ይድረስ ልብ ላላቸው የጎረቤት አገሮች መንግሥታት እና ዜጎቻቸውም።

ብል።
 „በጎ ነገር ከጥንት ጀምሮ ለበጎ ሰዎች ተፈጠረች፤
እንደዚሁ ክፉ ነገርም ለኃጢያተኞች ተፈጠረች።“
ከሥርጉተ©ሥላሴ
29.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።


·        ይድረስ ልብ ላላቸው የጎረቤት አገሮች መንግሥታት እና ዜጎቻቸውም።

ትናንት ቀን እኩል ላይ ማህል ላይ የለጠፍኩትን የአቶ ጃዋር መሃመድን ቃለ ምልልስ አዳምጥኩት። የቅድሚያ ማስጠንቀቂያም ይመስላል። ለጊዜው አንዱን ብቻ አነሳለሁ። ቀጥዬ በዚህው ቃለ ምልልስ ውስጥ ሁለተኛው እና ሦስተኛውን አትኩሮቴ የሳበውን ነጥብ መርጬ በሌላ ጹሑፍ እምጣበታለሁኝ። 

ምንድን ነው የአገሬ ሰው የሚለው „ወንዝ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው“ እንደሚሉት መሆኑ ነው … ብቻ ልብ ያላቸው መልዕክቱን በሚችሉት ሁሉ ቢያደርሱት መልካም ነው። ይህ ጉዳይ „ሳይቃጠል በቅጠል ነው።“ እስኪ መጠንቀቅ ይልመድብን። እስኪ አስቀድሞ ይሆናል፤ ይመታል ብለን እንሰብ። ጆሮ ያለው ልብም ይኑረን።

የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ካቢኔ ተግባሩን የጀመረበት አንድ መሠረታዊ ጉዳይ ነበር። በጫና እና በጠለፋ አንቆ ለማስቀመጥ ብዙ ተብሎበታል፤ ብዙም በወል ተሞክሯል። ዛሬ ላይ እንዲያውም በቅጡ ሳያስናዱ እዬተባሉ ደግሞ ይወቃሳሉ። ምኑን? ይመጣበታል።

ቅኑ ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ ሥራ ሲጀምሩ እንደ አዲስ ጠ/ ሚር አልነበረም። ዘመኑን ሙሉ ሲሳራበት እንደኖረ እንደ ጓዳቸው፤  በአዲሱ ማንነት ከህይወቱ ጋር አብሮ እንደ ኖረ የተወሃደ - በቅጡ የተደራጀ፤ ህሊናውን ለሁለገብ ፈታኝ አምክንዮዎች እና ክርክሮች ያሰናዳ፤ ጥልቅ በሆነ ሁኔታ ሉላዊ፤ አህጉራዊ እና ብሄራዊ ግንዛቤው በዳበረ እና በለማ መሰናዶ ነበር የጀመረው።
ለእኔ ለማአብይአብይለማ አንድ የትምህርት ክ/ ጊዜ ስለነበር ማስታወሻዬን ይዤ ቁጭ ብዬ የተማርኩበት ዘመን ከሊሂቃን ቢኖር ይህ ነበር ማለት እችላለሁ።

ብራና ላይ ከማገኛቸው ት/ ቤቶች እንደ ዕውቁ ሊቀ ሊቃውነቱ ዶር ፈቃደ በቀለ ጹሁፍ ማለት ነው። እህቴም መሰል እርምጃ እንደወሰደች ነግራኛለች። አብረዋት የሚሰሩ የኦሮሞ ወገኖቻችን እስኪገርማቸው ድረስ ነበር ያለችኝ።
አጎራባች አገሮች፤ በስሜን አሜሪካ እና ኢትዮጵያን በመንፈስ ለማያያዝ ያደረጉት የጥምረት ውህድ ልቅና ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ልቅና ደረጃው ከፍ ያለ አዲስ ታሪክ ነበር ለእኔ ትውልድ። 

