ልጥፎች

ከዲሴምበር 14, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ስለምን ወጣቶች ቅንነትን ይፈሩታል?

ምስል
ወጣቶች ቅንነትን መፍራት የለባቸውም። የፃድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል።  አንደበቱም ፍርድ ይናገራል። መዝሙረ ዳዊት ፴፮ ቁጥር፮ ከሥርጉተ© ሥላሴ(Sergute©Selassie) ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።   ·        ስለምን ወጣቶች ቅንነትን ይፈሩታል?   እንዴት ናችሁ የጸሑፌ መደበኛ ታዳማዎች አክባሪዎቼ? ደህና ናችሁ ወይ?   ወጣቶች ስለምን ቅንነትን እንደሚፈሩት አይገባኝም። ምክንያቱ ወጣቶች ተስፋቸውን፤ ራዕያቸውን፤ ትልማቸውን፤ ግባቸውን ማግኘት የሚችሉ ቅን ከሆኑ ብቻ ነው። ምክንያቱም ልዑል እግዚአብሄር / አላህ ከቅኖች መንፈስ ጋር ስለማይለይ አቅም እና ሃይል ይለግሳቸዋል እና።   ብዙ ሰዎች በመማር ውስጥ፤ በዲታነት ውስጥ፤ በውበት ማሪኪነት ልክ ስኬት ይገኛል ብለው ያስባሉ። ቅንነት ከሌላ ላላቸው ሃብት ሁሉ ተጠቃሚ የመሆን አቅም ያንሳቸዋል። ስለምን? ቅንነት በጎደለ ቁጥር ራስን ከተፈጥሮ ስለሚቀንስ። ቅነንት ድርቅ በመታው ቁጥር ራስን ከተፈጥሮ ስለሚያጓድል የውስጥ ሰላም ይራቆታል።   ቅንነት የሌለው ሰው የህሊና ሰላም የለውም። ኑሮው ሁሉ ያደባ እና አሉታዊነትን የተጎናጸፈ ነው የሚሆነው። አሉታ ደግሞ ግራ ነው። ግራ ደግሞ ራስነትን ያሳጣል። ኪሳራ።   ቅንነት ከሁሉ በላይ ተጠቃሚ የሚያደርገው የሰውን አንጎል ነው። የሰው አንጎል ቅንነት ካላው ሃሳብ ለማፍለቅ፤ ለመፍጠር፤ ለመመራመር፤ አርቆ ለማሰብ፤ ምናባዊ የሆኑ ትልሞችን ለመተንበይ ይቻለዋል።   ለቅኖች ነገ ብሩካቸው ነው። ቅኖች ነገሮችን በቅንነት ስለሚዩት ለነርባቸው ሃኪሞች ናቸው። ለጨጓራቸው ዳሳሾች ናቸው...

የአዳማ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ እና ዕድማታው።

ምስል
ማሰብ። „ቆይቼ እግዚአብሄርን ደጅ ጠናሁት፤ እርሱም ዘንበል አለልኝ፤ጩኸቴንም ሰማኝ።“ መዝሙር ፵ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ© ሥላሴ Seregute© Selassie 14.12.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።                                ህዝባችን ኑሮው ይህ ነው። ·        መነሻዬ ይሄ ነው። https://www.youtube.com/watch?v=A3yNyvpAVh0 #EBC   ለሁለት ሳምንታት በትምህርት ገበታቸው ላይ ያልተገኙት   የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተገባልን   ቃል አልተከበረም አሉ፡፡   እጅግ የሚገርሙ ነገሮች በዬ ዕለቱ ይደመጣሉ። የአዳማ ዩንቨርስቲ የሳይንስ እና የቴክኖሊጂ ተማሪዎች ለሁለት ሳምንት የዘለቀ የትምህርት ማቆም አድማ መትተዋል። ጥያቄቸውን አዳመጥኩት። ግን እዬተማሩ ማቅረብ  አይቻላቸውም ነበርን? ደግሞስ አሁን ኢትዮጵያ በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ ሆና ምን አለ ከችግሯ ጎን ቢቆሙ እንደ እጩ ሊቅነት።    ከቶ እነዚህ ምንዱባን ምን ይበሉ? https://www.youtube.com/watch?v=kuGKmclKGT8&t=207s የፍትህ ሰቆቃ - በኢትዮጵያ ሲፈጸሙ በነበሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ ተሰራ ዶክመንተሪ።   ለኢትዮጵውያን ልብ ቢሰራልን ኖሮ አሁን ባለው የአብይ ሌጋሲ ላይ  ምንም ጫና ባለመፍጠር ያ የጭራቅ ዘመን እንዳይመለስ ...

እኮ! መቼ ልምጣ እና ልይሽ፤ ዕንባዬን እንድታብሽ።

ምስል
„ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን የሚጠቅም አይደለም፤ ሁሉ ተፈቅዶልኛል ነገር ግን ሁሉ የሚያንጽ አይደለም።“ ( ወደ ቆረንቶስ ፩ኛቱ ምዕራፍ ፲ ከቁጥር   ፳፫ እስከ ፳፬ ) ከሥርጉተ© ሥላሴ (Sergute©Selassie) 26.11.2016  ( ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ ) ·         የ ኔዎቹ እስቲ ለህትምት ከበቃው።                                                                              መቼ መጥቼ ልይሽ?                                         ...