"ባልተገባ ጊዜ ሰው መግደል ውድቀት ነው" ተግተን እንጸልይ!

„ባልተገባ ጊዜ 
ሰው መግደል 
ውድቀት ነው።“ 
(ከጠ/ሚር አብይ አህመድ የተወሰደ)

„አንተ ግን ወገብህን ታጠቅ፤ ተነሥም፣
 ያዘዝሁህንም ሁሉ ንግራቸው፤
 በፊታቸው እንዳላስፈራህ አትፍራቸው።“
ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ከ፲፯ እስከ ፲፰
ከሥርጉተ©ሥላሴ
12.08.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

እምዬ ያንቺ ቅድስና ንጹሁን መንፈስ እንዲጠብቅ አምላካችን ይርዳን፤ አሜን!


እንዴት አደራችሁ ዋላችሁ አረፈዳችሁ ወገኖቼ ቅኖቹ ውዶቼ። ዛሬ እንቅልፍ አጥተው የከረሙት አይኖቼ ከናፍቆታቸው ጋር ተገናኝተዋል። ጸጥ ያለ እንቅልፍ ተኝቼ አደርኩኝ። በጥዋቱም በወጉ የተለመደውን ስላደርኩም አቅም አግኝቻለሁኝ። ከባድ ጊዜ ነበር ያሳልፍኩትኝ። በስልክ ሆነ በኢሜል አማገኛቸውን ቅኖችንም ረብሻለሁኝ ማለት እችላለሁኝ። ስለምን? ተስፋ ወደ ተስፋ ቆራጭነት ከተሸጋገረ እንደ ገና አቅም አቅግኝቶ አጎልብቶ ለማውጣት እና ራዕይን ቀጣይ ለማድረግ እጅግ ከባድ ስለሆነ።   

ለዘመናት የተካሄዱ ተጋድሎዎች በሰው ጥበብ ሳይሆን በልዑል እግዚአብሄር ጥበብ የተሰጠን ጸጋ፤ የተሰጠን መክሊት፤ የሁላችንም የምንለው ጥሩ የዘመን መንገድ ተስፋው አደጋ ላይ ሲወድቅ እንደ ዜጋ እንደ አንዲት ሩህሩህ ሴትም የውስጤ ማለት ይገባ ነበር።

 ትናንት በቀደመው አቅማቸው ልክ በነፃነት ሆነው ጠ/ ሚር አብይ አህመድን ማዬት መቻላችን የተፈጠረ ነገር አልነበረም ዋሾዎች፤ መርዶ ነጋሪዎች የሚሉ ወገኖቼን ተመልክቻለሁኝ። የጉዳዮችን ፍሬ ነገር ሥረ ነገር እንዲት በወጀብ እንደሚመሩም አስተውያለሁኝ።

እርግጥ ነው እባካችሁ ክፉ አትመኙበት ከሚል ቅንነት ሊሆን ይችላል። እንዲዳፈንም ስለሚፈለግ ሊሆን ይችላል። በሌላ በኩል አረጋጊ ነን የሚሉትም ያቀረቡትን ምስል እና የድምጽ ቅንብር አዳምጫለሁኝ። ያው እንደ ተለመደው ነው። በቆሞስ ኢንጂነር ስመኘውም የተደረገው ይሄው ነበር ባለቤቱ ያለችበትን ሁኔታ እናውቃለን ባዮች ናቸው ዛሬም ይሄንኑን የደገሙልን።

ዋናው ፍሬ ነገር ወገንህን፤ ዜጋህን፤ መድረክ ላይ የምታውቀውን ሰው ሲጠፍህ የት ነህ ብለህ ማሰብ ሰውነት ነው። ሰውነት የሚላከው በዚህ ነው። በሃሳብ ልተላይይ ትችላለህ፤ በዓላማም እንዲሁ ግን ደህና ነህን ብሎ መጠዬቅ ይገባል?

የት ሄደ ብለህ ማሰብ ይገባል። ምክንያቱም አካልህ ነው። የአንተ ነው። የእኔ ነው። የእኛ ነው። „ኢትዮጵውያን“ የሚባለውም ረቂቅ ጉልበታም የማንነት ጽንሰ ሃሳብ ውስጥ በዕውን ካለ ከኖረ ነፍስህ ስለ ኢትዮጵያዊነት ዘላቂነትም ኤሉሄ የምትል ከሆነ በሃሳብ የተለዬህም፤ ወይንም አንተ ፈቅደህ የተለዬኸውም የአንተ ደም እና አጥንት ነው። እንኳንስ የርህርህና አባ ወራው አሜኑ ሲጠፋ ቀርቶ።

