የመጀመሪያው የሲወዘርላንድ ቶፕ ሞዴል ጠይም ዕንቁ ሴበር አሸነፈ!


የመጀመሪያው የሲወዘርላንድ
ቶፕ ሞዴል ውድድርን የጠይም
ዕንቁ የ19 ዓመቱ ሴበር አሸነፈ!
„ቆይቼ እግዚአብሄርን ደጅ ጠናሁት፤
እርሱም ዘንበል አልኝ። ጩኸቴንም ሰማኝ።“
መዝሙር ፵፱ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
 23.11.2018
ከጭምቷ ሲወዘርላንድ።
                                          ሞዴል ማኑኤላ ፍራይ መሥራች።
                                             ጠይሙ ዕነቁ ሰይበር አሸናፊ!
                                          ሁለተኛ የወጣቸው ጠይም ዕንቁ።

ሙ እራሱ የሚገርም ነው ሴበር። አትራፊ፤ አዳኝ፤ ተከላካይ፤ ተገን ወዘተ የሚሉ ሥሞች ይመስሉታል። ቤተሰቦቹም ስለፈጣሪያቸው ዕውቀታቸው ጥልቅ ስለመሆኑ ያመለክታል። ሥምን መላክ ስለሚያወጣው።
                              ቤተሰብ ከድል ቀን ጋር።

ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የሲዊዘርላንድ ውደድር ጠይም ዕንቁ አሸነፈ። ሲዊዘርላንድ ውስጥ አንዲህ ዓይነት ውድድር ሲካሄድ የመጀመሪያው ነው።

ዝግጅቱን የጀመረቸው ብልኋ ሲዊዛዊቷ ማኑኤላ ፍራይ ናት። ትሁት ሰብዕና ያላት ተግባቢዋ፤ ፈግግታ የማይለዬት፤ ለስለሳዋ እና እና ታታሪዋ ዓለም አቀፍ ሞዴሏ ታላቅ ተግባር ነው የጀመረችው።  ለሲዊዘርላንድ እንግዲህ የመጀመሪያዋ መብራት መሆኗ ነው። ትባረክ ብያለሁኝ።

የጀርመኗ ዓለም አቀፍ ሞዴል፤ በአገረ አሜሪካ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ፤ የአሜሪካ የልዩ መክሊት ዳኛ የሆኑት ወ/ሮ ሃይዲ ክሉም ከ10 ዓመት በላይ እጅግ በርካታ ወጣቶችን ያፈራ በዬዓመቱ የሚካሄድ የጀርመን ኔክስት ቶፕ ሞዴል ግዙፍ ፕሮጀክት አላቸው።

ሞዴሏ በሚያሰናዱት የረጅም ጊዜ ሥልጠና፤ በፍጹም ሁኔታ የተደራጀ እጅግ ብዙ ባለሙያዎችን የሚያሳትፍ የውድድር ዝግጅት ነው። በርካታ ሴት ወጣቶች ለብዙ ዕድል በር ተከፍቷላቸዋል። የኛዋ ደልዳላ ሞዴል፤ የፊልም አክተር እና የቴቪዥን ሞደሬተር ወ/ት ሳራ ኑሩን ጨምሮ እጅግ የሚገርሙ፤ እጅግም የሚደንቁ ለአገር የሚያኮሩ ፈርጦችን ያፈራ ፕሮጀክት ነው ጀርመኔ ኔክስት ቶፕ ሞዴል። 

ውድድሩ መላ ዓለምን በመንቀሳቀስ የሚከናወን ሲሆን ቻሌንጁም የዛን ያህሉ ከባድ ነው። አብዛኛው ቻሌንጅ ወላጆቾች የቤት ሥራቸውን ስለማይሰሩ ሞራላቸውን አንጸው በማሰድግ እረገድ ከሚገጥም ችግር የተነሳ ነው። ሌላው ትንሽ ፈንገጥ ያሉ ዝግጅቶች ከብድ ያሉ ናቸው። እርግጥ ነው ያልተለመዱ በጎ ፈጣራዎችም አሉብት። በ2018 የጀርመን ቶፕ ሞዴል አሸናፊ ጠይም ዕንቁ ቶኒ እንደነበረች ይታወሳል። 

