ልጥፎች

ከጃንዋሪ 22, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የኢትዮጵያ ፖለቲካ መጠጊያ እንጨትን #አዘውትሮ ባያማትር። ቅንነት ማኒፌስቶ ይሁን።

ምስል
·       የ ኢትዮጵያ ፖለቲካ መጠጊያ እንጨትን # አዘውትሮ ባያማትር። ·       ቅንነት ማኒፌስቶ ይሁን። # ምዕራፍ ፲፭ " የቤትህ ቅናት በላኝ። "   ጤና ይስጥልኝ ማህበረ አወንታውያን፦ እንዴት አደራችሁልኝ ? ደህና ናችሁ ? የኢትዮጵያፖለቲካ መጠጊያ # እንጨት አዘውትሮ ፍለጋ ከሚባዝን እራሱን # ችሎ መቆመን ቢለማመድ ጥሩ ይመስለኛል። እንጨት እኮ # ምስጥ ይበላዋል፤ # ያረጃል ፤ ይወድቃል ጠንካራ ወጀብ በናጠው ቁጥር። አውሎን መቋቋም ሲሳነውም ይገረደሳል። እሳት ከጎበኜውማ ይፈልሳልም። ፍልሰቱ ለዘር ሳይበቃ ይሆናል። ስለሆነም የኢትዮጵያ ፖለቲካ በአቅሙ ውስጥ ማሰብን፤ በአቅሙ ውስጥ መስከንን፤ በአቅሙ ልክ መመኜትን፤ በአቅሙ ልክ ማቀደን፤ በአቅሙ ልክ እራሱን ማደራጀትን፤ በአቅሙ ልክ እራሱን መምራትን ይለማመደው። አቅም ከኖረ አቅም ያለው ተጨማሪ # አቅም በራሱ ጊዜ ከች ይላል። አቅም # አጃቢ አይሻም፤ አቅም በፕሮቶኮል ከፍ እና ዝቅ # አይደናገጥም ። ምኞትም ጥሎ አይበረግግም። ማን ይሁን ማን ? መታመን ካለበት፤ ማመንም ካለበት በውስጡ ባለው ሊያዘው፤ ሊያደራጀው፤ ሊመራው በሚችለው እራሱ በገነባው የአቅም አስፈፃሚ # ተቋም ብቻ ሊሆን ይገባል። ይህን ያደረጉ አገሮች፤ ማህበረሰቦች፤ በግል ህይወትም ቀውጢው የዓለም ሆነ የብሄራዊው ውጥንቅጥ ጦሮ ይሁን ኩነት፤ መልካም ጠረን ያለው ንቅናቄ ቢከሰት ሁሉንም በመረጋጋት የማስተናገድ...