ልጥፎች

ከሜይ 8, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ዓውሏዊ

 ዓውሏዊ #ተደባዳቢ የሃሳብ ገጠመኝን ማስከን ያስፈልጋል። ብስጩ የሆነ #ቦክሰኛ ንፋስም ይገጣማል፤ ወይንም መንፈሳዊ አቅምን ዘልቆ ገብቶ የሚሰባብር #ጦሮም ይገጥማል፤ ከዛ ጋር የማን ደም ፈሰሰ ከመባባል አረጋግቶ እንዲሰክን ማድረግ በእጅጉ ያስፈልጋል። ከአውሎውም ይሁን ከተበሳጬ የተለያዩ የንፋስ ዓይነቶች ጋር የማን ደም ፈሰሰ መባባል አይገባም። መሃል ላይ ያሉ፤ አክሰሱ ያላቸው #ታዳጊ ወጣቶች ይኖራሉ። እነሱ መንፈሳቸው #ለጋ ስለሆነ የሁለቱን ብስጩ የንፋስ ገጠመኝ የመሸከም አቅም ያንሳቸው እና የሥነ - ልቦና መሰበር ሊገጥማቸው ይችላል። ወጀብ ሲኖር ዝቅ ብሎ ማሳለፍ ፍርኃት ሳይሆን ብልህነት ነው። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። ሥርጉ 06/05/026

#ኢትዮጵያዊነት በራስ መተማመን ነው። (Confidence) (Vertraun) ነው። #ኢትዮጵያዊነት ተፈጥሮኛ ዲፕሎማትም ነው። እኛ ነው ልኩ መሆን ያቃተን።

  #ኢትዮጵያዊነት በራስ መተማመን ነው። (Confidence) (Vertraun) ነው። #ኢትዮጵያዊነት ተፈጥሮኛ ዲፕሎማትም ነው። እኛ ነው ልኩ መሆን ያቃተን።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፱።   ማህበረ ትህትና እንዴት አደራችሁ? እንደምን አረፈዳችሁ? እንዴትስ ዋላችሁ? ሁለት ተወራራሽ ዕርዕስ በአንድ ጭብጥ።   #ለአፍታ ።   እስቲ እኛን በእኛነት፤ እኔ በእኔነት፤ ሁላችንንም በሁለመናነት አመጣጥኖ፤ ቀምሮ፤ መጥኖ ያበጀንን ኢትዮጵያዊነትን መርምሩት። ቅጥልጥል፤ ቀንድ እና ልጥፍጥፍ የሚያሰኛቸውን ወገኖቼን አይመለከትም ጥያቄው። እንደ ሰው አስበን፤ ሰው ሆነን እንዘልቅ ዘንድ ውስጣችን እራስ እጉሩ ያሰበለ እንዲሆን ያደረገውን ጀግናውን ማንነት ከህሊናችን ሁነን እንሰበው።   #አይደፈሬው ደፋሪውን ያስተምራል።   ሁልጊዜ፤ ለምንግዜም ኢትዮጵያዊነት ኦክስጅናችሁ ሲሆን፤ የትኛውንም የፈተና ጋራ የመበገር አቅም ታገኛላችሁ። ኢትዮጵያዊነት የተደራጄ ተፈጥሯዊ የአቅም ልዩ መክሊት ነው። በኢትዮጵያዊነት ውስጥ የተመጣጠነ፤ ህብራዊ የሆነ ቀለማም መሳጭ ጸጋ አለ። ረቂቅ የሆነ በራስ የመተማመን አቅም አለ። ይህ አቅም ዩንቨርስቲ ገብታችሁ ብትማሩት የማታገኙት እንደ ላሊበላ አለት ጸንቶ የሚያጸና፤ ረግቶ የሚያረጋ #የመሰጠት ዲካ ነው።   #እርግጥ ነው ኢትዮጵያዊነት ተፈሪ ማንነት ነው። በልኩ መሆን ሲሳን ይፈሩታል። ይገባልም።    እርግጥ ነው ኢትዮጵያዊነት የሚቀናበት ማንነት ነው። ኢትዮጵያዊነት በጥበብ ውስጥ የሚዘልቅ የዊዝደም ጎዳና ነው። በኢትዮጵያዊነት ውስጥ መንፈስ ሲቀማጠል ይደለዋል። ለምን? እርግጠኛ የሚያደርግ ልዩ ኢነርጂ ስላለው። ኢትዮጵያዊነት ...

#ውሃዬ………

  #ውሃዬ ………   "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"   #ምዕራፍ ፲፱።   ኢትዮጵያ ~አገሬ ስስቴ ~~ናፍቆቴ የእኔ ~~~መጠሬዬ ክብሬ እና ~~~~ኩራቴ ንባቤ ~~~~~ትርጉሜ መንፈሴ ~~~~~~ሚስጥሬ ቀደምቷ ~~~~~ግርማዬ ጠይሟ ~~~~ዕንቁዬ ቡኔዋ ~~~~ቡናዬ እናት ~~~ሃይማኖቴ #ዓናቷ ~~ሐሤቴ ውድዬ ~ህብረቴ ቅኔዬ ~~ድጓዬ ኢትዮጵያ ~~~አገሬ የአፍሪካ ~~~~ፊደሌ መዝሙሬ ~~~~ሃናዬ ኃይሌና ~~~~መክሊቴ የእኔ ~~~~~ስጦታዬ ንባቤ ~~~ማዕረጌ ማርዳዬ ~ውበቴ ናርዶሴ ~~ሳባዬ መንዙማ ~~~ህብስቴ ሁሉዬ ~~~~~ዕውቀቴ አንች ነሽ ~~~~መንገዴ ፍልስፍና ~~~~ማዴ ሉሲዬ ~~~ዝናዬ ውዳሴ ~~ድርሳኔ ቅንዬ~ ´መቤቴ የተስፋ ~~መርከቤ የህቅታ ~~~ምግቤ የመኖር ~~~ቋንቋዬ ስዋሰው ~~~ውሃዬ ጠሐዬ ~~~~ብዙዬ ዘውዴ ~~~~~ጉልላቴ እቴጌ ~~~~ልዕልቴ ህብስቷ ~~~~ሥህኔ የእኔ ~~~የእኔ! የዕውነትም ~~ገዴ ለመርህም ~ቅርቤ የዕድምታ ~~ክቤ የአቋም ~~~ተቋሜ የሞራል ~~~~ዘቢቤ የጽናት ~~~~ግማዴ።   ፈጣሪዬ ሆይ! የማንነት ቀውስ ድርሽ እንዳይልብኝ በሙሉ የራስ መተማመን ሰብዕናዬን ገንብታ ያሳደገችኝ ልዕልት ኢትዮጵያን ጠብቅልኝ። አሜን።   ተፃፈ ~ ዛሬ 06/04/026 ሰዓት ~~ 08.20   ሥርጉተ©ሥላሴ። Sergute©Selassie. Selassie©Selassie.   #ኢትዮጵያዊነት #ከመፈጠሩ #በፊት #ፈተናን #አሸንፎ #የተፈጠረ #ሚስጢር ። See less