እኮ! መቼ ልምጣ እና ልይሽ፤ ዕንባዬን እንድታብሽ።
„ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን የሚጠቅም አይደለም፤
ሁሉ ተፈቅዶልኛል ነገር ግን ሁሉ የሚያንጽ አይደለም።“
( ወደ ቆረንቶስ ፩ኛቱ ምዕራፍ ፲ ከቁጥር ፳፫ እስከ ፳፬)
ከሥርጉተ© ሥላሴ (Sergute©Selassie)
26.11.2016 (ሲዊዘርላንድ- ዙሪክ)
·
የኔዎቹ እስቲ
ለህትምት ከበቃው።
መቼ መጥቼ ልይሽ?
እንባዬን እንድታብሽ
በእምነቱ እንድትዳስሽ።
ናፍቆኛልና እጅሽ
የበላሁበት ሞሰብሽ
ማን እንደ አንቺ ወደር የለሽ።
የፍቅር እመቤት ልዕልት ነሽ
የሉሲ
እናት ውብ ነሸ፤
የአዶሊስ ፍቅርት መኩሪያችን
ነሽ።
እመ-ብዙኃን ፍጽምት ቅድስት
የፍጥረት ግርማ ማገስ
ቀደምት!
እኮ!
መቼ ልምጣና ልይሽ?
በእምነቱ እንደትደባብሽ
ለርሃቤ እንድትለግሺ
ናፍቆቴን እንድታጎርሺ
የልቤን እንድታደርሺ
ስስቴን እንድታርሺ።
እኮ! መቼ
ልምጣና ልይሽ?
የናፍቆቴን
እንድታርሺ
እንባዬን
እንድታብሺ
በእምነቱ
እንድትደባብሺ!
ተጣፈ … ጳጉሜ 5 ቀን 2003 ዓ.ም ሲዊዘርላንድ-ቪንተርቱር
የኔወቹ ኑሩልኝ ማለፊያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