ልጥፎች

ከማርች 23, 2021 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አቅም።

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።   ዕለተ ማክሰኞ ማዕዶተ ይግቡ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ።   " ዝም ብዬ የመከራዬን ቀን እጠብቃለሁ። " ( ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯ )     አ ቅም። አቅም በግል ህይወት፣ በማህበራዊ ህይወት፣ በፖለቲካ ህይወት፣ በቤተሰባዊ ህይወት፣ በኃይማኖታዊ ህይወት ደሙ ነው። አቅም አልባ መኖርም፣ ህይወትም፣ ዓላማም ግብም ፍቅርም የለም። አቅም በተለያዬ እርከን፣ በተለያዬ ሁነት ሊሰጥ፣ ሊከፋፈል ይችላል። አቅም ነው ማሸነፍ። አቅም ነው ድልአድራጊነትም። አቅም በሁለት ልንከፍለው ብንችልም እንደ ፈንጋጣው ሥርጉትሻ ዕሳቤ ሦስተኛም አቅም አለ ብላ ታስባለች።   1) የሰለጠነ። 2) ያልሰለጠነ። 3) ቅብዓ። የሰለጠነው ክህሎት የምንለው፣ ክህሎት ግን ምንድን ነው ? ጭብጡን ላዘግይ እና ለወል ውል የሚሆኑ ሃሳቦችን ላንሳ። ራስን መግዛት፣ አዙሮ የማዬት ብቃትንና ጠንካራ ህሊናን ይጠይቃል። አንድ ኃይማኖተኛ ውጪያዊ ረቂቅ ኃይልን እንደሚፈራ ሁሉ፣ የህሊና ጥንካሬ ያለው ሰውም ደግሞ ህሊናው የሚያወግዘውን ተግባር # በመፆም ከራሱ ጋር # መጣላትን በህሊና ቁስል ማሰቃዬት አይፈልግም። 1) የ ሰለጠነ አቅም። ፕሮፌሽናሊዝም እንደ ማለት ነው። ከዲስፕሊን፣ ከትምህርት፣ ከተወሰኑ ዓመታቶች ጋር በረጅም ጊዜ ሰልጥኖ ሥራ ላይ ሲውል አቅሙ ሥልጡን ...