ጎንደር እንደ አባት አዳሩ ዓዋጅ አሰነገረ።

ጎንደር እንደ አባት
አዳሩ ዓዋጅ አሰነገረ።
„ሰማያት የእግዚአብሄርን ክብር ይናገራሉ፤
የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።“
መዝሙር ፲፰ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
 09.11.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።


ከሰላም ሚኒስተር ምስረታ ማግሥት ጎንደር ላይ የሰላም መንፈስ መናህሪያ አህዱ ሆኗል። እናም ሥርጉትሻ ደስ ብሏታል። ከእንግዲህ በኋዋላ ጦርነትን አክ እንትፍ ብለን ልንጸዬፈው ይገባል። ጦርነት የሚስገኘው ትርፍ ቢኖር አመድ እና በቀል ብቻ ነው። 

ጦርነት የትውልድ ብክነት ነው የሚያመጣው። ጎንደር ለ50 ዓመት ሙሉ በጦርነት መማቀቋ ልጅ ማውጣት አለመቻሏን ልብ ልትለው ይገባታል። ልጇቿ በህይወት ያሉትም ስደት ቅርምጥ አድርጎ ብልቷቸው ውጧቸው ቀርተዋል። ብቅ ሲሉ ደግሞ ኩርኩም ነው በዬ አቅጣጫው። መከራው ውሃ ያዘለ ተራራ ነው ልበላችሁ እኔም ስላለሁበት። 

የጎንደር ልጅ ቤተስ መረዳት ዋንኛ ፕሮጀክቱ ስለሆነ በጦርነት የተጎሳቀሉ ቤተሰቦችን ለመርዳት በሚያደረገው ግብግብ ወጣትነቱን፤ ክህሎቱን፤ ህይውቱን መክሊቱን ሁለመናውን ሲያባክን ኖሯል።

ከእንግዲህ ጎንደር ማንኛውንም አመጽያንን ላለማስጠጋት መቁረጥ እና መውስን ይኖርበታል። መንገድ መሪነቱንም ማቆም ይኖርበታል - ጎንደር። የተጠቀመው አንዳችም ነገር የለም። ቀን አውጥቶ ሁሉንም ለወግ ለማዕረግ አብቅቶ እናምሰግንህአለን ተብሎ እንኳን አይታወቅም።

ሁልጊዜ ለአጃቢነት ከመታጨት ውጪ ጎንደር ልጆቹን ከብክቦ እልቆ ለማውጣት የማይፈለግ ስለመሆኑ ከሥርጉተ ሥላሴ በላይ ሌላ ምስክር ሊመጣለት አይችልም ለጎንደር። ጎንደር ልብ ሊገዛ ይገባዋል። ጎንደር በማስተዋል ሆኖ የለውጥ አካልነቱን ሙሉ ልቡን ሰጥቶ ሊዋህደው ይገባል። ጥገናዊ ለውጡ ለጎንደር ቢጠቅመው እንጂ የሚጎዳው አንዳችም ነገር የለም።

ዛሬ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሱማሌው ፕሬዚዳንት ማህመድ አብዱላሂ ጎንደር ላይ ሲገቡ አቀባባሉ በዓዋጅ ነበር። ዓዋጅ አዋጅ እዬተባለ። ይህ የወል ትውፊታችን ለመጠበቅ፤ ለመንከባከብ ለማስቀጥል የሚችለው ደግሞ አገረ ኢትዮጵያ ሰላሟ ሲጠበቅ ብቻ ነው።

ስለሆነም ጎንደር "ሰላም ወይንም ሞት!" ብሎ መነሳት ይኖርበታል። ምክንያቱ በጦርነት ድቅቅ ብሎ አቧራ ለለበሰው የሥነ - መንግሥት ምስረታ የአገር እጬጌነት ቀጣዩ ተስፋ ከዚህ በላይ የመፍትሄ መንገድ ላይ ነው ያለና። ጥገናዊ ለወጡ ለጎንደር ይህሊናው ማህደሩ ነው። 


ጎንደር ዓለም አቀፍ መንፈሶችን ያነገበውን የ አማራ ተጋድሎ ይህለውና አብዮትን የሐምሌ 5/ 24 አብዮት አካሄዶ ላስገኘው ለውጥ ተጠቃሚ ለመሆን የሚችለው እራሱን በራሱ ገርቶ እና መክሮ ከጥገናዊ ለውጡ ጎን ሲሰለፍ ብቻ ይሆናል። የሰላሙ ዘብ እራሱ የጎንደር ህዝብ መሆን ይገባዋል። የህግ ወጥ የመሳሪያ ዘውውሩን ሁሉ መቆጣጠር ይኖርበታል ጎንደር። 

