ልጥፎች

እኛ የሚያስፍለግን የአብይ ጤነንት ከነቤተሰቡ ነው።

ምስል
„አያ ጅቦ ሳታማህኝ ብላኝ።“ „በአምላክህ በእግዚአብሄር ፊት የተጠላ ነውና ነውር ወይንም ክፉ ነገር ያለበትን በሬ ወይም በግ ለአምላክህ ለእግዚአብሄር አትሰዋ።“ ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ ፲፯ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ ©ሥላሴ 13.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ቀልቤን የሳበው ጹሑፍ ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን የጻፈውን ከሳታናው ብራና ላይ አገኘሁ እና ሁለት ነገሮችን ነቅሼ ማውጣት ፈለግሁኝ። ጹሑፉ የትናንት ነው የሻሸመኔው አሰቃቂ ግድያ ከተፈጸመ በፊት እና በኋዋላ ስለመሆኑ እማውቀው ነገር ስሌለ ልዝለለው። እርእሱ እንደምታዩት ነው። አሁን ያለው መፈንቅለ መንፈስ ኩዴታ የማን ስለመሆኑ በማን ስለመማራቱ ፍንጭ ማውጣት አልፈለገም። ሁሉንም ችግር ጠቅልሎ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ብቻ ላይ ነው የደፈደፈው። የችግሩ አንኳር ያለው ግን ኦህዴድ ላይ ነው። በተቀጥላ ብአዴን ላይም እዬታዬ ነው። አሁን በቅደመ ተከተል ሁለቱን እንሂድባቸው። „ህወሃት ከቤተመንግስት ተባሮ መቀሌ ከመሸገ ወዲህ ሁለት ግንባሮችን ከፍቶ በሰፊው እየሰራበት ነው ( መሳይ መኮንነ )“ August 12, 2018 ·       ቀዳሚው። „ከአንድ ሰሞን ዘመቻ ተላቀን በራዕይና ተልዕኮ በተቀረጸ የተግባር እርምጃ ላይ እናተኩር ዘንድ የሁላችን ቅን ልቦናና ዝግጁነት የሚጠይቅበት ወቅት ላይ ነን።“ እህ ቅንነት? ? ? ? መቼ ነው የእኛ የነፃነት ትግል ከንፋስ ወጀብ ወጥቶ የሰከነ ሥራ ሠርቶ የሚያውቀው። ይህን እራሱ ድርጅቱን ይጠይቀው። ጥያቄ ሚዲያውን ሳይሆን የራሱን የፖለቲካ ድርጅትን ግነቦት 7 ማለቴ ነው። ባለፈው ዓመት ይህን ግዜ ትንሳኤና ህይወት እኛ

ፈተና!

ምስል
ከዶር ገዱ አንዳርጋቸው የክብር የእራት ግብዣ ማግሥት ቀራንዮ! „ስለ ኃጢያትህ ንሰሃ መግባትን አትፍራ።“  ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፭ ከሥርጉተ©ሥላሴ 12.08.2018  ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ይህን የምታይ እናት፤ ይህን የሚያዩ ልጆች፤ ይህን የሚመለከት የውጭ ዜጋ ዛሬ ምን ሊሰማው እንደሚችል መገመት ይከብዳል?  መቼ ነው ከሃዘን የኢትዮጵያ እናቶች የሚወጡት? መቼ ነው ከዚህ እጅግ ከሰው በታች የሚያደርጉ ዘግናኝ አገዳደል እና ውርዴት የሚወጣው? እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ለማለት ሁሉ እያሰፈረኝ ነው። የቄሮ ንጉሥ አቶ ጃዋር መሃመድ ለአሱ ንግሥና የተደረገ የቀረበ ገጸ በረከት ነው የሰው ደም ሊቀርበልት ስለሚገባ። የሚገረምው እና የሚደንቀው በተሰቀለው ወገኔ ዙሪያ ቀርበው የአገዳደሉን ትርኢት እዬተመለከቱ ፌሳታቸው የሆኑ ወገኖቼ ደግሞ መኖራቸው ነው። ፖሊስ የሚባል የለም ከአቅራቢያው?    ምን ይባላል ይሄ የሰው አገር ወይንስ ምን ይባል? እንዴት ወገነህ እንዲህ ሆኖ ሲንጠለጠል አዬትህ ተኝተህ ታድራለህ? ምግቡስ ከጉሮሮ ይወርዳልን? የአቶ ጃዋር መሃመድ የመሪነት ደረጃ ይሄው ነው። መሪነት ማለት በዚህ እንዲህ በሆነ መልኩ ይገለጻል። ለዚህ ነው እንግዲህ በብሄራዊ ደረጃ „የቄሮ ምክር ቤት“ ለማቋቋም ጥናት ላይ መሆኑ የተደመጠው። ተረኞቹ ታራጆች ደግሞ ጠብቁ … ለዚህ አረመኔነት ነው እንግዲህ ከአዲስ አባባ እስከ ባህርዳር ድረስ ሚዲያዎችም፤ ባለስልጣኖችም ሥራ አጥተው ከፍ እና ዝቅ ሲሉ የባጁት፤ ለነገሩ ይህ መጀመሪያው ነው።  ገና የሚፈነዳ ሌላም ነገር ይኖራል። ከዚህ ሌላ ደግሞ ምን ሌላ ልትሉ ትሉኝም ይሆናል፤ ጭካኔ እኮ ሰው መሆን ማለት አይደለም። ሰው ከሰውነት ደረጃ ሲወጣ ነው ጨካኝ የሚሆነው።

