ልጥፎች

ከኦገስት 13, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

በለው! አቶ ንጉሡ ጥላሁን ደግሞ ምን እያሉን ነው?

ምስል
የመፍንቅል መንፈስ ማህበርተኞች የመንትዮሹ መልዕከታት ውጥረት። „እኔም ተመለስሁ፣ ከፀሐይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አዬሁ፤ እንሆም የተገፉት ሰዎች እንባ ነበር፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ በሚገፏአቸው እጅ ሃይል ነበር፤ እንርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።" መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ  ፩ ቁጥር ፬ ከሥርጉተ ©ሥላሴ 13.08.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። ·          ቁጥር አንድ https://www.zehabesha.com/amharic/archives/93457 ምርቱን ከግርዱ እንለይ ! ኦቦ አዲሱ ረጋሳ August 9, 2018 | „ነፃነት፣ወንድማማችነትና እኩልነት ካለፈዉ ታሪክም ሆነ ከባንዲራ በላይ ነዉ !“ ለቁጥር አንድ መልስ በዚህ ሰጥቻለሁኝ። እርግጥ ነው እንደ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ ባንዴራ ጨርቅ ነው ዓይነት አገላለጹን በሚመለከት አልነካካሁትም።  ሌላውን ጭብጥ ግን ትንሽ ሄጀባታለሁኝ። ለማያያዝ ነው ሊንኩን የለጥፈኩት የሁለቱ መንትዮሽ ፍንገጣ እና ጥሪያቸው መከተታል እኔ ቀደም ብዬ ስገልጻቸው ከቆዬሁት ይሁን አቶ ጃዋር መሃመድ ወደፊት እንዲመጡ የነበረውን ምኞቱ ጋር ሃዲዱን እንድታገነዝቡት ነው። በዚህ ሊንክ ለሁለቱ መንፈሶቹ ያለውን ዕይታ የገለጸበት ነው አቤቱ አቶ ጃዋር መሃመድ። https://www.zehabesha.com/amharic/archives/88248 „ ሕወሓት   ለማ   መገርሳን   ለጠቅላይ   ሚኒስተርነት   ለምን   አልፈለገችውም ?  –  ጀዋር   መሐመድ   ያብራራል  |...

የነፃነት አርበኛው የህግ ባለሙያው አቶ ታየ ደንደኣ ዕሳቤ እና እውነታው።

ምስል
ባለፈንጣጣው የኢትዮጵያ ፖለቲካ። „ወደ እግዚአብሄር ቤት በገባህ ጊዜ እግርህን ጠብቅ፤  ለመስማት መቅረብ ከሰነፎች መሥዕዋት ይበልጣልና፤  እንርሱም ክፉ እንዲያደርጉ አያውቁምና።„ መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ ©ሥላሴ 13.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ውዶቼ ሊንኩ ከሳተናው ብራና ያገኙሁት ነው። „ኦህዴድ እና ብአዴን፤ አቅማቸዉን ያባከኑ ታላላቅ ሃይሎች ! ( ታዬ ደንደኣ )“ ነሃሴ 9, 2018 https://www.satenaw.com/amharic/archives/62143 እንዲህ ይሉናል የነፃነት አርበኛው የህግ ባሙያው አቶ ታየ ደንደኣ … „የአማራ እና የኦሮሞ ህዝብ ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ቢያንስ 70% ይሆናል። በኢትዮጵያ ፓርላማ ኦህዴድ 190 አባላት አሉት። ብአዴን ደግሞ 150 የሚጠጋ አባላት አሉት። በድምሩ የአማራ እና የኦሮሚያ ተወካዮች 340 አከባቢ ናቸዉ። ይህ በፓርላማዉ እጅግ በጣም ወሳኝ ድምፅ ነወ። ብአዴን እና ኦህዴድ ቢተባበሩ ፓርላማዉ የሚያወጣዉን ህግ መቆጣጠር ይችላሉ። ሁለቱ ድርጅቶች ያልደገፉት ረቂቅ አዋጅ ሊፀድቅ አይችልም። ሁለቱ የፈለጉትን ረቂቅ አዋጅ ደግሞ በአብላጫ ድምፅ ማፅደቅ ይችላሉ። ስለዚህ ለኢትዮጵያ የዴሞኪራሲ መቀጨጭ ተጠያቂ መሆን ያለበት ሌላ አካል ሳይሆን ኦህዴድ እና ብአዴን ናቸዉ። ሁለቱ ሀይሎች ተባብረዉ ለኢትዮጵያ ዴሞኪራሲ እና ልማት ከመሥራት ይልቅ እርስ - በእርስ በመፈራራት አምባገንነት እና ድህነት በኢትዮጵያ ምድር እንድሰነብት አድርጓል“ በጣና ኬኛ ዘመን በአማራ...