ለዚህ ነው እኔ ማንም ሰው ሲታሠር፤ ዬትኛውም የፖለቲካ ድርጅት አቀንቃኝ ይሁን መንፈሱ ካቴና ላይ ሲውል ልዩነት ሊደረግበት አይገባም የምለው። አኩልም እምታገልለት። ሲፈታም ፍሰሃው ደስታው የሁላችን ሊሆን ይገባል የምለውም ለዚህ ነው። ሞተም ከሆነ አኩል ህምሙ ሊሰማን ይገባልም እምለው ለዚህ ነው።

እስር ላይ ያሉት ያልተፉትም ወገኖች በሚመለከት ከደረቅ ወንጀል ውጪ ያሉት ፍትህ እንዲያገኙ መትጋት አለባቸው የምለውም ለዚኸው ነው። ስለምን? የኢህአፓ መንፈሶች ተነጥለው እስር ላይ እንዲማቅቁ ሁሉ ለእኔ ግልጽ አይደለም እምተጋበትም ነው። ወገኖቼ ናቸውና። የነፍሴ አካሎች ናቸውና። ነፍሴ ካለ እነሱ ቀለም የለሽ ነው የምትሆነው።

ያ  ጥቂቶች የሚፈሩት፤ ወይንም የሆነ ነገር ለጥፈው ጫና ፈጣሪነቱን የሚያዋክቡት አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ብሄራዊ ሰንደቃችን ንጹህ የቀለማት ህብረት ውስጥ የእያንዳንዳችን ነፍስ ዜጋ ስለመሆናች ያመጣው ሚስጢር በዚኸው ይመሳጠራልና። በቀለሙ ውስጥ ያለው ህብራዊነት ነው ኢትዮጵያዊነት።

ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ረዘም ላሉ ቀናት መሰወር ነፍስን ሊጨንቃት፤ ነፍስን ሊያንጠለጥላት፤ ነፍስን እረፍት ሊነሳት ይገባ ነበር። ለእኛ ብቻ አይደለም ለራሷ ለእቴጌ ኤርትራም ቢሆን ብልሁ አጀንዳዋ ሊሆን የሚገባ ጉዳይ ነበር። ለእስልምና፤ ለክርስትና፤ ለዋቄ ፈታ፤ ለሚያምኑ እና ለማያምኑ ሁሉ አጀንዳ ሊሆን ይገባል። አፍሪካም ከዘረፋ የጸዳ ወጣት መሪ ማግኘቷ የሚስጥርነቷ ፍሬ ነገር ነው እና ሊጨንቃት ሊጠባት ይጋባል። ግሎባሉም ዓለም የኢትዮጵያ ሰላም መሆን በሁለገብ አቅሙ ዋነኛ ጉዳዩ ነው።

ይሆናል፤ ይሳከል ብሎ ባለሰበው መንገድ አብዛኛው የእኔ የሚለው መሪ በኢትዮጵያዊነት መንፈሱ ገዥ ሆኖ መውጣቱ ከሰብዕ አንፃር የራዕዮዋ፤ የትጋቷ ክፍለ አካል ስለሆን የእኔ ማለቷ የግድ ነው ፕላኔታችን እራሷ።
በሁለመና ብቃታቸው ነገ የዓለም መንግሥታትን ይመራሉ ተብለው ከሚጠበቁት መንፈሶች አንዱ ይህ የዶር አብይ አህመድ ንጹህ መንፈስ ነው። ማን ያውቃል ኢትዮጵያ የመንግስታቱን ማህበር የምትመራበት ጊዜም ይመጣ ይሆናል። ለምን አይሆንም? ይሆናል! አሁን እኮ አንገታችን የማንደፋት መድረክ ሲይዝ የማነፍርበት ሙሴ ነው ያለን።

የዛ ፍርቻ ነው የሰሞናቱ ሁለተኛው ግረግርም። የሰሞናቱ ፍራቻ ህብራዊነታቸው የፈጠረው ተጽዕኖ ቅናትን ወልዶ አንጃን አዋለደ።ለዚህ ነው“ ባልተጋባው ጊዜ ሰው መግደል ውድቀት ነው“ ያሉት። ቀጣዩ ደግሞ የመኪና፤ የአውሮፕላን አደጋ ይሆናል። 

ጨርሶ መጨረስ። እንግዲህ የቅኖች አማላክ ይጠብቃቸው። እሳቸውማ ከአሁኑ እጅግ በረቀቀ ሁኔታ ከተደራጀው፤ እጅግም ታስቦበት ከተከወነው የመከራ መረብ ያወጣቸው አምላክ ትንሽ ጥርጣሬ የሚባል ነገር ይፍጥራላቸው ዘንድ በጸሎት እንትጋ። ትንሽን ጥንቃቄ የሚባል ነገር ይሥራላቸው ከሆነ አምላካችን እንማጸን። ዙሪአቸውን የመቃኘት አቅም ይስጣቸው አዶናይ። ተቀድመን ነበር።