ቀደም ብዬ ያነሳሁት ተወቀሱ ያልኩት ተዚህ ላይ ላምጣውና ምንም መሰናዶ ሳያደርግ በሩን ቧ አድርጎ ለሴራ ማህበርተኞች ከፈተ የሚል ዕድምታ ስላማደምጥም፤ ስለማነብም ነው አሁን ከሆነ።

በመንፈስ እማ ኪዳን አስገብተውናል። አህቲ ድምጽ ስለ ነበረ ነው ፍቅርን፤ ምህርትን፤ ይቅርታ ይበል ያልነው። የተሰራው ግድፈት ያን የመንፈስ መያያዝ የሚያስቀጥል ተቋም አለመፍጠር ነው። 

በሚዲያ እንኳን ያለፉት ክንውኖችን የሚዘክር የተለያዩ አቅም ያላቸው መሰናዶዎች አልተደረገበትም። በቴሌቪዥን እና በራዲዮ በፊልም እና በቲያትር በበራሪ ጹሑፍ እና በፖስተሮች በተከታታይ መሰራት ነበረበት። ይህ አልተከወነም ክፍተቱ የተፈጠረው ደግሞ ከሰሜን አሜሪካ መልስ በገጠመው የተከደነ ጉዳይ ነው።

ከዚህ ሌላ ሁለቱም በጥምረት በሙያቸው ደህንነት ላይ እንደ መሥራታቸው ብርቱ ጥንቃቄ ሊያደርጉበት የሚገባውን ጉዳይ ቸል አሉት። እዚህ በአንዲት አጀንዳ ላይ መስማማት የማይችሉት፤ ቢስማሙ ከሰሞናት ሳይልፉ ጨዋታው ፈረስ ሲባባሉ የኖሩት።

 ስደት ላይ ስንት መከራ የሚያሰተናግደውን ስደተኛ ወገናቸውን ከአድርጉልኝ ውጪ ምን ላድርግላችሁ? ብለው የማያውቁት ወገናዊ አግልጋይነትን ሳይጀምሩት ነበር አገር የገቡት። በዚህ ላይ የተውልድ ክፍተትም አለ። የብቃት ሰፊ ልዩነት አለ። ያን ቦታ የማለምም ሽውታ አለ።
ይህን ቃለ ምልልሶችን ኦህዴድ ወደ ፊት ሲመጣ የነበረውን በስፋት ላጠና ሰው በዚህ ዘርፍ ካላይ በተቀስኩት ዘርፍ ዝርግ መንገድ ነው የተከተለው የአብይ ሌጋሲ። በመንግሥት በኩል ወደ 3000 የሚጠጋ ወገን ተፈናቀለ ቢባልም አስከ 13ሺህ ይደርሳል የሚልም አለ ቡራዩ እና መከራዋ።

የችግሩን መንስኤ እና ዕድምታ ይህን እንኳን ወጥ በሆነ መረጃ ለመስጠት አቅም እስኪያጣ ድርስ ያደረሰው ብበዙ ውስብስብ የተከዘነውን የተፎካካሪ መሪዎችን ሁነት የሚከታታል አንድ ሁነኛ ተቋም መፍጠር እለተቻለም። እዛው ከግንባሩ የደረሰውን አደጋ ለመቋቋም የሚያስችል ሙሉ አቅም እና ችሎታ ያለው ቀድሞ ሴራን የሚያከሽፍ ልዩ የደህንነት ሃይል በቀጥታ ከጠ/ ሚር ቢሮ ጋር ግንኙነት ያለው ማደራጀት ይገባ ነበር።

አሁንም እምሰማው ነገር አለ። በቁጥጥር ሥር ውሏል የሚል። ኖ! አንድ አቅጣጫ ብቻ አይደለም ሰፊ የሆነ በቅጡ የተደራጅ ጣማራ ሌሎች አፈንጋጭ ስኳዶች መኖራቸውን በማሰብ ቀበቶን ጠበቅ ማድርግ ይጠይቃል። 

