ኪናዊ ጥበቡ የሰጠን ልዩ የህሊና ሽልማት!


ያዝልቀው በሁለገብ  የእኛዊነት የመንፈስ ቤተኝነት!

„ይህ ሁሉ የሆነብሽ እኔን ስለተውሽ አይደለምን?
ይላል እግዚአብሄር አምላክሽ። አሁንስ የሺሖርን ውሃ ትጠጪ ዘንድ በግብጽ መንገድ ምን ጉዳይ አለሽ? የኤፍራጥስንም ውሃ ትጠጪ ዘንድ በአሦር መንገድ ምን ጉዳይ አለሽ? ክፋትሽ ይገስጽሻል፤ ክዳትሽም ይዘልፍሻል፤ አምላክሽንም እግዚአብሄር የተወሽ እኔንም መፍራት የሌለብሽ ክፉና መራራ ነገር አንደ ሆነ እውቂ፣ ተመልከቺ፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሄር“

ከሥርጉተ ©ሥላሴ 12.08.2018
ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።


እፍታ እንደዛሬ።

እነ ቅኖች እንዴት ቆያችሁልኝ? መቼም ሐሤት ሲኖር ፍንክንክ ስለሚያደርግ አሁንም ቅድምም እንዳያመልጥ በዛ ዙሪያ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል። የተራራቀ መንፈስ በእሱ በአንድዬ ሃይል ራሱ በኪነ - ጥበቡ ድልድዩ እዬተሰራ ነው እና። የፈረሰው የልዩነቱ ግድግዳ ነው፤ ፈረሰ ሙሉ ለሙሉ እኔ ማለት አልችልም። 

በሴራው ውሰጥ ሆነን፤ ሰው በማጥፍት ውስጥ ሆነን ማዕደኛ ስለምንሆን ነው። እጅ ለእጅ መያያዙ በአንዱ ቅን መንፈስ ውስጥ ሌላው መኖሩን ሳያረጋግጥ ነው አለሁኝ ብሎ አጁን የሚዘረጋው። 

የሰሞናቱ ትዕይንት የሳዬን ይህንኑ ሃቅ ነው። የአባቶቻችን የአብርሃም፤ የይህሳቅ አምላክ ግን አሁንም አልረሳንም። የማንደራደርበት ዋናው ነገር ኢትዮጵያ ፈጣሪ ከጥፋት የሚታደጋት መሆኑን ነው። የማንደራደርበት ሌላው ገዳይ ደግሞ አማኑኤል አማልካችን ኢትዮጵያን እንደሚወዳት ነው። በቸርነቱ ያተረፈን አምላክ ይመስገነው። በጸሎት እንትጋ። አቅማችን ይሄው ነውና። 

ጀመርነው ወይ ቅንነትን? ተወጠን ብል ይሻላል። የወጣልኝ ሰፊታ ነበርኩኝ ወጣት እያለሁን። ለዛውም ዲዛይኔ የተለዬ ነው። ጎንደር ተወልዳ በእኔ ዘመን ሞስብ ያልሳፋች ልጃገረድ ከምን ዓይነት ቤተሰብ ነው የተወለደችው ያሰኛል? 7 ዓመት ላይ ሁሉን ነገር እንጀምራለን። 

ራስን ማስተዳደር ማለት ነው። ሃላፊነት መቀበልን፤ ሃላፊነትን መውሰድንም። እና መጀመሪያ ውጥን የሚባለው በግራምጣ ከሆነ በርከት ያሉ ግርምጣዎች በውሃ የተራሱ ከሦስት ተተልትለው ይቋጠራሉ ሰበዙም ያው እሱ ብእሱ በግራምጣው ነው የሚሆን፤ ትንሽ ብቅ ማለት ሲጀመር ነው ውጥኑ ሰበዝ የሚጀመረው። ሰበዝሙ ባለቅልጥሙ ሳይሆን ለስላሰው ተመርጦ ነው። 

ስለዚህ ቅንነት አሁን ያለው ደረጃ እንደዛ በግራምጣ ቋጠሮ የተጀመረውን ዓይነት ነው። የሰው መፈጠር የመጀመሪያ ሦስት ቀናት ማህጸን ላይ ጽንሱ ሲያርፍ እንደ ማለት። እርቀቱን ተመልከቱን ምን ያህል ጊዜ እንደሚያስፈልግ …  ሙሉ እድገቱን ጨርሶ ልጅ መሆን ብቻ ሳይሆን ቁምነገር ላይ እስኪደርስ ያለውን የቆይታ ተጋድሎ … ወደ ሆዋላም ወላጆቹ ያለፉበትን የህይወት ተጋድሎ ሲሰላም እንዲሁ ማለት ነው፤ ለዚህ ነው እኔ „ምን ያህል እንደ ተጓዝኩ አላውቅም“ ስል እኔ ከመፈጠሬ በፊት የነበረውንም ሂደትም በምለሰት ያመልክታል …

