ስለምን ወጣቶች ቅንነትን ይፈሩታል?

ወጣቶች ቅንነትን

መፍራት የለባቸውም።

የፃድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል።

 አንደበቱም ፍርድ ይናገራል።

መዝሙረ ዳዊት ፴፮ ቁጥር፮

ከሥርጉተ© ሥላሴ(Sergute©Selassie)

ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።



 

·       ስለምን ወጣቶች ቅንነትን ይፈሩታል?

 

እንዴት ናችሁ የጸሑፌ መደበኛ ታዳማዎች አክባሪዎቼ?

ደህና ናችሁ ወይ?

 

ወጣቶች ስለምን ቅንነትን እንደሚፈሩት አይገባኝም። ምክንያቱ ወጣቶች ተስፋቸውን፤ ራዕያቸውን፤ ትልማቸውን፤ ግባቸውን ማግኘት የሚችሉ ቅን ከሆኑ ብቻ ነው። ምክንያቱም ልዑል እግዚአብሄር / አላህ ከቅኖች መንፈስ ጋር ስለማይለይ አቅም እና ሃይል ይለግሳቸዋል እና።

 

ብዙ ሰዎች በመማር ውስጥ፤ በዲታነት ውስጥ፤ በውበት ማሪኪነት ልክ ስኬት ይገኛል ብለው ያስባሉ። ቅንነት ከሌላ ላላቸው ሃብት ሁሉ ተጠቃሚ የመሆን አቅም ያንሳቸዋል። ስለምን? ቅንነት በጎደለ ቁጥር ራስን ከተፈጥሮ ስለሚቀንስ። ቅነንት ድርቅ በመታው ቁጥር ራስን ከተፈጥሮ ስለሚያጓድል የውስጥ ሰላም ይራቆታል።

 

ቅንነት የሌለው ሰው የህሊና ሰላም የለውም። ኑሮው ሁሉ ያደባ እና አሉታዊነትን የተጎናጸፈ ነው የሚሆነው። አሉታ ደግሞ ግራ ነው። ግራ ደግሞ ራስነትን ያሳጣል። ኪሳራ።

 

ቅንነት ከሁሉ በላይ ተጠቃሚ የሚያደርገው የሰውን አንጎል ነው። የሰው አንጎል ቅንነት ካላው ሃሳብ ለማፍለቅ፤ ለመፍጠር፤ ለመመራመር፤ አርቆ ለማሰብ፤ ምናባዊ የሆኑ ትልሞችን ለመተንበይ ይቻለዋል።

 

ለቅኖች ነገ ብሩካቸው ነው። ቅኖች ነገሮችን በቅንነት ስለሚዩት ለነርባቸው ሃኪሞች ናቸው። ለጨጓራቸው ዳሳሾች ናቸው። ለሚቀርቧቸው ትምህርት ቤቶች ናቸው። ቅኖች ትርፍ ነው መንገዳቸው ሁሉ። ስኬታቸውም በመዳፋቸው ነው። ስኬት ሲባል ከፍቅረ ንዋይ አገር ሳይሆን ከመንፈስ ርጋታ ስክነት የሚገኘው እርካታ ማለት ነው። ቅኖች የአስተሳሰብ ድሆች አይደሉም። አስፍተው ነገሮችን ስለሚመለከቱ።  

 

የቅኖች ትርፍነቱ የቁስ ላይሆን ይችላል። መቼም ከፍቅረ ንዋይ ዲታነት የህሊና ዲታነት ማለትም የአስተሳሰብ ድህንት የሌለበት መሆን ይብልጣል። ሰው የሚለካው በሚያስበው ልኩ ነውና። ሰው በሚያሰበው ልኩ ለመለካት ቀዳሚ ጉዳዩ ለሰውነቱ ለህሊናው ለነርቡ ለደሙ ቅን መሆን ሲችል ብቻ ነው።

 

ቅነንት ለራስም ቅን መሆንን ይጠይቃል። ለራስ ቅን ከተሆነ ለሌላው ለመስጥት ስስት አይኖርም። ለራሳቸው ነፃ ያልሆኑ ሰዎች ናቸው ነፃነት ለመስጠት ስስታም የሚሆኑት። ለራሳቸው ዴሞክራት ያልሆኑ ሰዎችም ለሌሎች ዴሞክራት ለመሆን ይቸገራሉ። ስለዚህም ተጫኝ ይሆናል። ተጫኝነት ስንቅ ቢሆን እንጂ ግብ አይሆንም። አያበረከትም እንደማለት።

 

ለሰው ልጅ ህሊና መስኖው ቅንነት ነው። ቅንነት ነው የመንገድ መሪ መሃንዲሱ። የመንፈስም ዲዛይነር። ቅንነት አይከፈልበትም፤ ቅንነት ጊዜ አይጠይቅም፤ ቅንነት ጉቦ ደጅ ጥናት ምልጃ አያስፈልገውም።

