ወርሃ የካቲት ለእኔ የቅኔው ልዑል፤ #ፓን አፍሪካኒስቱ የብላቴው ጸጋዬ ገ/ መንፈስ የሚከብርበት ዓውዴ ነው። ለእኔ ጸጋዬዚም + ኢትዮጵያኒዝም + አፍሪካኒዝም= #የዕውቀት ዘርፍ ነው ብዬ አምናለሁኝ።
ወርሃ የካቲት ለእኔ የቅኔው ልዑል፤ #ፓን አፍሪካኒስቱ የብላቴው ጸጋዬ ገ/ መንፈስ የሚከብርበት ዓውዴ ነው። ለእኔ ጸጋዬዚም + ኢትዮጵያኒዝም + አፍሪካኒዝም= #የዕውቀት ዘርፍ ነው ብዬ አምናለሁኝ። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #ምዕራፍ ፲፰ #እፍታ ። ክብሮቼ ማዕረጎቼም ቤተ ሥርጉትሻ ቅኖች ሆይ! ዛሬ የ፲፰ ዓመት መንፈሰ ጸጋዬ ጉዞዬ በምዕራፍ ፲፰ቱ የአጤ ፌስቡክ ማዕዴ ዘለግ ብሎ ይቀመራል። እኔ ወደ ብላቴው አቀናሁ ወይንስ እሱ ወደ እኔ መጣ። ቅኔውን ለባለቅኔወች፤ ዕድምታውን ለዕድምታ ባለሙያ ሊቀ - ሊቃውንታት ልተወው። ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንን በሚመለከት ለሙሉ ፲፰ ዓመታት የተጋሁበት፤ የተከሰስኩበት፤ ብዙ ፈተና ያስተናገድኩበት፤ ብዙም የተንገላታሁበት፤ የተገለልኩበት፤ ባን በሉት ብሎክ በእኔ ላይ ፈርሰስ ብለው ወክ እንዲህ ያሉበት፤ የተንበሸበሹበትም በኽረ ጉዳዬ ነው። በፓልቶክ በሉት፤ በድህረ ገጽ፤ አሁን አዲስ ገብ በሆነው የሚዲያ ዕድል ዩቱብም ሳይቀር #ፋክክሩ ለወረት ይደራል፤ የዘለቀ ግን የለም። ለምን? #በድንግልና የተወጠነ ስለማይሆን። አንድን የዕውቀት ዘርፍ ሊያዘልቅ የሚችለው የውስጥ #ቅንነት እና ንጽህና ብቻ ነው። የጸጋዬ ድህረ ገጽ ነበረኝ። በቦርድ ነበር የሚመራው። የልጆች ፕሮግራም ለመጀመሪያ ጊዜ የነበረው ድህረ ገጽ ነበር። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተገዢነት፤ ተጠቅላይነትን ይሻ ስለነበር አሻም በማለቴ ቦርዱ ተበተነ። ግን ብቻዬን እኩል የጀመርኩት የጸጋዬ ራዲዮ ስለነበር። ያ ቀጠለ። የመጀመሪያው ፕሮግራም ሲደመጥ ነበር በአክራሪ ኦሮሞነት እና በአክራሪ ኦርቶዶክስነት የተከሰ...