በተስተካከለ ሙላት ለመኖር ሆኖ መገኘት።

አሽካካች
„እግዚአብሄር እሱን መርጦታል እና ለባለመዳህኒት
ሥራውን ሥራለት እሱን ትሸዋለህን እና ካንተ አታርቀው“
መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፲፪
ከሥርጉተ©ሥላሴ
29.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

ጨረሯ ብቻ ደረሰኝ። ምን ደረሰኝ ብቻ አዳረሰኝ። እሷ ግን አትታይም። ስብሰባ ትሆንን? ወይንስ ሰማያዊ አልጋዋ ላይ ተኝታ … ወይንስ ጫጉላ ጊዜ ላይ ትሆን ወይንስ ከባዘታማዋ ፍራሽ ተኮፍሳ? ክብር ሲወድላት ደግሞም ሲያምርባት የለችም። ብቻ የለችም። ግን አለች ትንፋሿ ሀገር ያዳርሳል። መንፈሷ ይሆን የሌለው? ይሆናል። ምን ይሆናል ነው እንጂ። ግን ለምን? … እእ … ለምን …. እለምን …?

ጠብኩ፤ አልመጣችም። ለእኔ ለእራሱ የላከችው ለብ ያለ ጉድ ነው። ልም ነገር። ስትገርም። ለእናንተስ ይሄው የ እኔ ዕጣ ፈንታ ደረሳችሁ ይሆን? … አላውቅም። ቀና ብዬ ፈራ ተባ እያልኩ ተመለከትኳት … „ነገ ሌላ ቀን ነው“   አሃ! ብላ ጽፋለች።
ዝቅ ብዬ ስመለከትላችሁ ደግሞ „ይኽም ያልፋል“  ብላ ጻፈች … ጎሽ! አልኩና ተረጋጋሁ። ግን ለምን? አላውቅም። 

ለመሆኑ ያነበብኩትን እርግጠኛ ነውን? „ ነገ ሌላ ቀን ነው „ ብላ ስለመጻፏ እንደ ገና አዎን እንደ ገና አሻቅቤና ሻቅሌ*  ሳዬው ተለውጦ …„የማይቻለውንም መከራ ቢሆን በትእግስት ቻይው“ብላ ጽፋልኛለች። ወይ ጉዴ ግን … ለምን? አላውቅም። ዝቅ ብዬ እንደ ገና … አዎና! እንደ ገና ተመለከትኩኝ።
„ከመከራው በስተጀርባ ክብር አለ“ በማለት ደግማ ጽፋለች። 

ምን ማለት ነው ይሄ? ደግሞ እሷን ብሎ ትንቢተኛ፤ እሷን ብሎ ስለነገ ራዕይ ተንታኝ በታኝ … ከደንቀራው ጋር ስትደልቅ ከርማ ብዬ ልኮራፋት ስል በአንድ አቅጣ የላከችው ጨረሯ ተበራከተ … ተባዛ …ሳቀይንስ ተደመረ …   ተዳምሮ ተነሰራፋ … ሞቅ አንደ ማለት ዳዳኝ። በጨረሮቹ ልክ የተደረደሩ ትዕይንታዊ ስንኞች ኪንን አንግበው ይታዬኛል። ጠጋ ብዬ ልዳስሳቸው ስል በቅጽበት ቅጽበት አሆኑ የሚል እንደ ገና ተፃፈ። መነጠሬን ከኮሮጆዬ አወጣሁና በጥድፊያ ተያያዝኩት …

አንዱ ምን ይል መሰላችሁ … ወይ ጉድድድድድ …
„የጨለማ ፀሐይ“   ይላል። እ! አልኩኝ … ምን ማለት ይሆን ይሄ? ---------------ብዬ ሳመናታ እራሱን ቀዬር አድርጎ ፈታልኝ „ህልም“   ሲል … አህ! ብዬ ልቤን አዳመጥኩት። አሁን ወደ ቀጣዩ መልዕክት መሄድ እንደ አለብኝ ህሊናዬ ማስታወሻ ቢጤ ጫር ጫር አድርጎ ላከልኝ። ቀጣዩ …„የሰማይ ቤት  ሸንጎ“ የሚል መጣልኝ። ሃ! አልኩኝ። 

ይህ ደግሞ ምን ይሆን? ብዬ ሳመናታ ሌላ አንድ በአንድ ዘርዘር እያለ ጠብ አለ … ሳገጣጥመው … „የሞት አደባባይ“  ብሎ ቁጭ። በጣም ፈራሁ። ጨነቀኝ።
መነጠሬን ለማውለቅ ስታገል … እሱ ደግሞ ለካስ ከዓይኔ ላይ ማግኔት ተፈጥሮለት አሻም እንዳለ ተሰክቶ ቀረ ….ቀጥይ ማለቱ እንደሆነም ገባኝ። 

በምልክት ቋንቋ … ገና እኮነኝ ወደ ሁለተኛው ጨረር አልሄድኩም። መዳህ ታውቃላችሁ ዝም ብሎ ታቱ …ዥግራ … ከወፌ ቆመች ያልተደረሰ … ብልጭ ድርግም በሐመራዊነት … አንተ ደግሞ ምን ልትል ይሆን ብዬ ዳጥም ላጥም ይዞ ሊፈጠርቀኝ ግብግብ ስገጥም ….