ዛሬም ሲዊዘርላንድ በነበረው ውድድር ላይ ሁለት የጠይም ዕንቁዎች ለፋይናል ደርሰው ተባዕቱ ጠይም ዕንቁ አሸንፏል ሴበር። መቼም ወኩ ንጉሥ ነው የሚመስለው፤ ተዋናይ ቢሆን ንጉሥ ሆኖ ቢሰራ  ያሰኛል። ዛሬ ማሸነፉ ከሰብዕናው ሙላት ጋራ እርጋታው ይገባዋልም ያሰኛል። በከፍተኛ ብቃት ነው አሸናፊ የሆነው። ለማሸነፊያ ውድድሩ የነበረው የስባንሲንግ ሚኒዩት ፍራይደይ ከበርኒግ ነበር።

ለመጨረሻ ለዛሬ ትይዕይንት ያለፉት 5 ሲሆኑ አንዱ ጣሊያናዊ ነበር። ሦስቱ በታዩ የዕለቱ ራስን የማቅረብ ዝግጅት በልዩነት ብልጫ ከውድድሩ ሲሰናበቱ፤ የቀሩት ሁለት ጠይም ዕንቁዋች ግን ለመጨረሻው ፍጥጫ ተገናኙ። መቼም ይህ ሲዊዘርላንድ ላይ የታምር ያህል ነው። ሁለት ዘረ ቡኒ የሲዊዝ የመጨረሻ ተፋላሚ መሆን። አስተያዬቱን አላነብኩትም ምን ሊባል እንደሚችል። ጀርመን ቢሆን የተለመደ ነው፤ የሚገርመው ሞደሬቷራም ቅይጥ ዘር ያላት ደስ የምትል ወጣት ነበረች። አርብ አርብ አንድ ዝግጅት በፕሮ ሲብን አላት።

እራሱ ውድድሩ መጀመሩ ለእኔ ጀርመኖች አንደሚሉት ኡበራሹንግ ነበር፤ እንግሊዞች እንዲሚሉት ደግሞ ሰርፕራይዚንግ ነበር። ሲዊዘርላንድ ውስጥ አልፎ አልፎ ቢስተጓጎልም ሚስ ሽባይዝ  በዓመት ወይ በሁለት ዓመት ሲካሄድ ለተወሰኑ ቀናት ተጀምሮ  በአጭር ቀናት ይጣናቀቅ ነበር። ልክ እንደ ፆመ ፍልሰቲት ዓይነት ነው።

ይሄኛው ግን አንደኛ ከጀርመን የሚለዬው ተባዕቶችንም አሳትፏል። ይህ መቸም የሰፋ ልዩነት የሚያመጣ ነው፤ በአዲስነት ማለት ነው። ጀርመን ያሉ ተብዕቶች ሲቸግራቸው የሴት አልባሳትን ሁሉ ለብሰው ሲወዳደሩ ሁሉ አይቻለሁኝ። እርግጥ ነው ለረጅም ጊዜ አብረው ስለሚቆዩ ፈተናው እጅግ ከባድ ነው ወንዶችን ጨምሮ ማወዳደር።

የሲዊዙ አውሮፓ ላይ ብቻ ነበር ካስቲንግ የነበረው ጣሊያን ሚላኖ እና ሁለተኛው ሲዊዘርላንድ ዙሪክ ብቻ ነበር ካስቲንግ የነበራቸው። የሥራ ዕድል ደግሞ ወደ 6 /7 የሚሆን ነበራቸው። የመጀመሪያ ከመሆኑ አንጻር እኔ ድንቅ ነው ያለኝ። 

ሲዊዘርላንድ ልዩ ተስጥኦ  የሚባል ነገር ከቁጥር የማይገባ ጉዳይ ነው። ለዚዊዘርላንድ እያንዳንዱ ልጅ በአንድ ሙያ መመረቅ ነው ትልቁ ፕሮጀክት። እንዲህ መሰሉ ውድድር ጀርመን ሄደው ነው የሚወዳደሩት እንጂ ከዚህ ተስፋ አግኝተው አያውቁም ነበር። አሁን ትልቅ እርምጃ ነው እጅግ በጣም ድንቅም ዕድል ነው። ይህ በጣም የበዛ ቁጥብነታቸውን ሚዛናዊ እንዲሆን ያድርጋላቸዋል ብዬ አስባለሁኝ። 