መዘናጋት አያስፈልግም። የኖርንበት ፓለቲካ አተላ ነው። አተላን እንደ ንጥር ነገር ስንምግ ነው የኖርነው። በፈለገው ሁኔታ እና ጊዜ አንድ አይደለም ሁለት አይደለም ከዛም ባላይ ይህን መሰል ራዕይ ያላቸው መንፈሶች መኖራቸውን ማወቅ ይገባል። ይኸው አውከው እኮ፤ የስሜን አሜሪካ ጉዞ ያስተጓጎሉት። የጀርመን ጉዞም እንዲሁ ታቅዶለት ይሆናል።

ልብ ጥሎ የሚያስቀምጥ አይደለም። ምክንያቱም በዚህ መሰል ቅልቅል የኢትዮጵያን ፖለቲካ ማስተዳደር ግዙፍ ነገር ነው። ለዛውም አብይ ሆኖ ችሎት። አልታሰበም እንዲህ ዓይነት መሪዎች ከሰማይ ዱብ ይላሉ ተብሎ። በፕሮፓኦጋንዳ ሰልፈኛ የተኖረው ኢትዮጵያዊ ፓለቲካ ስንት ፊልም በአውንታዊነት በሚያወጣ መልኩ ክንውኑ በተስፋ ሲያሰግረን ስለምን አይደንግጡ። ለንጉሰ ነገስታቱ መብረቅ ነው።

ሰሞኑን የብአዴን ጉባኤ አስመልከቶ አቶ ደመቀ መኮንን የሰጡትን ረዘም ያለ ቃለ ምልልስ በ አማራ ቴሌቪዥን አዳምጠኩኝ። የሚሊዮኖች ድምጽ የሆነው ጋዜጠኛ ሽፈራው አንድ ወቅቱን ያልጠበቀ ጹሑፍም ጽፏል። ስለ ልዑላዊነት ጉዳይ ነው፤ በውነቱ ሃሳቡ ቢኖር እንኳን ጉባኤው እስኪያልቅ መጠበቅ ግድ ይላል። እንቅፋት መሆን ልብን ማሻፈት አያስፈልግም። ጊዜ አለ ለመወቃቀሱም፤ ለመካሰሱም። እዬዋጠን እኮ ነው ያለው መከራ፤

ወደ ቀደመው ስመለስ እኔ ያን ቃለ ምልልስ ሳዳምጥ የት ኑረው ነው እኔህ ሰው ነው ያልኩት። አቅሙም፤ ክህሎትም እርግጥኝነቱም የተናጋሪነቱም ጥበቡም ድንቅ ነው ያለኝ። ምን ለማለት ነው አዲስ የአምራር ብርሃን ኢትዮጵያ ውስጥ መፈጠሩን አቶ ደመቀ መኮነን ናሙና ናቸው። 

እኔ እንዲያውም ሙሉውን በጸጋዬ ራዲዮ ፕሮግራም አስተላልፈዋለሁኝ። በጣም ከልቤ ነው የገባው። ተናግሬ ነበር ከ አብዩ ጋር የማይሰራው ሰነፉ ብቻ እንጂ ለማማር የፈቀደ በ አጭር ጊዜ ክህሎቱ ይጨምራል ብዬ ነበር። ዋናው የአብይ እና የለማ ፕሮጀክት ሰው መሥራት ነው። ለዚህ እኮ ነው ዕውቀታቸውን ሲያስተላልፉ በገፍ የሆነው።

ራሱ ተፎካካሪ መሪዎች እኮ ይሁኑ አክቲቢስቶች የዛን ግልባጭ ለማድርግ መሞከራቸው ምንጩ አዲስ የሆነ እሸት የአመራር ብርሃናዊ ጥበብ በመፈጠሩ ነው። ያው የወንበር ህልመኞች፤ ዝቅ ብሎ መታዘዝን የማይሹት ይህን መሆን ባይችሉ ያው ኢትዮጵያ መሞከሪያ ጣቢያ አይደለች። 