„ተስፋ ይለመልማል“  አይልም መሰላችሁ። ዎህ! ተመስገን አልኩኝ። ከላ ሙላት ምን ትርጉም ያስፈልገዋል ብዬ ወደ ሶስተኛው ቸረር ላዘግም ስሰናዳ  ውልብልቢቴን ያዝ አደረገና … „ተስፋ ይጎድላል“ አለኛ! እቴ የምን ጭንጫ ነገር ነው የኳረተ …

መጀመር እንጂ ፍጻሜ የሌለው ሕይወት … የራስህ ጉዳይ ነው ፈንግጠው! ብየ ቀጨር መጨሬን ሰባስቤ መጭ ለማለት ስሰናዳ … ያለዬለት የነበረው ቀለም እዬነጠረ እዬነጠረ መውጣት ጀመረ … አረንጓዴ ~ ቢጫ ~ ቀይ! ዋው፡~! እንኳንም ለሀገሬ አፈር አበቃህኝ ብየ ጠላታችሁ ድፍት ይበል እና ፍግም ስል „ አትቸኩይ የሀገርሽ ጉድ ገና ነው።“ የሚል መልእክት በስተጀርባዬ ….… አንኳኳ …. እህ! አልኩኝና ደግሞ ምን ቀረ ከማርያም መቀነት ወዲያ ስል አራተኛው ጨረር ፊት ለፊቴ በራልኝ … „ሰንደቁ በእግር ብረት ታስሯል“  የሚል መልዕክት ፃፈልኝ። …

ደሜ ሲነተከተክ ተሰማኝና … እኮ እንዴት ስል? በድፍረት ያነን የተላከልኝን አራተኛ ጨረር አንጋጥጬ እያዬሁት አፋጠጥኩት  … ፈንግጪው እንዳይለኝ ግን ስሜቴ ተክ ተክ ትር ትር ይላል …

 „እንቅልፋም“ ተብሎ ተጻፍልኝ። ኧረ እኔ? ብዬ ያነን አራተኛ ጨረር ----- ላጣድፈው ፈራ ተባ ስል …. እኔ ትልቁ ችግሬ እንቅልፍ ማጣት ነው። መቼ ተኝቼ የማውቀውን ነው … ይህቺ ብዕር የሚሏት ቀለማም አለላ ሳለች ነጋ ጠባ ከእርሷ ጋር ነኝ … እያልኩ ስብተከተክ አምሰተኛው ጨረር ከች አለ።

„ከዚህስ ወዲያ! … እ¡¡¡“  የሚል በቃለ አጋኖና በትዝበት ስላቅ የቆዘመ ስንኝ ብቅ ጥልቅ እያለ ሩሄን መፈናፈኛ ነሳት። ነሰተኝ። ወይ አይዘድቅ ወይ አይነቀል። ወቼ ጉድ አልኩኝ። ማለት ነበረብኝ። 

ኧረ ባበቃልኝ ስል ተተካ ተረኛው „ትራስሽ ምን ግዴ ነው“ ተባልኩኝ። ያንት ያለህ ነው። ህም! እሺ ምን ልሁን? ምንስ ላድርግ? ይነገረኝ … እያልኩ ስንተባተብ ስድስተኛው ጨረር … ከች አለ …. እንኳንም ብዬ ሳላጨርስ … „አደብ - በሆደ ሰፊነት- ይመስጠር።“ ሲል ፈታልኝ። በተፈጥሮዬ ጮኽ ብሎ መናገር አይሆንልኝ። ግጥሜ አይደለም። 

አቤቶ በርን እንኳን ከልጅነት እስከ እውቀት አንድ ቀን ችሎት ገትሮኝ አያውቅም እንደ ተመሰጋገን ይሄው አለን። ግን ነገር ግን የአሁን አቤቱታ ቁሮ እንጂ የእኔ ማንነት አይደለም እያልኩ ብቻዬን እያወጋሁ፤ እጄን ከግራ ወደ ቀኝ … ከቀኝ ወደ ግራ ሳወራጭ --- ላችሁ … መንፈሴ መሳሪያውን ሲቀባበል ተሰማኝ … „ዛሬ! ዛሬ! ዛሬ! ቁረጭ - ምረጭ! ለህዝብ ጠቀም ተግባር ሰባራ ሰንጣራን ከባህር ከገደል ጠቅልለሽ ከነዲሪቶው ጣይ … በይ! በይ!“ በማለት ወጥሮ - ሰንጎ ያዘኝ።