 

ቅነንት በእጅ በመዳፍ ያለ ጉዳይ ነው። ቅን ለመሆን ቅናትን ማሰወገድ ያስፈልጋል። ቅን ለመሆን የሰው የሆነ ሁሉ አለመመኝት ይጠይቃል። ቅን መሆን ማለት ነገሮችን አስፍተው በአስተውሎት ማዬት መቻል ማለት ነው። ቅን መሆን ብቻ ነው ነገንም ማሳመር የሚችለው። ቅኖች ታጋሾች ናቸው። ትእግስታቸው ካሰቡት ያደርሳቸዋል።  

 

ቅን ማህበረሰብ መፍጠር የሚቻለው የዛሬዎቹ ወጣቶች ቅንነትን ሳይሸሹ መድፈር ሲችሉ ብቻ ነው። ለዛ ደግሞ አዎንታዊ መሆን መቻል ነው። አዎንታዊነት በራሱ ሜድቴሽን ነው። የደም ዝውውርን ያሳካል። የእውነት ነው የምላችሁ። አብሶ ወጣቶች ቅን ትውልድን ለማብቀል፤ ኮትኩቶ ለማሳደግ ከራሳቸው መጀመር አለባቸው። መቼ ሲባል? ዛሬ?

 

ምክንያቱም ዛሬ የእነሱን የቤት ሥራ ሊሠሩ የተሰናዱ ፈርጦች ስላሉ፤ እነሱ የጎደለውን ለመሙላት መትጋት ይጠበቅናቸዋል። እነሱም የነገ ባላደራ ስለሆኑ ለተተኪያቸው በዘመናቸው ቅንነትን ለማወረስ መትጋት ይጠበቅባቸዋል።

 

ወጣቶች ዛሬም የእነሱ ነው፤ ነገም የእነሱ ይሆናል፤ የነገ ወዲያም እርሾዎች ናቸው። እርሿቸው ግን በቅንነት ላይ የተገነባ ሞራላዊ ሰብዕና ሊሆን ይገባል። ቅን ከሆኑ ብቻ ነው ተስፋቸው የማይጠነዝለው።

 

የወጣቶች ታላቁ ድርሻ አገር ተረካቢነት ብቻ ሳይሆን አስረካቢነትም ነው። ለዚህ ታላቅ አገራዊ ሃላፊነት ደግሞ ቅንነት ነው የልቦና ድንጋጌ መጠሐፉ። ቅኖች አትራፊዎች ናቸው። የውስጥ ሰላማቸውን ለበላሃሰብ አሳልፍው አይሰጡምና። ሰላም ደግሞ መኖር ነው። መኖር ደግሞ ትውልድ ነው። ትውልድ ደግሞ አገር ነው። አገር ደግሞ አህጉር ነው። አህጉር ደግሞ አለም ናት።

 

ወጣቶች ዛሬ ባለው ሉላዊ ዘመን ከደጃቸው ብቻ ሳይሆን ሰፊዋ ዓለም  ከእነሱ የምትሻው የህሊና ሰብል አለ። ለዚህ ሃላፊነት መቅኖው ደግሞ ቅንነት ነው። ወጣቶች ሆይ እባካችሁን ቅን ሁኑ!


ወጣቶች ይህን ከታች የምለጠፈውን ሊንክ እንደ አንድ የትምህርት ዘርፍ ጊዜ ወስዳችሁ ደጋግማችሁ ልታደምጡት እና ልተወያዩበት ይገባል። ዛሬ ለወጣቶች ሮል ሞዴል መሪ አላችሁ፤ እድለኛም ናቸሁ። ዩንቨርስቲዎች፤ የትምህርት ተቋማትም በእረፍት ጊዜ በድምጽ ማጉያ ተማሪዎች እንዲያዳምጡት ቢደረግ፤ በዬዶርማቸው ድምጽ ማጉያ ተዘጋጅቶ ደጋግመው እንዲያስቡበት ቢደረግ መልካም ነው።

 

ዩንቨርስቲዎች ልብ ቢኖራቸው በእያንዳንዱ ንግግር ላይ ፓናል ዲሰከሽን፤ ሙግት ፍጭት ቢካሄድበት ትውልድን በቅንንት ማነጽ ይቻላል። ይህ ንግግር በሙሉ ሸፍጥ የሌለበት፤ አሉታዊ ኢጎ ዝር ያላለበት፤ ድንግል፤ በታማኝነት ቅንነት ከነተፈጥሮው የበቀለበት፤ የጸደቀበት እና ያሰበለበትም ነው።

 