ቅንነት ገና በሃሳብ ደረጃ እንኳን በህሊናችን አልሰከነም። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ እማነባቸው ይሄንኑ ገላጭ ናቸው። ትናንት በቅንጅት ምስረታ የተከፈለው መንፈስ ለመገናኘት እንኳን አቅም የለውም አገር ቤት እገባለሁ የሚለው መንፈስ። ይገርማል። ገማናችን ብዙ ነው።

ለነገሩ ቅንነት ተቋማዊ ትትርና በትጋት እና በተከታታይነት ይሻል፤ ቅንነትን አፋፍቶ ለማብቀል ለማጽደቅ ላመስበልም። ለዚህ ገጣሚ፤ ጋዜጠኛ እና የ አዲስ ሃሳብ አፍላቂ አቶ ፍጹም አስፋው አንድ ዝግጅት ጀምሯል "ቅን ልቦች" የሚል። ለመነሻነት ራሱ መጀመሩ ታላቅ አብነት ነው።

አሁን በብሄራዊ ደረጃ የቅንነት ዘር ነው ያለው። ብሄራዊ ተቋማዊ ለማድርግ ደግሞ እራስን የማሸነፍ ዝግጁነትን ይጠይቃል። ያ ያቀርብከው መንፈስ ስትጠቅም ብቻ የሚቀበሉህ፤ አትጠቅምም ስትባል ደግሞ እንደ አሮጌ አካፋ እና ዶሞ እንዲወረውሩኽ ራስን አዝግጠህ ከጀመርከው ትቢያ ሆነህ ትቀራለህ። አንተም እንሱ አለን የሚሉት አቅም እንዳለህ ማሳዬት አለበህ። ይህ ማለት ስተቀበልም ስትጣልም ግዑዝ አለመሆንህ ሰው ሆነህ ማሳዬት መቻልህን በመቻል ማበልጸግ ስትችል ብቻ ነው። ቅንነት የገብያ መደበር አይደለም። ሲፈልጉህ የሚሸምቱኝ ሲደላቸው፤ ሲያተርፉ ደግሞ ዋጋህ እንደወደቃ ወርውረው የሚጥሉህ።

  • መነሻዬ ይሄ ሊንክ ነው


Ethiopia: [ሰበር ዜና!] ከዶ/ አብይ ስለ ሶማሌ ክልልና የአቡነ መርቆርዮስ ጉብኝት የተሰጠ መግለጫ!

ሐሴትንም በፈርጁ።

ደንገዝገዝ ካለ ቀናት ወጋገን የታዬበት ማዕልት ነበር ትናንት። እህቴ እና እኔ ስንገናኝ በስልክ በመልካም ዜና ስለነበር እሷም እዬሳቀች እኔም ሰውነቴ ዝሎ እረፍት ባሰኘኜ ሰዓት በመሆኑ ወግ ደርሶን እድሜ ለአብዮ መንፈስ ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ የጋራ አጀንዳችን ሆኖ ለደቂቃ ስለ ቤተሰብ ሳናወራ ጊዜው ያልቃል። ያስታረቀንም የእሱ መንፈስ ነው። 

አገራዊ ጉዳይ የእኔ ብቻ ይመስላቸው ነበር። ብስለቱ ብቃቱ አላቸው እንደዛ ነው ያሰደግኳቸው። እድሎቼን ሁሉ የሰዋሁት ሰብዕናቸውን መቅረጽ ስለነበረብኝ ነው። ግን ፖለቲካ የህይወታቸው አጀንዳ ክፍለ አካል አድርገው የተቀበሉት አሁን ነው።

የሆነ ሆኖ ትናንት እሷም እፎይ ብላ፤ ከሃዘናዊ ስሜት ወደ ውበት ሳሎን ከመሄዷ በፊት ነበር ደስ ብሏት የደወለችልኝ። እኔ ደግሞ የዛለው መንፈሴን ለውዴቼ ገልጬ ላርፍ ስሰናዳ ነበር። ብቻ ነገረ አሜኑ ከሞት መልስ ስለነበረ መዛሉ ተወግዶ ስለሁኔታው አወጋን።