ኪናዊ ጥበቡ የሰጠን ልዩ የህሊና ሽልማት!

ምስል
ያዝልቀው በሁለገብ  የእኛዊነት የመንፈስ ቤተኝነት! „ይህ ሁሉ የሆነብሽ እኔን ስለተውሽ አይደለምን? ይላል እግዚአብሄር አምላክሽ።  አሁንስ የሺሖርን ውሃ ትጠጪ ዘንድ በግብጽ መንገድ ምን ጉዳይ አለሽ? የኤፍራጥስንም ውሃ ትጠጪ ዘንድ በአሦር መንገድ ምን ጉዳይ አለሽ? ክፋትሽ ይገስጽሻል፤ ክዳትሽም ይዘልፍሻል፤ አምላክሽንም እግዚአብሄር የተወሽ እኔንም መፍራት የሌለብሽ ክፉና መራራ ነገር አንደ ሆነ እውቂ፣ ተመልከቺ፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሄር“ ከሥርጉተ ©ሥላሴ 12.08.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። እፍታ እንደዛሬ። እነ ቅኖች እንዴት ቆያችሁልኝ? መቼም ሐሤት ሲኖር ፍንክንክ ስለሚያደርግ አሁንም ቅድምም እንዳያመልጥ በዛ ዙሪያ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል። የተራራቀ መንፈስ በእሱ በአንድዬ ሃይል ራሱ በኪነ - ጥበቡ ድልድዩ እዬተሰራ ነው እና። የፈረሰው የልዩነቱ ግድግዳ ነው፤ ፈረሰ ሙሉ ለሙሉ እኔ ማለት አልችልም።  በሴራው ውሰጥ ሆነን፤ ሰው በማጥፍት ውስጥ ሆነን ማዕደኛ ስለምንሆን ነው። እጅ ለእጅ መያያዙ በአንዱ ቅን መንፈስ ውስጥ ሌላው መኖሩን ሳያረጋግጥ ነው አለሁኝ ብሎ አጁን የሚዘረጋው።  የሰሞናቱ ትዕይንት የሳዬን ይህንኑ ሃቅ ነው። የአባቶቻችን የአብርሃም፤ የይህሳቅ አምላክ ግን አሁንም አልረሳንም። የማንደራደርበት ዋናው ነገር ኢትዮጵያ ፈጣሪ ከጥፋት የሚታደጋት መሆኑን ነው። የማንደራደርበት ሌላው ገዳይ ደግሞ አማኑኤል አማልካችን ኢትዮጵያን እንደሚወዳት ነው። በቸርነቱ ያተረፈን አምላክ ይመስገነው። በጸሎት እንትጋ። አቅማችን ይሄው ነውና።  ጀመርነው ወይ ቅንነትን? ተወጠን ብል ይሻላል። የወጣልኝ ሰፊታ ነበርኩኝ ወጣት እያለሁን። ለዛውም ዲዛይኔ የተለዬ ነው። ጎንደር ተወልዳ በ