እንደማናውቃቸው ሁሉ ዕድሉን ይሰጠን እና እኛም ያለንን እናሳያለን የሚል መንፈስ በሁሉም የወንበር ጥም ማህበርተኞች ዘንድ መኖሩን በርግጠኝነት አስቦ በሁሉም ዙሪያ ሳይዘናጉ የጀመሩትን አዲስ መንገድ „በደም“ ሳይሆን ህግን ባከበረ ሁኔታ፤ ትህትና በልተለዬው የዳኝነት ጥበብ መቀጠሉ መልካም ነው። እልፍኝነት ያለ ገደብ ጋዳ ነው። ልክ መኖር አለበት። ልብንም እንዲሁ። 

ጥንቃቄ ከሚሻው ጉዳይ አንዱ ይህን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የጀመሩትን የአፍሪካ የመንፈስ ውህድነት ፈርታይል ለማድርግ የጀመሩትን ብሄራዊ ጉዳይ ለመስበር ሌላም ከአገር ውጪ የሆነ አንድ እንቅሳቃሴ መጀመሩን ትናንት ከተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተረዳሁኝ። አቶ ጃዋር መሃመድ ኬኒያ ላይ በሦስት ቋንቋ ፕሮግራም ለመጀመር ያለውን መሰናዶ እንደ ዋዛ አጫውቶናል።

Ethiopia:በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አቶ ጀዋር መሀመድ የሰጡት ትንታኔ:OMN

Published on Sep 27, 2018

ሃሳቡ ኦሮምያን እንደ አገር አድርጎ ከጎረቤት አገሮች ጋር የመስመር ግንኙነት ለመፍጠር ነው። በስዋህልኛ፤ በሱማልኛ በኦሮምኛ ነው ዝግጅቱ የሚሰጠው። ይህ ማለት ኢትዮጵያ ያለውን ሱማሌ እና ሱማሌ ላንድ ያለውን የሱማሌ ዜጋ፤ ኢትዮጵያ ላይ ያለውን ኦረሞ እና ኬኒያ ላይ ያለውን ኦሮሞ፤ ኬኒያ ያለውን ኬኒያዊ እና ኦሮምያ ያለውን ኦሮምያ ለተነሰባት ትልዕኮ ስኬት „ሀ“ ብሎ መጀመሩ ነው።

እነ በኮ ሃርም ሲጀምሩት እንዲህ አድርገው ነው። ይህ ስሜት በቀጥታ ኤርትራን፤ ኢትዮጵያን፤ ጁቡቲን፤ ሱማሌን ኬኒያን ራሷን ለጥቃት የሚያጋልጥ ነው። ምክንያቱም የእሱ ተልኮ ግራኝዝም ስለሆነ። በሌላ በኩል  የኢትዮጵያን ልዑላዊነትም በጽኑ የሚፈትን ነው።

ይህ ፍላጎት ከኖረው እስከ ዛሬ ስለምን አልታቀደም?እንዲያውም በመከራው ዘመን አስፈለጊ ነበር። እሱ ጠላቱ ዋንኛው ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ነው። ኢትዮጵያዊነት ጠንክሮ እንዲወጣ አይፈልግም። በሌላ በኩል ክርስትና ዕምነትም እንዲሁ። አውነቱን አፍርጦ መነጋገር ያስፈልጋል።

ሌላው ሰላሙን የነሳው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ኬኒያ ሞገስ ሰጥታ አገሯን እንዲጎበኙ የክብር ጥሪውን ከፍተኛ  ዑክ ልካለች። ይህም ብቻ አይደለም የትም ቦታ ያልሆነ እርስቼው ከሆነ ይቅርታ የቀድሞው ፕ/ ባራክ ኦባማ ኬኒያን ሲጎበኙ እንኳን 21 ጊዜ መድፍ አልተተኮሰም። ኬኒያ ግን አድርጋዋለች። ያ ዕጹብ ድንቅ አቀባባል የ ዓለም ሚዲያም ተቀባብለውታል። ይህ ለኦነጋውያን፤ ለጃዋርውያን፤ ለአራርሳውያን፤ ለህዝቃኤላውያን የነፍስ ቃጠሎ ጉዳይ ነበር።