እንኳንም በሰላም በቸር ወሬ አገናኘን ተባባልን። የነባቢታችን ቤተሰብ ስለሆነው አገራዊ ጉዳይ እኔ ጭንቅ ላይ እንደ ሰነበትኩት ተመሳሳይ ስሜት ነበራት እሷም። ያው እሷ የእናታችን ደግነት የወረሰች ስለሆነ እንኳን የአብይ የቅንነት ሌጋሲ ቀርቶ ው የተሳሳተው ሰው ሳይሆን ስህተቱን የሠራው ሰይጣን ነው ብላ ነው የምታምነው።

የሆነ ሆኖ በትናነትናው ዕለት ሌላም ድንቅ ነገር ተከውኗል።
እርጋታቸው ጸጥታቸው ልታይ ልታይ አለማለታቸው ሁሉን ንቀው መኖራቸው ለእኔ ታቦቴ ናቸው ብፁዑ ንዑዱ አባታችን አቡነ መሪቀርዮስ። ስጸልይ፤ ጭንቅ ሲበዛብኛ፤ ፈተናዬ መፈናፈኛ ሲነሳኝ አዘውትሬ አነሳቸዋለሁኝ። 

በምድር ከሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን ጋር የምወዳቸው እሳቸውን ነው። ከወለደችኝ እናቴ በላይ። እጅግ አድርጌም ነው እምሳሳላቸው። ብፁዑናታቸው ቅድስት አገሬ ናቸው። ገነቴም!ዝም ብዬ የኖርኩት ጫና መፍጠር አልፈልክኝም። እግዚአብሄር በወደደው ጊዜ ይሁን ብዬ በተደሞ ኖርኩኝ። አሁን እንዲህ ውስጤን እማሳያችሁ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አንድ ስለሆነችልኝ ነው። 

ትናንት መጀመሪያ የጠ/ ሚር አብይ አህመድን ድምጽ፤ እና የሙሉ ነጻነት መንፈሳቸውን ስሰማ፤ ስመለከት ዕንባዬን እዬጠረግኩኝ ሻማ አበራሁኝ። የብጽዑ ወቅዱስ አቡነ መሪቀርዮስን የአባታችን ደህንነታቸውን ስሰማ ሻማ ድጋሚ አበረሁኝ፤ ከማንም የ ኢትዮጵያ መሪ ወይንም መሪ እሆናለሁ ብሎ ካሰበ፤ ከለመ ሊሂቅ በተለዬ መልኩ፤ ባልተለመደ መልኩ "ብጽዑ አባታችን" የሚል ሃይለ ቃል ከዶር አብይ አህመድ ስሰማም ሳልአሳዊ ሻማ አበራሁኝ፤
ለኢትዮጵያ እንዲጸልዩ ልጠይቃቸው ሲሉም አርባእቱ ሻማ አበራሁኝ፤ ዶር ደብረጽዮን ገ/ ሚኬኤልን አብሬ ሳይም ጣምራ ሁለት ሻማ አበራሁኝ፤ 



ብጹዑ ወቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስም ከጠቅላይ ሚር አብይ ጀርባ መስቀላቸውን ይዘው አይዞህ እኛ አለንህ በሚል አባታዊ ቸርነት ጥግት ሲሏቸውም ድርብ ሻማ አባራሁኝ።  የሻማ ቀኔ ነበር። ተመስገን! ስደት ላይ መሆኔን ሁሉ እዬረሳሁት ነው።

ጠ/ ሚር አብይ አሜኑ አህመድን ልዩ የሚያደርጋቸው ይሄው ነው። እንግዲህ ዋሽንግተን ዲሲ ይኖሩ የነበሩ  የአውራ ፓርቲ ሊቀ ሊቃውንታት ፈተናም ይሄው ነው። „የቅርብ መዋት የቹቻ መንከሪያ ይሁናል“ እንዲሉ ሆኖ አንድም ቀን ብጹዕ ወቅዱስ አባታችን አጀንዳቸው ሆነው ሄደው ጠይቀው፤ ስለጤንታቸው ተጨንቀው፤ ስለስብዕናቸው ጉዳያቸው ሆኖ፤ ስለ ኢትዮጵያ ደህንነትም እንዲጸልዩ ተማጽነው አያውቁም። 