ለዚህ ነው አብሮ አደገማቸው አርቲስት ጌትሻ ማሞ ፖለቲካን እንዲተዎው መክሬው ነበር ያለው። ሴራ ውስጥ ስላልተፈጠሩ በሴራ ለከተሙ ነፍሶች ጋር የሚመጥን የሴራ ድር መረብተኛ ወይንም ማህበርተኛ አይደሉምና። 

የተፈራው ለዛሬ ብቻ አይደለም፤ እንደተለመደው ያው አዲስ ያለማ መሬት ሲቀኑ ኑራዋል፤ ያ ማሳ ከቀና በኋዋላ ደግሞ ሌላ ይከፈስበትን እና አባ ቅንዬ በዛ በቅንነት በሁለገብም ንጥር በሙሉ አቅም ደክመው መንገድ ጠርገው ጎባጣውን አቃንታው ተስፋን ከተስፋው ጋር ሲያገናኙ ይገፉ እና ደግሞ ወደ ሌላ ምድረ በዳ ይላካሉ፤ አሁን በግር ግሩ ጠፍተው የእሳት እራት ሆነው ይቀራሉ ተብለው ሲታሰቡ የዓለም ሚዲያ አውራ አጀንዳ ሲሆኑ ነገ ያስፈራቸው ቅን ባልሆኑ ክፉ መንፈሶች የሆነው ሆነ። አትያዝ አይደባልም ቁም ነገሩ ምህረት መላኩ ነው …

ንጽህናቸው እና ቅንነታቸው ሆነ ቀናነታቸው ይህን መንፈስ ከገብያ ሄደህ በችርቻሮ ጉልት ላይ የምትገዛው አይደለም። ወይንም ስለተማርከው ብቻ የምታገኘው አይደለም። ወይንም ብዙ ሰው ስላጨበጨበልህ ብቻ መንበር ላይ የሚወጣህ አይደለም። 

ይህ መንፈስ በበቀለ ሰብዕና የጸደቀ ሙሉ አቅም ያለው ብልህነት ከፈጣሪ ከአማኑኤል የተሰጠ ብቻ ነው። ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጥብብን ፈልጓት አገኟትም። ስለሆነም ብልህነቱ ደግሞ ከጥበብ ጋር በውል የተዋሃደ ሆነ። ውህደቱ ደግሞ የሰሞናት አይደለም ምንጩም የአባይ ፏፏቴ የሆነው ምርቃቱ የልዑል እግዚአብሄር ስለሆነም ነው።  

ይህ የቅንነት ንጽህና ትውልድን ካለብክነት በመስቀጠል ረገድም የዘላቂ ጥሪት መሠረት ነው። አሁን የሰሞናቱ የሰራዊቱ ጅጅጋ የመገኘቱ ብልህነት አምክንዮ ከመንፈስ ለውጥ ጋር ተደሞውን ስመረመረው ምን ያህል ተጽዕኖ ፈጣሪ መንፈስ እንዳላቸውም ተገንዝቤያለሁኝ። 

ቀደም ባለው ጊዜ የወያኔ ሃርነት ሠራዊት ነበር የምንለው አሁን ግን ያለው ብሄራዊ ስሜት እና ወገናዊነት ድንቅ ነው ቃለ ምልልሱን ሳዳመጥው ህሊናው በምን ዓይነት እንዶድ ታጠቦ ነው እንዲህ የሆነው ያሰኛል። ይህን ለማደናቀፍ ነበር የሰሞናቱ ክፉ መንፈስ ነፍሳችን ዲፍሪጅድ አድርጓት የነበረው። „ባልተገባ ጊዜ ሰው መግደል ውድቀት ነው።“ 

ቅንነት ገና በመንግሥት በመሪ ደረጃ በወል ሃብትነት መሠረት መጣል ተጀመረ ቢባል አሁን ነው በዚህ ዘመን ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ጀምሮ። ሊቃናት ቅን ቢሆኑ ምርቃቱ ታክሎ ይህን መሰል ጸጋ እና ተቀባይነት አይደለም በረጅም ጊዜ ቆይታቸው በአጭር ጊዜም ማብቀል በቻሉ ነበር። ነገር ግን ቅንነቱ ስሌለ በአንዱ ሲሳፈ በሌላው እዬፈሰስ፤ አፍስን ስንለቅም፤ ለቅመን ስንሰበስብ ከረጢቱ ግን ቀዳዳ በመሆኑ ኪሳራን በኪሳራ ስናወራርድን ኖራልን።

