆች ከት/ቤት መልስ መግቢያ ማጣታቸው፤ እራሳቸውን ያጠፉ እህቶቻችን፤ ቆሎ ሽጠው ዛኒጋባ የቀለሱ ሜዳ ላይ መወደቅ አስተዋሽ አልባ መሆን፤ የወ/ ሃቢባ ሲራጅ ጣሪያ የነካ ጥጋብ ናዚያዊ ዕሳቤ፤ የመሪዋ የድጋፍ ድምጽ፤ በዬቤቱ የወረደው ዕንባ ይህን አመጣ … ገናም ይቀጥላል። እግዚአብሄር ተቆጥቷልና! እግዚአብሄር በፍጹም ሁኔታ አዝኗለኝ።

ይህ ሁሉ የሴራ አነባባሮ በንጹሃን ህይወት ላይ ሲደርስ ተጠያቂው ማን ነው ብሎ መጠዬቅ ይገባል። ተጠያቂው መታመን የካደው፤ ማዕት አውርድ ብሎ መሬት የደበደበው ቲም ለማ ነው። በሰው ምስል ለማዬት ይከብዳል እንደ አድህኖ ስዕል አዬው የነበረው ፎቷቸውን። 

ይድረስ ለአቶ አዲሱ ረጋሳ ካሉበት፤ ቤተ መንግሥትም ከተሆነ?


በለውአቶ ንጉሡ ጥላሁን ደግሞ ምን እያሉን ነው?


እኔ አቶ አዲሱ አረጋ የፈለገውን ቢሉ ምንም አይመስለኛም። በጥዋቱም እሳቸው እና አቶ ንጉሡ ጥላሁን ቲም ጃዋር ስለሆኑ ከዛ ግራጫማ ራሱን ከሳተ መንፈስ የተጠጋ ጤነኛ መንፈስ ለመግኘት አይታሰብምና።
የሜንጫ ሱናሜ ጳጳስ እና ቀዳሽ!

የሚገርመው ግራጫማ ራስመሳትን እንማራለን ብለው አዳራሽ ትናንት የተሰበሰቡትተቃዋሚ/ የተፎካካሪ/ የተቀናቃኝ ድርጅት የሚባሉት የጉድ መንፈሶች መሆናቸው ምን ያህል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሙጣጭ አስር እንደሆነ ነግሮኛል። ጢባ ጢቦ እዬተጫወቱባቸው ነው እነ አቦ ሌንጮ ለታ።

ለምን አይቀሩም? ከሬሳ መንፈስ ሬሳነትን ለመማር …? በበላያቸው ኑሯቸው የሚፈርስ ወገኖችህን አይተህ የዛ መንፈስ አድማጭነት እብንነት ነው። ሙትነት ነው። ለነገሩ ተፎካከሪ/ ተቀናቃኝ/ ተቃዋሚ የሚባለው ሙት መሬት ላይ ነው የሚገኘው። የኦነግን ማንፌስቶ አምላኪ ሆኖ። ብቻ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ብልሃት የሌለው ቅላት ነው የሆነው።

·       ዛነት።

የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያን በመክዳት፤ ለማጥፋት ከሚታትረው የኦነግ መንፈስን እነሱን ለመቅጣታ ሲል ነው ፈጣሪ እዮር እነዚህን በሰላም ከቤታቸው የወጡ ንጹሃንን እንዲህ የሳት አመድ እራት ቤዛ የሆኑት። እኔን! „ለሃጣን የመጣ ለጻድቃን“ እንዲሉ።

ይህን /ሚር አብይ አህመድ ያጡታል ብዬ አላስብም። ብልህ ስለሆኑ የፈጣሪ ቁጣ ስለመሆኑ ይረዱታል ብዬ አስባለሁኝ። እግዚአብሄር በእጅጉ ተከፍቶባቸዋል። የሆኑትን ገልጠው በመናገር ንሰሃ መግባት ይኖርባቸዋል።

ምርቃቱ በረከቱ እዬተነሳ ነው። ከዚህ በኋዋላ ሰውኛ ነገሩ እዬተሟጠጣ በአዲስ አረመኔያዊነት ተሃድሶ ደግሞ መከራው ይቀጥላል ማለት ነውየለማ ቲም ማዕት አውርድ ድብደባ ትርፉ ይሄው ነውና … ። ጭካኔ ነገሰ በሜንጫ ሱናሜ!

