የፕሮፌስር መስፍን ወ/ማርያም የሀዘን መግለጫ ወደ ብሄራዊ ሃዘን ቀንነት ተቀዬረ።
እንኳን ደህና መጡልኝ። የፕሮፌስር መስፍን ወ/ማርያም የሀዘን መግለጫ ወደ ብሄራዊ ሃዘን ቀንነት ተቀዬረ። እንደ ሥርጉተ ኮቦታው ላይ አንድ ሐውልት ሊሠራበት የሚገባ ይመስለኛል። „አቤቱ እኔን ለማዳን ተመልክት አ ቬቱ እኔን ለመርዳት ፍጠን“ መዝሙር ፳፱ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergurt©Selassie 11.03.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። · ሀዘን ። የሰማይ ቁጣ ማዋራረጃ ለሆኑት ንጹሐን የዐለም ዜጎች ፈጣሪ አምላክ ነፍሳቸውን አርያም ገነት ያስገባልን። አሜን ! ከሞቱ አሟሟቱ የከፋ ስለሆነ እንደ ሰው ለሚያስብ ዜጋ ከእህል እውሃ፤ ከእንቅልፍም ጋር የሚያገኛኝ አይደለም። ነፍስ ሰማይ ላይ አመድ መሆን ? እጅግም ሰቅጣጭ፤ እጅግም አስደንጋጭ፤ እጅግም የሚያርድ መከራ ነው ሰው ለሆነ ሰው። በሰውነት ሞራል ውስጥ ላለ ፍጡር። ቀንበጥ ልቧ ስስ፤ መንፈሷ አዛኝ፤ ህሊናዋ ንጹህ የሆነች ብራና ናት። ስለዚህም የተሰማትን ድንግላዊ የውስጥ ሃዘን እዬገለጠች የዚህ ማዕት፤ የዚህ መከራ ምክንያት ወደ ሆነው የልብ ሽፍትነት አስመልክቶ ትንሽ ማለትን እንሆ ወደደች። ሌሊት እንቅልፍ መተኛት አልቻልኩም። ቀንም ትናንት ማስረሻ የሆነው ብዕሬ ብቻ ነበር። ዳርዳር ብልም ዛሬ ግን የሚሰማኝን እውነተኛ ስሜት ለመግለጽ ወሰንኩኝ። የዚህ መ ዓት መሰረት ቲም ለማ የተሰጠውን መታመን ጥሶ ማዕት አውርድ ብሎ መሬት በመደብደ...