መልካም ዕድል #ለእምዬ ለሲዊዝ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን። #የሰላም #ንግሥቷ። #Viel Erfolg.

 

መልካም ዕድል #ለእምዬ ለሲዊዝ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን። #Viel Erfolg.
 
"የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፥
እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።"
 (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)
 
 No photo description available.May be an image of 1 person, playing football and playing soccerMay be an image of 3 people and textMay be an image of hospital and textMay be an image of 1 person, playing football and playing soccer
 
 
ዕለተ ቅዳሜ ልክ 18.00 ሰዓት #የእምዬ ሲዊዝ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከአቻው የእንግሊዙ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን ጋር በጀርመን በዶርትሙንድ ሲቲዲዮም ወሳኝ ግጥሚያ አላቸው።
 
ትናንት ባዬነው ጨዋታ ስፔን ጀርመንን በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ፤ ፈረንሳይ ፖርቹጋልን በተጨማሪ ጊዜ፤ በዛም መሸናነፍ አልችል ብለው በፔናሊቲ ዳኝነት ፈረንሳይ ለቀጣዩ ፍልሚያ እንደ ስፔን አልፈዋል። 
 
ለጀርመን የእግር ኳስ ጨዋታ ማለት #አገር ማለት ነው። #ትውልድ ማለት ነው። እንደ አስተናጋጅ አገር ጀርመኖች ቀጥለው ቢሆን የጨዋታው አትሞስፌር ልዩ ይሆን ነበር። ለመጨረሻ ጊዜ ሊሆን ይችላል ብዬ የማስበው የዕውቁ ተጫዋቻቸው የቶኒ ስንብትም ቢያንስ ለፋይናል ደርሰው ቢሆን ምኞቴ ነበር። ዕውነት ለመናገር ልቤ ተንጠልጥሎ ነበር የተከታተልኩት። መራር ስንብት። ለፔናሊቲ ደርሰው ቢሆን ምን አልባት ሊቀናቸው ይችል ነበር። 
 
በጨዋታው ላይ ከፍ ያለ ተጽዕኖም ያሳድራል። ጀርመኖች ብዙ ተፋልመዋል። የመጀመሪያ ጎል ስትገባባቸው ደነገጥኩ። ጥንካሬያቸው በቀጣይነት አሳሳቢ ስለሆነ በባህሬው። የሆነ ሆኖ የጀርመን ብሄራዊ ቡድን የሌለበት ጨዋታ ቀዝቀዝም፤ ለብም ብሎ በአገረ ጀርመን ይቀጥላል። ፖርቸጋልም ለፔፔ የመጨረሻው ይመስለኛል ለአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ። መራራ ስንብት። 
 
ለሲዊዝ ጨዋታው #ተራዝሞ #ከፔናሊቲ ከተደረስ #ስጋቴ ከፍ ያለ ነው። እግዚአብሄር አምልክ ስንት ጊዜ ጠብቃ ያገኘችው የቅድስት ሲዊዝሻ ዕድል ተሳክቶ ሳቋን አይ ዘንድ እመኛለሁ። ሲዊዝ ያላችሁ የኤክስፐርቶችን ትንተና መርምሩት። መቼ ይህን ዕድል እምዬ ሲዊዝ አግኝታ እንደ ነበር።
 
በፈለገ ሁኔታ፤ የፈለገ ነገር ቢፈጠር ግን የሲዊዘርላንድ የእግር ኳስ ቲም ያሳዬው ጽናት፤ ያሳዬው ሁለገብ ተሳትፎ፤ ብቁነት በቂ ስለሆነ የሚያስከፋ ነገር አይኖረውም ብዬ አስባለሁ። Egal was passiert sie ist klasse. Punkt. የሆነ ሆኖ ቸር ተመኝ ቸር ታገኝ ነውና በሲዊዝ ድል ከተጠናቀቀ እምዬ ሲዊዝ አዲስ የታሪክ ድርሳን ይኖራታል። ለነገሩ ጣሊያንን ከሰሞኑ ሸኝታለች።
 
በደቡብ አፍሪካው የዓለም ዋንጫም፤ ለዋንጫ የበቃውን ስፔንን እምዬ ሲዊዝ #አሸንፋ ነበር። #የተመሰጠረ #ብቃት! ከጀርመን ጋር በነበረው የምድብ #A ጨዋታም በበዛ ብቃት ነበር የተጫወቱት። ሙሉ 90 ደቂቃው በእምዬ ሲዊዝ መሪነት ነበር። ጀርመኖች ለአቻነት የበቁት #በተጨማሪ #ጊዜ ነበር። የሆነ ሆኖ ከምድብ A የቀረችው ብቸኛዋ አገር እምዬ ሲዊዝሻ ናት።
 
እምዬ ሲዊዝ የጀርመን፤ የፈረንሳይ፤ የጣሊያን እና የሮምሽ ቋንቋ ተናጋሪወች ፀሎት እና ድጋፍም አይለያትም ብዬ አስባለሁ። #ህብራዊነቷ ለዓለም ሞዴል ነው #የሰላም #ንግሥቷ። 
 
መልካም ዕድል ለጭምቷ በዕቴ ለእምዬ ለሲዊዝሻ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
06/07/2024
#ዲል ያለ #ድል ለእምዬ ሲዊዝሻ። አሜን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።