ስለምን? ከረጢቱ ቀዳዳነቱ ቅንነት ከሚባለው ንጹህ ፍልስፍና ጋር ትውውቅ ስላልነበረው። የ አብይ አቅም ሚስጢር ቅንነት ነው። አሁን ሊሂቃኑም ይህ ቅንነት ነጥፎ የባጀበትን ማሳቸውን ከአባ ቅንዬ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ አዲስ ችግኝ በማፍላት ራሳቸውን ገዝተው ራሳቸውን ማሸነፍ ያለባቸው ይመስለኛል። 

ቋሚ ተቋም ተከፍቶላቸዋል እና።ተከታዮቻቸውም ቢሆኑ እነሱኑ ተከትለው አውነታዊ ጉዳዮችን ሁሉ በአሉታዊ መንገድ ጦር የሚሰብቁበትን መንገድ እንዲያስተካክሉ ችግኙን አራብተው በማዳበሪያ ሳይሆን በተፈጠሯዊነት ራሳቸው ተለውጠው ሆነው በመገኘት ከሴራው ዓለም ወጥተው ቅን ለመሆን ይትጉ።

በአዋጅ በሚዲያ ተወዳጅነት ማፍራት አይቻልም። አንድም ሚዲያ አገር ውስጥም ይሁን ውጪ አገር አብይን በሚመለከት የሠራው ተግባር የለም። ከሳተናው በስተቀር። ነገር ግን አብይ ከነፍስ በላይ የሚሳሳለት መንፈስ ሆኗል። ይህ የፕሮፖጋንዳ የገብያ አዳራሽ የከፈተው የሞል ውጤት ሳይሆን የምርቃት ውጤት ነው። ለመመረቅ ቅን መሆን። አያስከፍልም ቅንነት።

የፖለቲካ ሊሂቃን ተከታዮቻቸው ለተልዕኳቸው ልጆቻቸው ናቸው። ልጆቻቸውን ሳያውቁ ቀድመው ደግፈው ሊነሱ በሚገባ ጎዳይ ላይ ያን ያህል እሰጣ ገባ በዬዘመኑ ያደረጉት እና አቅማቸውን የሚያባክኑበትን ሁኔታ ከልባቸው ሆነው ሊመረምሩት ይገባል። አብሮ መውደቅ ሲዘወትር የትነኝ ብለ መመረመር ያሰፈልጋል። መደገፈ መልካም ነው ግን በወጀብ ከሆነ አይጠቅምም።እርግጥ ነው አማራጭ ከማጣትም ነው።

የኖርንበት የአቅም ብክነት በኪሳራ እንጂ በትርፍ አይደለም የተጠናቀቀው። ተሸነፊ አድርጎናል። በዛ በተሸናፊነት መንገድ በ እልህ እና በጉልበት የነበረው እሰጣ ገባም ብሱ መንፈሶችን አሳጥቶናል። አሁኑ አዎንታዊ መንገዱን ቅቡል እንዲሆን የተገደዱት።

ሰው በህሊናው ቢመራ እንክርዳድ እና ፍሬን ለይቶ እንክርዳዱን በመተው ፍሬውን ግን ወገን ማድረግ ይገባ ነበር። የባጀነው ግን በነበረው መንገድ ሲንኳትን ዘጭ ነው የሆነው። አሁን በተፈለገ እጀባ የሚዲያ ሽፋን ቢሽቆጠቆጥ ተፈጥሯዊነቱን የመሸነፉን ማለቴ ነው በሥነ - ልቦና የመጠቃቱን አይሸብበውም።

ምክንያታዊ መሆን ብቻ ሳይሆን ዘመን እራሱ የሚሳጣቸው፤ የሚፈቅዳቸው ጭብጦች ይኖራሉ። ከእነዛ ጋር ተዋዶ መቀጠል ጠቃሚነቱ ሥነ- ልቦናን አይጎዳም። ሰው መሆን በህሊና ውስጥ ስለመሆኑም ይገልጣል። ለመልካም እሳቤ፤ ለቀና መንገድ ቅደመ ሁኔታ በፍጹም አያስፈልግም ነበር። እንኳንስ ወድቆ የማይውደቀውን ቀናውን አይተህ፤ ብትወድቅ እንኳኝ ከጸጸት መዳን ይቻላል። ቀናነት በፈለገው መስፈርት ይሆን አሸንፍህም ሆነ ተሸነፍህ ቢሆን ቢያንስ ወስጥህ ሰላም ይለግስዋል።