በፖለቲካ ስልጣን ውስጥ አብዩ ጉዳይ ተቀባይነት ነው። ፈጽሞ ፕርሰንት ሊወጣለት በማይችለው መልክ ነበር የቲም ለማ ቅቡልነት በህዝብ የተመረጠ ያህል እምነት የተጣለበት። ማዕት አውርድ ብሎ እንደ አባቶቹ መሬት ደበደበ እዮርም ዓለምን ያሰደመ የሰቀጠጠ እሳት ላከ …

የሚገርመው ይህ ለኦነጋውያኑ ድርጅት ከቁብ አልተቆጠረም። አልፎ ተርፎ የጥቁሮች መመኪያ ምልክት የሆነችውን ኢትዮጵያን ምድማዷን ለማጥፋት ተነሳ እንጂ። አቶ ሊብነ እንዳሉት ኦሮምያ እንድትኖር ኢትዮጵያ መጥፋት አለባት“ ያሉት ትንቢት ይፈጸም ዘንድ።

አግዚአብሄር ደግ አምላክ ስለሆነ ነው እንጂ ይህ ማዕት አወዳደቁ ሜዳ ላይ ባይሆን እና አዲስ አባባ ላይ ቢሆን ተብሎ ሲታሰብ ደግሞ ሌላ መከራ ነበረው …. ከቁጣው የተወሰነ ነገር እንደተቀነሰልን ማስተዋልም ይገባል። ይህም የንጹሃን አምላክ ያደረገው ነው።

ልዑል እግዚአብሄር ለአንድ ሰው ብሎ ምህረት ያደርጋል እና … ይህም እኔ ሳስበው ቅኖች አዲስ አባባ ላይ ሰልፍ ስለወጡ ይመስለኛል፤ ልክ ጠ/ሚር አብይን አህመድን ገድሎ ሬሳ ይዘን እንገባለን ሲባል የብጹዕን አባቶቻችን መንፈስ በጥበቡ፤ በልቀቱ እንዳዳናቸው ነው ትናንትም አዲስ አባባን የታደጋት አማኑኤል፤ ቤተ መንግሥትም ላይ ይሁን አፍሪካ አዳራሽ ላይ አውሮፕላኑ ቢወድቅ ኑሮ ብሎ ማስብ ይገባል … 

የቁጣው ቁር ባዶ ሜዳ ላይ መሆኑ ቢያንስ መሬት ላይ ያለ ሰው ተርፏል። ሰቀቅንም ቀንሷል። ለታበይ ልብ ግን ሰው ምኑም አይደለም። የሱ መሰረት ጭካኔ አረመኔነት ነው እና አምልኮቱ …

·       ማገዶ።

መከረኛው አዲስ አባባ አሁን ጢሶ ጢሶ መማገጃ ሆኗለኝ። መታቀብ፤ አደብ፤ ጭምትነት የሚባለው አሁን ላይ ሊሰራ የሚገባ አይመስለኝም። ምክንያቱም ኢትዮጵያ እራሷ ሞት ላይ ስላለች። በሰው ላይ ሰው እዬፈረሰ ሰለሆነ።

ህወሃት አንገቷን ቆረጠ፤ ኦዴፓ ህሊናውን ዘረፈ። ስለዚህም እዮር ተቆጣ። የፓትርያርኩን /ቤት ያስደፈረው ኦዴፓ ነው። ምክንያቱም ሌላ ዶር ፓትርያርክ ኦሮምኛ ተናጋሪ አዘጋጅቷል። በክብር ከስሜን አሜሪካ ተጠርተው ነው አዲስ አበባ ገብተው የቅዱስ ሲኖዶስ አንደበት እንዲሆኑ የተደረጉት። 

የጥምቀት ቡራኬ  በኦሮምኛ እንዲሰጡ ተደርጓል። ብፁዕ አባታችን ፓትርያርክ አባ ማትያስ እያሉ። በኦሮምኛ ቡራኬ መስጠታቸው አይደለም ቁም ነገሩ ሚኒሶታ ቆንሲላ /ቤት በሆነወ መልክ ነው ይህ ሊታይ የሚገባው።

ምልክት

እሳት በሀረርጌ ከሰማይ እዬዘነበ ነው። እግዚኦ!


https://www.satenaw.com/government-officials-doctors-among-ethiopian-crash-victims/

Government officials, doctors among Ethiopian crash victims


ለሰማዕቱ ነፍስ ይማርልን! አሜን!
ግፈኞችን ያስታግስልን አማኑኤል! አሜን!
አማኑኤል ይርዳን! አሜን!


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።