 በሁለቱም በኽረ ሃይማኖቶች በእስልም እና እና በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ደርሶ የነበረው መገለል መልስ ማግኘቱን ጎንደር ህሊናዬ ሊለው ይገባል። ለጎንደር ከዚህ በላይ የተስፋ ማህደር የለውም። 

ሌላው ጊዜ ገቢረ ለእግዚአብሄር ነው እና በአደብ፤ በእዮባዊነት ትጋት የሚከውን ይሆናል። ዛሬ አንድ ጹሁፍ ኢትዮ ሪጀስተር ላይ አንብቤያለሁ። ይገርማል መንፈስ ለመበትን የዛራው መርዝ ልበ ቢሶችን እንቶ ፈንቶዎች ገርመውኛል። የመተማ ገበሬዎች መከራ በአንድ ጀንበር የሚቀረፍ አይደለም። ዓለማቀፋዊ ነው የሠራዊቱም አወቃቀር እንዲሁ። ማዕካለዊ መንግሥት እራሱ እኮ ስንት ገማና ተሸክሞ ነው አገር እዬመራ ያለው። እራሱ የነፃነት ፈላጊው እንኳን ቀን አብሮ አለሁ ይላል ሌሊት ሲንድ ያድራል። 

እኛ በሰረናው የእጅ ሥራ ችግር ስንት ጫና እና ውጥረት ለጥገና ለውጡ እንደጨመርንበት እና መዋለ ጊዜውን እንደተሻመንበት ልብ ልንለው ይገባል። ለመጀመሪያ ጊዜ ጎንደር ሲሄዱ ጠ/ሚር አብይ አህመድም ህዝቡ ስብሰባውን ረግጦ ሄደ ተብሎ ተጽፎ ነበር። አብይ ለጎንደር ብቸኛው ጌጡ ነው። ብዬ የዛሬ ዓመት ጽፌ ነበር።

የሆነ ሆኖ ለሁሉም ጊዜ፤ ለሁሉም አደብ ያስፈልጋል። አሁን ዛሬ ይህ መጻፍ ነበረበትን? ወኔው ከኖረ ስሙ ስለምን አልተለጠፈም። አፍራሾች። ጹሑፉ እንዲህ ይላል አትዮ ሪጅሰተር ነው ያገኘሁት
"መተማ የሚገኙት የህወሓት አዛዦች ከመቀሌ በተሰጣቸው ትዕዛዝ አማራውን እየጨፈጨፉ ነው። መከላከያው ከመቀሌ እንጅ ከአዲስ አበባ አይታዘዝም" ይህን የሚሉት የወያኔ ሃርነት በጀት የተመደባላቸው ናቸው። ዛሬ ቀን ጠብቀው መንፈስ ለመበትን የሚተጉት። የ27 ቁልል ችግር በአንድ ጀንብር አይፈታም አብይ ሰው እንጂ መላዕክ አይደለም። በነፃነት ተጋድሎው ዘመን የተያዘ የተረዘዘውን ሲአብጠለጥሉ የነበሩት የስም ታጋዮች ከጥጋው ለውጥ በሆዋላ ድብዛቸው ነው የጠፋው። ብትክትኮች። ምክንያቱም በጀቱ ተቋረጠ። 

ይልቅ በሌላ በኩል ለሚያልፍ ቀን ወያኔ ሃርነት ትግራይ በሰራው ሴራ፤ በፈጸውም ጭካኔ እና አረመኔያዊነት ምክንያት ከትግራይ ወገኖቹ ጋር መቃቃር የጎንደር ሰው አይኖርበትም። ከቅማነት ወገኖቹ ጋርም ቢሆን ወጀቡን ዝቅ ብሎ ማሳለፍ ይኖርበታል። በመቻል ውስጥ ድልም ክብርም አለ። በመከራ ውስጥ ልዕልና አለ። ጥንታዊነት ሥልጣኔ ማለት ይህ ነው።

አባቶቹ በዛ በመጀመሪያው ዘመን እንኳን ከውጭ አገር ዜጎች ጋር ጋብቻ መስርተው ተዋልደዋል፤ ዘር አፍርተዋል በሚገባም ኢንተግሬት አድርገዋል። የቀለማችን ጠረኑ ራሱ ምስክር ነው። ጎንደር ውስጥ ቀለመቻው ለዬት ያሉ ቤተሰቦች አሉ። 