ሲዊዞች በዬትኛውም ለዬትኛውም የህይወት ዘርፍ የበዛ ቁጥብነት አላቸው። አብዛኞቹ የገዳም ሰው ነው የሚመስሉት፤ ግርግር አይወዱም፤ ሲቀርቡም በልክ ነው፤ አይደንቃቸው አይሞቃቸው። ከፍ ብለው መታዬት ፈጽሞ አይወዱ፤ ለሚዲያ መጋለጥ አይፈልጉም። ብቻ ልዩ ህዝብ ነው ሲዊዛዊው። ስክን ያሉ ናቸው።

አሁን ግን ክድን ብለው የሚኖሩበት ዘመን አይደለም። ዘመኑ በሁሉም ዘርፍ ሉላዊ እና ውድድር ስለሆነ የበዛ ቁጥብነት ዘመኑ የሚፈቅደው አይመስለኝም። ለዓለም የሚተርፍ የመክሊት ሥጦታ ተቀብሮ ዕድሜ ሲያልፍ የነበረው ሁኔታ ዛሬ ካለው ግሎባል ሁኔታ ጋር እጅግ የሚያሳዝነኝ ነበር። ብዙ አክተሮች፤ የጥበብ ሰዎች ብዙ ዕዳላቸው ታጥፏል ብዬ ነው እማስበው። አሁን ግን ተመስገን ነው። እኔ እጅግ ደስተኛ ነኝ።

የጀርመኗ ዓለም ዐቀፏ ሲተፋኒንም ዛሬ ተገኝታ ነበር በዳኝቱ ላይ በተጨማሪነት፤ የመገርመው እሷ የተደነቀችበት ወጣት ነው አሸናፊ የሆነላት አንተንስ ለኒዎርክ ፋሽን ሸው ብላው ነበር። ይህቺ ድንቅ ጸባዬ ሸጋ ዓለም አቀፍ ሞዴል ውጤትነቷ የወ/ሮ የሃይዲ ናት። እጅግ የምወዳት እና የማከብራት ናት። እርግታዋ ይመስጠኛል። የ እኔ ትልቁ ነጥብ እርጋታ ነው፤ የረጋ ነፍስ ይማርከኛል። ይህቺ ድንቅ ወርቅዬ በብዙ ተግባራት ላይ የምትሳተፍ እና ልዩ ሰብዕና ያላት ወጣት ናት። ወደ ሦስት ሚሊዮን የሚሆን ፈንም አላት። ሁለገብ ሞዴል ናት።

አሁን ወደ ሴበር ምለስት ሳደረግ አሸናፊው በቋሚነት የስባንሲግ ሚኑት የፋራይደይ ከበር አሸናፊ ስለሆነ ነው በቀጣይ አብሮ ይሰራል፤ በተጨማሪም ከታይም ሞዴል ኤጀንሲ፤ ከሜንቶስም ጋርም ተጨማሪ የሥራ ውል ይኖረዋል፤ በተጫማሪም አንድ ዘመን ያለ አዲስ ሞዴል መኪናም ተሸላሚ ሆኗል። በውድድሩ ሰሞናትም አንድ ካስቲንግ አሸንፏል። በድምሩ አራት ቋሚ የሥራ ጋር ዕድል ፏ ብሎ በሩን ከፍቶለታል። ዓለምም ይረባረብበታል ብዬ አስባለሁኝ የተሰጠው ነው። ወኩ ነፍስ ነው። እርጋታው ህይወት ነው። 

ሁተኛ የወጣችው ጠይም ዕንቁ ደግሞ ይህን የሞዴል ፕሮጀክት ስፓንሰር ያደረጉትን ኒቢያ ሲዊዝ እና ዴስንባህን ካስቲንግ አሸንፋ ሁለት ቋሚ ሥራ አግኝታለች። ሌሎች ተጨማሪ ሥራዎችንም ታገኝ ነበር። ነግር ግን በአዘቦት እምትለብሰው እጅግ ማራኪ እና ዓይነ ገብ ሲያደርጋት ለካስቲንግ ስትሄድ ግን የማይማርክ ስለመትልብስ አመለጣት ሁለት ታላላቅ ካንፓኒ። 

