ልጥፎች

ከሴፕቴምበር 29, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ይድረስ ልብ ላላቸው የጎረቤት አገሮች መንግሥታት እና ዜጎቻቸውም።

ምስል
ብል።  „በጎ ነገር ከጥንት ጀምሮ ለበጎ ሰዎች ተፈጠረች፤ እንደዚሁ ክፉ ነገርም ለኃጢያተኞች ተፈጠረች።“ ከሥርጉተ©ሥላሴ 29.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·         ይድረስ ልብ ላላቸው የጎረቤት አገሮች መንግሥታት እና ዜጎቻቸውም። ትናንት ቀን እኩል ላይ ማህል ላይ የለጠፍኩትን የአቶ ጃዋር መሃመድን ቃለ ምልልስ አዳምጥኩት። የቅድሚያ ማስጠንቀቂያም ይመስላል። ለጊዜው አንዱን ብቻ አነሳለሁ። ቀጥዬ በዚህው ቃለ ምልልስ ውስጥ ሁለተኛው እና ሦስተኛውን አትኩሮቴ የሳበውን ነጥብ መርጬ በሌላ ጹሑፍ እምጣበታለሁኝ።  ምንድን ነው የአገሬ ሰው የሚለው „ወንዝ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው“ እንደሚሉት መሆኑ ነው … ብቻ ልብ ያላቸው መልዕክቱን በሚችሉት ሁሉ ቢያደርሱት መልካም ነው። ይህ ጉዳይ „ሳይቃጠል በቅጠል ነው።“ እስኪ መጠንቀቅ ይልመድብን። እስኪ አስቀድሞ ይሆናል፤ ይመታል ብለን እንሰብ። ጆሮ ያለው ልብም ይኑረን። የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ካቢኔ ተግባሩን የጀመረበት አንድ መሠረታዊ ጉዳይ ነበር። በጫና እና በጠለፋ አንቆ ለማስቀመጥ ብዙ ተብሎበታል፤ ብዙም በወል ተሞክሯል። ዛሬ ላይ እንዲያውም በቅጡ ሳያስናዱ እዬተባሉ ደግሞ ይወቃሳሉ። ምኑን? ይመጣበታል። ቅኑ ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ ሥራ ሲጀምሩ እንደ አዲስ ጠ/ ሚር አልነበረም። ዘመኑን ሙሉ ሲሳራበት እንደኖረ እንደ ጓዳቸው፤  በአዲሱ ማንነት ከህይወቱ ጋር አብሮ እንደ ኖረ የተወሃደ - በቅጡ የተደራጀ፤ ህሊናውን ለሁለገብ ፈታኝ አምክንዮዎች እና ክርክሮች ያሰናዳ፤ ጥልቅ በሆነ ሁኔታ ሉላዊ፤ አህጉራዊ እና ብሄራዊ ግንዛቤው በዳበረ እና በለማ መሰናዶ ነበር የጀመረው። ለ...

በተስተካከለ ሙላት ለመኖር ሆኖ መገኘት።

ምስል
አሽካካች „እግዚአብሄር እሱን መርጦታል እና ለባለመዳህኒት ሥራውን ሥራለት እሱን ትሸዋለህን እና ካንተ አታርቀው“ መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፲፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ 29.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ጨረሯ ብቻ ደረሰኝ። ምን ደረሰኝ ብቻ አዳረሰኝ። እሷ ግን አትታይም። ስብሰባ ትሆንን? ወይንስ ሰማያዊ አልጋዋ ላይ ተኝታ … ወይንስ ጫጉላ ጊዜ ላይ ትሆን ወይንስ ከባዘታማዋ ፍራሽ ተኮፍሳ? ክብር ሲወድላት ደግሞም ሲያምርባት የለችም። ብቻ የለችም። ግን አለች ትንፋሿ ሀገር ያዳርሳል። መንፈሷ ይሆን የሌለው? ይሆናል። ምን ይሆናል ነው እንጂ። ግን ለምን? … እእ … ለምን …. እለምን …? ጠብኩ፤ አልመጣችም። ለእኔ ለእራሱ የላከችው ለብ ያለ ጉድ ነው። ልም ነገር። ስትገርም። ለእናንተስ ይሄው የ እኔ ዕጣ ፈንታ ደረሳችሁ ይሆን? … አላውቅም። ቀና ብዬ ፈራ ተባ እያልኩ ተመለከትኳት … „ነገ ሌላ ቀን ነው“    አሃ! ብላ ጽፋለች። ዝቅ ብዬ ስመለከትላችሁ ደግሞ „ይኽም ያልፋል“   ብላ ጻፈች … ጎሽ! አልኩና ተረጋጋሁ። ግን ለምን? አላውቅም።  ለመሆኑ ያነበብኩትን እርግጠኛ ነውን? „ ነገ ሌላ ቀን ነው „ ብላ ስለመጻፏ እንደ ገና አዎን እንደ ገና አሻቅቤና ሻቅሌ*  ሳዬው ተለውጦ … „የማይቻለውንም መከራ ቢሆን በትእግስት ቻይው“ ብላ ጽፋልኛለች። ወይ ጉዴ ግን … ለምን? አላውቅም። ዝቅ ብዬ እንደ ገና … አዎና! እንደ ገና ተመለከትኩኝ። „ከመከራው በስተጀርባ ክብር አለ“ በማለት ደግማ ጽፋለች።  ምን ማለት ነው ይሄ? ደግሞ እሷን ብሎ ትንቢተኛ፤ እሷን ብሎ ስለነገ ራዕይ ተንታኝ በታኝ … ከደንቀራው ጋር ስትደልቅ ከርማ ብዬ ልኮራፋት ስል በአንድ ...