ከጊዜ ጋር መራመድ ያልቻለ ምልከታ ይወድቃል፤ አዋዳደቁም ዘር አልባ ሆኖ ነው። ለበጎ ዕሳቤዎች ዳታ አያስፍልግም። በጎ ካላሰበ ሰው ሰውነቱ ምስል እንጂ ሰው አይደለም ማለት ነው። ወድቆ መነሳት ልብን የሚሞላው በቅንነት ውስጥ ኖረህ ከሆነ እንጂ በጠላትነት ተሰልፍህ ተዋግተህ ሲያሸንፍህ አሸናፊ ሆንኩ ብትል በህዝብ አደባባይ ደረጃህ እንደ ወደቀ ነው የሚቀረው።  

በምክንያት መደገፍ እና መቃውም ምን ሊያተርፍ ምን ሊያከስር እንደሚችል ህዝብ አይቶታል። ይህን ማገናኝት ካልተቻለ መሬት ላይ ዛሬ ያን የጠ/ ሚር አብይ አህመድን የቅንነት መንፈስ ያዬ፤ የተመለከተ በህይወቱ ውስጥ እውን መሆኑን ያረጋገጥ ህዝብ አንቅሮ ይተፋል። እናም ከባህር የወጣ አሳ ያደርጋል።

ሌላው ቀርቶ በስሜን አሜሪካኑ ጉባኤ ለአደባባይ ከወጡት ማለቴ ነው አሁን በተገኘው ዕድል እንኳን ጠንከር ያሉ የህዝብ ጥያቄዎች ጎልተው ሊቀርቡ ያልቻሉበት መሰረታዊ ምክንያት በተገፈፈ ነፃነት ውስጥ ምንም አይነት የተማከለ ተቋም ስላልነበረ ነው። 

ለዚህ ውጪ ላይ የነበሩ የነፃነት ትግሉን እንመራለን የሚሉት ሁሉ ሊያፍሩበት የሚገባ ጉዳይ ነው። በማህበራዊ ንቃተ ህሊናም ደረጃ እኔ በስሜን አሜሪካ በተካሄዱት ስብሰባዎች ላይ ጉልበታም አመክንዮችን በማቅረብ ረገድ ያዬሁት እምብዛም ነው። የተለያዩ የሃሳብ ተፋሰሶች መኖራቸው መልካም ቢሆንም ያን ያህል በበጋ በጠራራ ጸሃይ፤ በክረምት በበረዶ ሲካሄዱ የነበሩ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች፤ የብራና ላይ ትጋቶች፤ የኮሚኒቲ ራዲዮኖች ትጋት፤ የፓልቶኮች፤ የቴሌ ኮንፈረረንሶች፤ የድህረ ገጽ ዝግጅቶች፤  የተደከመበት ሁሉ አሰባሳቢ መረብ አልተሰራለትም ነበር ማለት እችላለሁኝ። ስንዱነታችን ታይቷል በወናነት።

ምክንያቱም ኢትዮጵያም የሃሳብ ፍሰት አፈና እዚህም አፈና ስለነበረ ነው። የሲቢክስ ድርጅቶች ሆኖ የሚዲያ አውታሮችን የማጠቃለሉ ተግባር በረሱ ብሰለታዊ የህሊና ተግባር ስላልተከወነበት ከዕለታዊነት ሊዘል አልቻለም። ቢያንስ ያጠቃልልካቸው እንኳን አቅም ያላቸው ሆነው በውስታቸው ጸንተው ለመቆዬት ስላልቻሉ ወጀቡ አብሮ አስምጧቸዋል።

አሁንም ይህኑኑ ይዘን አገር የምንገባ ከሆነ ለነገ በሃሳብ ህብራዊነት ያለው ቀለማም ትውልድ በመፍጠር እረገድ እጅግ አደጋ ላይ እንዳለን አመላካች ነው ለእኔ። ጊዜ ሁኔታ ቦታ አጋጣሚ የፖለቲካ ሃይል አሰላለፍን ሊለውጡ ይቻላሉ። ግን የተነሳህበት ዓለማ ግን መልስ እንዲያገኝ ትግል የጀመርክበት ጥያቄ መልስ ሳያገኝ ትጥቅ የሚፈታ ከሆነ አደጋው ብዙ ነው።

ለዚህ ምሳሌ እምወስደው የአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎን ነው። አሁን የማዬው ዝብርቅ የብአዴን ውጥንቅጡ ያልታወቀ ጉዞ ተጋድሎውንም መስዋዕትንቱንም ወጀብ ላይ የሚጥለው ነው የሚሆነው። አዲስ ሰው በመጣ ቁጥር፤ ተቀበል የተባልከውን እያጋፈፍክ  መፍትሄ የአማራን ህዝብ ይህልውና ጥያቄ ያስገኛል ቢባል ዘበት ነው።
አይደለም ብአዴን እና ሌላው ቀርቶ አማራው እራሱ ስለ ተጋድሎው ሃያለ ፍልስፍና ገና ፊደል አልቆጠረም እና። 

