እሳት በሀረርጌ ከሰማይ እዬዘነበ ነው። እግዚኦ!
ጸሎት!
„እግዚአብሄር ቁጣውን አይምልስም፤
ከእርሱ በታች ረዓብ የሚረዱ ይዋረዳሉ። „
መጽሐፈ እዮብ ፱፲ ቁጥር ፫
ከሥርጉተ©ሥላሴ
09.11.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
እም! የዘንድሮው ደግሞ የጉድ ነው። ክፋታችን በዛ። መቀሌ አካባቢ የተነሳው የመሬት መናጥ መጋቢት እኩሌታ ላይ ነበር። ሴረኞቹ የህውሃት ማህበርተኞች የጥገና ለውጡን ዕቃባ ለማድረግ ሌት እና ቀን በሚተጉበት ሁኔታ።
ከዛ ቀጥሎ በጉራጌ ዞን ተዉ አትበጥበጡ፤ አትወኩ፤ ይህን ምርቃት አትጋፉት ሲል ያልተለመዱ የሰማይ ሦስት ቁጣዎች በአንድ ላይ ታድማዋል ። ታይቶ የማይታወቅ ዶፍ፤ ተሰምቶ የማይታወቅ የእዮር ደምጽ ተከስቶ የማያዋቅ የመሬት መገመስ።
አንጅባራ ላይ ደግሞ ለማስታረቅ ይመስላል የምህረት እዬራዊ ታምር ታይቷል። ብሄራዊ ሰንድቅዓለማችን እዬተንቀሳቀሰ በራሱ ጊዜ ከፍ ብሎ ሰማይ ላይ ታይቷል።
በቅርብ ጊዜም በዛው በደቡብ ሌላ ቤቶችን ከሁለት የተረተተረ ማዕት ተክስቷል። ከሰሞኑ ደግሞ የወያኔ ሃርነት ትግራይ እና ኦነጋውያን፤ ሆኑ ጃዋርውያን ይሹት የነበረው የሱማሌ ትርምስ መጨረሻውን የተወራረደው አብዬተ ቤተ ክርስት- ያነናትን በማቃጠል፤ ሰማዕታትን በመውገር እና በመግደል ነበር። አሁን እዬሆነ ያለው ቁጥ ደግሞ ፕላኔታችን አስተናግዳው በማታውቀው ሁኔታ ነው።
ብፁዕን ቅዱሳን አባቶቻችን 4ኛው ፓትርያረከ ዘኢትዮጵያ አቡነ መርቀሪዮስ
ወደ መንበራቸው ፈቅደው ከስደት በተመለሱ ማግስት የሆነው የቤተ መቅደስ ድፈረት የዓለም አብያተ ቤተክርስትንያትን ሁሉ ያሳዘነው፤ ያ ድፈርት አሁን ከሰማይ እሳቱን እያዘነበው ነው። ለሃጣን የመጣ ለጻድቃን ሆኖ ነዋሪዎች
አሁንም ቁመው እያዬዩ ከሰማይ በሚወርድ ነበልባል ኑሯቸውን አመድ እያደረገው ነው።
እግዚኦ! „እንደ በዳላችን ሳይሆን እንደ ቸርነትህ አቁርልን ማለት ይኖርብናል።
የድህነቱ ላይበቃ በሰው ሰራሽ ችግር ሚሊዮኖች ወገኖቻችን ህፃናት እና አረጋውያንን ጨምሮ በግፍ የተፈናቀሉት በዚኸው ክልል ነበር።
ሴረኞች ከሴራቸው ቢታቀቡ፤ ሸረኞች ከሸራቸው ቢታቀቡ፤ ተንኮለኞች ከተንኮላቸው ቢታቀቡ፤ አድመኞች አድማቸውን ቢያስታግሱት፤ ጦርነት ናፋቂዎች ሳንጃቸውን ቢመልሱ፤ ምቅኞች ወደ ራሳቸው ተመልሰው አቤት
ቢሉት ሁሉም በአንድነት ወደ እግዚአብሄር ቢጮኽ ቀኑን በማስባርክ
ምርቃኑን ማስቀጠል፤ እዮራዊ ቁጣውንም ማስበረድ ይቻላል።
ሁሉም በእጅ ነውያለው ወደ መልካምነት ለመመለሰ ከፈቀደ የእዮርን ቁጣ ለማስተጋስ እራስን ማሸንፈ በፀሎት መትጋት ይጠበቅበታል። ጸሎት የማይፈታው ችግር ከቶውንም የለም። እሳት ከሰማይ እዬዘነበ ነው?
Ethiopian Info - አስደንግጭ መረጃ: በምስራቅ ኢትዮጵያ ሐረርጌ
እሳት ከሰማይ እየዘነበ ነው Harerge 2
ወደ ቅናዊ ልቦና ሁላችንም አማኑኤል ይመልስን። አሜን!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ቸር ወሬ ያሰማን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