እንግዲህ አሁን አገር ሲገባ በቅጂ የሚታይ ነገር ካልኖረ በስተቀር። ያም ቢሞር ያው ግልብጥ ነው የሚሆነው። አሁን አማራ አጀንዳችን ነው ቢሉ እንደሚሰማን ዓይነት የለበጣ ነገር ... 
ወደ ቀደመው ምልሰት ሲሆን ኢትዮጵያን ለመምራት ከነዚህ መሰል ብሄራዊ ዕሴት መነሳት ግድ ይላል። መሪነት የዳማ ጨዋታ አይደለም እና። 

ጠ/ ሚር አብይ አህመድን እና ሌሎቹን የብሄራዊ ፓርቲ መሪ ተፎካካሪ ስለሆኑት ሲታሰብ የሰማይ እና የመሬት ያህል ልዩነት አለው። አልጀመሩትም ገና ጽንሰ ሃሳቡን የአገር መሪነት ማለትን። "ለማ ፊቱ ኦሮሞ ይመስላል" አይደለምን የሚሉን?!

ይህን ዕድማታ የእድምታ ሚሰጢረኞች ይተርጉሙት። በጣም በእርግጠኝነት የምናገረው በፍጹም ሁኔታ ባለቅኔው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በልዑል እግዚአብሄር የተቀቡ መሆናቸውን ነው።

የተፈቀደላቸውን መንገድ ለማደናቀፍ መሞከር ጠቡ ከልዑል እግዚአብሄር ጋርም ነው። እንደ ራስ ተሰማ ናደው አያሰነብትምም። በጣም በተደጋጋሚ ዘመናዊ ሴራ የራስ ተሰማ ናደውን ሌጋሲ የማስቀጠል ሴራ ጠረን ይሸተኛል እያልኩ ስጽፍ ነበር። የሆነው ይሄው ነው።

 ባለቅኔው አቅም ጠገቡ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በሰው ሠራሽ ችግር ውስጥ ሆነ ለራሳቸው አላሰቡም ነበር። እነኛ ብፅዕን እሳቸውን አመነው ከዛ ክብካቤው ሞልቶ ከተረፈው አያያዝ ይቅርብን ብለው ውሳኔያቸውንም ሽረው አብረው ለመሄድ ሲወስኑ እዮራዊ ቃልኪዳን ነበር።

እና አባ ቅንዬ እዬባዊው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ነፃ ሲወጡ በልባቸው ያሰቀመጡትን ቅዱስ ነገር ቢኖር ብፁዑ ወቅደስ አባታችን አቡነ መርቀርዮስ ደህነንት ነበርና አፍታ ሳይቆዩ ወደ ዛው አመሩ።  ጭንቅ ላይ ነው የሰነበቱት። አፍ ባለው የቤተመንግሥት መቃብር ውስጥ ነው የነበሩት። ነፃ ሲወጡ መጀመሪያ ያደረጉት ይህን የቅድስና ተልዕኮ ነው።

ይህ ንጽህናቸው በራሱ ድርሳነ አብይ እንዲዘጋጅ ያስደርጋል። እኔህ ቅን ፍጥርት የሁላችንም ጽዳት የነሳው ሕሊናን በእንዶድ ነው እያነጹት ያሉት። ጽዳት የጎደለውን ሰብዕናችን እያጸዱት በቅንነት ንጹህ ውሃ ነው እያጠቡት ያሉት።

በዚህ በረከት ውስጥ በእዮር የተፈቀደላቸው ደግሞ ዶር ደብረጽዮን ገ/ ሚኬኤል ናቸው። ይገርማል አብሬ ሄጄ ልያቸው ብለው ፈቅደው መሄዳቸውን የዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ ዘገባ ዛሬ የምሥራች ላከልኝ። አለገኘሁትም ነበር ይሄን ጭብጥ።
awaze news

እኔ እኮ ባለቅኔው ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ እንደ ለመደባቸው እርቅ እንዲወርድ በራሳቸው አነሳሽነት ያደረጉት መስሎኝ ነበር። እኔ ያሰብኩት ልክ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን የባጀበትን ከሁሉም የሙግት ዓውዱን እና ሌሎች ተሞጋች መንፈሶች ጋር ለመቃራረብ እንደሚያደርጉት ጥረት ነበር ያስብኩት።