በዛው ላይ መሰናክሉን እንዲሁ „አማራ የለም“ ከሚል ጋር ወይንም „የትግሬ እና የአማራ መንግሥት በቃን“ ከሚል ጋር ስለ ተጋድሎ ዓላማ ውይይት ለማድረግ ማሰብ በራሱ ሰውነትን መሰረዝ ነው። እነሱም በተማከሉበት ይቀጠሉ አንተም የራስህን የቤት ሥራ እና ጉልበት እና አቅምን ፈጥረህ ሃሳብህን አሸነፊ ማድረግ እንጂ በዬጊዜው መሬት ላይ እዬተነጠፍክ ሽርፈራፊ የተስፋ ቃራሚ ለመሆን ከሆነ ስለምን ደመህን ገብርክለት? ስለምንስ አካልህን አጎደልክለት?

እንደ የአማራ የማንነት የህልውና ታጋድሎን ለመሰሉ በሳል የአቋም ፍልስፍናዎች ጠ/ ሚር አብይ አህመድን የመሰለ መሪ ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል። ለሞመገትም አቅም አላቸው። ህሊናቸውም ዝግ አይደለም። ሰው ብለው ስለሚነሱ። ለዚህም ነው ጣዕሜ የሆኑት። ስለዚህም ነው ነፍሳቸው ከነፍሳችን ጋር የተቆራኛው።

ሥራ ያልገቡ ለዛውም አሜሪካን አገር የሚኖሩ የአብይን ሌጋሲ ለማስቀጠል የሚጥሩ ቅን ዜጎች ሰንበት ላይ ነገርውኛል። ይህን ያደረገው ገንዘብ ተከፍሏቸው፤ በሚዲያ ስለ ዶር አብይ አህመድ እንደ ሌሎቹ ተቀስቅሶላቸው አይደለም። ምንም ነገር የማይፍልጉ ግን ለወዘተረፈ ችግራችን አቅማቸው ሙሉ ነው ብለው ስለሚያምኑ ብቻ ነው።

ከሁሉ በላይ የቅንነታቸው ንጽህና ነፍሳቸውን ስለገዛው የእኔ ስላላቸውም ነው።  ትናትን እህቴን በስልክ አግኝቻት ስትነገረኝ በህይወቴ የፖለቲካ ስብሰባ ልሄድ ያሰብኩበት ነበር እዚህ ኮሎንበስ መጥተው ቢሆን ኖሮ አለችኝ። እመጣይቃቸው ግን ስለሳቸው እዬተከታተልን ቢል መክፈል ያልቻልነበት ሁኔታ እንዴት እንደሚያዩት እጠይቃቸው ነበር ነው ያለችኝ። እስከዚህ ድረስ መመሰጥ አለ።

እና ያተረፉት የመንፈስ ስንቅ በቀላል ድርድር፤ በቃልል ውሽልሽል ግብግብና መንገድ የሚደፈር አይደለም። ይህን የጀመሩትን ጉዞ ማደናቀፍ በሚመለከትም ግልጽ ነገር አስተላልፈዋል ለሴሮኞች፤ ልክፉዎች፤ እምነታቸውን ቁርመጥ አድርገው ለሦስት ወራት ሴራ ሲዘረጉ ለባጁት „ባልተገባ ጊዜ ሰው መግደል ውድቀት ነው።“ እንዲገደሉ የተወሰነባቸው ያልተገባ ጊዜ ነው። ልትገድሉኝ ያሰባባችሁበት ጊዜ ውደቀት አስከታይ ነው ፍሬ ነገሩ።

ቢያንስ ቅን መንፈሶቼ ያልኳችሁ የወጠንኳቸውን አገራዊ ተልዕኮዎች መቋጠሪያ እስክሰራላቸው፤ ችግኞችን መብቀላቸውን እስኪረጋገጡ ድረስ ትእግስቱን ካጣችሁ ውደቀት መሆኑን እወቁት ነው ያሉት። አዎን አዌርነሱም ያ ነበር። በውደቀት እንዳይደመደም ነበር ተተግቶ የተሠራበት። የቄሮም ይሁን የ አማራ የህልውና ታገድሎ ግብዕቱ። 

