ልጥፎች

ከጁላይ 6, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

መልካም ዕድል #ለእምዬ ለሲዊዝ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን። #የሰላም #ንግሥቷ። #Viel Erfolg.

ምስል
  መልካም ዕድል #ለእምዬ ለሲዊዝ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን። #Viel Erfolg.   "የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፥ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።"   (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)         ዕለተ ቅዳሜ ልክ 18.00 ሰዓት #የእምዬ ሲዊዝ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከአቻው የእንግሊዙ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን ጋር በጀርመን በዶርትሙንድ ሲቲዲዮም ወሳኝ ግጥሚያ አላቸው።   ትናንት ባዬነው ጨዋታ ስፔን ጀርመንን በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ፤ ፈረንሳይ ፖርቹጋልን በተጨማሪ ጊዜ፤ በዛም መሸናነፍ አልችል ብለው በፔናሊቲ ዳኝነት ፈረንሳይ ለቀጣዩ ፍልሚያ እንደ ስፔን አልፈዋል።    ለጀርመን የእግር ኳስ ጨዋታ ማለት #አገር ማለት ነው። #ትውልድ ማለት ነው። እንደ አስተናጋጅ አገር ጀርመኖች ቀጥለው ቢሆን የጨዋታው አትሞስፌር ልዩ ይሆን ነበር። ለመጨረሻ ጊዜ ሊሆን ይችላል ብዬ የማስበው የዕውቁ ተጫዋቻቸው የቶኒ ስንብትም ቢያንስ ለፋይናል ደርሰው ቢሆን ምኞቴ ነበር። ዕውነት ለመናገር ልቤ ተንጠልጥሎ ነበር የተከታተልኩት። መራር ስንብት። ለፔናሊቲ ደርሰው ቢሆን ምን አልባት ሊቀናቸው ይችል ነበር።    በጨዋታው ላይ ከፍ ያለ ተጽዕኖም ያሳድራል። ጀርመኖች ብዙ ተፋልመዋል። የመጀመሪያ ጎል ስትገባባቸው ደነገጥኩ። ጥንካሬያቸው በቀጣይነት አሳሳቢ ስለሆነ በባህሬው። የሆነ ሆኖ የጀርመን ብሄራዊ ቡድን የሌለበት ጨዋታ ቀዝቀዝም፤ ለብም ብሎ በአገረ ጀርመን ይቀጥላል። ፖርቸጋልም ለፔፔ የመጨረሻው ይመስለኛል ለአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ። መራራ ስንብት።    ለሲዊዝ ጨዋታው #ተራዝሞ #ከፔናሊቲ ከተደረስ #ስጋቴ ከፍ ያለ ነው። እግዚአብሄር አምልክ ስንት...