ለካንስ ደጉ እግዚአብሄር ትግራይን መታደግ ፈልጎ ዶር ደብረጽዮን ገ/ ሚኬኤልን አነሳስቶ ምርቃትን፤ በረከትን ይፍታህን፤ ምህረትን፤ ይቅርታን እንዲያገኙ አነሳስቶ ለዓይነ ሥጋ ከብፁዐን ወቅዱስ አባታችን አቡነ መሪቀርዮስ ጋር አባቃቸው። ዕውነት ለመናገር ይህን ማንም አለገኘውም። እዮራዊ ስጦታ ነው ለትግራይም ለዶር/ ደብረጽዮን ገ/ ሚኬኤልም። ታዕምር እኮ ነው።

ዶር ደብረጽዮን ገ/ ሚኬኤል ብጹዑ አባታችን ቅዱስ አቡነ መሪቀርዮስ ዓይን ናፈቃቸው? አብሬ ልሂድ ብለው ጠዬቁ? ገድል ነው። ስንት ታምር ነው የሚሰማው፤ የሚደመጠው በዘንድሮው ምድር። 

እህቴ ቤተመንግሥት ትልቅ መስቀል ተሸክሜ አዬሁት ያለችኝ ነገር ይህ ከሚስጢሩ አንዱ ነው። የእነኝህ ብፁዕና አባቶቻችን በባዕታቸው መገኘት አምላክ ኢትዮጵያን አለረሳትም ማለት ነው።

9 መንግሥታት ነው ያላት ኢትዮጵያ አይደል? አህጉር እኮ ሆናለች። የቀደመውን በረከት ግን ተወሰደ - በትግራይ። የትኛውም ክልል መሪ ይህን አላደረገውም። አልፈቀዱም።

ብአዴን አቶ ጃዋርን መሃመድን ለመቀበል ሚሊዬነም ላይ ተገኝቷል በተወካዩ በአቶ ንጉሱ ጥላሁን አማካኝነት። ከአቶ ጃዋር በፊት ብፁዕና አባቶቻችን ነበር አገር የገቡት። ይህ ለብአዴን አጀንዳ አልነበረም። 

አሁን ሰማያዊ ረድኤትን ቀድሞ ለመቀበል የፈጠነው የትኛው ክልል እንደሆን መርምሩት። ረቂቅ ነው። የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት ሉዑካኑ ቦሌን ሲረግጡ የማላውቀው ስሜት ተሰምቷኛል ብያችሁ ነበር። ስለዚህም ነው በዚህ የሁለት ጊዜ የግድያ፤ የአንድ ጊዜ የእገታ ሙከራ ላይ ኤርትራ ትሆናለች ብዬ ቅንጣቢ ጥርጣሬ የማይኖረኝ።  ንጹህ ነገር ነበር እኔ ኤርትራን ስቀበል። በንጽህና መቀበል መልካም ነው። 

ዛሬም የተሰማኝ መሰሉ ንጽህና ነው። አደራ እምለው ዶር ደብረጽዮን ገ/ ሚኬኤል ይህን ንጽህና እንዳያቆሽሹት እና የትግራይን ትውልድ ከሞት እንዲያተርፉት ነው። ሞት ማለቴ የሥነ - ልቦና ሞት። መገለል ክፉ ነገር ነው። 

ለለጋ ለቀንበጥ ወጣቶች ይከብዳል መገልለን ተሸክሞ መኖር። እና ያ እንዳይፈጠረ ለአብይ ሌጋሲ ቀዳማይ መሆን ይጠበቅባቸዋል። እስከ ሞት ድረስ መቁረጥ ይጠበቅባቸዋል። ጊዜ ሳያጠፉ መትጋት አለባቸው … ይህን ካደረጉ በህይወታቸው ውስጥ ካበከኑት ጊዜ ያተረፉት እንዲበልጥ ያደርጉታል። 

ለነገሩ ብፁዕነታቸውን ሄዶ ለማዬት መፍቀድ በራሱ ለእኔ ከመንፈሳዊ ህይወት አንጻር ረቂቅ መልዕክት አለው።

ሌላው በዚህ በግድያ ግርግር፤ በእገታ ወከባ እኛ የለንበትም ነው መልዕክቱ። ድፍሩት የሚመጣው ደግሞ ከእውነት ነው። ይህን የደፈሩበት እውነት በውስጥ ስላለ ነው። ለዚህ ነው እኔ ሰሞኑን በምጽፈው ነገር ላይ ወያኔ ወያኔ አትበሉ ስል የሰነበትኩት። እውነቱን ያጠራው ደግሞ ይህ መንፈስ በቅድስና አዲስ መስመር ሃዲድ ቀይሶልናል። "ልብ ያለው ሸብ"