የአማራ የህልውና ተጋድሎወን በማግለል ለባጀቱም የሰሞናቱ ተውኔት የጸጸት መልክት የላከላቸው ይመሰለኛል። ሚዛን የሚያስጠብቅ ነገር መኖሩ መልካም ነው። ለበሰለ ፖለቲከኛ ይህ ፍልስፍና ልቡ ነው።   
የሆነ ሆኖ አብያችን የት ነው? የነበረው የሰሞናቱ ነገር ትልቅ ጫና ትልቅ አዌርነስም ፈጥሯል። ለዚህም ነው ከቤተ መንግሥት ውጪ እንድናያቸው የተደረገው። 

ድምጻቸውን እንድንሰማው የተፈቀደው። እርግጥ ነው ታግተውም ሥራ ሲሰሩ እንደነበሩ እኮ እናውቅ ነበር የሌላን ሌጋሲ እንዲያስፈጽሙ። ስለዚህ የምስራቁን መከራ ለማስቆም ከሳቸው የተሻለ የመፍትሄ ሃሳብ የሚያፈልቅ ሞግቶም መሰመር የማስያዝ አቅም ያለው የለም። ስለዚህ ያስፈልጉ ነበር። ለመንፈስ ጠላፊዎችም ቀጣይነት …

ምንም አልነበረም፤ አገር ሰላም ነው ለሚለው ሞኛችሁን ፈልጉ ነው የምትላችሁ ሥርጉተ ሥላሴ። እርእስ ያደርኩትን ነገር በማስተዋል እንድታዩት ነው። ውስጡን መርምሩት። ከልባቸሁ ውስጥ አስተውሉት - ከትቡትም።

የግድያ ሙከራው ባመኗቸው ሰዎች አማካኝነት ተካሂዶባቸዋል፤ ይህም ዕውነትም ነው። በፈጣሪ ጥበብ ተርፋዋል ይህም እርግጥም ነው። ያ ያዬሁት በህልሜ ወንበር ባዶ መሆንም ትክክል ነው። እገታ ነበር በትክክል ነበር። ይህን ለማስተባበል የሚወጡ መረጃዎች ሁሉ ስህተቶች ናቸው። እውነቱ እውነት ነው።

ይህ የታሪካችን ክፍለ አካል ነው። ምእራፍ አንድ በሁለት የግድያ ሙከራ ተጠናቋል። ተስፋ ጨለማ ውስጥ ነበር። አሁን ወጋገን ያለ ይመስላል ሁለቱንም የግድያ ሙከራ ቅንቡሩ ከአንድ አካል የወጣ ላይሆንም ሊሆን ይችላል ግን ቅናት የፈጠረው ነው።

ይህን እሳቸውም አሳምረው ያውቁታል ፈጣሪም ያውቃዋል። አንድ ቀንም እንደ ታሪካዊ ዕለት ያወጣዋል። አሁን ዓለም አቀፍ ፊገር ሆነው ስለወጡ በጫና፤ በማዕቀብ ሊደረግ የተፈለገው ነገር እንደ እኔ ከሽፏል ብዬ አስባለሁኝ። 

„ምን ያህል እንደ ተጓዝኩ አላውቀውም፤ 
ምን ያህል እንደምጓዝም አላውቀውም፤ 
አለማወቄን ስጠይቀው አለማወቁን ገለጸለኝ። 
ተስፋን እጠብቃለሁኝ“ 

ይህ የራሴ አገላለጽ ነው ተስፋ መጸሐፌ ላይ ከውጪ ሽፋኑ ያለ። ተስፋን እጠብቃለሁ የዘወትር ጉዳዬ ነው። እንዲያውም በጸጋዬ ራዲዮ እና በጸጋዬ ድህረ ገጽ ሁልጊዜ ስለተስፋ ሦስት ቋጠሮዎችን ወይንም መሪ ሃሳቦችን አቀርብ ነበር። አሁንም ደግሜ እላላሁኝ ስለ አብይ ሌጋሲ ቀጣይነት ተስፋን እጠብቃለሁኝ። እተጋለታለሁም። ነፍሴን መስጠት ካለብኝም እሰጥለታለሁኝ። 

ሴረኞች፤ ክፎዎች፤ ቀናቶኞች ያለሙት ተሳክቶ ቢሆን ግን ኢትዮጵያ በእርግጥም ወደ አልታወቀ መንገድ ትሄድ ነበር። የፈጠረው ደግሞ ህዝባዊ ማዕበሉ የሰጠው የመንፈስ ፍቅር የፈጠረው ቅናት ነው። ቅናቱ ደግሞ ከዬት ከማን ስለምን የሚለውን ሌላ ጊዜ በገርደምዳሜ እገልጸዋለሁኝ። ውልብሊቶችን ባለፉት ሰሞናት ጫፍ ጫፉን ጠቋቁሜለሁኝ።

