ልጥፎች

ከኦክቶበር 2, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ስለትውልድ፤ ለትውልድ፤ የትውልድ የሚሆን ሰብዕና የአጽናኝነት ዋዜማ ለእማማ #ስለመናፈቅ።

ምስል
  ስለትውልድ፤ ለትውልድ፤ የትውልድ የሚሆን ሰብዕና የአጽናኝነት ዋዜማ ለእማማ #ስለመናፈቅ ።   " ነፍሰ ጡር እናት፤ ፬ ሰላማዊ ሰወች?" መራር ስንብትን አስመልክቶ ቢቢሲ ዘግቧል።    "አቤቱ እንደ ቸርነትህ ብዛት ማረኝ ይቅር በለኝ፦" አሜን።   በወርኃ መስከረም ዓዲስ ዓመት፤ ዓዲስ ዘመን አዲስ ተስፋ ይጠበቃል። ከበዓላቱ ጋር የፈጣሪ ጥሪ ቢኖር ቢከብድም ይቻላል እንደምንም። በአደጋ፤ በጦርነት ሲሆን ግን እራስን ይመረምራል። እራስን ይፈታትሻል። በየዘመኑ ስለትውልድ፤ የትውልድ፤ ለትውልድ የሚሆኑ ተግባራት ቢከወኑም፤ ስንቃቸው አመድ፤ ለቅሶ #ራሮት ከሆነ ድካሙ፤ ብድሩ፤ ወለዱ ለምን እና ለማን ያሰኛል።   በቤተክርስትያን ግንባታ ላይ እያሉ እንደወጡ የቀሩት፤ በጦርነት ምክንያት በጤና ክሊንክ ላይ የተሰው ንጹኃን፤ " ሴቶች ሱሪ አትለብሱም" ተብለው የተፈጠረ ግጭት እና ጉዳት፤ በሰማይም በምድርም በአገረ ኢትዮጵያ ሆነ በዓለም ደረጃ የሚወርደው የቀልሃ መርዝ እና ማግስት ሲታሰቡ ተስፋን በተፈጠረበት ምርቃት ልክ #ተስፋነት ለመጠበቅ ይከብዳል።    የሰው ልጅ የተፈጥሮ አደጋን ለመቋቋም፥ የአየር ብክለት ላይ ተግቶ ሊሠራ ይገባው ነበር። ሚሳኤል፤ ቦንብ፤ ሮኬት ወዘተ ከማምረት ይልቅ። በሌላ በኩል እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ደሃ አገራት በረጅም ጊዜ ብድር ይሁን፤ በዕዳ፤ በእርዳታም ቢሆን የተሰሩ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን እሱ እራሱ ጥበቃ ማድረግ የማይችል ከሆነ፤ እንዲሁም ለአገልግሎት ተጠቀማዊም የደህንነት ዋስትና መስጠት ካልቻለ የአገር መሪነቱ ድርሻ፤ ደረጃን ይፈትነዋል #እርሱ #በእራሱ ።    በህክምና ተቋማት፤ በትምህርት ቤቶች፤ በሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚደርሱ የድሮን ይሁን የከባድ...