ዓውሏዊ

 ዓውሏዊ #ተደባዳቢ የሃሳብ ገጠመኝን ማስከን ያስፈልጋል። ብስጩ የሆነ #ቦክሰኛ ንፋስም ይገጣማል፤ ወይንም መንፈሳዊ አቅምን ዘልቆ ገብቶ የሚሰባብር #ጦሮም ይገጥማል፤ ከዛ ጋር የማን ደም ፈሰሰ ከመባባል አረጋግቶ እንዲሰክን ማድረግ በእጅጉ ያስፈልጋል። ከአውሎውም ይሁን ከተበሳጬ የተለያዩ የንፋስ ዓይነቶች ጋር የማን ደም ፈሰሰ መባባል አይገባም። መሃል ላይ ያሉ፤ አክሰሱ ያላቸው #ታዳጊ ወጣቶች ይኖራሉ። እነሱ መንፈሳቸው #ለጋ ስለሆነ የሁለቱን ብስጩ የንፋስ ገጠመኝ የመሸከም አቅም ያንሳቸው እና የሥነ - ልቦና መሰበር ሊገጥማቸው ይችላል። ወጀብ ሲኖር ዝቅ ብሎ ማሳለፍ ፍርኃት ሳይሆን ብልህነት ነው።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
ሥርጉ 06/05/026

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።