ስለሆነም ይህን ይትበሃል ማስቀጠል አሁን ያለው ትውድል ግዴታ ነው። አባቶቻችን ያለፉበትን የመቻቻል የአቃፊነት የወገናዊነት ሌጋሲ ለማስቀጠል ትናንትን ማድመጥ ቢጠቅም እንጂ የሚጎዳው ነገር የለም።

ራስን ከዘመን ጋር ለማዋህድ መፍቅድ ቅንነትን መንከባከብ አቃፊነትን መተግበር፤ መቻልን አፋፍቶ እና አልምቶ ማስቀጠል ሰላምን ወዶ የእኔ ብሎ መፍቀድ ጎንደር የዕለት መርሁ ሊሆን ይገባል። ጥላቻ የሰይጣን እንጂ የሰው ልጅ መርህ አይደለም። ሰው ሰውን የሚያሰኘው ሰው ስለመሆኑ ቃል ስለመሆኑ መቀበል ስመቻሉ ነው።

ትናንት ጠ/ሚር አብይ አህመድ እና ቡድናቸው የቅማንት እና  የወልቃይት የጠገዴ አስመላሽ ኮሚቴ አባላትን እንዳወያዩ አዳምጭለሁኝ። አጠቃላይ አገራዊ ችግሮች ጋር ሊፈታ እንደሚችል ተጥቅሷል አብሶ የወልቃይት እና የጠገዴ ችግር። 

ለዚህ መፍትሄ የሚሆን ብልህ ዕሳቤ የሰብዕዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ያሬድ ሃይለማርያም ያቀረቡት የመፍትሄ ሃሳብ መልካም ሆኖ አግኝቸዋለሁኝ። ዛሬ ቀኑ ስላልሆነ ዛሬ የእንግዳ ቀን ስለሆነ በዛ ላይ ብዙም ለመግፋት ፈቃድ የለኝም። ይደረሰብታል እና።

የማንነት ጥያቄዎች ወደ ደም አፋሳሽ ግጭት ሳያመሩ በፊት መንግስት አፋጣኝ
እርምጃ ሊወስድ ይገባል!
November 9, 2018
ያሬድ ሃይለማሪያም

የሆነ ሆኖ የጎንደር ሰው ሲወድም ሲጠላም እርምጃው እኩል ነው። ሲወድም እስከ ንፍጥ ልጋጉ ነው። ሲጠላም እንደዛው ነው። እንደምሰማው ከሆነ የጎንደር ሰው ልቡን ለአብይ ለማ ካቢኔ ሳይሰስት እንደ ሰጠ እና ፍቅርኑ ላለመቀነስ መስማማቱን ነው የማደምጠው። ይህን እኔ ተመስገን ብያለሁኝ። ደግሞም ይገባል።

ከዚህ ከጥገናዊ ለውጡ በኋዋላ ያለው ሰላማዊ መንፈስ ጎንደር ላይ እጅግ አበረታች ነው። ከሁሉ በላይ መንፈስ አረፈ። ከመንፈስ በላይ አይሆንም ቁሳዊ ፍላጎት።

እግረ መንገዴን አንድ ነገር ልበል፤ ዛሬ የፋናን ቀረፃ አልተዋጣለትም። ለእኔ መንፈስ ፋና ቀረፃው ጥራቱ አንቱ ስለሆነ እንዲህ ላለ ብሄራዊ እና ታሪካዊ ጉብኝት ምርጫዬ ነበር። ዛሬ ግን አልተዋጣለትም ሰፊ ድክመት አይቸበታለሁኝ። ስርክርክ ያለ ነው ለዛውም በ21ኛው ምዕተ ዓመት። 

የሆነ ሆኖ ዛሬ እኔ ከመቸውም በላይ ደስ ብሎኛል። ከዛ በመፈጠሬ ሳይሆን ጎንደር ላይ የሚነሱ እሳቶችን በቀላሉ ለማጥፋት ጋዳ ስለሚሆን ብቻም ሳይሆን በተጨማሪም ጎንደር ፊቱን ካዞረም ከባድ ስለሆነ ነው። አሁን እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ስታገኙኝ በህጻን ልቦና በድንግልና ነው። ሁለመናዬን ሳልስት ሳልቆጥብ ግልጥ አድርጌ እፈቅዳለሁኝ፤ እሰጣለሁኝም። 

