የመጀመሪያው የሲወዘርላንድ ቶፕ ሞዴል ጠይም ዕንቁ ሴበር አሸነፈ!
የመጀመሪያው የሲወዘርላንድ ቶፕ ሞዴል ውድድርን የጠይም ዕንቁ የ19 ዓመቱ ሴበር አሸነፈ! „ቆይቼ እግዚአብሄርን ደጅ ጠናሁት፤ እርሱም ዘንበል አልኝ። ጩኸቴንም ሰማኝ።“ መዝሙር ፵፱ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 23.11.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ። ሞዴል ማኑኤላ ፍራይ መሥራች። ጠይሙ ዕነቁ ሰይበር አሸናፊ! ሁለተኛ የወጣቸው ጠይም ዕንቁ። ሥ ሙ እራሱ የሚገርም ነው ሴበር። አትራፊ፤ አዳኝ፤ ተከላካይ፤ ተገን ወዘተ የሚሉ ሥሞች ይመስሉታል። ቤተሰቦቹም ስለፈጣሪያቸው ዕውቀታቸው ጥልቅ ስለመሆኑ ያመለክታል። ሥምን መላክ ስለሚያወጣው። ቤተሰብ ከድል ቀን ጋር። ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የሲዊዘርላንድ ውደድር ጠ...