እንዳውም እኔ ኬኒያን አመስግኜ ስጽፍ እስኪ ደግሞ ኬኒያ ላይ  መረብ ዘርጉ እዚህ በአገር ልጅነት የሞከራችሁት ሁሉ አይሆኑ ሆነባችሁ ብዬ ጽፌ ነበር። ከሁሉ ያቃጠለው ዶር አብይ አህመድ ፊት ለፊት ሲመጡ የኬኒያ የፖለቲካ ሊሂቃን የሱዳን ወጣት ሊሂቃንን ይጨምራል በተከታታይ ሰፊ የሆነ የሚዲያ ሽፋን ነው የሰጡት። ሲያሳርጉ ለአብይ እንጸልይለት እያሉ። እኔም ስጽፍ ሊንኩን እለጥፍ ነበር። ይህ የአንጎል ቁርጥማት ነው ለቅናተኞች። ይህ የጭንቅላት ክንታሮት ነበር ለግለኞች።

ሌላም ሚሰጢር አለ ኬኒያ በታሪኳ ኢትዮጵያን ያለተፈታተነች የሰላም ልዕልት ጎረቤታችን ናት። ኢትዮጵያም ኖሙናዋ ናት። በ ኢኢጦጵያ ኬኒያ ያላት ተስፋ ብዙ ነው ያው የፓን አፍሪካኒዝም ውስጥ ስለሆነች። አሁን ኬኒያ ላይ ጠናና የሆነ ዝንባሌ እንዲኖር ለማድረግ ይህ ትልም ታቀደ። አዲስ ተቀናቃኝ አገር መፍጠር ነበረበት ለኢትዮጵያ። ለእሱ ህልም አገር ለኦሮምያ ደግሞ አዲስ የጎረቤት አገር ግንኙነት መፍጠር።

ቅኖች፤ ---- መሬት ሲነቃ ታውቃላችሁ አይደል። አብሶ ዋልካ አፍር ከሆነ። ስንጥቁን ዲካውን ማግኘት እስኪቸግር ድረስ ማለት ነው። ንቃቃት ዙሪያ ገባውን መፍጠር ፈለገ። እና የመጀመሪያ ኢላማ ኬኒያ ሆና ተገኘች። ለኬንያ ለራሷ ከአሸባሪዎች ጋር ላለባት መከራ ሌላ መከራ በፈቃዷ ኬኒያ እዬገዛች ነው ያለችው።

ይህ ሁሉ የሚሆነው ኢትዮጵያ ተቀምጦ በእሷ አንጡራ ሃብት እዬተንፈራሰስ አዳዲስ አረሞችን መሬት ላይ አልበቃው ብሎው ብቸኛዋን ሰላማዊ ጎረቤት አገርን ኬኒያን ወጥመዱ ውስጥ አስገብቷል። ኬኒያውያን ኦሮሞዎች የይገባኛል ጥያቄ ቢያነሱለት ደስታውን አይችለውም። ሽፋኑ ሚዲያ ነው ጉዞው ግን ሽብርተኝነትን ማስፋፋት፤ ማበረታት፤ ሊንክን መፍጠር ነው።
 
ይህ መንፈስ ለራሱ ለኬኒያ ሚዲያም ተጨማሪ ጫና የሚፈጥር፤ ኬኒያ ውስጥ ለሚገኙ ለፖለቲካ ፓርቱዎችም ጠበቅ ያለ ራስ መርዝን ያወጀ ጠናና ጉዞ ነው። ይህ የሚዲያ ነፃነት ቢሆንም ጭካኔን የደፈረ ሚዲያ ግን ፈቃድ መሰጠት ኬኒያ ደህንነቷ ያለውን እንዝህላልነት ያሳያል። ሲጀምረው ለስላሳ አድርጎ ሊጀመረው ይችላል። መረቡን አሁን ዘርግቶ መጥቷል። ሲሰነብት ግን ለኬንያ ቁጭ ብለው የሰቀሉትን ቁሞ ማዋርድ እንዲሉ ይሆንበታል።  የአብይ የፍቅር ፓሊስ እንደ ገባው ፈተና ማለት ነው።