ንጽህና ደፋር ያደርጋል። ንጽህና እርግጠኛ ያደርጋል። ንጽህና ፊት ለፊት ሲወጣ አይታፈርበትም። ንጽህና አንገት አያስደፋም። ንጽህና ራስን ሲያነጻ በራሱ መንገድ ነው። ተመስገን። ደስ ብሎኛል እኔ።

በሌላ በኩል አሁን የተፈጠረው የክፉዎች ሴራ የአብይ ሌጋሲ ብቻውን እንዳይሆን ሌላ አዲስ አቅም ፈጥሮለታል ብዬ አስባለሁኝ። እራሱ አብሬህ ልሄድ እፈቅዳለሁ፤ ከጎንህ ልሆን እሻለሁ ማለት በራሱ እንቁ ነው። የፈለገ ከአንተ ጋር ቢወግነኝ ፈቃደኛ ነኝ ማለት ነው። „ጊዜ ገቢረ ለእግዚአብሄር“ "ጊዜ ለኩሉ።"  እግዚአብሄር ተግባሩን እዬከወነ ነው። 

የአባቶቻችን በባዕታቸው መገኝትም ማንዘርዘሪያ ሠርቶልናል። የሃይማኖት አባቶች በሚሊዬነም አዳራሽ በነበረው አቀባባልም የቁራዕን፤ የወንጌል፤ የተፈጥሮ አማንያንን መንፈስ ቦጎ አድርጎ፤ ፏ አድርጎ አሳይቶናል። ልዩ ጊዜ ነው። ተመስገን። ይህ ሰው ሰራሽ ዳንቴል አይደለም። የፈጣሪ ሥራ እንጂ።

እድሉ ያመለጣቸው ወገኖች ሁሉ ከዛ ንጹህ፤ ቅን፤ ጥሩ ሰው መንፈስ ጋር ማወዳደር ቀርቶ ማቀራረብም አልችልም። በዚህ በዛሬው እርምጃ ዶር ደብረጽዮን ገ/ ሚኬኤል የሠሩት ጥበብ ነው። በረከቱን ደግሞ በሂደት ያገኙታል። ምን ያህል አቅም እና ጉልበት እንዳለው። አብይን ከሴራ መረብ ያሰለቀቀው፤ ከተቃጠባት ሞት ያተረፈው፤ የብፁዕኑ አባቶች ጸሎት ነው።

እኔ ወደ አንድ መምጣቸው በራሱ ስቀበለው ከልቤ ነው። ስቀበልም ስቃወም ከልቤ ነው። የታይታ አልፈጠረልኝም። አንዲፈጠርብኝም አልፈቅድም። ወደ ቅንነት የሚመጡ መንፈሶች ሁሉ እንኳን ደህና መጣችሁ ሊባሉ ይጋባሉ።

እንኳንም ለዚህ የመጀመሪያ መቅድመ በረከት ተማራቂ ለመሆን አባቃዎት ልላቸው እደፈራለሁኝ ዶር ደብረጽዮን ገ/ ሚኬኤልን። 

መልካምነት፤ ትህትናን ለማድረግ መፍቅድን ስንቀበለው በንጽህና መሆን አለበት። ቅንነት ሲጠራቀም የአላዛሯ ኢትዮጵያ የድምጽ አልባዎቹ እናቶች እንባ ይቀንሳል።

ማከያ። 

ለትግራይ ተዋለጆች አማስስበው ግን ከላይ የተቀመጠው የወንጌል ቃል እናንትን ይመለከታል፤ ወደ ተፈጥሯችሁ ተመለሱ። ወደ ባዕታችሁ ተመለሱ። ወደ ብትህናችሁ ተመለሱ። ባልተፈጠራችሁበት መንገድ የሄዳችሁበት ስንኩል መስመር ሁሉ በቃህን ብላችሁ አሸነፋችሁ ድል አድርጉት። ጥያቄዎች ግን በትህትና እና በ አክብሮት ነው። ትህትናም፤ ቅንነትም፤ መልካምነትም መቀበል ያተርፋል እንጂ አያከስርም። ትውልድን ከብክነት መታደግም ታላቅ የተጋድሎ አውራ ነው። 

ጀግነነት እምለው እኔ እራስን ማሸነፍ መቻል ነው። አሁን ናሙናዊ መሪ አግኝታችሁዋል።

የአብይን የቅንነት ሌጋሲ ለማስቀጠል እንትጋ!

የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ!



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።