ልጥፎች

ከዲሴምበር 17, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ክርስትና እና እስልምና ዓይናችሁን አደራ ጠብቁ!

ምስል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት +  የኢትዮጵያ እስልምና ሃይማኖት  ዓይናቸውን የመጠበቅ አምላካዊ  ግዴታ አለባቸው። ክርስትና ማለት  ሆነ እስልምና መታመን ነው። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል“ መጽሐፈ ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute ©Selassie 17.12.2081 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ ምሩቁ ይስህቅ! ·        ጠብታ ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ የማካብራችሁ እና የምናፍቃችሁ የአገሬ ልጆች እንዴት አላችሁልኝ። አውሮፓ ስሜን አሜሪካ ያላችሁ እንዴት ይዟችኋዋል ብርዱ? ዘንድሮ በጋውም እረጅም ነበር፤ ክረምቱም ቀለል ያለ ነው እዚህ እንደ ሲዊዝ ከሆነ። ለነገሩ ገዳማዊቷ አገር ሲዊዘርላንድ በጋውም ሆነ ክረምቱ በልክ ነው፤ እጁን ታጥቦ የፈጠራት ብጽዕት ናት እና። በረድ የሚጥለው ተራራ ላይ ነው።  ሙቀትም በበጋ ምን አልባት ቢበዛ እስከ 5 ቀን ነው ከፍ ያለ የሙቀት ደረጃ የአዬር ንብረት ያለው እንጂ ቀሪው ለጤና ተመጣጥኖ እንደሚሠራ ምቹ ምጥን ነው። የገዳማዊት አገር ነገር እንዲህ ነው እንደ ህዝቧ ሁሉም በደንበር ነው፤ በልክ  …. የታደለች! ·        ዓይን። ብሩካን! ዓይን ፖስተኛ ነው። ዓይንም ብርሃን ነው። ዓይንም የምርምር ተቋም ነው ለአካላት ሁሉ። ዓይን በጥበብ ውስጥ የተቀመረ ተፈጥሮ ነው ያለው። ይህን ስል ግን ልበ ብርሃን የሆኑ ሉላዊ ዜጎችም እንዳሉን ነው እማስበው። የእነሱ አፈጣጠር ደግሞ ከማስተዋል ጋር ብልህነቱምን አርቅቆ ነው የፈጠራቸው። ልዩም ጸጋም ክህሎትም ነው ያላቸው። የሆነ ሆኖ ይህ ዘመን ለሁሉቱም ሃይማኖቶች ለክርስት እና እና ለእስልምና ዓይናችን ሊሉት የሚገባ ዘመ