በዛ የህፃናት ቅን ልቦና ካልተጠቀማችሁ፤ ከሾለካችሁት ደግሞ መልሳችሁ አታገኙኝም። ቁጭ ብዬ አልጠብቅም። ቅሬትም ትርፍ አካልም አይኖርም። እርግፍ አድርጌ ነው እምተው። ይህ እንግዲህ ከጎንደር ከማህበረሰቡ የወረስኩት ትውፊት ነው።

የሰው ልጅ ለሚሰጠው ፍቅር፤ አክብሮት ክብር ሊኖረው ይገባል። ያን የጠቀጠቀ፤ ያን ያቀለለ፤ ያን የሳተ ከሆነ ጊዜ የኩሬ ውሃ አይደለም። ትእግስት ሲያልቅ ክብርም ፍቅርም ይሰደዳሉ።

ስለዚህ ይህ አሁን በማዕከላዊ መንግሥት ያለው አትኩሮት የተገባ እና መሆን የነበረበት ነው። እንት አለም ጎንደር ደግሞ የሁሉም መንፈስ ማረፊያ ነው። እሷ ለራሱ ጥቅም ተግታ ባታውቅም። ሌላውም ባሊህ ብሎት ባያውቅም። 

የትም ቦታ በዬትም ሁኔታ በታታሪነት ይሁን፤ በግል ሚዲያ ላይ የጎንደር ልጆች ለኢትዮጵያኒዝም ትጉሃን ናቸው ከሥልጣን ሩጫው ባሻገር ባሉ አገራዊ ጉዳዮች አንቱ ናቸው።

ግን ለአካባቢያቸው ሰው፤ ለህዝባቸው ብጣቂ አትኩሮት፤ ተቆርቋሪነት ሰጥተውት አያውቁም። የራሳቸውን ሰውም አግዘው ባልሂ ብለው አይውቁም። ለውጩ ግን አልጋ ናቸው። ራሳቸውን ተላልፈው ነው የኖሩት።

ለዚህ ነው አካባቢያቸውን አቅም አለይህ ብለው ለሌላው ድልድይ ሆነው አሻጋሪ ሆኖነው በጎንደር በህዝቡ ትክሻ ላይ ጫና እና መከራ በዬዘመኑ ሲጭኑበት የኖሩት። ሲማግዱት የኖሩት። እነሱም በሁሉም የህይወት ዘርፍ ሾልከው የቀሩት በዚኸው ከራስ ላይ ለመነሳት ባላቸው ቸለልተኝነት ነው።

አዲሱ ትውልድ ግን እኛ ባለፍንበት ማለፍ የለበትም፤ አይኖርበትም። የራሱን ነገር አክብሮ አስከብሮ ወዶ እና አስወድዶ መነሳት ይኖርበታል። ለራሱ የፖለቲካ ዕውቅና እና ለአካባቢው ልማት እና እድገት፤ ለትውልዱ ሁለገብ ተሳትፎ ተግተው ሌት ተቀን መሥራት አለባቸው።

ጎንደር ሆነ በጠቅላላ የአማራ ህዝብ ልጆቹን ግዕዝ ማስተማር ለነገ የሚቀጥረው ጉዳይ ሊሆን አይገባም። ያን የአባቶቹን ሌጋሲ ሚስጢር ከምንጩ ለመቅዳት ይህ መሰረታዊ ጉዳይ ይሆናል።
  
የሆነ ሆኖ የ50 ዓመቱን የፖለቲካ ልግጫ አፈር ድሜ ያስጋጠው  
የኦሮሞ ደም ደሜ ነው፤ የጋንቤላውም ደም ደሜ ነው ሥርነቀል  የአብዮት ብሄራዊ ዓለም አቀፋዊ ጥሪ ዛሬን እንዲህ ወልዷል።

ከሰሞኑ እንኳን ሰው ልብ አላለውም፤ መንግሥትም እንዲሁ በጅጅጋ የተፈጠረውን የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ቤተ ክርስትያናት ውድመት እና ሰማዕታትን ህልፈት ጎንደር በተደሞ በማዬት የእስልምና ሃይማኖት ዓለም አቀፍ ባዕል ቅደመ ዝግጅት ላይ ያሳዬው የቀደመ ስልጡን ተግባር ጎንደርን ለመተርጎም አቅም እንዲያንስ አድርጎታል።