የሆነ ሆኖ ቀጣይ ጉዟችን ሴረኞች እና ቅናተኞች አስበው ለጊዜው ባይሳካላቸውም እነሱን መስሎ መቀጠሉ ግን ትውልዱን ከብክንት አይታደገውም። ያን የክፋ የመከራ ሰሞናት አሳልፈውም በሳቸው ዘንድ በጎ ሃሳብ፤ በጎ ምኞት ነው የተደመጠው።

በዛ በጎ ሃሳብ እና በጎ ምኞት ውስጥ ማህበርተኛን ማበራከት የቅንነት ጋላሪ በመፍጠር ላይ እያሉ ነው ለማስተጓጎል የተሞከረው። ሙከራው ግን በሰው የእጅ ሥራ ሳይሆን በፈጣሪ ጥብበ ከሽፏል። ሙሉ ለሙሉ ሰንኮፉ ተንቅሏል ማለት አልችልም የእኛ ከማድባት ሴራ ጋር ያለን ቁርኝት ለመታቀብ ጊዜ ስለሚያስፈልገው።

ብፁዕ አባታችን አብረዋቸው ባይኖሩ፤ አብረው ባይጓዙ ኖሮ መንፈሳቸውን በልዩ ቅድስና ጥበቃ ባያደርግላቸው ኖሮ ኑሮ ከሁለቱ አንዱ ይሳከ ነበር። ወይ እገታው ወይ የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እና ሌላው ክፉ ዜናው።  

ይህ የተፈጠረው አደጋ ግን ልንማርበት ይገባል። ይህን ክፉ አጋጣሚ በአሉታዊ አይቶ ከእንግዲህ ወዲያ እከሌን እንዳላይ፤ እከሌን እንዳልሰማ የሚያሰኝ ነገር መሆን የለበትም። መታመን ሲጣፋ የሚጎዳው ተቀባዩ እንጂ ሰጪው አይደለም። ስለምን? መታመን ከማንም በላይ የውስጥ ሰላም ፈጣሪነቱ መጀመሪያ ለራስ ስለሆነ። ይቅርታ ማድረግ ደግሞ እንኳንስ ለእኛ በሴራ፤ በአድማ በሸር እና በተንኮል ለኖር ቀርቶ በገዳማዊ ህይወት ለሚኖሩትም ፈተና የሚሆንበት ጊዜ አለ።

አሁን ተመልከቱ ትግራይ ለቅድስት ተዋህዶ ናሙና ናት። ጽዮን ያለችበት። ጽዮን ባለችበት አንባ ተቃዋሚዎች ተፈጠሩ የብፁዕን ቅዱስ አባቶቻችን የ4ኛው ፓትርያርከ ዘ ኢትዮጵያ የአቡነ መርቀርዮስ ከስደት ወደ አገር መመለስ በሚመለከት።

አያችሁ? ከገሃዱ ዓለም ወጥተን ደብረ ዳሞን ስናስብ ትግራይን ገዳማዊ ክ/ ሀገር ያደርጋታል። ሌሎችን ገዳማት ትቼ። ባዕትነቷ የትግራይ ለባህታውያን ነው። ስለዚህ ባህታዊ ናት ማለት ነበር። በዚህ ዘመን ሰው ተናግረው በጭራሽ አስከፍተው የማያውቁ ልታይ ብለው ሚዲያ ላይ ለመውጣት የማይፈቅዱ ቅዱስ አባት መሪቀርዮስ የሚል ታቦት መቅረጽ ቀድማ የነበረባት ትግራይ መሆን ሲገባት ሞገተች ይህን።

ስለዚህ በእኛ በጋሃዱ ዓለም ሰዎች ክፋት፤ ሴረኝነት፤ ምቀኝነት ቢኖር ብዙም ሊደንቀን አይገባም። እኛም ክፋትን ለማስወገድ ለማጽዳት በመንፈሳችን ውስጥ ማህበርተኞች እንዳንሆን ማሰቡ ነው የሚጠቅመው። ጠቃሚነት ጠቃሚ የሚሆነው ደግሞ ራስን ለጠቃሚ ሃሳብ ተጠቃሚነት ተሸናፊ ማድረግ ሲቻል ብቻ ነው።

https://www.youtube.com/watch?v=QN9CQEMiLVE&t=5s

Ethiopia: [ሰበር ዜና!] ከዶ/ር አብይ ስለ ሶማሌ ክልልና የአቡነ መርቆርዮስ ጉብኝት የተሰጠ መግለጫ!


የአብይ ነፍስ ያገባናል!
አብይም አጀንዳችን ነው!
የአብይ ሌጋሲ በልዑል እግዚአብሄር ፈቃድ ይቀጥላል!
ተግተን እንጸልይ!
የኔዎቹ ኑሩልኝ
ማለፊያ ጉዜ!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።