ማፍርስ፤ መናድ፤ ሰላም መንሳት፤ ማወክ፤ መታበይ፤ መጨከን፤ ሰውን እንደ ፍጥረት አለማዬት ይህ የተጠናወተው መንፈስ ኢትዮጵያ ላይም ህጋዊ ዕውቅና አግኝቶ እዬተንፈለሳስ ነው፤ አሁን ደግሞ ሁለተኛ ጣቢያውን እንዳ አንድ የጎረቤት አገር እዛ አዲስ የኢትዮጵያን ሉዕላዊነት የሚፈትን እኩይ ተግባር ወጥኗል። ለዚህ ደግሞ ኦነጋውያን ቀደመት መረቦች የሊሂቃኑ ግንኙነት ያግዘዋል።

አብሶ የኤርትራ መንግሥት እና የኢትዮጵያ መንግሥት ይህን ዝም ይሉታል፤ እግር አውጥቶ እስከሚሂድ ድረስ ይጠብቁታል ወይንስ ገና በእንጭጩ ይነቅሉታል? የአፍሪካ ህብረትስ ይህን በቸልታ ያዬዋልን? የናዚ መንፈስ ያለው ሰው እኮ ነው። እሰከ እለተ ህልፈቱ አይጠግብም፤ አይረካም። አፍሪካን ቢሰጠውም ወረራውን ይቀጥላል። ዓላማ አለው በጣም ጥልቅ።

የትም አይደርስም ሊባል አይችልም። ትልቁ አቅሙ ሽንፈትን አለመቀበሉ ነው። ለአንዲት ቀን ቢሆን አብይን ከዛ ወንበር ማዬት አይሻም። የቻለውን ሁሉ ሞክሮ ለጊዜው ከሽፎበታል። ስለዚህ ከሰይጣናዊ ተግባሩ ለሰከንድ ያርፋል ተብሎ አይታሰብም። የተፈጠረው ለምክንያት ነው።አይተኛም። አያንቀላፋም።

ደግሞ የሚገርመው ተሸንፎ አለመቅረቱን የማወቅ ብልህነቱ ነው። ይህን በተለያዬ ሁኔታ እኔ ገልጨዋለሁኝ። ግራጫማ ስብዕና ያለው እስከ ማለት የደረስኩትም በዚኸው ነው። ይህም ብቻ አይደለም እግዚአብሄርን ባገኘው ስለምን እንደፈጠረው እጠይቀው ነበር ያልኩት ለዚህ ነው።

አውቄዋለሁም፤ ላውቀው እችላላሁም የማይባል ወጣት ነው። እዚህ የደረሰው በራሱ አቅም ነው። ኮንፊደንሱ ደግሞ ካለው አቅም በላይ ነው። ቃለ ምልልሶቹ ሁልጊዜ የትእዛዝ ናቸው። ለወታደሮቹ ቀጭን ትእዛዝ ነው የሚያሰተላልፍበት በማንኛውም ቃለ ምልልስ።

አሁን እንዳሻው ከተለቀቀ አንድ ቀን ዓለምን የሚያስጨንቅ የሚንጥም ይሆናል። ቃለ ምልልስ ሲያደርግ ለእኛ ለተማላዎቹ ሊመስለን ይችል ይሆናል። አይደለም ለሠራዊቱ ነው …. አሁን አፍንጫቸው ሥር ተቀምጦ መረቡን በዓይነት ዘርግቷል። የ አብይን ሌጋሲ ይሁን የቲም ሌማን መንፈስ ጢባ ጢቦሽ እዬተጫወተበት ነው።
ያ መረብ ዛሬ ከወያኔ ሃርነት ሰዎች ጋርም ሊሆን ይችላል፤ ለእነሱም የማይራራ ስለመሆኑ ግን በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ። 