ይህ የተባ የአባት አደሩ ተግባሩ ብዙም የሚዲያ ሽፋን ባያገኝም ግን የሠራው ታምራት ታሪኩን የምንዘክር ልጆቹ ለትውልድ፤ ለልጅልጅ በሚቆይ መልኩ እንዘክርለታለን። 

ይህም ብቻ አይደለም የቡራዩ እልቂት እና የመስቀል ባዕል መከራም እንዲሁም የአርሲ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጫና በጽሞና እና በአርምሞ ጎንደር ተመልክቶ የመስቀል ደመራ ቦታ ፒያሳን የእስልምና እምነት አበው ያን ችግር ለመፍታት፤ ለማስከን የወሰዱት እርምጃ የጎንደርን ሚስጥራዊነት ያስመሰክራል።

ጎንደር ልቡም ህሊናውም ጭንቅላቱም ማግስትን ያሰበ፤ ትውልድን ያሰላ ሰላምን የናፈቅ የተደሞ ዕንቁ ባዕት ነው። ለዚህ ህዝብ፤ ለዚህ በሁሉም መስክ ራሱን አዬማገደ የሚነሱ እሳቶችን በብልህነት ለማጥፋት ለሚተጋ ህዝብ፤ ይህን መሰሉ አክብሮት እና አትኩሮት ሲኖር ልበ ገብ ህሊና ገብ ይሆናል። ብቻ ዛሬ እኔ ደስ ብሎኛል።

አቶ ሺመልስ አብዲሳም የመጀመሪያ ሥራቸው በዚህ ታሪካዊ ቦታ የሚስጢራት ንጥረ ነገር ባዕት ላይ መሆኑ ዕድለኛ ናቸው። የሰሞኑን ብልህ መግለጫቸውንም አዳምጫለሁኝ ከለማ አብይ መንፈስ ጋር ስለመሆናቸው ገብቶኛል፤ ብልሃቱም ገብቷቸዋል ብዬ አስባለሁኝ፤ ሴራውንም ከኩላሊቱ ተረድተውታል። አብሮ ለመውደቅ መታከት ነው በዬዘመኑ የኦሮሞ ሊሂቃን ግብ። ብቻ ለሳቸው ይህን መሰሉ አርቆ አሳቢነት ይጨርስላቸው ብያለሁኝ እኔው።

Ethiopia: ሊታይ የሚገባው ዘገባ - ለማ መገርሳ ለኦሮሞ ልጆች ያስተላለፈው ልብ የሚነካ መልዕክት | Lema Megersa | Dr Abiy | ODP


ሌላ ለአቶ ሽመልስ አብዲሳ ልነግራቸው እምሻው የጣና ኬኛ ወላጅ እናት የጎንደሩ የ አማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ አብዮት ስለመሆኑ ልብ ሊሉት ይገባል። የጎንደሩን አብዮት ተቅብሎ ደሙን የገበረለት ደግሞ ጎጃም ባለቅኔው ነው። አባቶቻችን „ነገርን ከሥሩ ውሃን ከጥሩው“ እንዲሉ … ጎንደር ለዬዘመናቱ የታሪክ እንብርት ናት። ታሪካችን ስለሆነ መዘከር ግዴታችን ነውና። 

ውዶቼ ቅኖቹ የጹሑፌ ታዳሚዎች ብዙም ስለ ኦሮሞ ሊሂቃን ገፋ አድርጌ ለመሄድ አቅም እያነሰኝ ነው። ደከመኝ። የሚታመን ጠፋ፤ በመንፈስ የሚዘልቅም ጠፋ፤ እውነት ለመናገር አንገቴንም እያስደፉኝ ነው፤ ይህም ሆኖ መልካም ነገር ሲዩ ትንሽ ማለት ስለሚገባ ይህችን በቁጠባ ግን ማለት ፈለግሁኝ። 

ዶር ለማ መገርሳ ግን ቀርቶባቸዋል እስካሁን ድረስ ጎንደርን አቅደው ሂደው አለማዬታቸው።
   
/ / አብይ አህመድ ከጎንደር የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ያደረጉት ውይይት

ለኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ለሶማሊያ ፕሬዚዳንት መሃመድ አብዱላሂ

በጎንደር የተደረገው አቀባበል

Published on Nov 9, 2018


ፎቶዎቹ በሙሉ ከ ኢትዮ ሪጅስተር/ ከሳተናው የተወሰደ ነው። አመሰግነዋለሁም ስለትጋቱ እና ምንጭነቱ። 

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።
መሸቢያ ጊዜ።

ኑሩልኝ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።