ማግስትን በቅጡ ያጠና መሃንዲስም ነው። አይሰለችም። እኔ አመቱን ሙሉ ነው ያደማጥኩት። ቅን የሆነ የፖለቲካ መሪ ጋር አላዛሯ ኢትዮጵያ ስትገናኝም በዘማናችን ይህ እድል መቅድሙ ነው።

 

ቅንቱ ደግሞ ልዩ ነው። ችግርን ከውስጥ የማደመጥ፤ ለችግር መፍትሄ አምንጭነት ብቻ ሳይሆን ሃላፊነት መውሰድን፤ ለስኬቱም ለመትጋት መወሰንን አክሎም ነው። 


በዚህ ንግግር ውስጥ በ7 ወራት የጠ/ሚር አብይ አህመድ ትልም በከባድ በተደራጀ አፍራሽ ቡድን ጋር እዬታገሉ በ10 ዓመት የማይታሰቡ ውጤቶችን አስገኝተዋል። ይህ ስኬት፤ እቅም እና ጉልበት ቅን ስለሆኑ ፈጣሪም ስለደጋፋቸው፤ ጸሎትም ስለረዳቸው ነው። 


ስለዚህ ወጣቶች መቅናት ያላባችሁ ስለ ቅኖች ምህንድስናስ እና ስኬት እንጂ ስለሸረኞች አፍራሽነት መሆን አይኖርበትም። ቅነነት የአቅም የተስፋ ጥገት ነው - የማይነጥፍ። ወጣቶች በጎ ነገርን ለመቅሰም ስልቹ መሆን አይኖርባችሁም። ትምህርት ከዩንቨርስቲዎች ብቻ አይደለም የሚገኘው። ከንግግሮችም ጭምር ነው። ንግግር የምትማሩት አንድ የ እውቀት ዘርፍ ሲሆን ተስጥዖም ነው። 

 

https://www.youtube.com/watch?v=irRwk5vK7A8

Ethiopia - Dr Abiy ahmed Synergy "መደመር" እዉነት ሲገለጥ

https://www.youtube.com/watch?v=-71OEmwCtfs

Ethiopia - Dr Abiy ለታጠቁ ሐይሎች ያስተላለፉት ግልጽ መልዕክት

https://www.youtube.com/watch?v=Ikngk4u74j0

Ethiopia - Dr Abiy እንዴት ሰዉ 1% ልዩነት ይሰቃያል?!

https://www.youtube.com/watch?v=k07ZojV5DXg&t=23s

Ethiopia - ….ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች! ትለወጣለች!

https://www.youtube.com/watch?v=3xAtKoIPh6E&t=12s

እድልን በታማኝነት መጠቀም ያስፈልጋል!

https://www.youtube.com/watch?v=riMkG5bt6Ns&t=25s

Ethiopia - Dr Abiy ፈረንጆቹን አሸማቆ መለሳቸዉ!!

https://www.youtube.com/watch?v=94K3DGsxxqw&t=48s

Ethiopia - Dr abiy ሚኒስትር ከመሆንህ በላይ ሰዉ ነህ!

https://www.youtube.com/watch?v=7qxh5EwWBa8&t=33s

Ethiopia ታሪክን በሚገባ ያብራሩበት ሙሉ ቪዲዮ

https://www.youtube.com/watch?v=vu-kkIUohRw&t=74s

Ethiopia - Dr Abiy ኢትዮጵያን ማሸጋገር ይቻላል!

https://www.youtube.com/watch?v=D1ZtxHOmt_w&t=68s

Ethiopia - New Dr Abiy - አንድ ሰዉ ብቻዉን መለወጥ ይችላል!

https://www.youtube.com/watch?v=sokxTcjrpv8&t=647s

ልብ የሚነካ አስገራሚ ንግግር Dr abiy ahmed # mind set

https://www.youtube.com/watch?v=NHhWHrJOuHU&t=47s

Ethiopia Dr abiy የሰዉ ልጆች ልዩ ብቃት ክፍል ሁለት

https://www.youtube.com/watch?v=AHyuaT4mqz4&t=6s

Ethiopia Dr abiy የሰዉ ልጆች ልዩ ብቃት ክፍል አንድ

https://www.youtube.com/watch?v=CmZu-f10Z4A&t=45s

https://www.youtube.com/watch?v=cYNQ6k4gLyU&t=64s

https://www.youtube.com/watch?v=SB8R7BxFdTI&t=11s

ኢትዮጵያ - ሚኒስትሩ በንባብ ለሕይወት ላይ / Ethiopian Minister about Reading and Life

 

 

ወጣትነት ከ አዎንታዊነት ጋር ቤተኛ መሆንን ይጣይቃል!

ወጣት አብነቱ ርህርህና ሊሆን ይገባል!

 

የኔዎቹ ኑሩልኝ።


መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።