አሁን ያጀቡት ኦቦ በቀለ ገርባም የፈተናቸው ሽልማት ጥቃት ይሆናል እሱ ተልዕኮው ሲያጠናቅቅ - ከተሳካለት። አያሳካለትም ልል አልችልም መያዝም መጨበጥም አይቻልም እሱን። መዳፌ ውስጥ አስገባሁት ብሎ ሊፎክር ዩሚችል የለም። እኩይነት ቁሞ ሰብዕና ተላብሶ ቢፈጠር እሱኑ ነው የሚመስለው። ህልመኛ ነው። ህልሙ መንፈስን ቅኝ ግዛት ማድረግ ነው። ደግሞም ተሳክቶለታል።

ዶር አብይ አህመድ ባክነው የሰበሰቡን መንፈስ ሁሉ በአንድ ጀንብር ነው የበተነው። አሁን የቀረው ጎረቤት አገሮችን ነው ማዕከሉን ኬኒያ ላይ አድርጎ የሚሻውን ያደርጋል። የአፍሪካዊነት ህልምን የዶግ አመድ ያደርገዋል። ምዕራቡ ዓለም እማ በሰሞናቱ እስር እና ሞት ዜና በቃን እስኪሉ ድረስ አጥግቧቸዋል።

አንድ ብልህ ሰው „ግራጫማ“ ሰብዕና ብዬ ስጽፍ ከልቡ ያሰገባው አልነበረም። መደማመጥ ቢኖር ብዙ የቀደሙ ተግባርት ሊከውን ይገባ ነበር። ሌላው አቋሙ እርምጃው ቅጽበታዊ ነው። ይህ ደግሞ ለማህረሰብ ቀወስ አደገኛ ሰብዕና ነው።፡አዲስ አባባ ስታዲዬም ላይ በኦቦ ዳውድ ኢብሳ አቀባባል ሲናገር ሳዬው የናዚ ፊልም ነው እኔ የታወሰኝ። ሰብዕናውን ያጠነው ሳይሆን ሆኖ የተፈጠረው እንደዛ ነው። መግደል ማሰቃዬት መጨከን የናፈቀው።

አብሶ ኬኒያ የምትገኙ ኢትዮጵውያን ይህን ጉዳይ በችልታ እንዳትመለከቱት - አደራዬ ጥብቅ ነው፤ በሌላ በኩል የኬኒያ ኢንባሲም ምደባ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህነው ይህነው ማለት ባለችልም ብርቱ ጥንቃቄ የሚያስፍለገው ጉዳይ ነው። እሱ የሚገባባት መስመር ከተገኘ ሰርስር ነው፤ ዘራፊነቱም የመንፈስ ነው። በዚህ ላይ ዓለም በሚዲያ ተዋህዳለች።

አሁን ብዙ ጊዜ ሽብርን ፕ/ ትራንፕ ከመጡ በሆወላ ቀነሰ የሚሉ አሉ። መልሶ ለማገገም እዬሰሩ ነው። ሊንኮቹ ደግሞ በዬትም ቦታ አሉ። ዓላማቸው ደግሞ ታዳጊ ወጣቶችን ነው። ኢትዮጵያ ፈቅዳ፤ አቅፋ ደግፋ ወዳ እና ለምና ወጪውን ሙሉ ችላ ከሊቅ እሰከደቂቅ ከፍና ዝቅ ብሎ የተቀበለችውን „አዲስ የሽብር ፖለቲካ“ ዛሬ ማህል አዲስ አባባ ነው ነገ ደግሞ በራሷ ጫካ ዱር ገደል ትኮምኩም¡ስለምን አሁን ኬኒያ ላይ OMN መከፈት ተፈለገ? ለመሆኑ ኦዴፓ ላይ ያሉ ወገኖቼ ምን ያስባሉ? አንደ ግንባርም ኢህዴግስ? ፍንክንክ አደረጋቸው ወይንስ የነገ የልጅ ልጆቻቻው መከራ ታያቸው? 

እልፍ ነን እና እልፍነታችን በተግባር እልፍ እናድርገው።
የኔዎቹ ኑሩልኝ
መሸቢያ ጊዜ።  


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።