ሌላው የፎቶ ካታሎጓን ረስታ ሄዳ ትልቅ ግድፈት ፈጸመች። ወደ ሥራ ሲሄዱ ቁልፍ ትቶ የመሄድ ያህል ነበር ግድፈቷ። እነዚህ ይመስሉኛል ለመጨረሻው የአሸናፊነት ዕድል እክል የሆኑበት። ቸለልተኛነት፤ ሰዓት አለማከብር በሞዴል ህይወት ውስጥ ይቅርታ የማያሰጡ አንኳር ጉዳዮች ናቸው።

ኩራተኛው እና የተወዳደሪዎች የቡድኑ መሪ የነበረው ሴበር ግን ዋንጫውን በልቷል። ለዬትኛውም ፋሽን ትርኢት ለኒዮርክ ፤ ለፓርሲ ለማይላንድ ቶፕ ነው። አጅግ የሚገርም ግርማ ሞገስ አለው። እጅግ የሚደንቅ እርጋታ አለው። እጅግ የሚገርም ትህትና አለው። እኔ እጅግ ደስተኛ ነኝ። ለብዙ የጠይም ዕንቁ ወጣቶች በሁለመናው ናሙና፤ ሮል ሞዴል ይሆናል የሚል ጽኑ ዕምነት አለኝ።

እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ፋሽን እውዳለሁኝ። እናቴ አረማመዴን እየገራች ነው ያሰደገችኝ። አሰልጥናኛለች። ከእኔ የተጠጋ ልብሰም ፍዳውን ነበር በልጅነት የሚከፍለው። ቀዳድጅ ብዙ ነገር ማድረግ እወድ ነበር። ፋሽን ሾዎ ይሁን ካታሎግ ማዬቱ እራሱ ያዝናናኛል። 

በጉጉት አርብ አርብ እከታታለው የነበረው ፕሮግራም ነበር የሲዊዝ የሞዴል ትዕይንት። ዛሬ ተፈጸመ። አዘጋጁ ቴሌቪዥን ፕሮሲብን ነበር።
በዚኽው አጋጣሚ ሞዴል ማኑኤላን አመሰግናታለሁኝ። ትባረክ። 

ጥሩ መሰናዶ፤ ጥሩ ዝግጅት ከተሟላ ትሁት አመራር ጋር ነበራት። ውሳኔዋም አርክቶኛል። የዛሬው ብቻ ሳይሆን የቀደሙትንም የመጨረሻ ውሳኔ እምትሰጠው እሷው ስለነበረች ዝንፍ ያለ ነገር አላዬሁባትም በማጣሪያዋ ላይ። ሰው የምታስቀድም ድንቅም ናት። ይህ በራሱ የሰማይ ስጦታ ነው። ምርጫዋም እጅግ እጅግ የሚያረካ ነበር። አኩርታኛለች።

በዚህ ሊንክ ተወዳዳሪወችን ማዬት ይቻላል። አራቱ የመጀመሪያዎቹ ዳኞች ነበሩ። በዳኞች ውስጥም ጠይም ዕንቁ ነበር። ዓለም እሚያምርባት እንዲህ ስትሆን ነው። ህብርነት በራሱ ሜድቴሽን ነው ለሉላዊቷ ዓለምዬ።

·      ቋሚ ዳኞች የነበሩት።  
Manuela Fray መሥራችም፤
Papis Loveday
Dandy Diary: Carl Jakob Haupt & David Kurt Roth
ነበሩ ቀሪ ተዋዳዳሪዎችንም በዚህ ማዬት ይቻላል ፎቷቸውን።

Switzerland's Next Top Model Starts This October 2018!

እግዚአብሄር ዓለም እና ሲወዘርላንድን ይጠበቅ። አሜን።
ህይወት ራስን የመፈተሻ እና የማስተዳደሪያ መንገድ ነው!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።