እሺ ምን ልሁን ? ፈወስ … ምንድ ላድርግ? አልኩ እጅግ በሚያባብል ህሊናን ዘና አድርጎ የጫጉላ ሽርሽርር በሠረገላ ፈሰስ በሚያደርግ ድምጽ ታዥነቴን ትህትናን አጋብቼ በክብር አሽሞንሙኜ ቀና አልኩ። አዎን! በተጠንቀቅም ጸጥ ረጭ ብዬ ቆምኩኝ።

ከዛ አዎን ከዛማ ሰባተኛውን ጨረር ላከችልኝ። እንዲህም ይላል  … „ የተግባር ስንቅና ትጥቅ ይኑርሽ“ በማለት የጉዳዩን አናት በዕለተ ሰንበት ጸበሉን ትእዛዝ አሳወቀችኝ። ይሁን! እሺ! ብዬ ልሰግድ ጎንበስ ስል እርገት ወረደ … ሰባቱም በአኃቲ ድምጽ …
„ቁረጪ! ትውልዳዊ ድርሻሽን ለመወጣት“  ብለው ሲናገሩ … በእነሱ ቅኔዊ ቃናዊ ድምጽ መጉላት ጉልበታምነት መሰለኝ … ከዙፋኗ ብቅ አለችና ብርኃኗን በመቁንን ሰደድ አደረግችልኝ። „እንዴት ነው ነገሩ ለብም አለደረገኝ። ከአንጀቴም አልደረሰም የብርኃን እናት ክብርት ስላት …“ „በተስተካከለ ሙላት ለመኖር ሆኖ መገኘት“       
በማለት ከልቧ አዎን ክልቧ îአሽካካች îE እቴጌ ጸሐይም በብትክትኮች ከትከት ብላ እዬሳቀችብን ነው …
  • ·       ዩ ማስታወሻ።

የማከብራችሁ እንዴት ናችሁ። ይህ ጹሑፍ ከ5 ዓመት በፊት የተጻፈ ነው። ምን አስመልከቶኝ እንደጻፍኩት እኔም አላውቀውም። በ2013/2014 ብቻ በአንዱ ጊዜ ዘሃበሻ አትሞልኝ ነበር። ይባረክ!

ይህን ብሎግ ስጀምርም አንድ ሰንበት ላይ አትሜው ነበር፤ አሁን የእኛ ነገር ከአልጋ ሲሉን ከአመድ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የእንጅባራ ገድል ጉዳይ ጋር ሳገናዝበው ዕድል ለእኛ የሰጠንን አጋጣሚ ሁኔታ በአግባቡ መጠቀም ተስኖን፤ ከሴራ ጋር መፈታት አቅቶን፤ ቅን መሆን አልችል ብለን፤ ዴሞክራሲን መሬት ላይ መጀመር ተስኖን፤ ነፃነትን ባገኘነው ልክ ወደ ተግባር ማሻገር አቅሙ ጠፍቶ ያቺ ድሃ አገር አሁንም ከማህጸኗ ታለቅሳለች። ተመክሯችን ሁሉ ስለነፃነት ዶግማ፤ ስለ ዴሞክራሲ ዶግማ ምንም። 

ችግር ፈቺ መሆን ቀርቶ ችግር ፈጣሪ ላለመሆን መቁረጥ ተስኖን የድሃ ልጅ ቤቱ ተስፋው ፈረሰ። ሰው አልባ ፓለቲካ ምድን ይሆን? ሰው አልባ ሃይማኖትስ? ሰው አልባ አገርስ? ለመሆኑ ከላ ሰው አገር አለን በፕላኔታችን? እኛ የምንፈልገው ያንን ነው።

ሚሊዮኖች ተፈቅዶ ይፈናቀላሉ። ተፈቅዶ የስቃይ በረድ ታዞላቸዋል በራሰቸወ ወገን በሥጋ እና በደማቸው።ብቻ ማስተዋል ብቻ ሳይሆን አደብም የነሳን መሆኑ ቢያስጨንቀኝም ወቅቱን ይገልጽልኛል ያልኩትን ጹሁፍ እንሆ።
  • ·       ከወን።

ልብ የት ይገዛ ይሆን? ማስተዋልስ የት ይፍለቅ? ትእግስትስ የት ይሸመት? ሰው ነኝ ለማለት ሰው መሆን ብቻ ይባቃልን? የቤት ሥራው ለቅኖቼ ብቻ ነው። ቅንነት በፖለቲካ መንደር የተቀበረባት አገር ብትኖር ኢትዮጵያ ናት።  

ኢትዮጵያዊነት ፈተና ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።

ማለፊያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።