ልጥፎች

ከዲሴምበር 11, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የፖለቲካ እስረኞች ወገኖቼ #አዋን ይፈቱልኝ፤ በእስር ቤት እያሉ ወገኖቼ ጤናቸው ይጠበቅልኝ እንጂ አይደለም በአክብሮት እና በትህትና #ተንበርክኬ ብለምን የሚቀርብኝ ቅርጥፍጣፊ ክብር የለም።

ምስል
  የፖለቲካ እስረኞች ወገኖቼ #አዋን ይፈቱልኝ፤ በእስር ቤት እያሉ ወገኖቼ ጤናቸው ይጠበቅልኝ እንጂ አይደለም በአክብሮት እና በትህትና #ተንበርክኬ ብለምን የሚቀርብኝ ቅርጥፍጣፊ ክብር የለም።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።    #ምዕራፍ ፲፯      እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ገና በጋሜ እና ታሬዬ ዘመን ጀምሮ ተከብሬ ነበር በፖለቲካ ተግባር ተኮትኩቼ ያደግኩት። እንደዛሬው ማህበራዊ ሚዲያ ቢኖር ከቶፕ ሁለገብ፤ ተከባሪወች እና ተወዳጆች መሃል የመሆን ዕድሉ የነበረኝ ሴት እሆን በነበረ።    ለእኔ የሙያ ብቃት፤ የሥራ ትጋት እና ቅልጥፍና ያግዛሉ በተባሉ መድረኮች ሁሉ እማርበት ዘንድ ሙሉ የዕድል በር የተከፈተልኝ ወጣት ነበርኩኝ። በእኔ ዘመን ዕንቁ ሴት ወጣቶች በርከት ያልን ነበርን። ከሁሉም ግን ለእኔ ይሰጥ የነበረው አትኩሮት እና፤ በእኔ ይጣል የነበረው ተስፋ ሰፊ ነበር።    ጎንደር ክፍለ አገር ብቻ ሳይሆን፤ ተወክዬ በሄድኩበት ቦታ ሁሉ ነበር። አርሲ ስመደብ ጢቾ በሠራሁ በሦስት ወሬ ነበር ለክፍለ አገር ኃላፊነት ሪኮመንድ የተደረግኩት። ተሰድጄም የሥራ ኢባሎሽኔ #A + ነው። #አገሬ #ሥራ ነውና። ያውም በበቃ ዲስፕሊን እና በትጋት። ሁሉንም የክብር አይነት አውቀዋለሁኝ። ለዚህም ነው ለውዳሴ፤ የማይደንቀኝ የማልንደፋደፈው ለጭብጨባ ሆነ ተከታይ ለማበራከት። በሌላ በኩል በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ብርቱ ናቸው ብዬ ለማምናቸው በገፍ የሰብዕና ግንባታ፤ ምስክርነት በቅንነት የመስጠት አቅሜም ምንጩ ይኽው ነው። በብዙ ሰው ድጋፍ ላይ ቁብ የለ ሰብዕና ስለአንድ ሰው ሰብዕና የመመስከር #አቅም የለውም። ለምን? ከእነሱ የተሻለ ሰብዕና እንዲወጣ ስለማይፈለግ። ...

#አደብ #ያጣ #ፍላጎት፤ #አደብ #ያጣ #ውድቀት #ያመጣል።

ምስል
  #አደብ #ያጣ #ፍላጎት ፤ #አደብ #ያጣ #ውድቀት #ያመጣል ። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #ምዕራፍ ፲፯ #ለምን ? 1) ስኬት በአደብ ያጣ ፍላጎት ስለማይገኝ። 2) አደብ ያጣ ፍላጎት ቁንጥንጥ ነው። 3) አደብ ያጣ ፍላጎት ስርክራኪ ይበዛዋል። 4) አደብ ያጣ ፍላጎት ተናዳፊ ስለሆነ። 5) አደብ ያጣ ፍላጎት የውስጥ ሰላሙ የታወከ በመሆኑ። 6) የመነሻ ገፊ ፍላጎቱ የራሱ አቅም ሳይሆን የጥገኛ አቅም ተሰላቢ ስለሚሆን። 7) አደብ ያጣ ፍልጎት ጎርፍ ይበዛበታል።   ስምንት) አደብ ያጣ ፍላጎት በሦስት ወር የሰው ልጅ ጽንስ ልጅ ሆኖ እንደሚወለድ ነው የሚያስበው። ኢ ተፈጥሯዊ ነው። ሁሉም ነገር የራሱ ስበታዊ፤ ስክነታዊ ሂደት ይጠይቃል። በአገራችን ባህልም "የእነ ተሎ ተሎ ቤት ግድጌዳው ሰንበሌጥ።" 9) አደብ ያጣ ፍላጎት ውጥኑ ቀን ቢወጣለት እንኳን ዕድሉን ለማስቀጠል አደብ አይኖረውም። መነሻው ሶርሱ አደብ የለሽ ነውና። 10) አደብ ያጣ ፍላጎት አድራጊውም፤ ተደራጊውም ስክነት ከአጣ ሰብና ስለሚነሳ ያረገረገ ስለሚሆን። አንድ ፍላጎት #ያረገረገ ከሆነ ደግሞ የተነሳለትን ፍላጎት አጽንቶ ለማስቀጠል አቅም ያንሰዋል። የትኛውም የአቅም ዓይነት #በጀት ነው። የመንፈስ ይሁን የልምድ፤ የልምድ ይሁን የክህሎት፤ የክህሎት ይሁን የመሰጠት፤ የመሰጠት ይሁን የመንፈስ፤ የመንፈስ ይሁን የመዋዕለ ንዋይ አቅም በጀት ነው። የሂሳብ ሥራ ይጠይቃል። ለዚህ ዕውቅና መስጠት፤ አቅምን ማሰባሰብ፤ አቅምን ማደራጀት፤ አቅምን መርቶ ለስኬት ለማብቃት አደብ ወሳኝ ጉዳይ ነው። #ለምን ያረገርጋል አደብ የለሽ ፍላጎት? #ተርገብጋቢ ስለሚሆን። ገፊው ኃይል ያልተረጋጋ ስሜት ሊሆን ስለሚችል፤ ተርገብጋቢ ፍላጎትን ይዞ የግል ህይወትን፤ ማህ...